addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

በአዲስ አበባ አንበሳ ግቢ ተረኛ ተንከባካቢ የነበሩት አቶ አለሙ የተባሉት ቀነኒሳ የተባለው አንበሳ ለህልፈተ ህይወት ዳረጋቸው።

vc
በአዲስ አበባ በተለምዶ አንበሳ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የአንበሶች እና የሌሎችም የዱር እንስሳት ማቆያ ማእከል ውስጥ የሞት አደጋ ተከሰተ።

አደጋው የተከሰተው በዛሬው እለት ተረኛ ተንከባካቢ የነበሩት እና አቶ አለሙ የተባሉት የአንበሶቹ አሳዳጊ እና ተንከባካቢ የአንበሶቹን ማዳሪያ እያጸዱ ባሉበት ወቅት ነው ከጥንቃቄ ጉድለት ባልተዘጋው በር የገባው ቀነኒሳ የተባለው አንበሳ ለህልፈተ ህይወት የዳረጋቸው።

የግለሰቡን ህይወት ለማትረፍ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ የግቢው ሰራተኞች ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅትም የግለሰቡን አስክሬን ከአንበሳው ለማላቀቅና ለመውሰድ ጥረት በመደረግ ላይ ነው።
source http://freedom4ethiopian.wordpress.com/

Single Post Navigation

Leave a comment