addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

ከ60 ሚ. በላይ ኢትዮጵያውያን ከጥገኛ ህዋሳት ጋር ይኖራሉ

kk
ጥገኛ ህዋሳት ካንሰር ሊያስከትሉ ይችላሉ
የጥገኛ ህዋሳት ምልክቶች
የምግብ ፍላጐት መቀነስ
የሆድ መነፋት
ማቅለሽለሽና ማስመለስ
ተቅማጥና የሰውነት ክብደት መቀነስ
ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካና የእስያ አገራት የጤና ሥጋት፣ በንጽህና መጓደልና በውሃ መበከል ሣቢያ የሚከሰቱ ችግሮች ናቸው፡፡ የአለም ጤና ድርጅት በ2002 ዓ.ም ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው፤ በንጽህና ጉድለት ሣቢያ፣ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በጥገኛ ህዋሳት ይጠቃሉ፡፡ ይህ የጤና ችግር ህፃናትን ለሞት ለሚዳርገው የተቅማጥ በሽታ መንስኤ በመሆን በርካታ ቁጥር ያላቸውን ህፃናት ለሞት እየዳረገ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ በ2003 ዓ.ም ባወጣው ሌላ መረጃ፤ በዓለማችን 1.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ንጽህና የጐደለው ምግብና ውሃ በመጠቀማቸው ምክንያት በጥገኛ ህዋሳት በመጠቃት፣ ለህልፈተ ህይወት እንደሚዳረጉና ከእነዚህም ውስጥ 90 በመቶ ያህሉ ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት እንደሆኑ ጠቁሟል፡፡
ከግልና ከአካባቢ ንጽህና መጓደል ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ወደ ሰውነታችን ውስጥ የሚገቡትና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው በመተላለፍ ለከፍተኛ የጤና መጓደልና ለሞት የሚዳርጉት ጥገኛ ህዋሳት፣ በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትንና በተፋፈገ አካባቢ የሚኖሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች በስፋት እንደሚያጠቁ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡
በእስራኤል አገር የሚገኘው የበንጉርዩን ዩኒቨርሲቲ፣ የትሮፒካልና የኤድስ በሽታዎች ምርምር ማዕከል ኃላፊ ፕሮፌሰር ዜብ ቢራቶንዊች ለ15 ዓመታት ባካሄዱትና በ2011 ዓ.ም ይፋ ባደጉት ጥናት፤ በአገራችን ከ60 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ከጥገኛ ህዋሳት ጋር እንደሚኖር አረጋግጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ በጥገኛ ህዋሳት በከፍተኛ መጠን የተጠቁ ህዝቦች ከሚኖሩባት የአለም አገራት አንዷ መሆኗን የጠቆመው ጥናቱ፤ ህዝቡ ምግቡን አብስሎ የመብላትና ውሃን አፍልቶ የመጠጣት ልምዱ አነስተኛ በመሆኑና በአብዛኛው ጥሬአቸውን የሚበሉ ምግቦችን የሚያዘወትር በመሆኑ በቀላሉ በጥገኛ ህዋሳት ይጠቃል ብሏል፡፡ በጥገኛ ህዋሳት ከተጠቁት የአገሪቱ ነዋሪዎች አብዛኛዎቹ ህፃናት መሆናቸውን ያመለከተው ጥናቱ፤ በተለይ ትምህርት ቤት የሚውሉ ታዳጊ ህፃናት የችግሩ ተጠቂ ይሆናሉ ብሏል፡፡ ህፃናት መሬት ላይ የሚወድቁ ምግቦችን ወይንም ማንኛውንም ነገር ወደ አፋቸው የመላክና የቆሸሸ እጃቸውን በአፋቸው ውስጥ የመክተት ልማድ ስላላቸው በቀላሉ ለጥገኛ ህዋሳት እንደሚጋለጡ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
ከግል ንጽህናና ከመፀዳጃ ቤቶች ችግር ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የሆድ ውስጥ ጥገኛ ህዋሳት በስፋት እንደሚታዩ የገለፀው ጥናቱ፤ በአዲስ አበባ ከሚኖረው ህዝብ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ከጥገኛ ህዋሳት ጋር እንደሚኖር መረጋገጡን አውስቷል፡፡
ጥገኛ ህዋሳት የተበከለ ውሃን በመጠጣት፣ ንጽህናው ያልተጠበቀና በተለያዩ ባክቴሪያዎች የተበከለ ምግብ በመመገብና በቆዳችን አማካኝነት ወደ ሰውነታችን ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ከጥገኛ ህዋሳቱ መካከልም “ለካንሰር ህመምና ሞት ሊዳርጉ የሚችሉ እንደማገኙባቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር አንተነህ ተስፋዬ እንደሚገልፁት፤ ጥገኛ ህዋሳቱ የአንጀት መድማት፣ የአንጀት መዘጋት (መታጠፍ) እና የአንጀት ቁስለትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
የተለያዩ የሆድ ውስጥ ጥገኛ ህዋሳት እንዳሉም ይናገራሉ – ዶክተሩ፡፡ ከእነዚህ መካከል ፕሮቶዞዋ፣ ሲስቶድሶና ኔማቶድስ የተባሉት በስፋት እንደሚታዩ ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ህብረተሰቡን በስፋት እያጠቁ ካሉት የሆድ ውስጥ ጥገኛ ህዋሳት መካከል ጃርዲያ፣ አሜባ፣ ወስፋትና ኮሶ ዋንኞቹ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ችግሩ በወቅቱ ታውቆ ተገቢው ምርመራና ህክምና ካልተደረገለት ለካንሰር ህመምና ለሞት ሊያጋልጥ እንደሚችል ዶክተር አንተነህ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ጃርዲያ የተባለው ጥገኛ ህዋስ በተበከለ ውሃ ሣቢያ የሚከሰት ሲሆን ለመጠጥነት የሚውለው ውሃ በአግባቡ ፈልቶና በሚገባ ተጣርቶ በጥቅም ላይ ካልዋለ፣ ጃርዲያን የተባለውን ጥገኛ ህዋስ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡ አሜባ በአንጀት ውስጥ በመራባት አንጀትን የሚያሳብጥና የሚያቆስል ሲሆን ይህም ጥገኛ ህዋስ በወቅቱ ተገቢውን ምርመራና ህክምና ካላገኘ በስተቀር የአንጀት ካንሰር ሊያመጣ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
ጥገኛ ህዋሳቱ ወደ አንጀት ውስጥ ከገቡ ከጥቂት ቀናት በኋላ እጅግ በከፍተኛ መጠን በመራባት በሽታን ያስከትላሉ፡፡ አንድ ሰው በጥገኛ ህዋሳቱ ከተጠቃ በኋላ በበሽታው እስከሚያዝ ድረስ የተለያዩ አይነት ምልክቶችን እያሳየ የሚቆይ ሲሆን ምልክቶቹ በታዩ ጊዜ ወዲያውኑ የሠገራ ምርመራ በማድረግ ችግሩን ለማወቅ እንደሚቻል ዶ/ር አንተነህ ይናገራሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በጥገኛ ህዋሳት የተጠቃ ሰው፤ የምግብ ፍላጐት መቀነስ፣ የሆድ መነፋት፣ የማቅለሽለሽና የማስመለስ፣ የተቅማጥና የሰውነት ክብደት መቀነስ ምልክቶች እንደሚታዩበት የጠቀሱት ዶክተሩ፤ ምልክቶቹ በታዩ ጊዜ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ ጥገኛ ህዋሳቱ ወደ አንጀቱ ውስጥ ገብተው ረዘም ላለ ጊዜ ከቆዩ ግን የአንጀት መዘጋት (መታጠፍ)፣ የአየር ቧንቧ መዘጋት፣ የፊኛ ኢንፎክሽን፣ የአንጀት ቁስለትና ውስብስብ የጤና ችግሮችን ከፍ ሲልም የፊኛና የአንጀት ካንሰርን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡
በጥገኛ ህዋሳቱ ሳቢያ የሚከሰተውን የጤና ችግር ለማስወገድና ወደ አንጀታችን ውስጥ እንዳይገቡ ለመከላከል፣ የግልና የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ፣ ራስን ከተበከለ ውሃና ንፅህናው ካልተጠበቀ ምግብ መከላከል አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁት ዶክተር አንተነህ፤ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚያዘወትረው ጥሬ ሥጋን የመመገብ ባህል በእጅጉ አደገኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ ጥገኛ ህዋሳት ያለበት ሰው ካለ አፋጣኝ ምርመራና ህክምና ማድረግ እንደሚገባው የገለፁት ዶክተሩ፤ ያለበለዚያ ግን በሽታውን በቀላሉ ወደሌሎች እንደሚያስተላልፍ ተናግረዋል፡፡
ሰሞኑን “Wash Ethiopia Movement” በግዮን ሆቴል ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ እንደተገለፀው፤ ንጽህናው የተጠበቀ ውሃን በመጠጣትና የግልና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅ በሽታ አምጪ በሆኑ ተህዋሲያን (ባክቴሪያዎች) ሣቢያ የሚከሰተውን በሽታ በግማሽ መቀነስ ይቻላል፡፡ ማንኛውም ሰው ከመፀዳጃ ቤት ሲወጣ፣ ምግብ ከማብሰሉ ወይም ከመመገቡ እንዲሁም የህፃናትን ንጽህና ከጠበቀ በኋላና ህፃናትን ከመመገቡ በፊት እጆቹን በንፁህ ውሃና በሣሙና መታጠብ እንደሚገባው ባለሙያዎቹ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ጐበዝ! ከጥገኛ ህዋሳት ጋር እኮ ነው የምንኖረው፡፡
http://addisadmassnews.com/

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: