addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የታሰሩት ኮሚቴዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ የጠሩት የዚያራ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቀቀ

ስኬታማው የዚያራ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቀቀ!
ህዝበ ሙስሊሙ ለመሪዎቹ አጋርነቱን፣ ለዓላማው ፅናቱን ዳግም አረጋገጠ!!!
እሁድ ሕዳር 22/2006
xx
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው፦

ህዝበ ሙስሊሙ በግፍ ለታሰሩት መሪዎቹ ያለውን ፍቅርና አጋርነት የገለጸበት የዛሬው ‹‹ኑ! ለመሪዎቻችን በዚያራ አጋርነታችንን እናሳይ!›› የዚያራ ፕሮግራም በስኬት ተጠናቀቀ!

ጀግኖቻችን በሚገኙበት ቅሊንጦ በተካሄደው በዚህ ዚያራ ገና ከማለዳው በርካታ ህዝብ የቦታው ርቀትና የጉዞው አስቸጋሪነት ሳይገድበው በቦታው ላይ ተገኝቶ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ከሁሉም አቅጣጫዎች እና ከአጎራባች ከተሞች የመጣው ህዝበ ሙስሊም ለዚያራው ሲጠባበቅ ከእስር ቤቱ አጠገብ የሚገኘው ሰፊ ሜዳ በረጅም ሰልፍና ጠያቂዎች በሚያቆሟቸው መኪናዎች ተሞልቶ አርፍዷል፡፡ ፍጹም ግብረ ገብነትና መተሳሰብ በታየበት በዚህ የዚያራ ፕሮግራም በሺዎች የሚቆጠሩ ዘያሪዎች ተሳትፈው የነበሩ ቢሆንም እድሉን አገኝተው መሪዎቻችንን የጠየቁት ግን ብዙ አልነበሩም፡፡ በቦታው ከተገኘው ሰው መብዛት ባለፈም የጥየቃ ሂደቱን የማጓተት ተግባር ቦታውን በወረሩት ፖሊሶች እንደተፈጸመ ብዙዎች ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ለሁለት አመታት በዘለቀው ሰላማዊ ትግላችን መሪዎቻችን በግፍ ሳይታሰሩ አስቀድሞ የነበረን ወኔ እና አጋርነት ዛሬም ከብዙ ግፍ እና መከራ በኋላም እንደፀና መገኘቱ በሚደንቅ ሁኔታ ተስተውሏል፡፡ መሪዎቻችን እንጂ አላማቸው አለመታሰሩን፣ ይህም የማይታሰር አላማ ከግብ እስከሚደርስ ህዝበ ሙስሊሙ ግዳጁን እንደሚወጣ የዛሬው ርቀት እና እንግልት ያልበገረው የዚያራ ፕሮግራም አስመስክሯል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ለዚያራ መገኘቱን ተከትሎ በመኪና የተጫኑ የፌደራል ፖሊስ ወታደሮች ከነትጥቃቸው መጥተው ቦታውን በመውረር ትንኮሳ መሰል ድርጊቶችን ለመፈጸም የሞከሩ ቢሆንም ሰላማዊው ህዝበ ሙስሊም ግን በትእግስት ሁሉንም አሳልፏል፡፡ በሰላማዊ የእስረኛ ጥየቃ ፕሮግራም ላይ ለምን ወታደሮች መገኘታቸው እንዳስፈለገም ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ከአወሊያ እስከ አንዋር እና የዒድ ህዝባዊ ተቃውሞዎች እንደሚያደርገው ሁሉ ዛሬም ሰላምን የማስከበሩን ሚና ሰላም አስከባሪ ከሚባሉት በተሻለ ኃላፊነት ሲወጣ ውሏል፡፡ ሌሎች ታሳሪዎችን ለመጠየቅ የመጡ የተለያየ እምነት ተከታይ ወንድምና እህቶች ረጅሙን ሰልፍ ተቀላቅለው እንዲጠብቁ ፖሊሶች ለማስገደድ ሞክረው የነበረ ቢሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ግን በመተሳሰብ ስሜት ለመደበኛ ጠያቂዎቹ ቅድሚያ በመስጠት ቶሎ እንዲስተናገዱ የድርሻውን ተወጥቷል፡፡

በዛሬው ውሎ ምንም እንኳን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ አጋርነቱን ለመግለፅ በቦታው ቢገኝም ለአጫጫር ዚያራ እድሉን ያገኙት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ የጥየቃ ሰአቱ ሲጠናቀቅ ሙስሊሙ ወደየቤቱ የተመለሰው ከወትሮው በተለየ የጥየቃ ሰአቱ ዘግይቶ እንዲጀመር በመደረጉ ቅር እንደተሰኘ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አጋርነት የማሳያ ፕሮግራሙ በስኬት በመጠናቀቁ እንደተደሰተ ነበር!

በማረሚያ ቤቱ የሚገኙት የሰላም አምባሳደሮቻችን እንደተለመደው አጋርነቱን የገለጸላቸውንና ገና ሲያያቸው እምባው የሚቀድመውን ህዝብ አጽናንተዋል፡፡ ህዝብ ላነሳቸው ህጋዊ ጥያቄዎች መፍትሄ ለማፈላለግ በሰላማዊ መንገድ የታገሉት መሪዎቻችን ከመታሰር እና መሰቃየታቸውም በላይ የወከላቸው ህዝብ ደህንነት እንደሚያሳስባቸው ከፍርግርግ ጀርባ በሙሉ ወኔ የሚታየው ፊታቸው ያስታውቅ ነበር፡፡ ህዝበ ሙስሊሙም በሃገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የመሪ እና ተመሪ ጥብቅ ቁርኝቱን አሳይቷል፡፡ በነሱ መታሰር የታሰረው መላው ህዝበ ሙስሊም መሆኑን፣ የፖለቲካ ውሳኔ የሚሰጥበት መጪው ቀጠሮም በህዝብ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ እንደሆነ ከወዲሁ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ውድ የሰላም አምባሳደሮቻችን ሆይ!!! መስዋእትነታችሁን ከንቱ የምናደርግ አይደለንም!!!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
Posted by Addisu Wond.
http://www.zehabesha.com/

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: