“የመለስ አለመኖር ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው” ሚስ አና ጎሜዝ
“የመለስ አለመኖር ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው”
ሚስ አና ጎሜዝ
( ይህ ጽሑፍ ህዳር 2006 ቁጥር 22 በወጣው ፋክት መጽሔት ተቀንጭብ የተወሰደ ነው)
ጥያቄ(ፉክት)
ላለፋት ስምንት አመታት የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት ትከታተይ እንደነበር ከምትፅፊያቸው ፁሁፎች፣ በፓርላማ ከምታነሺያቸው ሀሳባች እና ክርክሮች ለመረዳት ችያለሁ። ያለሽ አስተያየት ምንድን ነው?
መልስ(አና)
… እንደነገርኩክ ላለፋት ስምንት አመታት ወደ ኢትዮጵያ መምጣት አልቻልኩም። አሁን ያለውን በሚገባ መናገር ያስቸግራል።
ጥያቄ
አረ እንደው ከምታነቢያቸው ፁሑፎች፣ ከምትሰሚያቸው ሪፖርቶቾ በመነሳት…
መልስ
የመለስ አለመኖር ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው። ነገሮች የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆኑ እንኳን የፖለቲካው ምህዕዳሩን ለመክፈት የተሻለ አጋጣሚ ይፈጥራል ብዬ እገምታለሁ። መለስ በጣም ጎበዝ መሪ ቢሆንም አጭበርባሪ እንደሆነም መዘንጋት የለበትም። የእርሱ ገለል ማለት በሩን በተሻለ መንገድ ለመክፈት የሚፈጠሩ እድሎችን ያሰፉል።
ባለፋት ስምንት አመታት የአውሮፓ ዜጎችን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ኢንቬስተሮች በዚች ሀገር መዋዕለ-ንዋያቸውን ማፍሰሳቸውን ተረድቻለሁ። በተመሳሳይ መንገድ የመሬት ቅርምቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው በዚህ ወቅት መሆኑ መርሳት የለብንም። በዚህ ወቅት የሕንድና የሳውዲ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መሬት ቅርምት በሰፊው እንደተሳተፋ አውቃለሁ። በራሳቸው ሀገር ቁራሽ መሬት የሌላቸው ደሀ ገበሬዎች በሞሉባት ሀገር መሬትን ገንዘብ ላቀረቡ የውጭ ባለሀብቶች ማከፉፈል ከፍተኛ በደል ነው።
በአገሪቱ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የስራ-አጥነት አለ። ስራ-አጥነት በአውሮፓ አገሮችም ያለ ቢሆንም በኢትዮጵያ ካለው የኑሮ ውድነት አንፃር ሲመዘን ችግሩን የከፉ ያደርገዋል። ይሄ ለመንግስት ትልቅ ጫና ነው። አብዛኛው ወጣት የትምህርት ዕድል እያገኘ ሲመጣ ራሱን ከቀረው አለም ጋር ማነፃፀሩ አይቀርም። ባለስልጣናቱ ወደዱም አልወደዱም የለውጥ ማዕበሉን የሚቀበሉበት ጊዜ ይመጣል። አሁን ግን ሁሉንም የመወሰን ዕድሉም ይሁን ኃላፊነቱ ያለው በኢትዮጵያዊያን እጅ ብቻ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
=========================
ማስታወሻ፦ ሚስ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ስትሆን <> የሚል ሪፖርት ለፓርላማ አባላቱ በማሰማቷ በገዚው ፓርቲ(ኢህአዴግ) ጋር መቃቃሯ ይታወቃል።
(ሙሉ ፁሑፉን ከመጽሔቱ ጀባ ብያለው (ሙሉ ፁሑፉን ከመጽሔቱ ጀባ ብያለው )