addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

ኢሬቴድ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በህዝብ ስም እስከመቼ የወያኔ ፕሮባጋንዳ ማሰራጫ ይሆናሉ?

ከ አዲሱ ወንድ 12. 21. 2013
qq
የኢትዮጵያ ሬዲዮ መደበኛ ስርጭቱን በ1935 ጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደግሞ በ1964 የተመረቀ ቢሆንም በይፋ ከመመረቁ አስቀድሞ በ1963 አዲስ አበባ ላይ የተካሄደውን ታሪካዊውንና የመጀረመሪያውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ አስተላልፏል፡፡የኢትዮጵያ ሬዲዮና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ1995 ተቀላቅለው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን መስርተዋል፡፡ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም ቢሆንም ወያኔ አንባገነን በመሆኑ የራሱን ፕሮባጋንዳ ማሰራጫ አድርጎታል። አምባገነኖች የሚገዙትን ህዝብ ለመቆጣጠር ከሚወስዷቸው እርምጃዎች ቀዳሚው የመረጃ ፍሰትን መቆጣጠር ነው። እነሱ ከሚሉት ውጭ እንዳይሰማ ለማድረግ ወደ ህዝብ ጆሮ የሚደርሱትን ነገሮች ሁሉ የመቆጣጠር ተግባር ይፈጽማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ውሸትን ደጋግሞ በማውራት እውነት
ለማስመሰል ይተጋሉ። ይህ የአምባገነን ሥርዓቶች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ወያኔም በጉልበት ሚኒሊክ ቤተመንግሥት ከገባበት እለት ጀምሮ እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው። ወያኔ የመረጃ አውታሮችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ቀንና ሌሊት ውሸቶችን እውነት ለማስመሰል ይጥራል። ኢትዮጵያ ውስጥ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ስለሌለ አንዳንድ ወገኖቻችን ወያኔ ደጋግሞ የሚናገረዉ ዉሸት እዉነት ቢመስላቸዉ ልንፈርድባቸዉ አይገባም።
• ኢትዮጵያዊያን በዘረኝነት እጅግ በተማረሩበት፤ አገሪቷ በአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ሥር ወድቃለች በሚባልበት በአሁኑ ወቅት ከላይ የተጠቀሱት ሚዲያዎች የሚያወሩት በወሬ ብቻ ስለፈጠሯት በአካል ግን ስለሌለችው ኢትዮጵያ ነው።
• አጠገባቸው ሰቆቃ ሲፈፀም፤ ህፃናት ሲገደሉ፤ እናቶች ሲደፈሩ፤ ተማሪዎች ሲደበደቡ እያዩ “የኢትዮጵያ” ቴሌቪዥንና ራድዮ የሚያወሩት በወያኔ አገዛዝ ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩ ስለመሆናቸው ነው።
• ከአንድ ጎጥ የወጡ ሰዎች ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው ሃገሪቷን እየቦጠቦጧት ባሉበት ባሁኑ ወቅት፤ በዘራቸው ከጎጡ አባላት ውጭ የሆኑት አጃቢዎች የምስለኔን ያክል እንኳን ሥልጣን የሌላቸዉ መሆኑ እየታወቀ፤ ዘርና ሃይማኖት መሠረት ያደረጉ ግጭቶች አገሪቷን እያመሷት
እና እነዚህን ሁሉ በገዛ ዓይኖቻቸው እያዩ “የኢትዮጵያ” ቴሌቪዥንና ራድዮ የሚያወሩት ፍቅር ሞልቶ ስለመትረፉ እና የብሄር ብሄረሰቦች መብት ስለመከበሩ ነው።
• እነዚህ ሚዲያዎች ወታደሩ፣ ፓሊሱ፣ ደህንነቱ እና ራሳቸው የሚዲያ ተቋማቱ ሁሉም በዘረኝነት የተተበተቡ፤ ከሙያዊ ኃላፊነት ይልቅ ለጆሮ ጠቢነት ይበልጥ ትኩረት የሚሰጡ መሆናቸው እየታወቀ ስለዚህ ጉዳይ ትንፍሽ የማይሉ፤ በግልባጩ “ውጤት-ተኮር”፣ ቢ.ፒ.አር. እያሉ የሚያደናግሩ አደንቋሪዎች ናቸው።
• ፍርድ ቤቶች በፍትህ እያላገጡ ዋሾ ሚዲያዎች ትዕዛዝ የተሰጠባቸውን ዶሴዎች እየቆጠሩ ስለፍርድ ቤቶች “ምርታማነት” መጨመር ያወራሉ።
• የገበሬው ማሳ ተቀምቶ ለባዕዳን በመሰጠቱ ምክንያት የበርካታ ቤተሰቦች ለቅሶ ሰሚ ባጣበት ወቅት እነኚህ የክህደት ሚዲያዎች ሚሊኒየነር ስለሆኑ ገበሬዎች ድራማ ሰርተው ያሳያሉ።
• አገዛዙ ብር እያተመ፤ ድንገተኛ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔ ለውጥ እያደረገ አውቆ የፈጠረውን የኑሮ ውድነት በችርቻሮ ነጋዴዎች ላይ እያሳበበ “ስግብግብ ነጋዴዎች” ያመጡት ውድነት ነው እያለ ህዝብን እርስ በርሱ ማባላት ሙያው አድርጎታል።
• “ልማታዊ ጋዜጠኛ” እየተባለ የሚሸነገለው አድርባይ ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ እናቶች ልጆቻቸውን በፈረቃ የሚመግቡበት ዘመን መሆኑን እያወቀ፤ ምናልባት በገዛ ራሱ ኑሮም ጭምር ተጨባጭ እውነታውን እያየው መዋሸት ስላለበት ይዋሻል። ጥቂት ዘረኛ የገዢው ወያኔ አባላትና ምስለኔዎቻቸው ህይወት የምድር ላይ ገነት መምሰሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ መሻሻል ምልክት ነው እያለ ዓይኑን በጨው አጥቦ ይነግረናል። ይህ ዓይነቱ ሚዲያ ነው አሁን የኢትዮጵያን አየር ያጣበበው።
ይህ ሁሉ በአንድነት ሲስተዋል የነፃ ሚዲያ አስፈላጊነትን እጅግ አንገብጋቢ ያደርገዋል። ለመሆኑ
• ዘወትር ስለፈጣን ግስጋሴ ቢነገረውም የሚበላውን ያጣውን የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላትና ምስለኔዎቻቸው ስለሚያጋብሱት ገንዘብ ማን ሹክ ይለዋል?
• በጋምቤላ ገበሬ ላይ የደረሰው በደል በከፋም፣ በአሶሳም፣ በሲዳማም እየደረሰ መሆኑን እና በደሉ መላው አገሪቷን ያጠቃለለ መሆኑን ለህዝባችን ማን ይነግረዋል?• በኢኮኖሚ ለማደግ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መጠመቅ የማያስፈልግ መሆኑን የሌሎች አፍሪቃ አገሮች ልምድ
እያጣቀሰ ማን መረጃ ይሰጠዋል?
• በአገራችን ያለው ዘረኝነት በቶሎ ካልተገታ ወደ አስከፊ አዘቅት የሚወስደን መሆኑ ከዚሁ መንገድ ተጉዘው መራር ጽዋ ከተጎነጩ አገሮች ልምድ ጋር አስታኮ ማን ይነግረዋል?
• የኢትዮጵያ ህዝብ እውነት መች እና በምን ይሰማል? እነዚህ ነገሮች ሁላችንንም ሊያስጨንቁን የሚገቡ ጉዳዮች
ናቸው። ስለሆነም ለእውነት የቆመ ነፃ ሚዲያ በሃገራች ለማምጣት በአነድነት እንነሳ ።

Posted by Addisu Wond

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: