addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

የጃዋር መሀመድና የአንዳንድ አጨብጫቢዎች አደገኛ መንገድ በአጭሩ (ዋቅጅራ ሶሪ-)

mmmm
-“በእናቴ መንዜና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነኝ፤ በአባቴ የአርሲ ኦሮሞ እና ሙስሊም ነኝ፤ ከኔ ወዲያ ለኢትዮጵያዊነት ምልክት ሊሆን የሚችል የለም” ጃዋር ይህን ያለው ከዓመት በፊት ወጣቱ ተንታኝ እየተባለ በኢሳት በተደጋጋሚ ይቀርብ የነበረ ሰሞን ነው።
የተመቼው እና ፖለቲካዊ ንግዱ የደራለት ሲመስለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ተመሣስሎና አድፍጦ የቆየው ጃዋር መሀመድ ፤በግብጽ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ የሙርሲ ባለስልጣናት በአባይ ግድብ ያደረባቸውን ንዴት በግልጽ በቴሌቪዥን ተሰባስበው እየፎከሩ በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲዝ ቱ ሰማ። የሙርሲ ባለስልጣናት ከሰነዘሯቸው አማራጮች አንዱ ፦”የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን የሙስሊም ክንፍ ወይም ኦብነግን ማስታጠቅና መርዳት” የሚል መሆኑን የሰማው ጃዋር ሳይውል ሳያድር በአልጀዚራ ላይ ቀርቦ በግልጽ “ኦሮሞ ፈርስት”በማለት የኢትዮጵያዊነት ቆቡን አሽቀንጥሮ ጣለ። ሜንጫው ተከተለ፤የሙስሊሞችን የመብት ትግል ከኦነግ ጋር እያገናኘ ተናገረ፣ ኢትዮጵያውያን ከኦሮሚያ ይውጡ! እያለ መፈክር ሲያሰማ ተደመጠ…
እባብ ልቡን ዐይቶ እግር ነሳው እንዲሉ፤ አምላክ የሙርሲን መንግስት በአጭሩ ቀጨው እንጂ፤ የሙርሲ ሰዎች በስልጣናቸው ቢቀጥሉ ኖሮ የጃዋር መንገድ ወዴት ወዴት እንደነበር መገመቱ ቀላል ነው።
ከክፉ መንገዱ ሊመለስ ያልቻለው ጃዋር በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰባቸውን መከራ ተከትሎ በኖርዌይ የሚገኙ ተከታዮቹ ”እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም! ወንጀለኞች አይደለንም!” በማለት ስለወጡት እና የበርካቶችን ልብ ስላደማው ሰልፍ “ትክክል ነው” ብሎ ፃፈ። ሌላም ኢትዮጵያዊነትን የሚፃረር በርካታ ነገሮች ፃፈ፣ተናገረ።
ጃዋር በአጭር ጊዜ እነኚህን ሁሉ ስህተቶች አድርጓል። ፈጽሟል። ኢትዮጵያዊ ነኝ ለሚል እና በትክክል ስለ አገር ምንነት ለገባው ሰው ጃዋርን ለመኮነን እና ለመለየት ከነዚህ ስህተቶች አንድኛው ብቻ በቂ ነበር። ሆኖም ከልጅነት እና ከእልክ የመጣ ስህተት ይሆናል፣ ልጁ ነገ ጧት ከስህተቱ ተጸጽቶ መንገዱን እየመረመረና እያሻሻለ ሊመጣ ይችላል፤ ይህን ልጅ ብናቀርበውና በትክክለኛው መንገድ መሄድ ቢችል በዕውቀቱ አገሩንና ወገኑን ሊያገለግል ይችላል.. በሚል እሳቤ አንዴና ሁለቴ አልፈነዋል። ይህን ለፍቅርና አብሮ ለመኖር እንደተሰጠ ዕድል ስላየሁት ምንም አልመሰለኝም ነበር። እሱ ግን ከስህተቱ ሊመለስ አልቻለም።በተቃራኒው ጭራሽ እየባሰበት መጣ። ጃዋር እየሄደበት ያለው መንገድ፤ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ያለውን ርቀት አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ዓየን። የጃዋር ችግር ከግለሰቦችና ከፓርቲዎች ጋር ቢሆን የፈለገውን ያህል ዘመን ቢወስድ መታገሱና ማባባሉ ሊያስኬድ ይችል ነበር። ጃዋር ደጋግሞ እየወጋ ያለው ግን ኢትዮጵያዊነትን ነው። መንገዱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማፈራረስ ነው። ምንም ለማያውቁ ታዳጊ ህፃናት የፈጠራ ድርሰት እየተረከ ትውልድ እየለያየ ነው። አገር በጥላቻ እንዲናጥ እያደረገ ነው።
ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይመለስም እንዲሉ፤ ጽንፈኛው ጃዋር በአሁኑ ወቅት ከህወሀቶች ጋር በመሆን የዓፄ ምኒልክን ምስል ከሂትለር ጋር መሳ ለመሳ እያደረገ መበተን የደረሰበት ደረጃ ላይ ደርሷል። የማንነታችን( የኢትዮጵያዊነታችን) መሰረት፤ ማላገጫና መቀለጃ መቀለጃ ሆኗል። በበኩሌ ከዚህ በላይ በኢትዮጵያዊነት ላይ መሳለቅ ያለ አይመስለኝም። ለምን ምኒልክ ተነኩ አይደለም እያልኩ ያለሁት። ህወሀቶችም ምኒልክን ለዓመታት ሲከሱ ሰምተናል። ደግሞም ምኒልክ ይህን ፈፅሟል፣ይህን አድርጓል..የሚለው ክስና ወቀሳ አግባብ ያለውና ለውይይት በር የሚከፍት ስለሆነ ችግር የለውም። ጃዋርና ተከታዮቹ ግን ወደ አደገኛ ጽንፍ በመሄድ “ምኒልክ ሂትለር ነው” የሚል ጸያፍ፣ርካሽና ጨርሶ ለውይይት የማይጋብዝ ቅስቀሳ ነው እያደረጉ ያሉት። ጃዋር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ይህን ሲያደርግ ኢትዮጵያዊነትን፣ነፃነትን፣ማንነትን፣ እየናደና እያፈረሰ ነው ለማለት ነው የፈለግኩት። ስለሆነም ከሰፊውና ኢትዮጵያዊነቱን ለአፍታም ተጠራጥሮ ከማያውቀው ከወንድማችን የአሮሞ ህዝብ ጋር በፍቅርና በአንድነት መኖራችን ይቀጥላል፡፡ ወይም በግልጽ ለመናገር ያህል እኛ በኢትዮጵያዊነታችን ቅንጣት ጥርጥር የሌለን ኦሮሞዎች ከወንድሞቻችን ጋር በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር በፍቅርና በአንድነት መኖራችንን እንቀጥላለን።አገር ለማፍረስና ለመገንጠል እንዲሁም በብሔረሰቦችና በሀይማኖቶች መካከል ጥላቻና ልዩነትን ለመፍጠር ተግተው እየትቀሳቀሱ ካሉት ከጽንፈኞቹ ከነ ጃዋር ጋር ግን ልዩነታችን ሰፍቷልና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ልንታገላቸው ይገባል። ከወያነ ጋር የሚደረገው ትግል፤ ልጆቹንና ጉዳይ ፈፃሚዎቹን እነ ጃዋርን ሊያጠቃልል ይገባል። አውቀውም ይሁን ሳያውቁት በወሳኝ ሰዓት የኢትዮጵያውያንን ትግልን በማደናቀፍ የወያነን ዕድሜ የማስቀጠል ተልዕኮ እየፈጸሙ ያሉትን እነ ጃዋርን በቸልታ ልናያቸው አይገባም።
* * * *
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከላይ በጠቀስኳቸው ባለፉት ሂደቶች እኔን ከጃዋር በላይ ሲገርመኝና ሲያበሳጨኝ የቆየው ታዲያ “ኢትዮጵያ አገሬ” እያሉ ነጋ ጠባ የሚፎክሩ ሰዎች ተግባር ነው።በተለይ አንዳንድ “አክቲቪስት”ነን የሚሉና ነፋሱ ወደነፈሰብት እየጋለቡ የሚያራግቡ አጨብጫቢዎች፣ ነፃ ለመውጣት የምናደርገውን ትግል በመጎተትም ሆነ አገርን በማፍረስ እየተደረገ ባለው ሴራ ከጃዋር በላይ ተጠያቂ መሆናቸውን ሊያውቁት ይገባል።(ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው ሁላችሁም ታውቋቸዋላችሁ ብዬ ነው HL &BT) ነው።ያልገባኝ ነገር እነኚህ አክቲቪስት ተብየዎች አገር ለመገንጠል እየተጋ ካለ ጽንፈኛ ጋር የሚታከኩት ምን ትርፍ ለማግኘት ነው የሚለው ነው… የሀገር ጉዳይ የምንሞዳሞድበት እና የምናመቻምቸው ጉዳይ አይደለም። በኢትዮጵያ ጉዳይ ቁማር መቆመርና እከከኝ-ልከክህ መጫዎት አይቻልም። ከፈለጉ ምርጫቸውን አስተካክለው ከጽንፈኛው ከጃዋር ካምፕ ይቀላቀሉ። ያ ካልተመቻቸው ደግሞ በኢትዮጵያ ባንዲራ ስም መነገዳችውን ያቁሙ።
የሀገር ጉዳይ የዕውቀት ስታንዳርድ እያወጣን የምንሞጋገስበት፣ የምንኮፋፈስበት እና በፌስ ቡክ የምንጫዎትበት አይደለም።
Posted by Addisu Wond.

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: