addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

ጃዋርና መንጋዎቹ (ክፍል 4)

mmmm
ዓለማየሁ መሀመድ (ክፍል 4)

ምጥን መረጃ (ሀ)

አባ ሜንጫ ሰሞኑን ያልረገጠው ደጅ፡ ያላንኳኳው በር የለም። ቦይኮት በደሌን ከማወጁ ቀደም ብሎ በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ዶይቼ ቬሌ የአማርኛ ፕሮግራም አንድ የውይይት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ነበረ። በዚህ ውይይት ላይ ሶስት እንግዶች በአጼ ሚኒሊክ ዙሪያ ይሟገታሉ። አንጋፋው የኦሮሞ ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አንደኛው ተሳታፊ ነበሩ። ለእኚህ ጉምቱ ፖለቲከኛ የነበረኝ ትልቅ ግምት ተሸርሽሮ አፈር ከድሜ አሽቀንጥሬ የጣልኩት በዶይቼቬሌው ውይይት ላይ ነው። ጃዋርና እሳቸው በእድሜና በአገላለጽ ካልሆነ በቀር ፈጽሞ የሚለያዩበት ነገር አጣሁባቸው። በእስተርጅና መዘባረቅ በእርግጥ በእሳቸው አልተጀመረም። በእሳቸውም የሚቆም አይሆንም። ለኢትዮጵያችን እንደአባት የምመለከታቸው፡ ወጠጤ ፖለቲከኞች ሽምጥ ቢጋልቡ እንኳን የሚመልሱ፡ የሚያስታርቁ ብዬ ተስፋ ከጣልኩባቸው አዛውንት አንዱ አቶ ቡልቻ ነበሩ። ሰው ሲረክስ ለነገ እንደማይል የተረዳሁትም በእሳቸው ነው። ቀለሉብኝ። ከወርቅነት በአንድ ጊዜ የቆርቆሮን ዋጋ እንኳን ልሰጣቸው ከበደኝ።

ለማንኛውም የዶይቸቬሌው ውይይት አቶ ቡልቻ የዘረኝነት በሽታ የተጠናወታቸው፡ እንደ ወጠጤዎቹ አባ ሜንጫ በተረት ተረት ሀገር ለማመስ ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን ነበር ያጋለጣቸው። ከታሪክ ጋር ተላተሙ። አሻሮ ይዘው ከቆሎ ጋር ሞገቱ። አፈታሪክ ሰንቀው ከታሪክ ምሁር ጋር ቀረቡ።ከዚያም የሆነው ሆነ። በውይይቱ አቶ ቡልቻ በዝረራ ተሸነፉ። በቅጽበት ከሰፊው የፖለቲካ ስብዕናቸው ወርደው፡ ወደ ጎሳ መንደር ጓዛቸውን ጠቅልለው ገቡ። አቶ ቡልቻ የእድሜአቸውን መሆን አቃታቸው። በጠባብነት ጽኑ ህመም እንደሚሰቃዩ ተረጋገጠ። እናም በዜሮ ወጡ።

ይሄኔ በራሱ ጊዜ የኦሮሞ መሪነትን አክሊል የደፋው አባ ሜንጫ(ጃዋር) ከኒውዮርክ ተወነጨፈ። ለጀርመን ሬዲዮ የአማርኛ ፕሮግራም ክፍል ደብዳቤ ሰደደ። መንጋዎቹን አስፈርሞ፡ በዕለቱ ውይይቱን የሚመራው ጋዜጠኛ ‘’የሚኒሊክ የልጅ ልጅ ልጅ ነው፡ ሆን ብሎ; ያልተዘጋጁትን አቶ ቡልቻን በማቅረብ የኦሮሞን መብት አልከሰከሰው; ስለዚህ ጋዜጠኛው ከስራ ይታገድልን’’ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለሬዲዮ ጣባያው ሃላፊዎች ላከ። መቼም ልቡ ተራራ ነው። መንጠራራት ያውቅበታል።ባዶ ሜዳ ተወጠረ። ከማጠሩ ደግሞ መወጠሩ።

የጀርመን ሬዲዮ ሃላፊዎች ደብዳቤው ሲደርሳቸው ጉዳዩን የተረዱት በተቃራኒው ነው። ለካንስ እንደዚህ ያለ ሞጋች ውይይት ማዘጋጀት ይቻላል? የሚለው ነው ለጀርመኖቹ ጎልቶ የታያቸው። እናም ጋዜጠኛውን በርታ አሉት። አቶ ቡልቻ የተዘረሩት ስላልተዘጋጁ አልነበረም። ይዘው የቀረቡት አፈታሪክ ስለሆነ እንጂ። ተረት ተረት። እነጃዋር የወረወሩት ሰይፍ ዶለዶመ።

ምጥን መረጃ(ለ)

የአኖሌ ፈጣሪ; የሻዕቢያ ሴራ አስፈጻሚ; በስደተኛ ስም ስለላና ጸረ ኢትዮጵያ መርዙን በየሄደበት የሚተፋው ተስፋዬ ገብረአብ ሰሞኑን ድምጹን ያጠፋ የመሰላቸው ካሉ ተሳስተዋል። የቦይ ኮት በደሌ ዘመቻ ስውር አስፈጻሚ ስለመሆኑ የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውኛል። ተስፋዬ ሆላንድ የሚገኝ አንድ ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይዞት የወጣውንና ሚኒሊክን ጡት ቆራጭ አድርጎ ያቀረበበትን ዘገባ በሙሉ መረጃውን ያቀበለው ተስፋዬ ነው። ጃዋርና ተስፋዬ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ጋብቻ መፈጸማቸው የተረጋገጠበት አንዱ ማሳያ የተስፋዬ ለሆላንዱ ጋዜጣ የተንሸዋረረ መረጃ መስጠቱ ነው። ጃዋር ከስንቱ ተጋብቶ እንደሚዘልቅ እኔጃ! ኢትዮጵያ የምትጠፋ ከሆነ ከአጋንንት ጋርም ይወዳጃል። ለማንኛውም የሆላንዱ ጋዜጣ የተሰጠውን መረጃ ሳያላምጥ እንዳለ ዘርግፎታል። የሌላኛውን ወገን ሀሳብና አቋም ሳያካትት ጋዜጣው ታሪካዊ ስህተት ሰርቷል። በቀጣይ ኢትዮጵያውያን እዚህ ጋዜጣ ላይ ጫና ፈጥረው ይቅርታ እንዲጠይቅና በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያወጣ ማድረግ አለባቸው። ተስፋዬ ለውለታው የኦሮሞ ፈርስት መድረኮች ላይ እየተጋበዘ ነው።

ወደ ጉዳዬ ተመለስኩ

የጤሰው አቧራ በእርግጥ ሰከን እያለ ነው። የተቀሰቀሰው የጥላቻ ዘመቻ በረድ እያለ ነው። ጃዋራውያን በሌላ ሃይል ጣልቃ ገብነት የመጣን ውሳኔ ቀምተው በአስረሽ መቺው ለቀናት ቆይተዋል። ጃዋርና መንጋዎቹ ዳቦ ሳይቆረስ ስም ላወጡት የጥላቻ ዘመቻቸው(የቁቤ ትውልድ) ከወያኔ ባገኙት ቀጥተኛ ድጋፍ ያዙኝ ልቀቁኝ ብለው ከሰነበቱ በኋላ አሁን ጥርሳቸውን እየሞረዱ ነው። ከጥላቻ በቀር መልካም ነገር ለማሰብ ያልታደለውን አእምሮአቸውን እያስጨነቁት ነው። ማጥፋት እንጂ ማልማት ሲጀምርም ያልፈጠረላቸውን እጆቻቸውን ከፌስቡክ መንደር ለማያልፈው ጫጫታቸው እያሰናዷቸው ነው። የጭብጨባ ስካሩ ያለቀቀው አባ ሜንጫ(ጃዋር) ከታላላቁቹ የትምህርት ተቋማት ስታንፈርድና ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲዎች ያገኛቸውን ምጡቅ እውቀቶች ትራሱ ስር ወሽቆ መንጋውን ለሌላ ዙር የጥላቻ ዘመቻ ሊያሰማራ ጫቱን በማመንዥክ፡ ውስኪውን በመጨለጥ፡ የኒውዮርክን ኮረዶች በማማገጥ ጋር ታጅቦ እየተዘጋጀበት ነው። መቼም ፈጣሪ የልቡን አውቆት ለእባብ እግር ነሳው ነው የሚባለው? የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ወደ ሰማይ ቀዘነ ብሎ የነገረኝ ማን ነው?

በእርግጥ ማስረጃዎቹ እስከአሁን ከእጄ አልገቡም:: እየጠበኳቸው ነው። ለመዘግየቱ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለነገሩ ወያኔ እኔ ማስረጃዎቹን እየጠበኳቸው እያለ ሊያግዘኝ ነው መሰለኝ በይፋ ጋብቻቸውን አብስሯል። መቼም አመስግኜ የማላውቀውን ወያኔን ዛሬ ላመስግነው ይሆን? ደግ ነው። አንዳንዴም እውነት ታምልጣችሁ እንጂ!

የሄኒከን ኮንሰርቱን የመሰረዝ ውሳኔ የመጣው ከወያኔ መንደር በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ስለመሆኑ በእርግጥ ጃዋራውያን ያጡታል ብዬ አላስብም። አልጠብቅምም። ለራሳቸው እያጨበጨቡ፡ ውስኪ እየተራጩ መሆናቸው በአደባባይ እያሳዩት ያለው ጩኧት ቢሆንም በውስጣቸው ፡ በልባቸው ግን ወያኔን እያመሰገኑ ተላላኪውን ኦህዴድን ያኑርልን እያሉ መሆናቸውን መቼም ልብና ኩላሊት መመርመር የሚችለው ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው;; እነሱ ለራሳቸው ከካዱ ማለቴ ነው። ለማንኛው ወያኔ በኦህዴድ አማካኝነት ለሄኒከን ኩባንያ ማስፈራሪያ ሰጥቷል። የጸጥታ ዋስትና የከለከለው ወያኔ በጃዋርና መንጋዎቹ ጫጫታ ያልተንበረከከውን ሄኒከንን በመጨረሻም እጁን ጠምዝዞ ኮንሰርቱን እንዲሰርዝ አድርጎታል። የእነጃዋርና ወያኔ ጋብቻን ያሳበቀው ይኧው የኮንሰርት መሰረዝ የባረቀበት ይመስላል። ጃዋራውያን የሌላን ውሳኔ መንትፈው መጨፈራቸው ብዙም ርቀት ያልወሰዳቸው ለምን ይሆን? ከማጥቃት ወደ መከላከል በፍጥነት ተገልብጠው ‘’ድሉ የእኛ ነው;; ማንትስ ይመስክር; የአኖሌ አጥንት እሾክ ሆኖ ይውጋን’’ ዓይነት መሃላ እያዥጎደጎዱ ያሉት ማን ሞግቶአቸው ነው?

እግር ጥሎኝ ከፓልቶክ መንደር ባለፈው ሳምንት ጎራ ብዬ ነበር። የጃዋር መንጋዎች ‘’ጄኖሳይድ’’ ብለው ፓልቶክ ከፍተው ይንጫጫሉ። እንደ ቢንቢ ጆሮ ላይ ይጮሃሉ። የጡሉትን የአማርኛ ቋንቋ እያቀላጠፉት ሚኒሊክን ይረግማሉ። ቴዲን ይዘልፋሉ። አማራው ላይ የስድብ ናዳ ያወርዳሉ። የገረሙኝ ሁለት ነገሮች። አንደኛ ጄኖሳይድ ብለው የጫጫታ መድረክ መክፈታቸው ነው። ካልጠፋ ስም ምናለ ይህቺ የኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረአብ የብእር ጭማቂ በሆነችው የፈረደባት ‘’አኖሌ’’ ስም እንኳን ቢጠሩት? ወይም ‘’ጡት’’ ቢሉት?

ሌላው እድሜው ለአቅመ መናገር ያልደረሰ ሁሉ ማይክ እየጨበጡ ቋንቋ መለማመጃ፡ አፍ መፍቺያ ያደረገው አጼ ሚኒሊክ ላይ መሆኑ ነው። ይገርማል። አንድ ዓይነት ሰዎች። መንጋዎች። እንደ ሳሙና ፋብሪካ አንድ ዓይነት ምርቶች። ከንቱ።

ታዲያ ከዚያ ከጄኖሳይ ፓልቶክ ክፍል ለደቂቃዎች ቆይቼ ነበር። ድንገት የፓልቶክ ክፍሉ መሪ ብቅ አለና ‘’ኦቦ አባዱላ ገመዳ እዚህ ክፍል እንዳሉ እናውቃለን;; ጀግናው ወንድማችን! እናመሰግናለን;; እባካችሁ ለዚህ ወንድማችን ምስጋና እናቅርብለት;; አባዱላ –ገለቶማ!!’’ የፓልቶክ ክፍሉ መሪ በሞቅታ ይሁን በቴዲ ኮንሰርት መሰረዝ- ደስታ አስክሮት አይታወቅም እንደ ህጻን እየቦረቀ ምስጋናውን አዥጎደጎደጎደው። መንጋው ተከትሎ ለአባዱላ ገመዳ አበባ አበረከተለት። የፓልቶኩ ሎቢ ለአባዱላ በተበረከተ አበባ ተሽቆጠቆጠ። ጃዋር የለም። ስሙ አይጠራም። ቦይ ኮት በደሌ ዘመቻ አይነሳም። ኮንሰርቱ እንዲሰረዝ ያደረገው አካል ተመሰገነ። ተወደሰ። ‘’አባዱላ –ገለቶማ’’።በስውር ወያኔ የምስጋና መዓት ሸመተ። ለካንስ ምድረ የወያኔና ኦህዴድ ሹማምንት ነው በጄኖሳይድ ፓልቶክ ክፍል የሚርመሰመሰው?!

ታዲያ እነ ጃዋር ለምን ውስኪ ይራጫሉ? መንጋዎቹ ለምንስ መለኪያ ያጋጫሉ? ቺርስን ምን አመጣው? ኮንሰርቱ እንደሚሰረዝ ቀድሜ አውቄ ነበርና ጃዋር ዳንኪራ ሊመታ እንደሚመጣ ገምቼ ነበር። የሄኒከንን ውሳኔ ይፋ መሆን ተከትሎ ጃዋርና መንጋዎቹ ድል አደረግን ብለው ሰማይ ምድሩን ሊቀውጡት እንደሚችሉ ጠብቄ ነበር። የሆነውም የገመትኩት; የጠበኩት ነው። የህንድ ፊልም ቀሽም ነው የሚባለው የሚጠበቅ የሚገመት ቀጥሎ ስለሚሆን ነው። እነጃዋር እንደ ህንድ ፊልም ቀሽም ሆነው ብቅ አሉ። ዋንጫውን ለራሳቸው ሸለሙ። ለራሳቸው አጨበጨቡ። ራሳቸውን አወደሱ።አሞገሱ። አባ ሜንጫ ደግሞ አበጠ። ትልሿ ልቡ ተራራ አክላ ልትፈነዳ ደረሰች። ተንጠራራ። ተወጠረ። ከማጠሩ መወጠሩ።

የወያኔ የፌስ ቡክ ሰራዊት

ዳንኤል ብርሃኔ የሚባል አንድ ከፌስ ቡክ መንደር የማይጠፋ፡ ተከፋይ የወያኔ የፌስቡክ ሰራዊት ጠርናፊን የማያውቅ ያለ አይመስለኝም። ስለዚህ የወያኔ ጃንደረባ ብዙም የማውቀው ነገር የለም። በጫት ሱስ የሚስተካከለው እንደሌለ ሳር ቅጠሉ የሚመሰክሩለት፡ እነበረከት ስምኦን ምን እያሰቡ እንዳለ ለማወቅ ይሄን ጃንደረባ መከታተል ብቻ እንደሚበቃ የነገሩኝ ወዳጆቼ ናቸው። የፌስ ቡክ ሰራዊት ተዘጋጅቶለታል። ከወያኔ የመረጃና የደህንነት መስሪያ ቤት ሚስጢራዊ መዋቅር ተዘርግቶለታል። በጀት ተመድቦለታል። ስራ የፈቱ፡ በየዩኒቨርሲቲው ዓመታት ቢቆዩ የማይመረቁ ጆሮ በመጥባት ጆሮአቸውን ያሳበጡ አማተር ካድሬዎችን በስሩ አድርጎ በማህበራዊ መድረኮች ላይ ከዘመተ ሰነባብቷል።

ዳንኤል ጭፍን ነው። ዓይኑን በጨው አጥቦ ጥቁሩን ነጭ ነው ይላል። ሀፍረት፡ ይሉኝታ፡ ዕውነት፡ ሀቅ ሲያልፉም አይነካኩትም። ወያኔን ቀለም እየቀባ በየፌስ ቡኩ ግድግዳ ይርመሰመሳል። አጀንዳ ሲሰጠው ፌስቡክ፡ ቲውተርና ብሎጉ ላይ ይዘረግፋል። አጨብጫቢዎቹና አማተር ካድሬዎቹ ያጅቡታል። ወያኔን ቆንጆ ነው እያለ ይዘላብዳል። ሁል ጊዜም ያበሳጨኝ የነበረው የዳንኤል መርመጥመጥ ሳይሆን እሱ በቸከቸከ ቁጥር የሚሟገቱት የሚላፉት ናቸው።

ዳንኤል የሰሞንኛው የእነጃዋርና መንጋዎቹ ጩኧት የወያኔ የመደናበር ውጤት የመዘዘው የመጨረሻው ካርድ መሆኑን በይፋ አሳይቷል። ዳንኤልና ጃዋር ተስማምተው አንድ አጀንዳ ቀርጸው ተነስተዋል። ዳንኤል የጃዋር አለቃ ሊሆን ይችላል። ኦህዴድ የወያኔ አለቃ መሆን እንዴት ይቻለዋል? እናም ጃዋር ከኒው ዮርክ፡ ዳንኤል ከድሬዳዋ ተመሳሳይ እሳት መትፋት ጀመሩ። ዳንኤል ሌላም ተረት ተረት ጀባ ብሎናል። ጃዋር ሚኒሊክን ጡት ቆራጭ አድርጎ ይጮሃል። መንጋዎቹን ያስጠናል። ዳንኤል ደግሞ ሚኒሊክ ወደትግራይ ሰራዊታቸውን ሲያሰማሩ የትግራይ ወንዶችን ቆለጥ ይቆርጡ ነበር አለና አረፈው። የባሰ አታምጣ ነው መቼም። ትግራይ ላይ የቆለጥ ሀውልት እንዳያቆሙና በሳቅ እንዳያፈነዱን??!!!

መንጋዎቹ

የኦሮሞ ወንድሞቼና እህቶቼ በእርግጥ ሁሉም ከጃዋር ጋር እያበዱ ነው ማለት አይቻልም። የጃዋር ስካር ወላፈኑ የደረሳቸው፡ የሰሙትን ሳያላምጡ በስሜት ብቻ ተደፋፍረው ሞቅታ ውስጥ ገብተው ድንኪራውን እያቀለጡት ላሉት ጃዋራውያን የማሰቢያ ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል ባይ ነኝ። ጃዋር ሲለቀልቅ ተንጋግቶ ማጫፈር ጃዋርን አሳበጠው እንጂ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ስንዝር እንኳን ፈቅ አላደረገውም። በጃዋር ፌስ ቡክ ላይ እያደፈጡ ለሚውሉ የኦሮሞ ወንድሞቼና እህቶቼ ከመንጋው ወጥተው ማሰብና ሰከን ማለት እንዳለባቸው ብመክራቸው ደስ ባለኝ። በዘር ማሰብ የደካማነት ሁሉ መጨረሻው ነው። አንድ ሰው አቅም ሲያጣ ሮጦ የሚወሸቀው በዘር ስብስብ ውስጥ ነው። መዳንም መሞትም በጅምላ አይደለም። በሰማይም በምድርም ለፍርድ የምንቀርበው በግል እንጂ በዘር ስብስብ አይደለም። የጃዋር መንጋዎች ሰከን በሉ። ከስካር ውጡ። ሃንግቨር ላይ ያላችሁም በቶሎ ተላቀቁ።

ማጠቃለያ

ወያኔ ኦህዴድን አሰማርቷል።የመጨረሻውን ካርድ ስቧል። ተስፋዬ ገብረአብ ስራውን እየሰራ ነው። ጃዋር እናት ድርጅቱን ለማዳን የሞት ሽረት ትግል ላይ ነው። ኦህዴድን(ወያኔን)። የቦይ ኮት በደሌ ዘመቻና የሰሞኑ ጫጫታ የወያኔ ስሌት መሆኑን ያላመነ ካለ እሱ አውቆ የተኛ ነው። ቢቀሰቅሱትም አይሰማም። በታሪክ መጽሀፍት ውስጥ ተደብቆ የመቶ ዓመት ክስተትን በሸውራራው እያነሱ ዛሬን በጨለማ መጋረድና የነገን ተስፋ ማጠልሸት የ21ኛው ክፍለዘመን ጭንቅላት አይደለም። ጃዋር ከንቱ ነው። በእድልም በጥረትም ለማይገኙት ከሚከብዱት ከታላላቆቹ የትምህርት ተቋማት ዕውቀት ሸምቶ እሱ ዘር ቆጠራ ውስጥ ጭልጥ ብሎ በመግባት የህዝብ እልቂት የሚጋብዝ መሆኑ ከማንም በላይ ለተማረባቸው ዩኒቨርሲዎች ውርደት ነው። ድንጋይ 40 ዓመትም ውሃ ውስጥ ቢቆይ መዋኘት አይችልም። ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቻቸውን አይከታተሉም ማለት ነው? ሰው መቀየር እንደማይችሉ ፍንጭ የሰጠበት ይሆን የጃዋር ሁኔታ?

ሽልም ካለ ይገፋል ቦርጭም ከሆነ ይጠፋል። የእነጃዋር ዳንኪራ ከአንድ ሰሞን ግርግር እንደማያልፍ ይታወቃል። ይኧው እየከሰመ ነው። ወያኔ ለጊዜው እፎይታን አግኝቶ ሊሆን ይችላል። እነጃዋር አዲስ አበባ ገብተው የጨፌ ኦሮሚያን ስልጣን የሚቆጣጠሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። የኦሮሞና የሌላው ኢትዮጵያዊ ትግል ግን ፈር ይዟል። እነጃዋር የወያኔ ነፍስ ለማስቀጠል ያደረጉት መፍጨርጨር ብዙም ርቀት አልወሰዳቸውም። ከዚህ በኋላ ምናልባት የቀናት ጉዳይ እንጂ ጫጫታው እስከመኖሩም ይጠፋል።

ቸር እንሰንብት
source http://ecadforum.com/Amharic/archives/10653/
Postedd by Addisu Wond.

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: