addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

አዜብ መስፍን ሕዝቡ ለመለስ ፋውንዴሽን ብዙ ለማዋጣት ፍላጎቱ ከፍተኛ ነው ቢሉም፡ ሕዝቡ – የሕወሃት ጦር ጭምር – ዘረፋውን ተቃወመ

ነሃሴ ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም (ኢሳት ዜና):-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሠራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ($10.00) ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሠራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። ባለፉት 3 ቀናት መከላከያን ጥሎ የጠፋ አንድ ወታደር እንደገለጸው፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ እንደሚገኝና የሚከዳው ሰራዊት ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል። በተከዜ አካባቢ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ የአንድ አካባቢ ሰዎች የሆኑ የመከላከያ አዛዦች እየተጠቀሙ ነው የሚለው አባሉ፣ ከእነሱ ውጭ ያለው የመከላከያ አባል በችጋር እየተጠበሰ ባለበት ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል እንደገና መዋጮ መጠየቁ ብዙዎችን ስሜት የረበሸ ሆኗል ብሎአል።

እነሱ ተጨማሪ ገቢ አላቸው፣ እኛ ግን የምትሰጠንን ደሞዝ እንኳ ቆጥበን ለቤተሰቦቻችን እንዳንረዳ በመዋጮ እና በሰበብ አስባብ ይወስዱብናል ሲል ተናግሯል።

በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣ በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።

________________________

በሌላ በኩል ደግሞ ቀደም ሲል ኢሳት እንደዘገበው፡ ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በሚል በአገሪቱ ያሉ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው በአማካኝ ከ17 እስከ 25 ሚሊዮን ብር ከህዝብ እንዲሰበስቡ ቢታዘዙም የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈለገው 300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች ትርፉ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። በአማራ ክልል 106 ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ለፋውንዴሽኑ ማሰሪያ 2 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ይሰበሰባል።

በኦሮምያ ደግሞ ከ205 በላይ ወረዳዎች ሲኖሩ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል። በትግራይ ከ38 ወራዳዎች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ፣ በደቡብ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ሲዋጣ፣ በአዲስ አበባ የሚወጣው ደግሞ እስከ 2 ቢሊዮን ብር ይደርሳል። በመላ አገሪቱ በሚገኙ ወረዳዎች ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣ ሲሆን፣ ለፋውንዴሽኑ ከተበጀተው 300 ሚሊዮን ብር ውጭ ያለው ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅና ቁጥጥር የሚያደርግ አካል አለመኖሩንም ምንጮች ገልጸዋል።

ደሃው በምግብ ውድነት: ነጋዴው በግብር: አርሶአደሩ በማዳበሪያ እዳ እየተሰቃዩ ባለበት ጊዜ ይህን መክፈል አይቻልም በማለት ተቃውሞ ያስነሱ ሰዎች፣ ተቃውሞቸአውን የሚሰማቸው አካል አላገኙም። አንዳንድ ዜጎች ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ለኢሳት በመላክ፣ ዝርፊያው እንዲቆም ህዝቡ ተቃውሞ እንዲያሰማ እየጠየቁ ነው። የመለስ ፋውንዴሽን፣ የቀድሞውን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን የሚዘክሩ ስራዎችን የመስራት አላማ አለው። ፋውንዴሽኑ በህዝብ ፈቃድ እና ከመንግስት በሚሰጥ ገንዘብ ይሰራል ተብሎ ቢነገረም፣ ህዝቡ ለማዋጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ በግዴታ እንዲያዋጣ እየተደረገ ነው። ከህዝብ ፈቃድ ውጭ የተሰራ ፋውንዴሽን ፣ ኢህአዴግ እስካለ ጊዜ ብቻ እንደሚቆይ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፣ ፋወንዴሸኑ ከደሃው ኢትዮጵያዊ ገንዘብ መሰብሰቢያና ሃብት ማካበቻ መሆኑንም አክለዋል።

________________________

ወደምናስታውሰው፡ ነግር ግን ማስታወሳችንን ወደምንጠላው ስንመለስ፡ በቅርቡ ወይዘሮ አዜብ መስፍን በቴሌቢዥን ቀርበው፡ ለመለስ ፋውንዴሽን ሕዝቡ ከፍተኛ መዋጮ ለማድረግ ስሜቱን ገልጿል ሲሉ መስማቱ ይታውሳል። ይህም፡ በዚህ እንኳ ለመታመን አለመብቃታቸውን እንደገና አረጋግጧል።

በተጨማሪም፡ እንደ መዥገር አሁንም በቅጥፈት ዓለም ውስጥ ኑሮአቸውን ለማደላደል የሚጥሩት ኢትዮጵያዊቷ (ትግራዊቷ? ወልቃይት ጸገዴይቷ?) ማሪ አንቷኔት ወይንም ኢሜልዳ ማርቆስ መሆናቸውን ለመገንዘብ ከማስቻሉ ባሻገር፡ በሙቱ ስም እንደተለመደው በዘረፋ ሃብት በማካበት ሲሰማሩ ምንም የማይሰማቸው፡ ሰው በላ፡ የሚያሳፍሩ የዘረፋና የቅጥፈት ቋት መሆናቸውን አሳይቷል።

አዜብ መስፍን ሊገነዘቡ የማይችሉት አንድ ሀቅ አለ – የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁላቸውንም አክ እንትፍ ካለ ስንብቷል!

ምናልባትም ቅጥፈት፡ ስግብግብነት፡ ይሉንታ ዕጦት፡ ሃሰትና ጭካኔ የሕወሃት ሰዎች እውርነት መንስኤ ሊሆን ስለሚችል፡ ይህም የጋርዮሽ ባህሪ ሳይሆን አይቀርም። ለዚህ ነው ከነወሮበላ ባህሪውና እስከነምናምንቴው፡ የሕወሃት አስተዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ የተጠላና በመንግሥትነት ዐይን የማይታይ የሆነው!

ሁላቸውንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፋረድበት ቀን እሩቅ አይደለም!

________________________

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: