addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

ቴዲ እያለን ያለው ፓራራምችንን ወደ ታም ተራራም ቀይሩ ነው !!!

111
ልክ ..ሜሬ አርምዴን ወደ አርምዴ ሜሬ እንደቀየረው፡፡እናም ሜሪ ዘበናዮች ስማችሁን ቀይሩ ባባታችሁ ስም አርምዴዎች ሁኑ! ከዛም አረመደመደው ትሆናላችሁ!!

.የሰሞኑ የቴዲ አፈሮ ነጠላ ዜማ ሳስብ ትዝ የሚለኝ አንድ የአማርኛ ተረትና ምሳሌ ነው፡

አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
አንድዶ ለብልቦ አቃጥሎ ፈጃችሁ..

የሚል በአጤዎቻችን ዘመን በአንዱ ግፍና በደል በዛባት አንዲት ባለቅኔ የጠለቀቀየዛን ዘመን ኘጠላ ዜማ ነው፡፡የዚህ ቅኔ ፍቺ ለማግኘት አማርኛ ቋንቋ ጸናጋሪ ብቻ ማወቅን አይጠይቅም፡፡የተባበት ዘመን ነባራዊ ሁኔታና የባለቅኔው አስተሳብና አመለካትም ይጨምራል እንጂ፡፡አባሌ ስለ ቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም የሆነ አንድ መስመር ነገር ለማለት ፈልጌ ነው፡፡በደንብ በሀረግና በአርፍተ ነገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በቃል ደረጃም ወርዶ ምንሊል ፈልጎ ነው ለሚለው ነገር ሌላ ጊዜ የምንመለስበት ቢሆንም፡፡የቴዲ አፍሮን የዘፈን ግጥሞች ብዙ ጊዜ ላስተዋለ ሰው በብዛት ጊዜ /ታሪክ ተምሳሌታዊናንቡር ጠቃሽ የሚባል ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ይህንን ነገር ወደፊት በስፋ የምናየው ይሆናል ፡፡ለዛሬ ግን ልክ እላይ ….አንድ እግር በርበሬ….በተባለበት መንገድ የእነ ሰባ ደረጃ፣ዘበናይና አርምዴ ሜሪ…ትንሽ ፍንጭ ለመስጠት፡፡የአንድ እግር በርበሬ አይነት መልእክት ለህዝብ ለማስተላለፍ ..እንደተለመደው ..ማምለጫ ..የሚባለው የቅኔ ማልበሻ ስልት መጠቀም ግድ ነው፡፡አንድ እግር በርበሬ ፊትለፊት ሲታይ ከጓሮ/ከማሳ ስለበቀለው የተክል አይነት ቢመስልም ሲፋቅ ግን ስለአንድ ግፈኛ ንጉስ የሚናገር ነው፡፡ቴዲ አፍሮ የገጠር ልጅ ቢሆንና ጥሪውንናብሶቱን ይገልጽ የነበረው እንዲህ ባለ ..አንድ እግር በርበሬ …ይሆን ነበር ይሆናል፡፡ የከተማ ልጅ ስለሆነ ግን ነገሮችን የከተማ ስሜትና ህይወት እያለበሰ ነው፡፡የሚገርመው ደግሞ በዚህ ዘመን ስሜቱን የሚገልጽበት፣ ምሳሌ ሊሆነው የሚችል ነገር አላገኘም መሰለኝ ወደኋላ ሄዶ .የዚህን ዘመን ስንትና ስንት ፎቅ ጥሎ ፍቅሩን በሰባ ደረጃ ላይ ጥዷታል፡፡ ለጉዟችን ቲኬት የምንቆርጠው እዚህ ጋ ነው፡፡ቴዲ አፍሮ በዚህ ዘመን ምን አጥቶ ነው ወደ ኋላ የሄደው በማለት፡፡ሰባ ደረጃንስ ለምን መረጠው? ከድሮ ነገር ሌላ ጠፋ እንዴ ? ሜሪ አርምዴ ምን ትሰራለች? ብዙ ጥያቄ ከከመርን በኋላ ወደ መተንተን እንገባለን፡፡ አሁን ጊዜያችን አይደለም፡፡ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ጠብቁን፡፡

ቴዲ አርቆ የቀበራቸው መልእክቶቹ ሲተኮሱ ምናልባትም ቃላት ብቻ ሳይሆኑ ሚሳኤልም ሊወጣቸው ይችላል፡፡ቴዲ አፍሮ ከእስር እንደወጣ በራሱ ህይወት ዙሪያ ላይ በብዛት የተጠመዱ ግጥሞችን ነበር ያበዛ የነበረው፡፡ፍቅርና ትዳ ር የለበሱ ሙዚቃዎች፡፡በቃ ተነፈሰ መብራቱም አለቀበት ብዬ ነበር፡፡ትቼው ነበር፡፡ አሁን መመለሱ ሳይ እኔም ደስ አለኝና በእሱ ላይ በደንብ ለማሰብ፣ ለማውጣትና ለማውረድ ግድ የሚል ሙድ ውስጥ ገብቻለሁ፡፡ፓራራም በበዛበት ሀገር ጥበብና ብስለት ተጠቅሞ እንዲህ ታም ፓራራም እያለ ..ስለአንድ እግር በርበሬ ሲነግረን ዝም ማለት ያለብን አይመስለኝም፡፡እንዳልኩት ነው ፡፡ወደፊት ፡፡ለአሁን ግን የዛን ዘመን የሰባ ደረጃዋ ዘመን ቀበጥ ግን ሰለሀገሯ ግድ ስለነበረችው ዘበናይ ሜሪ አርምዴ አንድ ነገር ልስጣችሁ፡፡ሜሪ አርሜዴ ምን እንኳን የዘመኑ ኮተት ካልዘመንሽ ብሎ ቢያስቸግራትም አስተሳሰቧን እንዳባቷ ነበር፡፡ቴዲም ሜሪን አርምዴ ብሎ ነው የጠራት፡፡ምንም ዘበናይነት ቢከብድባትም መብለጭለጭ ብታበዛም፡ በአስተሳቧ ግን የአባቷ ዘመን ሰው ነበረች፡፡ቴዲ የዝህንዘመን ነገር ለማሸነፍ የዚህ ዘመን ሰዎች በአባቶቻችን እንድንጠራ ፣ እንደእነሱ እንድናስብ ይፈልጋል፡፡ቴዲ አፍሮ በዚህ ዘመን ጆኖችና ጆሲዎች መንፈስ የጠከፋ ነው የሚመስለው፡፡ወደ አባቶቻችሁ ርስት ተመለሱ እያለ ነው፡፡ሜሪ አርምዴን ወደ አርምዴ ምሪ ነገሩ እንደዛ ነው፡፡በዚህም ላይ ብዙ ይባልበታል፡፡ለወደፊቱ ይጠብቁን፡፡ወርም ሁለት ወርም ይፍጅ አይቀርም ፡፡ለዛሬ ግን በሰቧ ረጃዋ ዘመን ሰው በዘበናይቷ ሰው፣ቴዲ በአባቷ ስምየጠራት፣ልክ እንድባቷ ባላት፣ ለዚህ ዘመን ዘበናዮች ..አትነሱም ወይ እየዘመኑ ሀገር መውደድ አይቻልም ወይ ..የሚል መልእክት ያስተላለፈባትን ሰው ፡፡የአርምዴ ምሪን ኧረ ፋኖ ፋኖ እጋብዟቿለሁ፡፡ተጋበዙልኝ፡፡ከዛም ቴዲ አንድ እግር በርበሬን–ለመንቀል ሰባ ደረጃ መውጣት ነው ብሎናልና መልካም ጉዞ ወደ ሰባ ደረጃው፡፡https://www.youtube.com/watch?v=_0nqeHJUMu8

ኩርፊያው ለማነው ኩርፊያው ለማነው
ጦር ሲወረወር ለእኔም ላንተም ነው!
( ከተሳሳትኩን አላውቅም እንዲህ የሚል ግጥም አለው)
Play Video
Ethiopian Music by Merry Armide Fano.

በ፸ ደረጃ፡ ትግል ቃስቃሽ ሙዚቃ በሰምና ወርቅ

Tedy Afro’s ቀረርቶ for ዘበናዮች

ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ !
ኧረ ተው በለው
ኧረ ተው በለው

አብረህ ተነስተህ አናቱን በለው
አይዦሽ እናቴ አትጨነቂ
እኔ አለሁልሽ ክብርሽ’ ጠባቂ!
እንደ ቆላ ወፍ እንደ ግሪሳ፥
ያረፈው ልቤ ደግሞ ተነሳ
ተም–ተራራም ተራራም!
ተም–ተራራም ተራራም

…ሲመሽ ወደ ማታ ሁሉ ዘግቶ በሩን….
…ታም ታራም ሳረገዉ ብቅ በይ ክራሩን…

፸ ደረጃ ((ውጣውረድ፣ከባድ ፈተና))

7 (ሰባት)ያለበት ነገር ሁሉ እወዳለሁ እናም ለዛ ነው ያለፕሮግራሜ ወደዚህ ገጽ የመጣሁት!!እግረ መንገዴ ልንገራችሁ፡ በቅርብ ቀን አንድ ሰበር ዜና ወይም ልዩ የምስራች ብል ይሻላል፡ይዤ እመጣለሁ-በቅርብ ቀን!!

——-በሰባ ደረጃ—–

ከመኮንን ድልድይ ከእንጨት ፎቁ በላይ
ሲመሽ እንገናኝ
መጣሁ አንቺን ብዬ ሳይከብደኝ እርምጃዉ
በሰባ ደረጃዉ

አዝማች፡
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
በፍቅር ማነቂያዉ ዶሮ እንዳይል በከንቱ እረ አንቺን ወዶ ..(ዶሮ ማነቂያ፣ ዕሪ በከንቱ)
ክራሩን ስትሰሚ ብቅ በይ ቆሞያለሁ ከበርሽ ማዶ

ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ

ማታ ማታ
ማታ ማታ

አምጣት ከጎኔ ትቀመጥ
እንጀራ አይቀርብም ካለወጥ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለዉ
ማነዉ ካላችሁ ማነዉ ማነዉ?

ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሏን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ

ዘበናይ ዘበናይ….

ሲመሽ ወደ ማታ ሁሉ ዘግቶ በሩን
ታም ታራም ሳረገዉ ብቅ በይ ክራሩን

ታም-ታራራም-ታራራም…..

ፀጉራን ተተኩሳዉ እንደ አርምዴ ሜሪ
ዘበናይ ናት ፍቅሯን በክራር ነጋሪ.

ታም-ታራራም-ታራራም…..

ሄዶ ከኮሪያ ዘማች ሲመለስ
ያወሳል ናፍቆቱን በክራሩ ድምጵ
ፍቅርሽ አስጨንቆ መላወስ አቃተኝ

ተደናበርኩልሽ ጥይት እንደሳተኝ
ሳተና ነበርኩኝ ተካሽ በመዉ ዘሬ
ለዘበናይ ብቻ እጄን ሰጠሁ ዛሬ

አዝማች

በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
እንደ አውራ ዶሮ ክንፍ ኮቴን እየሳብኩት መሬት ለመሬት
በዞርኩት ገላሽን ሳትወጣብኝ ፀሀይ ሳይነጋብኝ ሌት

ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ

ማታ ማታ
ማታ ማታ

ሞልቶ በአራዳ የአርመን ዳቦ
ሳሳ አካላቴ ሰዉ ተርቦ
አቅፎ ገላዉን አልጠገብ ያለዉ
ማነዉ ካላችሁ ማነዉ ማነዉ?

ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሏን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ

ዘበናይ ዘበናይ….

አይወጣም ደረጃ ቢፈጥን ሴሼንቶ
እንደኔ ካሌደ በፍቅር ተገፍቶ

ታም-ታራራም-ታራራም…..

መድፈሪያሽ ወርቅ ነዉ ብርም አይገዛሽ
ልብ የሌለዉ ሀብል ግድም አይሰጥሽ

ታም-ታራራም-ታራራም…..

ከአንገትሽ ላይ አርጊኝ እንደማርትሬዛ
ወደወዲያ እንዳልል አደብ እንድገዛ
ተከለከለ አሉ የንጉስ አዳራሽ
የክት ያለበሰ አይገባም በጭራሽ
መጣሁ ከኮሪያ ይዤልሽ ሰዓት
በፓሪ ሞድሽ ላይ አምርሽ ታዪበት

ዘበናይ ዘበናይ….

ግጥምና ዜማ፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግ፣ ኪቦርድ እና ቤዝ ጊታር፡ ዳግማዊ ዓሊ
ናሙና ዝግጅት፡ አብርሃም ዘዉዴ
ክራር፡ ታመነ መኮንን
ድምጵ ቀረጳ፡ ክብረት ዘ/ኪዮስ
ፕሮዲዩስድ፡ በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: