addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

ጃዋር ወጣቱ የፖለቲካ ስካር ፣ የ-ግለት እና የግለኝነት አብሾ ( ሄኖክ የሺጥላ )

እንጀራውን > በተገፉ እና በተከፉ ሰዎች ታሪክ ላይ ያደረገ ሰው ፣ ህይወቱን በሰዎች መከራ ላይ የገነባ ሰው ፣ ኑሮውን ባጋጣሚ ለድምጽ አልባ እና አቅም አልባ ወገኖቹ ለታይታ በመቆጨቱ ፣ የድንቡሎ መና ሰው የመሆን አቅሙን የነጠቀበት ሰው ፣ ከሚያገኘው ቤሳ ጋ ፍቅር በመውደቁ ብቻ ሕዝባዊ መቆጨትን ፣ ወይም ለተጠቁ በጋራ መጮህን የግል ንብረቱ ሊያደርግ የሚያስብ ሞኝ ፣ስለምንም አይነት ምድራዊ ምክንያት ፣ ስለ ስብአዊነትም ሆነ ስለ አንድነት እና ፍቅር ልታስረዳው ፣ ልታስተምረው ወይም ልትመክረው አትችልም ። እኔ ብሎ እየኖረ ለእኛ ነው የማለቅሰው የሚል ጠባብ ፣ ራሱን ከተበተበበት የግለኝነት ውል አልባ ቋጠሮ ፣ ከኔ-ወዲያ ላሳር በሚለው ምስኪን ነብሱ ውስጥ ሁሌም የምታየው ትንሽነቱን ብቻ ሳይሆን ፣ ተፈጥሮው ትልቅ ለመሆን ያልተፈጠረ ፣ ትልም አልባ ፣ ሕልም አልባ ጭንጋፍነቱንም ጭምር ነው ። እንዲህ አይነት ሰው ምንምን ወደ ፊት የመግፋት አቅም የለውም ፣ ግን ደሞ እንደ ጨጎጊት የመንፈስን መቀነት መያዙ ፣ እንደ እሾህ የሚራመዱ እግሮችን መውጋቱ ፣ ማድማቱ እና ትንሽም ቢሆን እንከን እና ስንካር መሆኑ ግልጽ ነው ። ምክንያቱም ራሱን ትልቅ ለማድረግ ፣ ከፊት ሆኖ ለመታየት እና ለመግነን ማናቸውንም አይነት ክፋት ከመፈጸም ልቡ ተው የሚለው አይነት ስላልሆነ ፣ ምክንያቱም የጆሮ ግንዱ የተሸከመው የስጋ ቅጠል፣ ከራሱ ሌላ ማናቸውንም አይነት ድምጽ ለማዳፈን የተሰራ የመስሚያ ቅንቡርስ እንጂ የማዳመጫ አካል ስላልሆነ ።
ጃዋርን ሳስብ ከላይ የገለጽኩት ሁሉ ገልጾ የማይጨርሰው አይነት ሰው እንደሆነ እረዳልሁ ። በጃዋር ልቦና ውስጥ ሀገር የሚባል ነገር የለም ፣ ሕዝብ የሚባል ነገር የለም ፣ ወገን የሚባል ነገር የለም ! ለጃዋር አማራ ፣ ኦሮሞ ፣ ጉራጌ ፣ ወዘተ የሚባል ኢትዮጵያዊ የለም ፣ በጃዋርኛ ፖለቲካ ውስጥ የምትመለከተው ጃዋርን ብቻ ነው ። የጃዋር ቁባ ነው የሚያበራው ፣ ኦሮሞነት ከጃዋርነት ቀጥሎ የሚመጣ ፈሊጥ ነው ። በመሰርቱ ጃዋር ትልቅ የማንነት ቀውስም ያለበት ሰው ነው ። ይህንንም ስል ጃዋር እራሱን ለራሱ ሲል ክዶ ያመነ ፍጥረት ነው ። ምን ማለቴ ነው ? ሃሳቡን በአዲስ መስመር እናብራራው
ጃዋር ከመንዜይቱ እናቱ እና ከ ኦሮሞው አባቱ የተወለደ ባለ ውብ ቀለም ኢትዮጵያዊ ነበር ። ምን ያረጋል ነበር ብቻ ሆነ ። ጃዋር ንጉስ ዔድፐስን ይመስለኛል ( ልዩነቱ ጃዋር እናቱን ገሎ አባቱን ማግባቱ ካልሆነ በስተቀር !) እንጂ ታሪካዊ ስሜታቸው አንድ አይነት ነው ። አባቱን ገሎ እናቱን ያገባ ሰው ትልቅ ሀጥያት ሰራ ልንል እንችላለን ፣ እናቱን ገሎ አባቱን የሚያገባ ወንድ ግን ምን ሊባል እንደሚችል እኔ አላውቅም !
ጃዋርን በተለያየ የፖለቲካ መተጣጠፍ ውስጥ ነው የማውቀው ። ከዚህ በፊትም ገልጨዋለሁ ፣ የጃዋር መንፈስ የቀንድ አውጣ አይነት ነው ፣ ኮሽ ሲል የሚጠቀለል ፣ ጭጭ ሲል የሚዘራጋ ። ጃዋር ብልጥ ነው ፣ ብልህ ግን አይደለም ! ብልጠት ደሞ ከአንድ ቤተሰብ የማያልፍ ታሪክ ያለው አቋቋም ነው። ለዚህም ነው የታሪክ አምድ ዋልታዎቹን የገነባው በብልሆች ጥበብ እንጂ በብልጦች ማንነት ላይ ያልሆነው ።
ጃዋር ያልሆነውን ሆኖ ለማያውቀው ነገር የቆመ አጋፋሪም ይመስለኛል ። ምሳሌ ልጥቀስ
የኢትዮያ ሙስሊሞች ( በይበልጥም ሙስሊም ኦሮሞዎች ) የአቢሲኒያን የፖለቲካ የበላይነት መያዝ እንዳለባቸው የሰበከበትን አንድ ቪዲዮ አስታውሳለሁ ። ግን ጃዋር ማን ነው ? እስልምናን እሱ የሚቆረቆርለትን ያህል ያውቀዋል ወይ ? ይህንን አጠገቡ ያሉት ሰዎች ነገ ከነገ ወዲያ ወጥተው እንደሚመሰክሩ አልጠራጠርም ። አንዳንድ ግልጥ ማስረጃዎችን ግን ለመጠቆም እወዳለሁ ። ጃዋር የራሱ ቤት ( ማጀቱ ) እስልምናን ያውቃል ወይ ? መልሱ አጭር ነው አያውቅም ። ከላይ እንደገለጽኩት ጃዋር ለእስልምና የቆመው በእስልምና በኩል መቆም እንደሚችል ስለሚያውቅ ብቻ ነው ! ጃዋር ለኦሮሞውጭ የቆመው ፣ በኦሮሞውጭ ስም መቆም እንደሚችል ስለሚረዳ ነው ። በጃዋር ዓለም ከጃዋር ፊትም ሆነ ከጃዋር ወዲያ ማንም የለም እሱና እሱ ብቻ ።
ዛሬ በኢትዮያ በሸዋ እና በወለጋ ኦሮሞዎች የሚደረገው ትግል የጃዋር ትግል የሆነው ስላመነበት አይደለም ፣ አጋጣሚ ስለፈጠረለት እንጂ ። አንድ የኦሮሞ ሕዝብ መረገጥ የሚቆጨው ሰው በምን አይነት ሂሳብ ነው የኦሮሞ የማንነት መሰረት የሆነው የኦሮምኛ ቋንቋ በሌላ ሚዲያዎች ሲነገር ሲሰማ ሊከፋው የሚችለው ? እንዲህ ማለት ነው
ለምሳሌ ጃዋርየቀዶ ጥገና ሀኪም ቢሆን ፣ ከበሽተኛው ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን በአድ ነገር ለማውጣት የበሸተኛውን ሆድ ዕቃ ከፍቶ እንደጨረሰ በሽተኛው ራሱ የቀዶ ጥገና ሀኪም መሆኑ ሲረዳ ፣ ይሄማ ቢድን ስራዬን ስለሚቀማኝ ቢሞት የሻላል ብሎ የሚል አይነት ሀኪም ነው ። በጃዋር ውስጥ ከጃዋር ሌላ ማንም የለም ። ሊኖርም አይችልም ! ጃዋር ወጣቱ የፖለቲካ ስካር ፣ የ-ግለት እና የግለኝነት አብሾ። ሕዝብ ሞኝ ነው ያሉ ቂሎች ዛሬ የት እንዳሉ አለማወቅህ ግን ያሳዝነናል ።
jewar

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: