addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the month “June, 2013”

Thousands gather for rival rallies in Egypt

321
Cairo – Thousands of people have converged on Tahrir Square, the focal point of the Egyptian revolution, to demand the resignation of Egypt’s first democratically-elected leader, Mohamed Morsi.

The scene on Sunday was a far cry from a year ago today, when supporters packed the square to celebrate Morsi’s inauguration. Now many are back to blame him for a stagnant economy, worsening security and an ongoing lack of basic services.

Demonstrators waved red cards and chanted “irhal” – “leave”, and promised to camp in the square until Morsi resigns. Thousands more have joined marches headed for the presidential palace, and are expected to arrive around dusk.

“It’s the same politics as Mubarak but we are in a worse situation,” said Sameh al-Masri, one of the organisers on the main stage. “Poverty is increasing, inflation is increasing. It’s much worse than Mubarak.”

Morsi came to power last year following the revolution against dictator Hosni Mubarak.

Protesters directed their anger not just at Morsi but the ruling Muslim Brotherhood, which in two years has gone from a banned movement to the rulers. “Mosques should be for religion, not for politics,” said Ahmed Sultan, a student.

The US government was also the target of anger, with one banner reading: “America supports killers of the Egyptian people”.

Al Jazeera talks to political analyst Shadi Hamid
The anti-Morsi protests have been organised by a grassroots campaign calling itself Tamarod, meaning “rebellion” or “insubordination”, which claims to have collected the signatures of 22 million Egyptians demanding the president leaves office.

The petition has no legal standing, but it has nonetheless tapped into widespread public anger towards Morsi. The president has made a number of controversial decisions since taking office, most notably a November decree which shielded his decisions from judicial review.

Egypt’s economy is in free-fall: The pound has dropped in value by nearly 20 percent since he took office, foreign investment has withered, and businesses are paralysed by widespread fuel and electricity shortages.

“He’s borrowed money from everyone in the world,” said Said Ahmed, referring to $11 billion in loans Egypt has received from Qatar, Saudi Arabia and Turkey to prop up the economy. “Who’s going to pay for that? Our children.”

Human rights abuses are widespread, rights groups say, with Morsi’s administration doing little to rein in the notorious security services.

“We gave him the confidence to … correct what Mubarak had done to Egypt, but he didn’t. So we have the right to withdraw the confidence that the Egyptian people gave him,” said Eman el-Mahdy, a spokesperson for Tamarod.

Calls to resign

Morsi’s supporters liken the calls for his resignation to a coup, arguing that the only way to remove him is through new elections. They carried signs at Friday’s rally insisting that the president’s “legitimacy is a red line”.

“If we are saying that we have a majority, and the opposition are saying that they have a majority, how can they decide?” asked Nader Omran, a spokesman for the Freedom and Justice Party – the political wing of Muslim Brotherhood.
“What is the other solution for this dilemma, except the ballot box?”

Mass protests mark Morsi’s tumultuous year
It remains to be seen if Tamarod’s campaign can sustain their momentum after Sunday.

Even if the protests draw large crowds, the calendar might work in Morsi’s favour: Brutally hot Cairo days could stifle protests, and the dawn-till-dusk Ramadan fast, which begins around July 8, will discourage public demonstrations.

Role of the military

But there are fears that the protests on Sunday could descend into violence.

Clashes have spread across governorates outside the capital in recent days, with four Brotherhood supporters killed in attacks on the group’s offices, and two people killed in fighting in Alexandria on Friday, including a US citizen.

Amid the growing unrest, tanks and other military vehicles have started to appear on the streets of Cairo.

General Abdel Fattah al-Sisi, the defence minister, warned last week that the army had a duty to “prevent Egypt from slipping into a dark tunnel of civil unrest”.
http://www.aljazeera.com/news/middleeast/2013/06/20136300534547448.html

የአልሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ገደሉ

cc
(ቪኦኤ) የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ዛሬ መግደላቸውን የአማፂው ቡድን ቃል አቀባይ ዛሬ አስታወቀ፡፡ አንደኛው የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ የታወጀበት ነው፡፡
አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ’አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ በአባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ማለታቸውን አመልክቷል፡፡

“ሁለቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ አሻፈረን ብለው አንገራገሩ፣ በተኩስ መካከል ተገደሉ፤ አምላክ ነፍሳቸውን ይማርና በገነት ያስቀምጥ፡፡ ሃሣቡ እነርሱን ለመግደል አልነበረም፡፡ በቁጥጥር ሥር አውለን እሥልምና ችሎት ፊት ልናቀርባቸው ነበር፡፡” ነው የሚለው ከዚህ ጋር የተያያዘው አብዱልአዚዝ በሶማሊኛ ያሠራጨው መልዕክት፡፡

ሰዎቹ የተገደሉት ከሞቃዲሾ 350 ኪ.ሜ በስተደቡብ በምትገኝ ብራቫ የምትባል ከተማ ውስጥ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የተገደሉት ሰዎች እነማን እንደሆኑ የአል-ሻባብ ቃል አቀባይ አልተናገረም፡፡ ይሁን እንጁ የቪኦኤ ሶማሊኛ አገልግሎት የተለያዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን አነጋግሮ ኢብራሂም ሃጂ ጃማ ወይም ኢብራሂም አል-አፍጋን ወይም በተቀጥያ መጠሪያው አቡ ባካር አል-ዛይሊዪ እየተባለ ይጠራ የነበረውና ሼኽ አብዲሃሚድ ሃሺ ኦልሃዬ ወይም በቅፅል ሞዐሊም ቡርሃን መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

መሪዎቹ የተገደሉት የዛሬ አሥር ቀን ሰኔ 12 መሆኑንም የቪኦኤ ምንጮችን የጠቀሰው የሶማሊኛ አገልግሎት ዘገባ አመልክቷል፡፡

የአል-ሻባብ ምንጮች እንደሚሉት አል-አፍጋን የተገደለው ከመስጂስ እየወጣ ሳለ በተተኮሰበት ተርታ ጥይት ሲሆን ሙዐሊም ቡርሃን የተገደለው ከቤቱ ተይዞ ከተወሰደ በኋላ ነው፡፡

ሌሎችም ተኩሶች የተሰሙ እንደነበረ ቢታወቅም የደረሰ ጉዳት ወይም ጥፋት ይኑር አይኑር ለጊዜው አልታወቀም፡፡

ይህ አጋጣሚ ከተፈጠረ ከሁለት ቀናት በኋላ ለተገደሉት ሁለት ሰዎች የቅርብ ወዳጅ እንደነበረ የሚነገረው ዋነኛው የአል-ሻባብ መሪ ሼኽ ሐሰን ዳሂር አዌይስ ከአካባቢው በጀልባ ካመለጠ በኋላ ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ተይዞ እጁ ለመንግሥት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ከተገደሉት አንዱ ኢብራሂም አል-አፍጋን በአል-ሻባብ ውስጥ በርካታ የሥልጣን ቦታዎች የነበሩት ሲሆን የቡድኑ ምክትል መሪ፣ የገንዘብ መምሪያው ኃላፊና የኪስማዮ ገዥ ሆኖ ሠርቷል፡፡

ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ያሉበትን መረጃ ለሚሰጥ በእያንዳንዳቸው ራስ የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ ማስታወቂያ ካወጣችባቸው ሰባት የአል-ሻባብ መሪዎች አል-አፍጋን አንዱ ነው፡፡

አል-አፍጋን ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቨርጂንያ ውስጥ ይኖር የነበረ ሲሆን እአአ በ1980ዎቹ ውስጥ ከሙጃሕዲን ጎን ተሰልፎ ለመዋጋት ወደ አፍጋኒስታን መሄዱንና በ1991 ዓ.ም የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ሲወድቅና ሥርዓተ-መንግሥቱ ሲፈራርስ እጅግ የከፋ ዓይነት ጂሃድ ወደ ሶማሊያ ማስገባቱና ሶማሊያ ውስጥ የመጀመሪያውን የጂሃድ ማሠልጠኛ ሠፈር ማቋቋሙን ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

አል-አፍጋን ከአል-ቃይዳው መሥራችና መሪ ኦሣማ ቢን ላደን ጋርም ብዙ ግንኙነቶች እና ንግግሮች እንደነበሩት ቢን ላደን በ2011 ዓ.ም ከተገደለ በኋላ ሲናገር ይሰማ እንደነበር ታውቋል፡፡

ሌላው ተገዳይ ሙአሊም ቡርሃን አል-ሻባብ ውስጥ ዋነኛ የሚባል የሃይማኖት ሊቅ እና የቡድኑ የመማክርት ምክር ቤት አባል እንደነበረ ተገልጿል፡፡

የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ዛሬ መግደላቸውን የአማፂው ቡድን ቃል አቀባይ ዛሬ አስታወቀ፡፡ አንደኛው የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ የታወጀበት ነው፡፡

አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ’አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ በአባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ማለታቸውን አመልክቷል፡፡

Audio http://realaudio.rferl.org/voa/AMHA/2013/06/29/7bb1ed17-29ad-4c75-b778-a8320144d533.mp3

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=4839

በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀው መከላከያ ሂሳቡ እንዳይመረመር ታዘዘ

vv-የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ባቀረበው ሪፖርት የመከላከያና የደህንነት ተቋማት
የፋይናንስ አያያዝ ከፍተኛ ችግር እንዳለበት ማመልከቱን ተከትሎ በየመ/ቤቶቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት በቀጥታ
እነዚህን ተቋማት በተለየ ሁኔታ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ እየተረቀቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ለፓርላማው ባቀረቡት የ2004 ዓ.ም
የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ ሪፖርት በተለይ በዘጠኝ መ/ቤቶች 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር
ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኖ መገኘቱን፤ ከዚህ ውስጥ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብሩ የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑን
መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
እነዚህ ተቋማት ላወጡት ገንዘብ ትክክለኛ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ተጠይቀውም ማቅረብ አለመቻላቸውን ለፓርላማው
ሪፖርት ካደረጉ በኋላ በተለይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈረጌሳን ጨምሮ የተለያዩ ሹማምንት ሪፖርቱን
በአደባባይ እስከማብጠልጠል የደረሰ ትችት ሲያቀርቡ ተደምጠዋል፡፡ ዋናው መከራከሪያቸውም የመከላከያ ወጪ ሚስጢር
ነው የሚል ነበር፡፡

ይህንን ተከትሎ የፓርላማ አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ በቴሌቪዥን ቀርበው “ባልተሟላ ሰነድ
ወጪ ተደረገ ማለት ብሩ ተበላ ማለት አይደለም” በማለት ማብራሪያ ለመስጠትና ተቋሙን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ
ሞክረዋል፡፡

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያቸው የሆነውን መግለጫ ትላንት ጠዋት
በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡበት ወቅት በተመሳሳይ መንገድ መከላከያን ኦዲት ማድረግ
ሚስጢር ማባከን መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ሁኔታውን ለማስተካከል አዲስ ሕግ እንደሚወጣ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ዋና ኦዲተር በአዋጅ ቁጥር 669/2002 መሰረት የፌዴራል የመንግስት ተቋማትን ኦዲት የማድረግና የማስደረግ ሙሉ ሥልጣን

እንደተሰጠው ጠቅላይ ሚኒሰትሩ አስታውሰው በዚህ ሕግ መሰረት ባለፉት ዓመታትም መከላከያን ጨምሮ ሁሉንም ተቋማት ኦዲት ሲያደርግ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ በሚያዚያ ወር 2004 ዓ.ም የ2003 የሂሳብ ሪፖርት ለፓርላማው ቀርቦ እንደነበር በዚህም ሪፖርት መሰረት

ከተወቀሱት ተቋማት መካከል መከላከያ አንዱ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ በ2003 በጀት ዓመት በመከላከያ 133 ነጥብ
8 ሚሊየን ብር ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩን፣ የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በወጪ
ተመዝግቦ መገኘቱን ሪፖርት አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ካልተቻለው ገንዘብ መካከል 1
ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የመከላከያ ሲሆን ፣ 54 ነጥብ 3 ሚሊየን ደግሞ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ 33
ነጥብ 34 ሚሊየን ብር የአገር ውስጥ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ መሆኑ መጠቀሱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ መ/ቤቱ
እንደዘንድሮ ከፍተኛ ቅሬታ ያላቀረበ ሲሆን የዘንድሮ ቅሬታ ምናልባትም በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ላይ ተጽዕኖ በማሳደር
ነገሩን ለመሸፋፈን የታሰበ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል፡፡

ምንጮቻችን እንደገለጹት በአገሪቱ ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጸምባቸው ተቋማት መካከል ግንባር ቀደሙ መከላከያ መሆኑን
አስታውሰው አንድ ወርሃዊ ደመወዙ 4 ሺ ብር የማይሞላ ከፍተኛ የመከላከያ ሹም በአዲስአበባ ቁልፍ ቦታዎች ጭምር
በሚሊየን ብር የሚገመቱ ቪላዎችንና ሕንጻዎችን የሚገነባበት እንዲሁም ትልልቅ ንግዶችን የሚያንቀሳቅስበት ሁኔታ
የአደባባይ ሚስጢር ነው በማለት የእነአቶ ኃይለማርያም ሙግት ጥቅሙ ለሙሰኞቹ ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ ሕግ በቀጣይ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ዋና ኦዲተር ሕጉ እስኪጸድቅ
መከላከያና የደህንነት ተቋማትን ኦዲት እንዳያደርግ መታዘዙንም ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ 60 ከፍተኛ ጀኔራሎች መካከል 58ቱ በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሀት አባል ሆነው የመጡ ናቸው።

መከላከያን ከላይ ሆነው የሚዘወሩት 7ቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በሙሉ የህወሀት ታጋዮች ናቸው። ባለፉት 22 አመታት በዚህ ከፍተኛ

አመራር ውስጥ የሌላ ብሄር ተወላጅ ተካቶ አያውቅም።

በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሀይለማርያም በአባይ ግድብ ዙሪያ ከተቃዋሚዎች ጋር እንደማይነጋገሩ አስታውቀዋል።

ኢሳት ዜና

ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

1የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ – ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና መጠላለፍ ነው ብለዋል። ጄ/ል ክንፈ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደሆነ ያስታወሱት ምንጮቹ ከስልጣን ሊያግዳቸውም ሆነ ሊያወርዳቸው የሚችለው በህግ ስልጣን የተሰጠው ጠ/ሚኒስትሩ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚሁ መሰረት ስልጣኑ በአዋጅ የተቀመጠው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪይም ቢሆንም – በግልፅ የሚታየው ግን ከህግ ውጭ የጄ/ል ሳሞራ ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ ከመሆኑ በተጨማሪ የታገደውን ጄ/ል ወደ ቦታው የሚመልሰው በተቃራኒው የቆመውና በሕወሐት ውስጥ ያለው የነስብሃት ቡድን መሆኑን ምንጮቹ ያመለክታሉ። አቶ መለስ ይዘውት የቆዩትና “በሕገ-መንግስቱ ተሰጠ” ከተባለው ስልጣን በአብዛኛው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ሊሰጥና ሊተላለፍ አልቻለም ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ ቁልፍ የሆነው የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነትን ጨምሮ በርካታዎቹ ሕገ-ወጥ በሆነ ሁኔታ በሕወሐት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን ምንጮች ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም ፥ « ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን እንዲሁም « አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ ያለውን ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በሌላም በኩል የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ብ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ በበኩላቸው፥ ከእንግሊዝ አገር ረቀቅ ያለ መሳሪያ በማስመጣት በስካይፕ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉትን ግንኙነቶች በመጥለፍና ተዛማች የስለላ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ከገለፁ በኋላ « ግንቦት ሰባት ከግብፅ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለህዝቡ ከነገርነው ከጎናችን ይቆማል፣ ግንቦት ሰባትን በማውገዝ የእንቅስቃሴው ተባባሪ አይሆንም፣ በአገር ውስጥ ያሉትም ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ህዝቡ አይቃወምም፤ እንዳውም ለመንግስት ድጋፍ ይሰጣል፤» በማለት በተሰብሳቢ መኮንኖች ጭምር ገረሜታን የፈጠረ ንግግር ማድረጋቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። በዚህም ለሕዝብ ያላቸውን ግምትና የግንዛቤ ደረጃ ያመላከተ ነው ያሉት ምንጮቹ የጄ/ል ተክለብርሃን የእውቀት ደረጃ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። የኤንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአቶ ደብረፂዮን ጭምር በበላይነት እንደሚመራና አቶ ሃ/ማሪያም የሚያውቁት እንደሌለ ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በሕገ – መንግስቱ መከላከያ ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ ቢደነግግም፣ ከወረቀት በዘለለ ተግባር ላይ ሲውል እንደማይታይና የነሳሞራና ተከታዮቻቸው ተደጋጋሚ አቋምና ተግባር በቂ ማስረጃና ማሳያ መሆኑን ምንጮቹ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል። በመጨረሻም፥ የታገዱ ሌሎች ጄኔራሎችን ጉዳይ እንዲሁም ባለፈው ወር በሳሞራ ትእዛዝ የተባረሩ የሕወሐት ጄነራሎች ወደ ከፍተኛ ንግድ መሰማራት በተመለከተ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።

source,,,: http://www.zehabesha.com/

የሀገር ልጅ ፌስቲቫል ነገ ይደረጋል፤ መታሰቢያነቱ ለጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ እና አቶ ተስፋዬ ተደርጓል!

as
ከወዳጃችን ጋዜጠኛ ካሳሁን ፌስ ቡክ የተቀዳ ወሬ!

የሀገር ልጅ ፌስቲቫል ነገ June 30
የኢትዮጵያ ስፖርት በሰሜን አሜሪካ
፨መታሰቢያነቱ ለፒያሳው ልጅ ፍቅሩ ኪዳኔ (Secretary General of the African Sports Journalists Union (1970-1974), member of FIFA Press Committee, director of the executive officer of the president of The IOC )እና ለአቶ ተስፋዬ ለማ (The late Tesfaye was a composer, choreographer, conductor, and cultural expert)zxከወዳጃችን ጋዜጠኛ ካሳሁን ፌስ ቡክ የተቀዳ ወሬ!

፨ከገቢው ላይ በዐረብ ሀገር ለሚሰቃዩ እህቶቻችን የሚሰጥበት
፨ዘፋኞች መሐሙድ አህመድ፣ ቴዲ አፍሮ፣ቴዲ ታደሰ፣ ጃሉድ፣ ብርሀኑ ተዘራ…
፨እውቅ ኳስ ተጨዋቾች ኃይሌ ካሴ፣ ለማ ክብረት፣ ተካበ ዘውዴ፣ …
፠ዋና እንግዳ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ
ሰብሰብ፣ሞቅ ደመቅ፣ ሸብረቅረቅ…

*ESFNA SINCE 1984
(photo from left Fikru kidane & Tesfaye Lemma)
http://www.abetokichaw.com/

የውጭጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁንም በስብሰባ ላይ ሲዋረዱ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/4854 qw

ሰበር ዜና በጎንደር ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላት መታሰራቸው ቁጣን ቀሰቀሰ

09-አንድነት በየትኛውም የመንግስት ህገወጥ ጫና ሰልፉን እንደማይሰርዝ ይፋ አድርጓል

በጎንደር ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 4 የአንድነት አባላት በፖሊስ መታሰራቸው በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ አንድነት ምንም አይነት ህገወጥ እስር በጎንደር የተዘጋጀውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደማያስቆመው አሳውቋል፡፡

ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ በጎንደር ሰኔ 30 የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የሚመለከት በራሪ ወረቀት በማሰራጨት ላይ የነበሩት አለልኝ አቧይ፣ ዋኘው፣አብርሀም ልጅ አለም፣አንጋው ተገኝ የተባሉት የአንድነት አባላት ህገወጥ በሆነ መንገድ በአካባቢው ፖሊሶች መታሰራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችን እንዳስቆጣ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመላክቷል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወረቀት በመበተናቸው ብቻ የታሰሩት ግለሰቦች ሁኔታ የስርአቱን አምባገነንነት አመላካች ነው፡፡

የዞኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች “እስር ለጎንደር ነዋሪ በተለይም ለአንድነት አባላት አዲስ አይደለም” ካሉ በኋላ “የታሰሩት አባሎቻችንን ለማስፈታት ከምናደርገው ጥረት ጎን ለጎን የቅስቀሳ ስራው እንዳይስተጓጎል ተጨማሪ አባላት የቅስቀሳ ስራውን እንዲቀጥሉ ወደ ስፍራው ልከናል፡፡” ብለዋል፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሙላት ጣሰው ለሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ ለአቶ ግዛቴ አብዩ ስልክ በመደወል የታሰሩት የአንድነት አባላት በአፋጣኝ መፈታት እንዳለባቸው ተናግረው ገዢው ፓርቲ የሚያደርገው አፈና ከህዝባዊ ንቅናቄ እንቅስቃሴያችን አያስቆመንም በማለት አሳስበዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ የሚጠበቅበትን ስለሰልፉ የማሳወቅ ተግባር አጠናቆ ቅስቀሳ የጀመረ ቢሆንም በበጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ የተቃውሞ ሰልፉን አላማ የሚያብራራ በራሪ ወረቀት በማሰራጨት ላይ የነበሩ አባላቱ በህገወጥ መንገድ ከመታሰራቸውም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን አባላት የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያ ወደ ጎን ብለው ቅስቀሳውን አጠናክረው መቀጠላቸውንና የአከባቢው ነዋሪም በራሱ ተነሳሽነት በራሪ ወረቀቶችንና መረጃዎችን በማስተላለፍ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ዞን አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታውቀዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ በጎንደር ለሚደረገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የጎንደር ከተማና አከባቢው ነዋሪዎች በስፋት እንዲሳተፉ በቀየሰው ስትራቴጂ መሰረት ስኬታማ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ሁለተኛው የቅስቀሳ ቡድንም ዛሬ ወደ ጎንገር መንቀሳቀሱ ታውቋል፡፡

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=4743#sthash.UBpKOHPk.dpuf

ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?

445
ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?

ባለፈው ጊዜ አንድ ወዳጄ ጋር አዲሳባ ስልክ ደውዬ ሳናግረው በአካባቢው ከእርሱ ድምጽ ጎልቶ የሚሰማ የመኪና ጥሩንባ ሰማሁና ይሄ ሁሉ የመኪና ጥሩምባ ምንድነው… ብዬ ጠየኩት፡፡

ሃይለማሪያም ደሳለኝ እየገቡ ወይም እየወጡ ነው መሰለኝ መንገድ ተዘጋግቷል፡፡ አለኝ፡፡

ወዲያውም ቀጠል አድርጎ፤ እንደ ሀቁ ቢሆን ኖሮ መንገድ መዘጋጋት የነበረበት ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ሳይሆን ለተመስገን ደሳለኝ ነበር… አለኝና በቁጭት፤ ይሄው የሚያጅቡትን አያቀውቁምና… እልኩ እያታዘብኩ ነው…! ሲል አወጋኝ!

ተመስገን ደሳለኝ ገዢውም ተገዢውም ፓርቲ ሊያመሰግነው የሚገባ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ነገር ግን ገዢዎቻችን ማመስገን የሚቆጥር ይመስል ሰውን ማመስገን አይወዱም፡፡ ስለዚህ ተሜንም በማመስገን ፈንታ ከሰሱት፡፡ ጎሽ በማለት ፈንታ እንደ ጎሽ ሊወጉት ቀንዳቸውን አሾሉበት፡፡ እሰይ በማለት ምትክ ሰይ ባንከረባብት ብለው ለሁለቱም አሰቡት፡፡ (ለማሰርም ለማሰደድም) (ሰይ ባንከረባብት በልጅነታችን ብይ ጨዋታ ላይ ተወርዋሪዋ ብይ ጉድጓዳ ውስጥ ብትገባም የተቃራኒውን ብይ ብትመታም ነጥቡ እንዲያዝልን ውል የምንገባባት ቃል ነበረች፡፡)

ተመስገን ደሳለኝ እንዲሰደድ መንግስት ከፀሎት ጀምሮ ሁሉንም አይነት የትግል ስልቶችን እንደተጠቀመበት ትዝ ይለኛል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ጊዜ ምንም የቀጠሮ ወረቀት ወይም መጥሪያ ሳይሰጠው በራዲዮን፤ “ተመስገን ደሳለኝ በሌለበት የፍርድ ሂደቱ ታየ ለሚቀጥለው ጊዜ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርበው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል!” የሚል አይነት ዜና በሰላም ቁጭ ብሎ ሻይ በሚጠጣበት ካፌ ውስጥ ሰማ፤ (እናጋን ካልን ደግሞ ዜናውን እንደውም ያነበቡት ተሜ ልክ ዜና ሲሰማ አይተው ነው…! ማለት እንችላለን…) የዚህ ዜና አላማ ግልፅ ነበር፡፡ ተሜ ደንግጦ ፖሊስ ሳይዘው በፊት መንገዱን እንዲያያዘው ማድረግ ነበር፡፡ ወዳጃችን ግን፤ ብታስሩኝ ባለ ጊዜም ባለ ብረትም ናችሁና እግሬ እምቢ ማለት አይቻለውም፡፡ ለመሰደድ ግን እሺ የሚል እግር የለኝም፡፡ ብሎ እንቅጩን ነገራቸው እና የመጣው ምጣ ብሎ ቁጭ አለ…

በነገራችን ላይ ተመስገን እስከ አሁን ድረስ በመንግስት የተሰነዘረበት ክስ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ እንደው የሪከርድ መዝጋቢ መስሪያ ቤቶች የሚያስታውሳቸው አጥተው እንጂ ከዚህ ሁሉ ክስ ጋር አብሮ መኖር የቻለ ጋዜጠኛ ብለው ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሚያሰፍሩት ሁሉ ይመስለኛል፡፡ መንግስታችን በክስ ላይ ክስ ሲደራርብ ሲደራርብ ክሱ ተቆልሎ አለመናዱም የእግዜር ተዓምር ነው፡፡ አንዱ ሳይቋጭ አንዱን አንዱ ሳይቋጭ አንዱ ክስ ሲመጣ በአሁኑ ሰዓት ተመስገን ደሳለኝ ከሃምሳ በላይ ክሶች ጋር ተመስገን ብሎ እየኖረ ነው፡፡

የተሜ እና የእኛ ፍትህ ጋዜጣ “መለስ ሞቱ” በማለቷ እኛ ሳንል ምን ሲደረግ እንዲህ ትያለሽ ተብላ ከሳላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ተደረገች፡፡ (የመለስ አምልኮ ይሎዎታል ተመስገን…!) አንዱ ሲዘጋ በአንዱ እንከሰታለን በምትለው ስትራቴጂ መሰረት፤ አዲስ ታይምስ ተተካች፡፡ አዲስ ታይምስ ደግሞ “ብር ከየት አምጥታችሁ ነው…” ተብላ ህትመቷ ተከለከለ፡፡ መንግስታችን እንደሆነ ኮሚክ ነው ጮክ ብለን በያይነቱ ስናዝ ራሱ “ብር ከየት አምጥተው ነው” ብሎ ይጨንቀዋል፡፡ በእርሱ ቤት እርሱ አበል ያልሰጠው ሰው፤ ወይም ከአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ያልተበደረ ሰው ምንም ገንዘብ የለውም…!

ተመስገን እና ጓደኞቹ እጅ መስጠት ብሎ ነገር አያውቁም ነበር፤ እና ከየትም ከየትም ብለው ድጋሚ ልዕልና ጋዜጣን አበረከቱልን፡፡ መንግስት መንግስት ሆኖ እንጂ… በብስጭት ካቲካላ ይጠጣ ነበር፡፡ ግን ሳይጠጣም ሞቅ አለው፡፡ ሰከረም፡፡ እናም ልዕልናንም ጥርቅም አድርጎ ዘጋት፡፡ (ይህ ውሳኔ የሞቅታ ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም)

ተመስገን ደሳለኝ ሲናገር ሰዎቻችን ደስ አይላቸውም፡፡ እናም በተቻለ አቅም ዝም ማሰኘት ይፈልጋሉ፡፡ ልጁ ግን በቀላሉ ዝም ብሎ የሚያስደስታቸው አልነበረም፤ በማህበራዊ ድረገፆች የሚተነፍሰውን ይተነፍስ ጀመር፡፡

ኢህአዴግ ሰው እንደማትንቅ ያወኩት እኔ ምስኪኑን ሳይቀር ለመከታተል የደህንነት ሰው የመደበች ዕለት ነው፡፡ ለተመስገን ደሳለኝማ ሁሉን አቀፍ የትግል ስልት ነው የተጠቀመችበት፡፡ በእውነቱ ከሆነ፤ ለአንድ ግለሰብ ሁሉን አቀፍ የትግል ስልት መጠቀም ትልቅ የሀይል ብክነት ነው፡፡ ፍጹም ተመጣጣኝ ያልሆነ ርምጃ፤ ጎጆ ቤትን በሚሳኤል እንደ መደብደብ በሉት…

ተሜ በኢህአዴግ ክሶች ብዛት፤ በኢህአዴግ ሚዲያዎች ማስፈራራት፣ በኢህአዴግ የደህንነት ሰዎች ከበባ፣ በኢህአዴግ ማተሚያ ቤቶች አድማ አበሳውን አየ፡፡

“አንበሳው” መንግስታችን ተመስገን ግለሰብ ነው ብሎ አልናቀውም፡፡ ያለውን አቅም ሁሉ ተጠቅሞ ሊገድበው ተንቀሳቅሷል፡፡ እርሱን ለመገደብ ያላደረገው ነገር ቢኖር ቦንድ ግዙ ብቻ አላለንም፡፡ ለአባይ የምንገዛው ቦንድ ብዙ ነገር ይገድባልና!

አሁን ተመስገን ደሳለኝ ከሜዳው ላይ ጠፍቷል፡፡ ከመንግስታችን ሃይል የተሞላበት አጨዋወት አንጻር እስከዛሬም በቃሬዛ አለመውጣቱ የሚገርም ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ ችሎ ሜዳው ላይ ስናየው እኛ ደስ ይለን ነበር፡፡ አሁን ታድያ ሲጠፋብን ጊዜ በአዲስ መስመር ላይ ጮክ ብለን እንጮሃለን እንጂ እንደምን ዝም እንላለን…

ተመስገን ደሳለኝ ሆይ ማን ደስ ይበለው ብለህ ጠፋህ…!

http://www.abetokichaw.com/

ወይዘሮ አዜብ”ለመንግስት ተመላሽ ሊደረግ የነበረ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000)

qwስብሃት ነጋ …ህዝብን የሚያደነቁሩትን እነበረከትንና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያምን እርቃናቸውን አስቀሩ::
ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ።
አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ « አላማና ግብ » አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ « .በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ። » ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..«አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች።
« ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።
ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ።
አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።
http://addis12.wordpress.com/

ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

“ግብረሰዶማዊነት ወደፊት!”
123
በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሴኔጋል ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር እንደሚገባው አስታወቁ፡፡ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት ሰዶማውያንን የሚደግፍ ውሳኔ ሰሞኑን በማሳለፉ ደስታቸውን ገለጹ፡፡ የሴኔጋሉ አቻቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይወነጀሉ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናገሩ፡፡
ሰሞኑን በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝታቸውን በጀመሩባት ሴኔጋል የግብረሰዶማውያንን መብት በተመለከተ ለአፍሪካውያንና ለመሪዎቻቸው ማብራሪያና “ትምህርት” ሰጥተዋል፡፡ “መንግሥታት ዜጎቻቸውን እንዴት ሊያስተናገዷቸው ይገባል፤ ሕጉስ እንዴት ሊያያቸው ይገባል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊስተናገድ ይገባዋል” በማለት “ግብረሰዶማዊነት ወደፊት” የሚያስብል ንግግር አድርገዋል፡፡
አፍሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ኦባማ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት የግብረሰዶማውያንን መብት ሊያስከብር የሚችል ውሳኔ ማስተላለፉ እንዳስደሰታቸው በጉብኝታቸው ወቅት ጠቁመዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ውሳኔ ለጋብቻ መጠበቅ ከለላ የሚያደርገውን Defense of Marriage Act (DOMA) የተባለው ሕግ ለወንድና ሴት ተጋቢዎች ብቻ በማለት ያስቀመጠው ከለላ የግብረሰዶማውያንን መብት ይጻረራል በማለት ነበር፡፡ ስለሆነም በፍርድቤቱ ውሳኔ መሠረት በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል የተፈጸመ “ጋብቻ” ከፌዴራል መንግሥት የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞችን ሊያስከለክል አይገባም በማለት ወንድ ሚስትም ሆነ ሴት ባል ያላቸው ሁሉ የጥቅሙ ተካፋይ እንዲሆኑ ፈቅዶላቸዋል፡፡ እንዲሁም በካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት የሰዶማውያን ጋብቻ እንዲቀጥል ፈቃድ የሚሰጥ ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድቤቱ አስተላልፏል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ግብረሰዶማዊነት በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በበኩላቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይከሰሱ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናግረዋል፡፡ “በጣም በመቻቻል” የምንኖር ነን ያሉት የሴኔጋሉ መሪ አገራት ውስብስብ የሆኑ ሕጎችን በራሳቸው ጊዜ በተግባር ላይ እንደሚያውሉ በመጥቀስ የኦባማን ሃሳብ ተግሳጽ በተሞላበት ምላሽ አስተናግደውታል፡፡
በመቀጠልም አገራቸው ሴኔጋል ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት ያቆመች መሆኗን በመናገር አሜሪካ ግን ይህንን እስካሁን ተግባራዊ አለማድረጓን በመጥቀስ ኦባማን ተሳልቀውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ወንጀለኞችን በሞት የመቅጣት ህግ ከ30 በላይ ግዛቶች ውስጥ ተግባራዊ ሲሆን በተለይም በቴክሳስ በሰፊው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት እንደገና ከተጀመረ ከ1974ዓም በኋላ የቴክሳስ ጠቅላይግዛት 500ኛዋን ወንጀለኛ ሰሞኑን በመግደል የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡
“ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”
በፈረንሣይ አብዮት አካባቢ ህዝቡ መራቡን በተለይም የፈረንሣይ ጭሰኞች መቸገራቸውና በረሃብ እየተንገላቱ መሆናቸውን የተነገራት ልዕልት ማሪ አንቷኔ (“Qu’ils mangent de la brioche”) “ከራባቸው ኬክ ይብሉ” ብላ መልሳለች እየተባለ ለዘመናት ሲዘበትባት ኖሯል፡፡ ልዕልቲቱ ይህንን ለማለትዋ የተረጋገጠ ነገር ባይሆንም ነጻነት፣ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ … ለጠማው የአፍሪካ ሕዝብ ባራክ ኦባማ “የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር ይገባል” በማለት መሠረታዊውን የህዝብ ጥያቄ ችላ ማለታቸው “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” የማለት ያህል እንደሆነ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ጠቁመዋል፡፡
በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት “ለውጥ” እና “ተስፋ” ቀዳሚ ዓላማቸው አድርገው የበርካታዎችን ቀልብ የሳቡት ባራክ ኦባማ፤ ለአፍሪካ መሠረታዊ ችግር እስካሁን ጆሮ አለመስጠታቸው ብዙ የተባለበት ነው፡፡ ሰሞኑን በአሜሪካ ምክርቤት “ኢትዮጵያ፤ ድኅረ መለስ” በሚል ርዕስ በተደረገው ምክክር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የተናገሩትን በድጋሚ ያስታወሱም አሉ፡፡ በወቅቱ አቶ ኦባንግ ያሉት “ኦባማ ለምርጫ በተወዳደረ ጊዜ ጥቂት ደመወዝ የሚከፈላቸው ኢትዮጵያውያን የምርጫ ዘመቻውን ደግፈው ነበር፤ እስካሁን ከኦባማ የሰሙት ነገር የለም” በማለት ነበር፡፡
ከምዕራባውያን የሚመነጨውን ማንኛውንም ነገር – ከፖለቲካ እስከ ማኅበራዊ አመለካከት – ትክክለኛ አድርገው ለሚቀበሉ ግብረሰዶማዊነት ሥልጣኔ ይመስላቸዋል በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ የሃይማኖትና የማኅበረሰብ ሳይንስ ጉዳዮች ምሁር “ጋብቻ” የሚለውን ቃል ለሁለት ወንዶች መጠቀም እርስበራሱ የሚጋጭ ጉዳይ ነው በማለት ተመሳሳይ ጾታ ብሎ ጋብቻ ማለት የተሳከረ አነጋገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “ይህ የሰዶማውያን መብት ይከበር የሚለው ጉዳይ በሕግ እየጸደቀ ሲሄድ ድርጊቱን ከሃይማኖታቸው አኳያ የሚቃወሙ ሰባኪያን የሃይማኖት ትምህርታቸውን በሚያስተምሩበት ቤ/ክ ይሁን መስጊድ ወይም ምኩራብ ግብረሰዶማዊነትን እየተቃወሙ ሰበካ ማድረግ በህግ የሚያስጠይቃቸው ይሆናል” በማለት ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን የማኅበረሰብ ቀውስ ጠቁመዋል፡፡
22የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ፣ … ዕጦት ላንገላታውና በአምባገነኖች መዳፍ ሥር ለሚሰቃየው የአፍሪካ ሕዝብ በቃላት እንኳን ድጋፋቸውን ከመስጠት እስካሁን የተቆጠቡት ኦባማ አሜሪካ በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አገሮች ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ፍላጎቱ እንደሌላት በማያወላውል መልኩ ያረጋገጠ መሆኑ የብዙዎች ግንዛቤ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ኃይል ጥያቄ ውስጥ የሚጥልም ነው፡፡
በአውሮጳ የፖለቲካ ምጣኔሃብት ተመራማሪ የሆኑ እንደሚሉት “አሜሪካኖች እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዓይነቱን አምባገነናዊ አገዛዝ እስኪያስመልሰው ድረስ በዕርዳታ ገንዘብ ካሽሞነሞኑ በኋላ “ኢህአዴግን ምን እናድርገው” በማለት “ምክር ስጡን” እያሉ በሕዝብ ሰቆቃ ላይ ያላግጣሉ፡፡ ሲሻቸውም ደግሞ አፍሪካ ድረስ በመሄድ “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” በማለት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን ችግር ያልሆነውን የግብረሰዶማውያን መብት መከበር ይሰብኩናል፡፡ ታዲያ ለዚህ ልግጫ መልሳችን መሆን የሚገባው “ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ነጻነታችንን አንለምንም፤ አሜሪካ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት እንድትሆንብን አንፈልግም” በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ምክርቤት በተካሄደው ምክክር የተናገሩትን ዓይነት ቁርጠኝነት ነው በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡33100ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው የኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት በአሁኑ ጊዜ በበጀት ቀውስ ምክንያት በርካታ ሠራተኞች ደመወዛቸው እየተቆረጠ ባለባት አሜሪካ አነጋጋሪ መሆኑን ዋሺንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡ የደኅንነት ሰዎችን እንዲሁም 14ሊሞዚን፣ 56 ጥይት የማይበሳቸው ድጋፍ ሰጪ መኪናዎች፣ ሙሉ የህክምና ባለሙያዎችን የያዘና ጀቶችን የጫነ መርከብ … ለፕሬዚዳንቱና ለቤተሰባቸው ጥበቃ በማድረግ ሥራ ላይ እንደሚውሉ ጋዜጣው ያብራራል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ በደቡብ አፍሪካ የሁለት ቀን ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰኞ ወደ ታንዛኒያ ያመራሉ፡፡ የአባታቸው የትውልድ አገር ነው የሚባለውን ኬኒያ ሳይረግጡ በዚያው ወደ አገራቸው እንደሚያቀኑ የጉዞ መርሃግብራቸው ያስረዳል፡፡44
http://www.goolgule.com/

Post Navigation