addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the category “Amharic News”

Prime Minister Abiy Ahimed about Haseb

Zemedkun Bekele

https://youtu.be/PJlxfE0LWmc?si=c2zFEvtGpq_g9YgEhttps://youtu.be/PJlxfE0LWmc?si=c2zFEvtGpq_g9YgE

Breaking News About Teddy Afro Dec 2014


ESAT

የማለዳ ወግ …የሃና አባት አቶ ላለንጎ ሃይሶ አና እናቷ ወሮ ትርፊ ተናገሩ! ያማል ፣ ያማል ፣ ያማል …ይህም ያማል !

2222
ነቢዩ ሲራክ
እህት ሃና በሰው አራዊቶች ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተደፍራ ወድቃ ያገኟት አባት ልጃቸው ህክምና ታገኝ ዘንድ ከሆስፒታል ሆስፒታል ስለተንከራተቱበት ፣ የህክምና እርዳታ ስለተነፈጉበት አሳዛኝ ሂደት ሀገር ቤት በሚተላለፈው ኤፍ ኤም ራዲዮ ተናግረዋል ። አባት ሲናገሩ ለሃና ህክምና ማድረግ ያልቻሉት የመንግስት ህክምና ተቋማት ሳያንስ ፖሊስ ጉዳዩን እንዲመረምር በልመና ካሳኩ በኋላ ህክምና ማግኘት ባለመቻላቸው የሚረዳቸው አጥተው ተጎጅ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቤታቸው ወስደው ስላሳደሩበት እንግልት ሰምተናል ፣ ይህም ያማል: (
እንደ አባት አቶ ላላንጎ ገለጻ ልጃቸው እህት ሃና ከጋንዲ ጥቁር አንበሳ ከጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ ግልጋሎት ተነፍገው ተንከራተዋል ። ወደ መጨረሻም በዘውዲቱ ሆስፒታል አልጋ ተሰጥቷን መታከም መጀመሯንና በህክምና እያለች የምስክርነት ቃሏን በደል አድራሽ ያለቻቸውን ሶስቱ በፖሊስ ተይዘው ቀርበው ለይታ ማሳየቷን አባት ተናግረዋል ። ሃና በመጨረሻ ሰአቷ ከምስክርነት አልፎ በኑዛዜዋ በጉዳዩ የሉበትም ያለቻቸው እንዲለቀቁ መናገሯንና ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት አላት ያለቻትን ጓደኛዋን ፖሊስ ” በቂ መረጃ የለም!” በሚል እንደለቀቃት ሲናገሩ ይህም ከሃዘን በላይ ሃዘን እንደጨመረባቸው ቅሬታቸውን ተናግረዋል !
ምስኪኗ እናት ወሮ ትርፊ …
የሃና እናት ወሮ ትርፊ የልጃቸው የሃናን ስቃይ መመልከታቸውን ፣ በማደንዘዣ መቃጠል መንገብገቡ በረድ ሲልላት ነፍስ እየገዛች የሆነው ሁሉ መናገሯን እያነቡ እያነቡ ከአድማስ ራዲዮ ጋር የተናገሩት እናት የሃናን በደል መደበቁ ትድናለዕ የሚል ተስፋ ስለነበራቸው እንደነበር እያነቡ ልብን በሃዘን በሚሰብር ስሜት ተናግረዋል … በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት ” በሃና ግፉ ይብቃ ሲሉ ባስተላለፉት መልዕክት እንዲህ ” … እኔ ያለኝ ነገር በሃና ሁሉም ነገር እንዲቀር ፣ ለምን አሁንም ትውልዱ አየተበላ ነው ፣ ህጻን እየተበላ ነው ፣ የህጻናት መብት እንዲከበር ፣ ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጥ ነው የምፈልገው ፣ ልጀ አትመጣልኝም በቃ ምን አደርጋለሁ? አሁንም እንደቀጠለ ነው … ለእኔ እንደሁ አትመጣልኝም ….ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጥ ነው የማስተላልፈው! ” የዚህች እናት ህመም ህመማችን ነው ! መልዕክታቸው መልዕክታችን ነው ! ያም ሆኖ ይህም ያማል ፣ ያማል ፣ ያማል !
አዎ በርካታ ሃናዎች በአረብ ሃገራት መካከል የሁለትዮሽ ውል ባልተደረገበት ሁኔታ ለኮንትራት ስራ ወዳለሁበት ጃገር ተልከው ግፍ ተፈጽሞባቸው አይቻለሁ ፣ ሰምቻለሁ! ምንዱባኑ ታዳጊዎች እድሜያቸውን ቆልለው በመጡ በርካታ እህቶች ባልጠነከረ ለጋ ገላቸው ተጎድቷል። ግፍን አስተናግደውየተረፉት ተርፈው በመንግስት ወኪሎች አማካኝነት ሱሸኙ በቂ ህክምናና ፍትህ አግኝተው አላየንም። ይህ ሆነና እውነቱ ግፉአኑ ተገፍተው ወደ ድሃ ጎጇቸው ለመሸኘታቸው እማኝ ነኝ ። የእኒያ እናቶች ድምጽ እንደ ሃና እናት ባንሰማውም የሰቆቃ ህይወታቸውን ፣ በድህነት ቤት የተረከቧቸውን ልጆቻቸውን ህይወት እናስበው !
በእህቶቻችን ደልላ የበለጸጉት ክፉዎችን ዛሬ ወደ ፍርድ የሚያቀርባቸው ቀርቶ ዝንባቸውን ” እሽ ” ማለት የሚቻለው የለም ! ይባስ ብለው ዛሬ ዳግም ወደ አረብ ሃገራት የተዘጋው የኮንትራት ስራ ይጀመር ዘንድ እያጎበጎቡ ነው! ይባስ ብለው የኮንትራት ስራው የመጀመሩን ለእነሱ የሃሴት ለእኛ መርዶ የሚሆነውን ቀን መቅረብ ባለጊዜዎች ናቸውና በድፍረት እየነገሩን ነው! ይህም ያማል ፣ ያማል ፣ ያማል 😦
ባደገች በተመነደገች ሃገራችን እየሆነ ያለውን ላሰበው ያማል …ያኔ ታዋቂው ድምጻዊ ዶር ጥላሁን ገሰሰ በቂ ህልምና የሚያገኝበት ሆስፒታል ጠፍቶ መንከራተቱን አስታውሰን ፣ የሃናን የህክምና ተቋማት ግፍ የተፈጸመባትን እህት መታደግ አለመቻላቸውን ስናስበው ልባችን በሃዘን ይሰበራል 😦 ይህም ያማል ፣ ያማል ፣ ያማል ይህም ያማል ! ዛሬ ህመማችን ጸንቷል ፣ የጸናው ህመም የሚታከመው ደግሚ ትክክለኛ ፍትህ ስናገኝ ብቻ ነውና ፍትህን ተጠምተናል ፣ ፍትህን እንሻለን !
ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 13 ቀን 2007 ዓም
— Ze-Habesha

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው ምርቃት አካሄደ

111111
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ባስመረቀበት ወቅት የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው መሆኑ ተመልክቷል።
ህዝባዊ ሃይሉ ለኢሳት በላከው መግለጫ የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ ‘’ህዝባዊ ሃይላችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኛና አፋኝ የወያኔ ስርዓት ከህዝብ እና ከሃገራችን ጫንቃ ላይ አስወግዶ በምትኩ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት ጊዚያት በርካታ ስራዎችን በመስራት አስተማማኝ ድርጅታዊ አቋም ላይ ይገኛል’’ ማለታቸውን ጠቅሷል።
የኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው ባንድ ድርጅት ጥላ ስር ትግላቸውን አስተባብረው ለመታገል የሚያደርጉትን የውህደት ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ባደረሱበት ወቅት ላይ መርቃቱ መደረጉን ያወደሱት ኮማንደሩ፣ የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው እንደሚሆንም ተናግረዋል።
ኮማንደሩ ‘’ስልጠና ለአንድ ታጋይ የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት በተግባር ለቆምንለት ዓላማ እና ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንደምታውሉት ሙሉ እምነቴን እገልጻለሁ‘’ በማለት ለስልጠናው መሳካት የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ከዚህ ቀደም 4 ተከታታይ ምርቃቶችን ማካሄዱ ይታወሳል።
ESAT

ESAT Bezhi Samint Bandiraw October 2014

«ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን።» የብአዴን አመራሮች

11
በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ጫናው በርትቷል፤
በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ። የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሃፊ የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በእሱና በሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ ዛቻ እንደሚፈጸምባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ «ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም» ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ጠበቃው ገልጿል። በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል ተብሏል። ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ «ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ» በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ገልጿል።
ጠበቃው በ28/1 እናርጅ እናውጋ ለቀጠሮ ባቀናበት ወቅትም የእናርጅ እናውጋ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ስራው በረኩ እና የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ እና ሌሎችም ከፖሊስና ከጸጥታ የመጡ አመራሮች «ምን ልታደርግ ነው? ልትቀሰቅስ ነው?» በሚል እንዳዋከቡትና አቶ ስራው በረኩ «አንጠልጥዬ ነው እስር ቤት የማስገባህ። ማንም ሊያድንህ አይችልም» ብለው እንደዛቱበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጿል። «የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነህ በፍትህ ስርዓቱ መገልገል አትችልም፣ ጥብቅናህን መልቀቅ አለብህ፣ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ ትጽፋለህ፣ የፍትህ መምሪያ ሃላፊውን (ጸጋየ መንግስቴ) ችግር እንደሚፈጽምብህ በነገረ ኢትዮጵያና በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ጽፈህበታል፣ እንዲህ እያደረክ መኖር አትችልም፣ አንተን ገሎ መጣል ቀላል ነው፣ ለነፍስህ የምታዝን ከሆነ አገር ልቅቅ» ብለው እንደዛቱበት ገልጿል።
ሌሎች ጠበቃ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሄዱ «እሱ ማለት ሰማያዊ ነው። ሰማያዊ ደግሞ የአክራሪ ሙስሊም ፓርቲ ነው። እናንተ ለምን ከእሱ ጋር ትሄዳላችሁ?» ብለው እንደሚያስፈራሯቸውና ደንበኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሰሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ጠበቃው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ጠበቃውን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባል ሆነው ማደራጀት መብታቸው መሆኑን ሲገልጹ የብአዴን አመራሮች «እናንተ እኛን ስለማትረዱን ነው። እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም። ወንድ ከሆናችሁ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን» በሚል ለህግ የማይገዙና ለሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት እንደሌላቸው አሳይተውናል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑ ነጋዴዎች ከፓርቲው እንዲለቁ ለማድረግ የንግድ ድርጅታቸውን እንደሚዘጉ እያስፈራሩ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ለአብነት ያህልም አቶ ይኸይስ ቀጸላ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር «ሻይ ቤት ከፍተው እያደራጁ ነው። የንግድ ድርጅቱን እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበታል። በመሆኑም ካላረፉ ሻይ ቤቱን እንዘጋዋለን» እያሉ እንደሚያስፈራሩ ታውቋል።
የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የገዥው ፓርቲ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እርምጃዎች እየተጠናከሩ ቢሆንም እርምጃው እነሱ ተጽዕኖ በመፍጠራቸው የመጣ በመሆኑ ይበልጡን እንደሚያበረታታቸውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አቶ መኳንንት አበበን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችን የእጅ ስልካቸው ላይ በመወደል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

የተቦርነ በየነ እና የመሳይ መኮንን ውይይት በቴዲ አፍሮ የፍርድ ቤት ውሎ ላይ (Video)

ቴዲ አፍሮ ታስሮ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ በ30 ሺህ ብር ዋስ መለቀቁን ዘ-ሐበሻ በትኩሱ መዘገቧ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ማምሻውን ኢሳት ራድዮ ተቦርነ በየነ እና መሳይ መኮንን በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎና የክሱ አንደምታ ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት አሰምቷል። ይከታተሉት።

Posted by Addisu Wond.

አስደንጋጭ ዜና/ ማዕተብ ማሰር ሊከለከል ነው!

222
በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ትምህርት
ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን
ማዕተብ ማሰር እንደሚከለከል የፌዴራል
ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሺፈራው
አስታወቁ!
የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖና የፀረ
አክራሪነት አጀንዳ ተገን
በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ላይ ርእዮታዊ
እና ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን በማስተጋባት
የሚታወቁት ሚኒስትር
ሺፈራው፣ ይህን መናገራቸው የተጠቆመው፣
ከነሐሴ 18ቀን 2006 ዓ.ም.
ጀምሮ እስከ መስከረም 17 ቀን 2007
ዓ.ም. ድረስ በዘለቀውና በኹለት ዙሮች
በተካሔደው የመንግሥት መካከለኛ
አመራሮች ሥልጠና ላይ ነው፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተካሔደውና 800
ያህል መካከለኛ አመራሮች
በተሳተፉበት የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና
‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ
መንግሥት ግንባታና ፈተናዎቹ›› የሚለውን
ሰነድ የሚያብራራና በፓወር
ፖይንት የተደገፈ ጽሑፍ ያቀረቡት ሚኒስትሩ
የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖ መነሻ
ያደረገ ነው የተባለ ጥያቄ ከአንዲት ተሳታፊ
ቀርቦላቸዋል፡፡
እንደ ስብሰባው ምንጮች፣ የተሳታፊዋ
ጥያቄ፣ ‹‹በቢሮ ፊታቸውን
ተሸፍነው የሚመጡ ሙስሊሞችን
አለባበሳቸው ከቦታው አንፃር ያለውን
ተገቢነት በማንሣት እንዲያወልቁ
ስንጠይቃቸው ‘እኛ ይኼን የምናወልቅ ከኾነ
ኦርቶዶክሱም ክሩን ይበጥስ’ ይሉናል፤ ይኼን
እንዴት ነው የምንታገለው?›› የሚል ነበር፡፡
‹‹መንግሥታችን ሴኩላር ነው›› ሲሉ
በጠያቂዋ የተጠቀሰውን ዐይነት
አለባበስ የተቹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ማተቡም
ቢኾን የጊዜ ጉዳይ
ነው፤ እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ
ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም
ቢኾን መውለቁ አይቀርም፤›› የሚል ምላሽ
መስጠታቸው ተገልጧል፡፡
ማዕተብ÷ የሲኦል መሠረት የተናወጠበት፣
ሰውንና እግዚአብሔርን ለዘመናት
ለያይቷቸው የነበረው የጠብ ግድግዳ
የተናደበት፣ የሞት ኃይሉ ተሽሮ የትንሣኤ
መንገድ የተከፈተበት መስቀል ትእምርት
በመኾኑ በተሳሳተ የሴኩላሪዝም ግንዛቤ
‹‹ማዕተቡም ሊወልቅ ይችላል›› ማለት፣
‹‹ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ
አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር
ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፤ ጉዳዩንም
ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ታሪካዊ
ትውፊት እንደማፋለስ የሚታይ ነው!
ሁላችንም ምዕመናን ማዕተባችንን ጠበቅ
በማድረግ ለእምነታችንን ያለንን ፍቅር እስከ
መስዋዕትነት የምንገልጽበት ጊዜ ቀርቧል!
ማተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ
እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ
ፊተኛ ነንና አንዳንሆን ኋላኛ
ህዝቤ ተነቃቃ ተነስ አትተኛ
ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን ጩኽቱ
የተዋህዶ ልጆች አሁነ ነው ሰዓቱ
አይተን እንዳላየን ስንቱን አሳልፈናል
የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል
አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር
ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ሚስጢር
ተዋህዶ ሀይማኖቴ
የጥንት ነሽ የአናትና አባቴ
ማህተቤን አለበጥስም
ትኖራለች ለዘላለም!
ሼር በማድረግ ለሁለም ሰው መረጃውን
እናድርስ!!

ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት በመኮብለል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የሚቀላቀሉ አባላት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት መካከል የአየር ኃይል ባልደረባ ይገኝበታል።
ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት በመኮብለል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የሚቀላቀሉ አባላት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት መካከል የአየር ኃይል ባልደረባ ይገኝበታል።
በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያለውን የአንድ ቡድን የበላይነትን እና ሠራዊቱ የሀገርና ሕዝብ አገልጋይ መሆኑ ቀርቶ የወያኔ ቅጥረኛነትን በመቃወም በተለያዩ የሠራዊቱ ክፍል ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን በተለያዩ ጊዜያት መቀላቀላቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን የደብረዘይት አየር ኃይል ባልደረባ ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ የተባለ የተዋጊ ጦር ሄሊኮፕተር አብራሪ የሀገራችን ኢትዮጵያን የግፍና የመከራ ጊዜን ለማብቃት እየተደረገ ያለውን ትግል ለመደገፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅሏል።ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ ለአርበኞች ድምጽ ሬዲዮ እንደገለጸው ከሆነ “የአየር ኃይሉ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በሕ.ወ.ሓ.ት ሰዎች የተያዘ ሲሆን እንኳንስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሊያስከብር ቀርቶ እንደተቋም በሁለት እግሩ መቆም ተስኖት በውጪ ቅጥረኞች ትከሻ ላይ የተመሰረተ” መሆኑን ገልጿል።
የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝን በትጥቅ ትግል ለመፋለም በተለያዩ ጊዜያት የወያኔ አየር ኃይል አባላት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የተቀላቀሉ ሲሆን ከወራት በፊት ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሺዋስ የተባለ የተዋጊ ጦር ጀት አብራሪ ግንባሩን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው።
ሰሞኑን ግንባሩን ስለተቀላቀለው የአየር ኃይል ባልደረባ ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ ሰፊ ዘገባ ይዘን እንደምንመለስ ከወዲሁ እናስታውቃለን። 66

Post Navigation