addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “August 2, 2013”

ሰበር ሰበርበር ዜና….ሩሲያ 2013….የጥሩ እና መሲ ደርቢ ቀርትዋል!!!

33333
የናንተ አገልጋይ ቲም ኢትዮጲያ ሳይቀር ሁለቱን ሲፋቀሩ ፎቶ ለጥፍዋል፤ጥሩነሽ ዲባባና መሰረት ደፋር በሩጫ ዘመናቸዉ ፍጹም መሳጭ ፉክክር አድርገዋል..በተለይ ያቺ 7ተኛዋ የዳይመንድ ሊግ ፉክክር ለመሰረትና ጥሩነሽ የመም ላይ መጠማመድ ሁነኛ ምክንያት ሁኑዋል…አሁንም ብዙዎች ይህንን ትንቅንቅ በሞስኮ በረዶ አየር መሀል ያልማሉ..እኔ ግን እንደዚህ ልበላቸዉ…ጥሩነሽና መሰረት በሞስኮ አብረዉ አይሮጡም..መጀመሪያ ላይ ሁለቱም በ5ትም በ10ስር ሺም ለመተያየት ፈልገዉ ተፈቅዶላቸዉ ነበር፤ከቀናት በሁዋላ ግን ይሄ ነገር ለዉጤቱ መጥፎነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል ተቀይርዋል..ጥሩነሽ በ10ሺ ብቻ— መሰረትም በ5ሺ ብቻ –እንዲወዳደሩ ከፌዴሬሽኑ ጋር ተስማምተዋል…፡‹ሁለቱ ለአሽናፊነት ሲጠባበቁ አዲስ ያልታወቀች አትሌት ልትጠቀምበት ትችላለች-በዛ ላይ በአንድ ዉድድር ላይ ብቻ ዝግጅታቸዉን እንዲያደርጉ ነዉ ነገርየዉ የተወሰነዉ፤
ይህንን ነገር የሰማዉ ወዳጄ ሩዋጭ ከተማ (ተቀማጭነቱን አሜሪካ ያደረገ የማራቶን አትሌት)–ዉሳኔዉ ጥሩ ነዉ..በተለይ ሁለቱም የወርቅ ሩዋጮች ስለሆኑ በየፊልዳቸዉ አንድ ወርቅ ማስተማመን ይችላሉ..ድርብ ወርቅ ደግሞ ለጥሩዮ አዲስ አይደለም..በከባዱ ኦሎምፒክም አድርጋዋለች..በህይወት ዘመንዋ ማግኘት የሚገባትን ሁላ አሳክታለች..መሰረትም የኦሎምፒክና የአለም ዉደድሮችን አሽንፋለች..ስለዚህ ዉሳኔዉ ጥሩ ነዉ፤ብሎኛል..አስተያየቱ በእግር ኳስኛ ስንቃኘዉ —ኳስ በመሬት–አይነት ነዉ፤
እንደኔ እንደኔ ግን ጥሩነሽና መሰረት በሁለቱም ርቀቶች መሳተፍ የሚያስችል አቅም አላቸዉ..በሎንዶንም ይህን አሳይተዋል..እናም ከዚህ ዉድድር በሁዋላ ወደ ጎዳና ሩጫ ሊሳቡ ይችላሉ..የትራኩ ዉድድር ያለሁነኛ ተፎካካሪ እርቃኑን ቀረ ማለት አይደል??ታድያ አሁን ቢፈሳፈሱ እኛንም ከፍ ዝቅ አድርገዉ ድል ቢደራረጉ ጥሩ አደለም አላችሁ??ስለወርቁ እንኩዋን እምብዛም ስጋት የለም..ሁለቱ በሮጡበት ሁላ ዘንደሮዉ የተጋፋቸዉም የለም..ምን አላችሁ ታድያ..ሞስኮ ያለ ጥሩመሰ ደርቢ…
saied kiarA

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ መታገድ

z
ፖሊስ ከዚሁ መስጊድ ፣ ሶላት ከመጀመሩ በፊት አንድ ምዕመን ከሶላቱ በኋላ ደግሞ ወደ 15 የሚሆኑ ምዕመናን ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ማሰሩን ፣ በአካባቢው እስከነበረበት ጊዜ ድረስ መመልከቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግሯል ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሙስሊሞች በየሳምንቱ አርብ ከሶላት በኋላ የሚያካሂዱትን ተቃውሞ በከለከለ ማግስት ዛሬ በተለይ አዲስ አበባ በተለምዶ ፍልውሃ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ታቅዶ የነበረው ተቃውሞ ሳይካሄድ ቀረ ። ፖሊስ ከዚሁ መስጊድ ፣ ሶላት ከመጀመሩ በፊት አንድ ምዕመን ከሶላቱ በኋላ ደግሞ ወደ 15 የሚሆኑ ምዕመናን ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ማሰሩን ፣ በአካባቢው እስከነበረበት ጊዜ ድረስ መመልከቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግሯል ። ዮሐንስን በስልክ አነጋግረነዋል ።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ
AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC
http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_16994521_mediaId_16994421

ሰበር ዜና ከወላይታ === መንግስት አንድነት ፓርቲ ላይ የክስ ድራማ እያዘጋጀ መሆኑ ተደረሰበት

11111111
መንግስት በወላይታ ሶዶ በአንድነት ፓርቲ ላይ የሀሰት ድራማ በመስራት ላይ ነው፡፡ መንግስት በመስጊድ ውስጥ በድብቅ ያሰራጨው ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለአመፅ የሚቀሰቅስ በራሪ ወረቀት የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር የሆኑት ወ/ሮ ሀድያ መሀመድ እንዳሰራጩት በማስመሰልና የሀሰት ምስክሮችን በማጋጀት ስራ ተጠምዷል፡፡ ወ/ሮ ሀድያ መሀመድንም “በራሪ ወረቀቱን እንድበትን አንድነት ፓርቲ ነው ያዘዘኝ” እንዲሉ እያስገደዷቸው መሆኑን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አስታውቀዋል::
‪#‎millionsofvoicesforfree‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬

ታላቅ የሕዝባዊ ስብሰባ ጥሪ በፍራንክፈርት በፍራንክፈርት በፍራንክፈርት ከተማ ጀርመን – የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

32
ከተመሰረተ 41 አመቱን በማስቆጠር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነቱን ለመጎናፀፍ፡ ለመጎናፀፍ፡ ለመጎናፀፍ፡ መሰረታዊ የሆኑ ዴሞክራሲያዊ ዴሞክራሲያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶቹንና የሀገሩን ሉአላዊነት ለማስከበር በሚያደርገው በሚያደርገው የትግል እንቅስቃሴ በግንባር ቀደምትነት የበኩሉን አስተዋፅዖ በፅናት እያበረከተ ይገኛል።።። ላለፉት 22 አመታት በወያኔ ዘረኛና አምባገነናዊ አምባገነናዊ አምባገነናዊ አገዛዝ የተነሳ ሕዝባችን በአሁኑ ወቅት ከሚገኝበት እጅግ አሳሳቢና አሳዛኝ ሁኔታ በኢትዮጵያዊነታቸው በኢትዮጵያዊነታቸው በኢትዮጵያዊነታቸው በእጅጉ የፀኑና ለሕዝባቸው ቀናኢ የሆኑ እንደ ኢሕአፓ የመሰሉ ሀገር ወዳድ ኃይሎች ከምንጊዜውም ከምንጊዜውም በበለጠ ትግሉን የመምራት ኃላፊነት የሚጠበቅባቸው የሚጠበቅባቸው የሚጠበቅባቸው ለመሆኑ የምንገኝበት የምንገኝበት የምንገኝበት ሁኔታ የሚያመለክተው የሚያመለክተው የሚያመለክተው እንደሆነ ግልፅ ነው።።።። ይህ ከፍተኛ መስዋዕትነን መስዋዕትነን መስዋዕትነን እያስከፈለ በተለያየና ሁለገብ በሆነ መልክ የሚደረገውም ትግል ስኬታማ ይሆን ዘንድ መጠናከርና መስፋፍት እንዳለበት ለክርክር የሚጋብዝ አይደለም።። አይደለም። ይህንን ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ደግሞ እነዚህ ድርጅቶች ከሕዝብ ጋር በተለይም የወደፊት ሀገር ተረካቢ ከሆነው ወጣት ትውልድ ጋር መወያየትና የጋራ ግንዛቤ ለማግኘት በመጣር ትግሉን አንድ እርምጃ ወደፊት መግፋት የግዴታ እንደሚል ግልፅ ነው።

Read more: http://www.ethiolion.com/Pdf/08012013Public_meeting_in_Frankfurt.pdf

የቃሊቲ እንግልት፤ – ከግርማ ሠይፉ ማሩ

xcc
ጎበዝ እንግዲህ እዚህ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጉድ ሳይሰማ አይታደርም አይደል፡፡ ዛሬ ከአቤል አለማየሁ ጋር አንዱዓለም አራጌን እና ርዕዮት ዓለሙን እንጠይቅ ተባብለን ወደ ቃሊት ወረድን፡፡ ለዛሬው የነበረን ዕቅድ ሁለቱን ብቻ የማየት ነበር፡፡ ለዚህም እንዲሆን በቂ የሚባል ሰዓት ይዘን ልክ ከቀኑ አምሰት ሰዓት ላይ ቃሊት በር ደረሰን፡፡ በቅርቡ ቃሊት የሚገኙትን ወዳጆቻችን ለመጠየቅ የተለሳለስ ሁኔታ መኖሩን በአገኘሁት አጋጣሚ የገለፅኩ ሲሆን ይህንኑ ሃሳብ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ለአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ገልፀውት ነበር፡፡ ምሰጋናችን አንድ ሳምንት ሳይሞላው እብድ ይሻለዋል እንጂ አይደንም እንደሚባለው ሆኖ አገኘነው፡፡

ዛሬ (ሐሙስ ሐምሌ 25) ቃሊት በሩ ላይ ስንደርስ አንድ አንድ ነገር እንግዛ በሚል ቆም ባልንበት አጠገባችን ያሉት ዘቦች እኔን እየተመለከቱ ሲጠቃቀሱ ተመለከትኩ፣ ውይይቱን ያስነሳው በበሩ ላይ የቆመው ባለ አንድ ኮከብ ማዕረግ ባደረገ በአሁኑ አጠራር ረዳት ኢንስፔክተር (በቀድሞ ምክትል የመቶ አለቃ) ነው፡፡ ባደረገው ማዕረግ ልክ ግን ያልሆነ ሰው ነው፡፡ በሚያደርገው ነገር እምነት እንደሌለው የሚያሳብቀው ንግግሩ ብቻም አይደለም ሰሙን ለመናገር ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ማነኛውም የመንግሰት ሰራተኛ አገልግሎት ሰጪ ሙሉ ስሙን በግልፅ መፃፍ እንደሚጠበቅበት ግልፅ ነው፡፡ ይህ ባለ ማዕረግ ግን ይህንን አለማድረጉ ብቻ ሳይሆን ሲጠየቅ ስሙን ለመናገር ድፍረት የለውም፡፡ እንግዲህ ለዚህ ነው ኮኮብ ማዕረግ በትከሻው ላይ የተደረገለት እና ለዚህም በሚል ደሞዝ የሚቆረጥለት፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ ከዚህ ከፍ ያለ ማዕረግ ያለው እሼ ግደይ (በቅፅል ስሙ ሻቢያ) የሚባል ሰሙን አልናገርም ብሎ ህዝብ በተሰበሰበበት ተሳድቦ፣ ይህ ስድብ እኔን ሳይሆን የምክር ቤቱን ክብር የነካ ነው ብዬ ከስሼው ነበር፡፡ በኋላ ላይ የምክር ቤት አባል መሆናቸውን አልተናገሩም እንዳውም ተሳድበዋል የሚል ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል በሚያስብል መልኩ መከላከል ጀምሮ ነበር፡፡ የዛሬው ረዳት ኢንስፔክተር አልተሳደቡም ሰደበኝም አላሉም በዚህ አደንቃቸዋለሁ፡፡

ወደ ዝርዝር ድራማው ከመግባቴ በፊት ግን አንድ ነገር ማለት ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ የተገልጋዩን መታወቂያ እያገላበጡ የሚያዩ አገልጋይ ነን እያሉ የሚመፃደቁ ሁሉ በህግ አምላክ ስማችሁን ቢቻል ከነፎቶ የሚገልፅ ነገር በደረታችሁ ላይ አድርጉልን፡፡ ይህን የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ በአሰቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ያድርግልን እላለሁ፡፡ እዛው በምዝገባ ላይ ከነበረች ረዳት ሳጅን (ሰሜ አስቴር ነው ብላኛለች) እንደሰማሁት ባጁ አለ የሚል ነው፡፡ ከፍተኛ የመንግሰት ሀብት ወጥቶበት ከተዘጋጀ በኋላ ለምን እንደማይደረግ ግን መልስ እንፈልጋለን፡፡ በነገራችሁ ላይ በደርግ ጊዜ ፖሊሱ ሁሉ የመለያ ቁጥር በደረቱ ላይ ያደርግ ነበር፡፡
ከላይ እንደገለፅኩላችሁ ሲጠቃቀሱ የነበሩት ዘቦች ጋ ጠጋ ብዬ በቀልድ ዓይነት ልክ ናችሁ በቴሌቪዥን የምታዩኝ ግርማ ነኝ ብዬ ተቀላቀልኳቸው፡፡ መዋሸት ጀመሩ እኛ ሰለአንተ አልተነጋገርንም ብለው በአድማ ዋሹ፤ ችግር የለም ብዬ መንጃ ፍቃድ ሰጠዋቸው ስሜን ተመልክተው እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ የቀበሌ መታወቂያ አምጣ አሉኝ፤ ለምን? አልኳቸው፣ በዚህ አናስገባም፡፡ ሌላ ጊዜ በዚህ ነው የምገባው ብል የሚሰማኝ አጣው፡፡ ደግነቱ መኪናዬ ውስጥ የቀበሌም የምክር ቤትም መታወቂያ ስለያዝኩኝ ሄጄ አምጥቼ ይህው የቀበሌ መታወቂያ ብዬ ሳሳይ አማረልኝ ያለች አንዷ ገብቶሃል ቁጭ በል የሚል ትዕዛዝ ሰጠችኝ፣ አልገባኝም፣ ስላት በሚገባህ ቋንቋ ይነገርሃል ብላ ተናግራ ልታናግረኝ ዘለግ ካለም ልታስፈራራኝ ስትፈልግ፣ የምችለው ቋንቋ አማርኛ ነው ከዚህ ሌላ ካለሽ አምጭ አልኳት፡፡ አታካሮው በዚህ አበቃ ይህች ሴት በዛው ሄዳ ቀረች፡፡ ከጀርባ ሄዳ እሼ ግደይ (ሻቢያ) እንዳደረገው ልትከሰኝ ማለት ነው፡፡ ይህ አካሄድ ተቋማዊ እንደሆነ የገባኝ በኋላ ነው፡፡

እኔም በረዳት ኢንስፔክተሩ ትዕዛዝ መሰረት ሰልክ ተደውሎ እስኪፈቀድ ቆይ ተባልኩ፣ እሺ ብዬ ቁጭ ብዬ ስጠብቅ ለ45 ደቂቃ ቆየው፡፡ በዚህ ቆይታዬ አጠገቢ ካለው ኢንስፔክተር ጋር ለምን ሰሙን እንደማይነግረኝ፣ ይህ ደግሞ ተገቢ እንዳልሆነ፣ እየነገርኩት እርሱም ባይለጠፍ ችግር እንደሌለው ሲያስረዳኝ ቆይቶም ሲሰለቸው እንደሚያጣራ ሄዶ ሲጠፋ ጊዜውን ገደልነው፡፡ በመሃሉ ሌሎች ተሰተናጋጆች መጥተው ሲገቡ ሲወጡ እያየሁ አንድ ጥያቄ ጠየኩት ለምንድነው መንጃ ፍቃድ አይሆንም ያልከኝ? እዚህ ቁጭ ብዬ በመንጃ ፍቃድ ሌሎች እየገቡ አይቻለሁ አልኩት፡፡ እዚህ ድረስ መጥተው ሰዎች እንዳይጉላሉ ነው ብሎኝ አረፈው፡፡ የምክር ቤት አባል አጉላሉ ተብላችኋል ወይ? ብዬ ያልጠበቀውን ጥያቄ ዱብ ሳደርግ አጠገቤ የነበረችው መዝጋቢ ሳጅን አይደለም እኔ አላውቅህም እነርሱ ግን ስላወቁ የሚያጠሩት ነገር እስኪያጣሩ ብሎ ነው ተወው ብላኝ ቅድም ስለ አንተ አልተነጋገርንም ብለው የዋሹትን አጋለጠች፡፡ እኔም በዚሁ አበቃው፡፡ ድንገት ሌላ ሴት መጥታ በዋናው በር ይሂዱ! አይናደዱ ብላኝ ወደ ዋናው በር አመራሁ፡፡ በሩ ጋ ስደርስ፤

• ወዴት ነው? የሚል ጥያቄ በአንድ ታዛ ስር ያለች ሴት ፖሊስ አቀረበችልኝ፡፡
• እስረኛ ልጠይቅ፡፡
• በዚህ ነው የሚጠየቀው? ብላ ስትጠይቀኝ
• በመጠየቂያው በኩል በዚህ ሂድ ተብዬ ነው ብዬ መለስኩ፡፡
• ለምን?
• ለምን እንደሆነ የሚያውቁት ወደዚህ እንድሄድ የላኩኝ ናቸው፡፡ በዛ በኩል ተከለከልኩ በዚህ እንድሄድ ታዘዝኩ፡፡
• አትናደድ ከተናደድክም እዚሁ ጨርስና ትገባለህ ብላኝ እንደገና ታናድደኝ ገባች፡፡

አሁን እንግዲህ ሌላ እላፊ ቃል እንዳትናገር በሚል የምክር ቤት አባል መሆኔን የሚያሳይ መታወቂያ ሰጠኋት መታወቂያዬን ይዛ ወደ ውስጥ ገባችና ተመልሳ መጥታ ይግቡ አለችኝ፡፡ ውስጥ ስገባ ወደዚህ ወደዚህ ብለው አንድ ዘብ መድበው ከአንዱዓለም ጋር አገናኙኝ፡፡ እውነት እላችሁ አለው ከአንዱዓም ጋር ብዙ መጫወት አልቻልንም፡፡ ርዕዮትንም መጠየቅ ሰዓት ረፈደ፡፡ እንደዚህ አድርገው አዋክበው ስልችቶን እንድንቀር፣ ጠያቂ አጣው ብሎ አንዱዓለምን ተስፋ እንዲቆርጥ ነው እቅዱ፡፡ ከአንዱዓለም ጋር የምናወራውን የሚያደምጠው ዘብ መውጣት ስለምፈልግ ከመውጣቴ በፊት ግን የተቋሙን ኃላፊ ማግኘት እፈልጋለሁ፣ ዝም ብዬ ከዚህ ግቢ አልወጣም ስለው ደውሎ ሐጎስ የሚባል ስው ጠራላኝ፡፡

እኔ ቢሮ ውስጥ ሆኜ በስርዓቱ ነበር መነጋገር የፈለኩት፡፡ አንዱዓለም እንዲገባ ተደርጎ እዛው በቆምኩበት ለምን እንደዚህ እንደሚደረግ ቢቻል በክብር ካልተቻለ እንደ ዜጋ ለምንድነው የማልስተናገደው የሚል ጥያቄ አቀረብኩለት፡፡ በር ላይ ያሉት አሰተናጋጆች የምክር ቤት አባላት እንዴት እንደሚስተናገዱ ስለማያውቁ ነው፡፡ እኛ በስነ ስርዓት ለማስተናገድ ብለን የበላይ አካል ጠይቀን ነው የምናስገባው (ልብ በሉ የበላይ አካል ጠይቀን የሚለውን) አቶ ግርማ እርሶ ያውቃሉ ለምን እንደታሰረ፣ እርሶም ትንሽ ትዕግሰት ቢያደርጉ ጥሩ ነው በር ላይ ካሉ ሰዎች ጋር ለምን ይጨቃጨቃሉ፡፡ ይቅር ብለን ነው እንጂ ስብዕናዬን ነክቶኛል ብለው አቤት ብለዋል ብሎ አረዳኝ፡፡ እሺ (ሻቢያ ትዝ አለኝ) ሰዎቹ ይጠሩ አልኩና ተጠርተው መጡ (በር ላይ በሚገባህ ቋንቋ ብላ የተሰወረችው ዘብና መግቢያ ላይ እትናደድ እያለች የማላቀውን ጥያቄ ስትጠይቀኝ እና ስታናድደኝ የነበረች ብዙዬ የምትባል ሴት መጡ)፣ ምን እንዳደረኩ ሲጠየቁ ሲናገሩ ይቆጣሉ ወደሚል ዝቅ ብሎ እነርሱን አሰናበታቸውና ከዛሬ ጀምሮ እስረኛ ለመጠየቅ ሰመጣ ሐጎስ ብዬ በዋናው በር ብቻ እንድመጣ በዚሁ መሰረት እንደ ምክር ቤት አባል ወንበር ተዘጋጅቶልኝ እንደምስተናገድ መመሪያ ተሰጠኝ፡፡

የዛኑ ዕለት ሪፖርት ጋዜጣ ላይ ክቡር ሚኒስትር በሚል ርዕስ ስር ያነበብኩት ትዝ አለኝ፡፡ ተጠሪ ወደ አልሆኑበት ተቋም እየደወሉ የስራ መመሪያ የሚቀበሉ፣ በማያገባቸው ገብተው መመሪያ የሚሰጡ እንዳሉ በፌዝ አድርጎ ይነግረን ነበር፡፡ የቃሊቲ የበላይ አካል ማን ነው? ይህ ስው ከቃሊት ተደውሎለት የተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ መጥተዋል እናስገባቸው? ወይስ አናስገባቸው? ተብሎ የሚጠየቀው ከውጤቱ እንደተረዳሁት ይህ ሰው የሰጠው መልስ አስገቧቸው ግን አጠገባቸው ሰው መድቡና ምን እንደሚያወሩ አድምጡ ነው የሚለው፡፡ ይህ ምን ያህል ውርደት እንደሆነ ለሚያዘውም ለሚታዘዘውም ግልፅ ይመስለኛል፡፡ ሌላው ሐጎስ ያለኝ በምን እንደታሰረ ታውቃለህ ነው ያለኝ፡፡ አዎ አውቃለሁ አንዱዓለም ሲሰርቅ፣ ቦንብ ሲያፈነዳ አልተያዘም ባለው የፖለቲካ አቋም እንደታሰረ እና የፖለቲካ እስረኛ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ለዚህም ነው ከአምስት ሺ እስረኛ በተለየ ሁኔታ አንዱዓለምን ልንጠይቅ የምንታገደው፡፡ ሐጎስ ግን አንዱዓለም ይህን ጥያቄ ሲጠይቀኝ ምን አስቦ ይሆን፡፡ አንዱዓለም አሽባሪ ነው ብሎ አያምንም፡፡ ለነገሩ የማረሚያ (ለእነ አንዱዓለም እስር ቤት) ስራው የመጣለትን እስረኛ መጠበቅ ብቻ ነው መሆን ያለበት እንጂ ለምን እንደመጡ ማወቅ ያለባቸው አይመስለኝም፡፡ እረ በህግ፣ መታሰራችን አንሶ መጠየቅ ስንከለከል፣ ወይም መጎላላት ሲደርስብን ወዴት ነው ልትገፉን የምትፈልጉት? ብለን ለመጠየቅ ግድ ይለናል፡፡ የኢትዮጵያ ህገ መንግሰት አንቀፅ 21 በጥበቃ ስር ስላሉ ዜጎች ግልፅ ድንጋጌ አለው፡፡ ከዚህ በተፃራሪ የተፃፈ ህግ፣ መመሪያ ደንብ፣ ወዘተ ህገ መንግሰቱን እንደመናድ ይቆጠራል፡፡ ከሳሾቻችን ህገ መንግሰቱን ስለ ማክበርና ማስከበር በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 9 ማንበብና ተግባራዊ ማድረግ ግድ ይላችኋል፡፡

ethiopforem

የኢህአዴግ/ሕወሓትን አስቀያሚ እና ኢ-ሰብዓዊ ድራማዎችን ሲጋለጥ

የኢህአዴግ/ሕወሓትን አስቀያሚ እና ኢ-ሰብዓዊ ድራማዎችን እናጋልጥ – እስላም ክርስቲያኑ፣ መላ ብሔር ብሔረሰቦች በኢህአዴግ ድራማ ሳትታለሉ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክረን መቀጠል አለብን…
xz
1-ጫካ እያሉ የትግራይ ሕዝብ አልተከተለንም በሚል የሓውዜንን ከተማ በጭካኔ በደርግ የአውሮፕላን ቦምብ እንዲደበደብና ሕዝባቸው በግፍ እንዲጨፈጨፉ ሴራውን አቀነባበሩ፣

2-ኦነግን አሸባሪ ነው ብሎ ለማስጠላት ፣ አዲስ አበባ በሚገኘው የትግራይና ግዮን ሆቴሎች ላይ ቦንብ ራሳቸው በማፈንዳት ንጹሃን ዜጎችን ገደሉ፣

3-የቀድሞው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር የነበሩትን ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያትን ለማሰርና ማህበሩን ለማፈራረስ ራሳቸው ያስቀመጡትን የጦር መሣሪያ እነ ዶ/ር ታዬ ለሽብር ሊያውሉት ሲሉ ተያዙ በማለት የሃሰት ክስ መሠረቱባቸው፣ በሃሰት ምስክርም አሠሯቸው፣

4-በምርጫ 97 ቅንጅትና ህብረት በመላው ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝተው ኢህአዴግ በዜሮ ሲሸነፍ – የምርጫ ኮሮጆ በመገልበጥ ተሸንፎ አሸነፍኩ ሲል፣ በታክሲዎችና በአንበሳ አውቶብስ ላይ ራሳቸው ፈንጅ አጥማጅ፣ ራሳቸው ጠቋሚ፣ ራሳቸው የተጠመደ ፈንጅ አምካኝ በመሆን የሽብር ድራማቸውን ሲያሳዩን ቆይተዋል፣

5-የሙስሊሙን እና የክርስቲያኑን ተቻችሎና አብሮ የመኖር የረጅም ጊዜ ታሪክ ለመበጥበጥና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር፤ በኢህአዴግ ካድሬዎች አማካይነት በርካታ ቤተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ፣ በጅማ በሻሻ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ላይ እሳት በመስደድ በርካታ ክርስቲያኖች በእሳት ተቃጥለው በገጀራ ተጨፍጭፈው እንዲገደሉ ተደረገ – (ግን በወቅቱ እንደ ሼህ ኑሩ ኢማም የድራማ ግድያ አንድም ቃል አልተተነፈሰም ነበር)፣ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ ግን ድርጊቱ የኢህአዴግ ቆሻሻ ድራማ መሆኑን ስላወቀባቸው የታሰበው የሃይማኖት ግጭት ሳይሳካላቸው ቀረ፣

6-በኦሮሞው እና በአማራው፣ በሐረሪውና በአማራው፣ ላይ የብሔር ግጭት ለማስነሳት በበደኖ በአርባ ጉጉ እና በሌሎችም ቦታዎች አማራዎችን በግፍ እንዲጨፈጨፉ ተደረጉ፣ በአኝዋኮችና በኑኤሮች መካከልም የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተካሄደ

7-የፀረ-ኢትዮጵያውያኑ የጣሊያን ባንዳዎቹ የሹምባሽ አስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ እና የሹምባሽ ዜናዊ አስረስ ልጅ፤ የተባበሩት መንግሥታት ጸሐፊ ለነበሩትና ለኢትዮጵያ ድህነትና ውድቀት እድሜ ልኳን ያለመታከት ስትለፋ የኖረችው የግብጽ ዜጋ ለነበሩት ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሌ ኤርትራ እንድትገነጠል የተማጽኖ ደብዳቤ ለፃፈው፤ አሰብን ለኤርትራ ሰጥቶ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጎ ለኑሮ ውድነት ለዳረጋት፤ ባድሜ ላይ ከ 60 ሽህ በላይ ንጹሕ ዜጎች እና ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ በጦርነት እንዲወድም አድርጎ ባድሜን ለኤርትራ አሳልፎ ለሰጠው ፀረ-ኢትዮጵያዊው መሪ ለመለስ ዜናዊ – የግዳጅ ለቅሶ እንዲለቀስ፣ በየ ቀበሌውና በየእድሩ ድንኳን እንዲጣል፣ ድህነት አባሯቸው ሳይሆን መለስን ተማምነው ጎዳና ተዳዳሪ እንደሆኑለት የማስመሰል ድራማውን ያለእፍረት ሲያሰማን ኖሯል ፣

8-የሙስሊሙ ኅብረተሰብ ስለሃይማኖቱ መከበር የሚያደረገው ሰላማዊ ትግል ሲያስፈራው ጀሃዳዊ ሓረካት የሚል የተቀነባበረ ኢህአዴጋዊ ሓረካት የድራማ ፊልም ሠርቶ በሚዲያዎቹ ቢያሠራጭም የሙስሊሙን ትግል ሊገታው ባለመቻሉ የደሴውን የሃይማኖት አባት ሸህ ኑሩ ኢማምን በኢህአዴግ ካድሬዎች በማስገደልና የእርሳቸውን ግድያ በግድ ተቃወሙ እየተባሉ ሙስሊሙ ሰልፍ እንዲወጣ በማድረግ ሙስሊሙ ደግፎናል የሚል ድራማ እየሠረሩ ናቸው፣ ሐምሌ 19 ቀንም በአንዋር መስጊድ ላይ ሙስሊሙ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ሲያቀርብ የሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ ሕገወጥ ለማስመሰል የኢህአዴግ ካድሬዎች ባንዲራ እንዲቀድዱ አስደረገ፣
http://ethioandinet.wordpress.com/

የሚሊዮችኖች ድምጽ በመቐለ፣ ባህር ዳር፣ በጅንካ እና በወላይታ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል

በትግራይ – መቐለ ውስጥ አንድ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ተክለፃዲቅ እና በዚህ ሳምንት “መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ” ተብሎ የነበረው የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ የማነህ አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በህገወጥ መንገድ የታሰሩ መሆኑ ተገልጿል። ሆኖም ዛሬ ምሽት ከእስር መፈታታቸው ነው ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለከተው። Read on PDF
2
http://ethioforum.org

ጋዜጠኛ ወይስ ካድሬ?- ከኢየሩሳሌም አርአያ)

1
ኢየሩሳሌም-አርአያ

የሪፖርተር ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዙሪያ ያቀናበረውን የተንኮል ወጥመድ ተመርኩዤ በሰጠሁት ምላሽ ዙሪያ የማነ አስገራሚና ከርእሰ ጉዳዩ ጋር የማይገናኝ “መልስ” ለመስጠት ሞክሯል። ካድሬ ሆኖ የቀረበው የሪፖርተሩ የማነ ምላሹን ሲጀምር በኢትኦጵ ጋዜጣ በኢየሩሳሌም…ይቀርብ የነበረውን ዘገባና የፃሓፊውን ማንነት ከጠቀሰ በኋላ « በ2005 እ.ኤ.አ ችግር ውስጥ ሊከቱን ከነበሩ…» ይላል። መለስ ዜናዊ የሚመሩት ፓርቲ 18 ጋዜጠኞችን እስር ቤት በመወርወር፣ ከጋዜጣ ዝግጅት ክፍሎቹ ንብረትና ገንዘብ በሃይል በመዝረፍና ሁሉንም ነፃ ፕሬሶች በሃይል በመዝጋት የወሰዱትን እርምጃ ነው…የማነ «ችግር ውስጥ ሊከቱን..» ሲል የመለስ/በረከትን የፈጠራ ክስ ..እርሱም ቃል በቃል የደገመው። በተጨማሪ በነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ በጅምላ የተወሰደውን እርምጃ አለቃው አማረ አረጋዊ በጋዜጣው በወቅቱ ደጋግሞ በርእሰ አንቀፅ በ ደረጃ የፃፈውን « አርፋችሁ ተቀመጡ ያልነው ይህ እንዳይመጣ ነበር..» እያለ የቸከቸከውን እንድናስታውስ አድርጎናል። ከዚህ አልፎ የቅንጅት መሪዎች ላይ በማላገጥ ለገዢው ፓርቲ ግልፅ የሆነ ድጋፍ እንዳለው ያረጋገጠበትን አንዘነጋውም። “ኢህአዴግ በምርጫ መሸነፉን በዘገበና “ የሽግግር መንግስት ይቋቋም” ብሎ በፃፈ ማግስት ነበር፥ ተግልብጦ የጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ አመራሮችን መታሰር በመደገፍ በየጎዳናው የተረፈረፉ ንፁሃን ዜጎች ደም ላይ ሲያላግጥ የታየው። እንዲያውም « እነኢንጂነር ሃይሉ ሻውል በቃሊቲ እስር ቤት መንግስት መሰረቱ» ሲል ለመሳለቅና በህዝቡ ቁስል ለማላገጥ ሞክሯል። ዛሬም እነ የማነ ናግሽ የህዝብን ያልሻረ ቁስል እየቆሰቆሱና የተወሰደውን እርምጃ እያቆለጳጰሱ እግረ መንገዳቸውን የገዢው ፓርቲ ደጋፊነታቸውን በአደባባይ ሊነግሩን ይዳዳቸዋል። አንድ ነገር ማወቅ ያለብህ አንተ የምትሰራበት ጋዜጣ 10ሺህ የማይሞላ ኮፒ ሲያሳትም እነኢትኦጵ፣ ነፃነት፣ ምኒሊክ፣ አስኳል…የመሳሰሉት ጋዜጦች እስከ 160 ሺህ ኮፒ በማሳተም በህዝቡ ከፍተኛ ተቀባይነት ነበራቸው። ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው!! ሪፖርተር ብቻውን ቀርቶም 10ሺህ ኮፒ መድረስ አልቻለም። ሽመልስና አለቃው ይህንኑ ጠቅሰው አማረን ፊት ለፊት አብጠልጥለውታል። « ፍትህ » ጋዜጣ እስከ 40ሺህ ኮፒ ያሳትም የነበረው ከናንተ ኋላ መጥቶ ነው። ህዝብ ሁሉንም ስለሚያውቅ መርጦ ያነባል። በህብረተሰቡ ተቀባይነት የማጣቱ ምስጢር “ የምታራምዱት ፅንፈኛ አቋም ወይም ወገንተኛነታችሁ” ነው።
በዚህ ያላበቃውና ራሱን “ ፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ ነኝ” ሲል የገለፀው የማነ ናግሽ፥ “በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ስለሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብትና የነፃነት ጥያቄ ዘገባ እንደሚቀርብ፤ ከፈለገም የጋዜጣው ድረገፅ ላይ በመግባት መመልከት እንደሚቻል” ያለሃፍረት ሊገልፅ ሞክሯል። በእርግጥ የበረከት ልሳኖች ኢ.ት.ቪና ራዲዮ እንደሚያቀርቡት « በሽብርተኛነት የተከሰሰው እስክንድር ነጋ ማስረጃና ምስክር ቀረበበት..ተፈረደበት» ዜናዎች በሪፖርተር ጋዜጣ ሲወጡ እንደነበር አይካድም። ይህንን ነው « ዘግበናል» የምትለው?..ይህንን ድራማ የመንግስት ሚዲያዎቹ ቀርቶ ካንጋሮው ፍ/ቤት አስቀድሞ ተፅፎ የተሰጠውና ያሳለፈው ፍርደ ገምድል ውሳኔ፣ ከመነሻው የበረከት « ድርሰት» ለመሆኑ « አኬልዳማና ጀሃዳዊ ሃረካት» በቂ ማስረጃ ናቸው። አንተም አለቃህም እውነቱን ሸፍናችሁ የገዢውን ፓርቲ ድርሰት ስለደገማችሁ ይሆን? .. በእስክንድርና በሌሎቹም ንፁሃን ዙሪያ « ዘገባ ሰራን፣ ዜና ለጠፍን..» እያልክ የምትቀባጥረው?…በጣም የሚያሳፍረው የሙስሊሙን ጥያቄና ሰላማዊ ተቃውሞ በተመለከተ « በየጊዜው ዘግበናል» ብለህ ያለአንዳች ህፍረት ልትናገር መሞከርህ ነው። እውነታውን ታዛቢው ወገን ይፍረድ! ?..ይልቅ ሰላማዊ የሆነ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄን በማንሳታቸው በድሬዳዋ በፖሊሶች የተወሰደውን እርምጃ እንዴት እንደዘገባችሁት ላስታውስህ?..« በድሬዳዋ በተፈጠረው ግጭት አንድ የዘጠኝ አመት ታዳጊ ከመሞቱ በቀር የከፋ ጉዳት አልደረሰም» ብላችሁ በጋዜጣው ፃፋችሁ። እንዲህ አይነት ዜና “ዘገባ” ይሰራል?…”የከፋ ጉዳት ደረሰ” የሚባለው ስንት ታዳጊዎች ሲገደሉ ይሆን?..ይህን ልትነግሩን ትችላላችሁ?..ደግሞም ስለሙስሊሙ ፍትሃዊ ጥያቄ አንድም መስመር እንዳልፃፋችሁ አስረግጬ ልነግርህ እወዳለሁ!!
ቀጠልክና፥ « ሕገ መንግስቱን እናከብራለን፣ አንተና መሰሎችህ ምን እንድንፅፍ እንደምትፈልጉ እናውቃለን..» ስትል አስገራሚና የተደበቀ የሚመስለው ማንነትህን ግልፅ አውጥተሃል። የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄም ፥ “በህገመንግስቱ የተቀመጠው የሃይማኖት ነፃነት ይከበር፤ መንግስት በሃማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቁም፤ የሃይማኖት መሪዎቻችንን የመምረጥ መብት ይረጋገጥልን፤” የሚሉ ናቸው። በአንፃሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋግመው የሚቀርቡት ጥያቄዎች ገዢው ፓርቲ ራሱ ላወጣው ሕገመንግስት ተገዢ እንዲሆንና የዜጎች መብትና ነፃነት ይከበር የሚል ነው። ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ « ህገመንግስቱን እናከብራለን» በማለት መግለፅህ ሌላውን በህገወጥነት ለመወንጀል በማሰብ ይሆን?..ይህቺ ገለፃህ የነበረከትን የሰለቸ የማስፈራሪያና ሌላውን የመወንጀያ ዲስኩር ቃል በቃል የደገመች ናት። አያያዝክና፥ « አንተና መሰሎችህ የምትፈልጉት..» ብለሃል፤ “ምንድነው የምንፈልገው?.” ግልፅ ብታደርገው ጥሩ ነበር። ነገር ግን ምን ለማለት እንደፈለክ ከግምት በላይ መናገር ይቻላል፤ ይኸውም « ስለሕወሐት ምንም አንፅፍም፤ ስለነአዜብና ተከታዮቻቸው ዘረፋ አናጋልጥም፣ የምንፅፈው አማረ ስለሚጠላውና አጥብቆ ስለሚቃወመው በረከት ስሞኦን፣ ስለአላሙዲና አብነት..ብቻ ነው የምንፅፈው» ለማለት እንደፈለክ አያከራክርም። የሚያሳዝነው « ፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ ነኝ » ባልክበት ብእር መልሰህ ጋዜጠኞችን በጅምላ ለመፈረጅና እንደገዢው ፓርቲ የተለመደ የፈጠራ ለመስጠት መሞከርህ ነው። በጣም አሳፋሪ ነው!! ባጭሩ “ ሚናህን ለይተህ” አደባባይ መውጣትህ የበለጠ የአንተና የአለቃህ « አቋም» እንዲታወቅ ማድረግህን ልገልፅልህ እሻለሁ።

እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው

የኢህአዴግ መልስ በጉጉት ይጠበቃል
ssaa
አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር “… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል።
“ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የነበረውን የምክክር ስብሰባ የመሩት የአሜሪካን ምክር ቤት እንደራሴ /ኮንግረንስማን/ ክሪስ ስሚዝና ሌላዋ ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ ኢህአዴግ እስር ቤቶችን እንዲያሳይ፣ የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችንም ይሁን ከሙስሊሙ ኅብረተሰብ በግፍ ለእስር የተዳረጉትን እንዲያስጎበኝ ለሚቀርብለት ጥያቄና በጸረ ሽብርና ህጉ ዙሪያ የሚሰጠው ምላሽ በጉጉት ይጠበቃል።
ምክክሩን ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፣ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” በማለት የገለጹት ክሪስ ስሚዝ፣ ከባልደረባቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ የሚያመሩት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን አቋም ለመመርመር የሚያስችላትን ስራ ለመስራት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ከምክክሩ በፊትና በኋላ ክሪስ ስሚዝ በሰጡት ጠንካራ አስተያየት የተደናገጠው ኢህአዴግ አዲስ ዘመን በሚባለው ልሳኑ “አሜሪካ የኢትዮጵያ አጋርና ወዳጅ መሆንዋን አረጋገጠች” በማለት የሌሎች ተናጋሪዎችን ወደጎን በመተው የአምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶን ብቻ አንድ ሃረግ ንግግር ቀንጭቦ ዘግቦ ነበር። በአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ባልተለመደ ሁኔታ የተብጠለጠለው ኢህአዴግ ወዳጆቹን ለማረጋጋት ያማሞቶን ጠቅሶ ያሰራጨው ዜና በወቅቱ በደጋፊዎቹ የፌስቡክ ገጽ ላይ በስፋት ተበትኖ ነበር።
sa
እንደራሴ ኬረን ባስ
ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ መሆኗን ያመላክታል የተባለው የአዲስ አበባ ጉብኝት አስመልክቶ የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኢህአዴግ የፖለተካውን ምህዳር በማጥበብ፣ በጸረ ሽብር ህጉ እያሳበበ የመናገርና የመሰብሰብ መብትን ማፈኑ፣ የነጻ ሚዲያና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማነቁ፣ በተለይም በእስር ቤት የሚሰቃዩ ወገኖችን በአካል በመገኘት በማነጋገር አቋም ለመውሰድ መታቀዱን አመልክተዋል። ይህም ከፖለቲካ እስረኞች ጀምሮ፣ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ጥያቄ ከፍ አድገው በማንሳታቸው ለእስር የተዳረጉትን ወዘተ የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡
“የሚሆነው እስከሚሆን መጠበቅ ነው” በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ አንድ ዲፕሎማት እንዳሉት ነሐሴ 10 ወይም 11 ቀን 2005 (ኦገስት 16 ወይም 17፤ 2013) ወደ ኢትዮጵያ የሚያመሩት ሁለቱ እንደራሴዎች፤ ለኢህአዴግ የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች እጅግ መሰረታዊ እንደሆኑ ይናገራሉ።
“ጉብኝቱ የሽርሽርና እንደተለመደው አይነት የሁለትዮሽ ስብሰባና ስምምነት ለማድረግ አይደለም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እስር ቤቶችን እንዳይጎበኙ እንደከለከለው ማድረግ አይችልም” ብለዋል። ሲያስረዱም “በደቡብ ሱዳን ያለው የፖለቲካ ኡደት፣ በሶማሊያ ጭብጡ ያለየለት ሁከት፣ በኤርትራ ያለው የዛለ መንግስት እጣፈንታና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ጥቂቶች እንዲበለጽጉ ያደረገው ኢህአዴግ መጨረሻው አሜሪካንን በእጅጉ ሃሳብ ላይ ጥሏታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ የሄደው ቁርሾና የጥላቻ ፖለቲካ ሳይፈነዳ ኢህአዴግን ማረቅ የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል። ይህንን አጀንዳ አሜሪካ በቀላሉ ተጭበርብራ የምትቆልፈው አይሆንም።”
“የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ህገደንብ” የሚል ስያሜ ያለው ህግ ኢትዮጵያን የሚመራው ኢህአዴግ ከአሜሪካ መንግስት ለሚፈልገው ማናቸውም ድጋፍ መሟላት የሚገባቸውን የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብት ግብአቶችን በቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ነበር። ይህ ህግ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ አፍስሶ በአሜሪካን ጎትጓቾች (ሎቢዪስቶች) ዘመቻ ያካሄደበትና የወቅቱ የቡሽ አስተዳደር “እንዝላልነት” ታክሎበት ሊመክን ችሏል። ይህን ህግ እንደገና ለማጸደቅ እንደሚሰሩ በግልጽ የተናገሩት ስሚዝ፣ “አሁን ፖሊሲያችንን ዳግም የመፈተሽያ ጊዜ ላይ ነን። ቁም ነገሩ ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር መቆሙ ላይ ነው። ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር እንቆማለን” በማለት አቋማቸውን ግልጽ አድርገው ነበር።
በዚህ ይሁን በሌላ ምክንያት የመለስ ምትክ የሆኑት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና የስኳር ሚኒስትሩ አቶ አባይ ጸሐዬ ሰሞኑንን “የዲሞክራሲ ማበብ የህልውና ጉዳይ ነው” በማለት ለተለያዩ መገናኛዎች በየፊናቸው የተናገሩትን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በስፋት ዘግቦታል። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታው ከመለስ እጅ በተካሄደው ርክክብ መሰረት አፈናውን አጠናክሮ የቀጠለ ስለመሆኑ ከየአቅጣጫው የሚጎርፈው መረጃ ከወትሮው በተለየ ይፋ እየሆነ ነው።
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየመራ ያለው ህወሃት በራሳቸው በአሜሪካኖቹ ቋንቋ ‘አሸባሪን መዋጋት’ በሚል ሰበብ ምዕራባውያንን ሲያልባቸው ቢቆይም “ሽብርንና ሽብርተኛነትን የመታገል ትብብር ግን የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመርገጥ ፍቃድ ማግኛ አይደለም። የመብት ረገጣ ሽፋን ሊሆን አይገባም” ሲሉ በጀርመን ሬዲዮ የመረረ ንግግር ንግግር የተናገሩት እንደራሴ ስሚዝ “ዛሬ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ጊዜ ላይ ነች” በማለት ከሁለት ወር በፊት የተናገሩትን ከዳር ያደርሱት ይሆን የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ወቅት ተደርሷል፡፡
http://www.goolgule.com/

ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!

ጲላጦስን ሔሮድስን ጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል
cc
የየሱስ ክርስቶስ ክስ፣ ፍርድና ሞት ተገቢው የሕግ አሠራር የተከተለ አይደለም፤ ጉዳዩም እንደገና መታየት አለበት በማለት ኬኒያዊው ጠበቃ ዶላ ኢንዲዲስ ሔግ ለሚገኘው ዓለምአቀፉ ፍርድቤት ክስ ማሰማቱን ጀሩሳሌም ፖስት ኬኒያ የሚታተመውን ናይሮቢያን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የቀድሞ የኬኒያ ፍርድቤት አፈቀላጤ የነበረው ይኸው ጠበቃ በወቅቱ የሮም ቄሣር የነበረውን ጢባሪዮስ ቄሣር፣ ጲላጦስን፣ የአይሁድ መሪዎችን፣ ንጉሥ ሔሮድስን፣ የአሁኑን የጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል፡፡
“ማስረጃው በመጽሐፍቅዱስ ላይ ይገኛል፤ ይህንን ደግሞ ማንም ሊክድ አይችልም” የሚለው ጠበቃ የሱስ በወቅቱ ተገቢውን ፍርድ እንዳላገኘ ጉዳዩም በትክክል በፍርድ ሒደት ውስጥ እንዳላላፈ ጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ ሁለት ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁን ያሉት የጣሊያንና የእስራኤል መንግሥታት በዚያን ጊዜ (በስቅለት) የነበረውን የሮም ህግጋትን አሁንም በሕጋቸው ውስጥ በተግባር እየተረጎሙ ስለሆነ ተጠያቂ ናቸው ብሏል፡፡
ክሱን የማቀርበው የየሱስ ወዳጅ (ጓደኛ) በመሆን ነው ያለው ጠበቃ አስቀድሞ ለኬኒያ ከፍተኛ ፍርድቤት ተመሳሳይ ክስ አቅርቦ ውድቅ በመደረጉ ጉዳዩን ወደ ለዓለምአቀፉ ፍ/ቤት መውሰዱ ተጠቁሟል፡፡
በወቅቱ ተገቢው ምርመራና የፍርድ አሠራር እንዳልተፈጸመ የተናገረው ጠበቃ በቦታው የነበረ “ተፍተውበታል፣ በበትርና በጡጫና በጥፊ መትተውታል፣ አሠቃይተውታል በመጨረሻም ላይ ሞት እንደሚገባው ፈርደውበታል” የሚለው ጠበቃ ኢንዲዲስ የሱስ እንዲናገር እንኳን ዕድል እንዳልተሰጠው ተናግሯል፡፡
ስለ ጉዳዩ እንደሚያውቁ የተጠየቁ አንድ የዓለምአቀፉ ፍ/ቤት ኃላፊ ሲመልሱ “ፍርድቤቱ ይህንን ክስ የማየት ሥልጣን የለውም፤ ፍ/ቤቱ የሚመለከተው በመንግሥታት መካከል የሚከሰት ክርክርና ክስ ነው፤ ይህንን ክስ ለመመልከት በጽንሰሃሳብ ደረጃ እንኳን የማይቻል ነው” በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡
ጠበቃ ኢንዲዲስ ግን ተገቢና ትክክለኛ ክስ እንዳቀረበ በእርሱ የሕይወት ዘመንም ፍትህ ተፈጽሞ ለማየት እንደሚበቃ ያለውን ተስፋ ተናግሯል፡፡
በጌትሰማኒ የመጨረሻውን ጸሎት ኢየሱስ ካደረገ በኋላ የሮም ወታደሮችና የካህናት አለቆች መጥተው በያዙት ጊዜ በሁኔታው ህገወጥነት የተናደደው አንደኛው ደቀመዝሙር (ጴጥሮስ) በሰይፉ የአንዱን አገልጋይ ጆሮ ቆርጦ ነበር፡፡ የጴጥሮስን ድርጊት የተቃወመው የሱስ ሲመልስ አስፈላጊ ከሆነ “12 ሌጊዮን (ከ60ሺህ – 90ሺህ) መላዕክት” በቅጽበት በማዘዝ ራሱን መከላከል ይችል እንደነበር መናገሩን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል፡፡ (ማቲዎስ፡26፤53)
http://www.goolgule.com/

Post Navigation