addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “August 31, 2013”

አዜብ መስፍንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ግምገማ እና ጥናት በይፋ ተጀምሯል::

cxበወያኔ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን የሆነውን እና ለመለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው አዜብ መስፍን ቅርብ የነበረውን እንዲሁም የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ አቶ ዘርኡ አንገታቸው በስለት አሳርዶ፣ የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነው በገመንድ አንቆ..የገደለ እና ብዙ ወንጀሎች የሰራው በሙስና የተዘፈቀው ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ መንገዶች ሁሉ ወደ ወይዘሮ አዜብ እያመሩ መሆናቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::
ይህ በሙስና እና በጭካኔው ወደር ያልተገኘለት የሕወሓት የደህንነት አናት በበቀለኛው በአቶ ስብሃት ቡድን በኩል በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ ከስልጣን ወርዶ ከቆየ በኋላ ስልታንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት በሚል ተወንጅሎ ወደ ወህኒ ተወርውሯል::ይህ ግለሰብ በአሁን ወቅት በወህኒ ቤት ከሚገኘው ከቀድሞው የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ድይሬክተሩ እብሪተኛው ገብረዋሃድ ወልደጊዮርጊስ ጋር በከፍተኛ ደረጃ ወዳጅነት እና ቅርርብ ያለው ሲሆን ገብረዋህድ በበኩሉ ከወይዘሮ አዜብ ጋር የተለየ ግንኙነት የነበረው እና አስተማሪዋ የነበረ ሲሆን ለዚህም ስልጣን ያበቃችው እሷ እንደሆነች ሲታወቅ የጸጥታ ሹሙ በቁጥጥር ስር መዋል ወይዘሮ አዜብን ለመያዝ እሳቤ ያደረገ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል::
ወይዘሮ አዜብ መስፍን በቅርቡ የተላያዩ የህወሓት ድርጅቶችን በጋራ ከሚመራው ኤፈርት ተብሎ ከሚጠራው ድርጅት ስራ አስኪያጅነት መውረዳቸው የታወቀ ሲሆን በስልታን ዘመናቸው ድርጅቱ ኦዲት የሂሳብ ምርመራ ተደጎለት የማያውቅ እና ለመንግስት አስፈላጊውን ግብር እና ሪፖርትም ጭምር ያልሰጠ በመሆኑ በቀድሞው ስራ አስኪያጅ ላይ የቀረበው ክስ ወይዘሮ አዜብንም የሚጠብቃቸው እና በቤተሰቦቻቸው ስም የተመዘገቡ ቀረጥ መከፈል ሲገባቸው ያልከፈሉ ጨረታ በዝምድና ሳያሸንፉ የሚወስዱ አላግባብ የሚበለጽጉበት ሁኔታዎች በምርመራ መገኘታቸው በባለቤታቸው ስም እና ዝና ለመነገድ መሞከራቸው ከፓርቲው ውጪ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ሴትየዋ በአቶ ስብሃት ቡድን ጥርስ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል::
ወይዘሮዋ ባለበታቸው በነበረበት ሰአት ከከፍተኛ ደረጃ የሚፈሩ እና ፓርቲውን ለመዘወር በየስብሰባው አደገኛ ቃላቶችን የሚናገሩ የነበሩ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የአሁኑ የደህንነት ሹም ወንጅለውት ከስልጣን በማውረድ አሁን ወደ ወህኒ የወረዱትን ወልደስላሴን ማሾማቸው ይታወቃል::የስበሃት ቡድን ደጋፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ በዚህ ጉዳይ ቂም ቋጥረው መለስ ከሞቱ በኋላ እስከዛሬ ድረስ ከወይዘሮ አዜብ ጋር የጎሪጥ እንደተያዩ ነው::
በአንድ ወቅት እብሪተኛ እና የሃያልነት ስልጣን በእጇ የነበረው አዜብ ባለቤቷ ከሞተ በኋላ ቀስ በቀስ በፖለቲካ ባላንጣዎቿ እየተገፋች ዋጋቢስ እየሆነች መታለች::በአሁኑ ወቅት አዜብ ምንም አይነት ስራ የሌላት እና ቤት ውስጥ ተቀምታ የምታሳልፍ የፖለቲካ ቁማር የተበላሽባት ወይዘሮ ሆናለች::ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት በችሎታ ማነስ እና በሙስና ከኤፈርት የተባረረችው አዜብ በእፈርት ስር የሚተዳደሩ ሰራተኞች ከፍተኛ የሆነ ስሞታ ሲያሰሙባት እና ሲከሷት እንደነበር ይታወቃል::
ምንጮቹ እንዳመለከቱት ወይዘሮ አዘብ በአባይ ወልዱ በሚመራው የሕወሓት አንጃ ውስጥ በረከት ስምኦንን አስከትላ እየተንቀሳቀሰች ሲሆን መሰረቱን መሃል አዲስ አበባ ላይ የተከለው እና ማእከላዊ መንግስቱን እንዳሰኘው የሚያሽከረክረው በደብረጺሆን እና በደህንነቱ ሹም ጌታቸው የሚመራው ሌላው የሕወሓት አንጃ ስብሃት ነጋን አስከትሎ “ብረታሙ” በሚል መጠሪያ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ::ይሀ ብረታሙ እያለ ራሱን የሚጠራው የሕወሓት አንጃ የጸረ ሙስናን ዘመቻውን በበላይነት የሚመራ ሲሆን ወይዘሮዋ ቤተመንግስት በነበሩ ጊዜ የፈጸሟቸውን አሰቃቂ ሙስናዎች እና ተግባራት ለፍትህ ለማቅረብ አስፈላጊውን ጥናት እና ግምገማ እያደረገ ነው ሲሉ ምንጮች መረጃውን ሰተዋል

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

gf
አቶ በረከት

በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።

Short URL: http://www.zehabesha.com/

How Can We be Free? (Henoke Yeshetlla’s Poet, Part I)

mk
August 30, 2013

by HENOKE YESHETLLA

How can we be free if we are shackled by the despondency of silence, even at the stake of the most dismissive, improbable and fatiguing house hold compliancy.

How can we be free, if we are keenly scrutinized by our self generated fear, if we are dwarfed by our tear, if we are mitigated by our delusional prosperity? How can we be free if we are pushed to the calamites of the cynical power and become the proponent of that power? History is secular and obscure for us, we don’t know that we have an inverted and diminished sense of view to what we clamed we knew, basking in the ambiance of self contradiction and having a contra positive personality is a well known yet calculated decisions for us, an amenable day to day life, a life that we endorse and die to live for…Who we are, what are we…? How can we be free?How Can We be Free (Henoke Yeshetlla

Our forefathers believed in God and lived not in the state of self exultation, nor we inherited this care free personality from them but we exhausted their hope and exulted in our failures. How can we be free, if we still believe in ignorance, in-sensitiveness, negligence and absurdity? How can we be free while being the power house of delinquency, blasphemy, an alien to the glimpse of fertility, phobic to an incessant struggle, and inferior to our own moral values and principles?

How can we be free, if we are silenced when the judge irrationally persecute and prosecute the innocence, the police arresting the teenagers and the elderly , the army kills the religious…how can we be free?

How can we be free, with a fluctuating self representation of ours to a palpitating incident ray of an un- free voices?

We are a feeble to our existence, always marching but to recede, always fighting but to surrender, always, fighting but to die, always grouping but to crack down, always standing but to fall! We have no objective nor values to die for, we have no stamina to the cause we believed is right, we are insufficient of our own sufficiency, we stick to what is called hit and run; we are truly a geek for our own calamity, a virus to our own flesh, and an assurance to our own disgrace! How can one be free?

source,,http://ecadforum.com/2013/08/30/how-can-we-be-free-henoke-yeshetlla-poet-part-i/

ተመስገን እላለሁም ፣ አልልምም !

bbbbb
በሰላም አውሎ ላሳደረኝ ፈጣሪ ስተኛም ሆነ ስነሳ ” ተመስገን ፈጣሪየ! ” የምትለዋን ምስጋና ከማቅረብ ተቆጥቤ አላውቅም ። ቸርነቱ የማያልቅበት ፈጣሪ አምላኬ አጉድሎብኝ አያውቅም! ጤና ስጠኝ ስለው ጤናውን ፣ ጥበብ መላ ላጣሁለት መላ ስጠኝ ስለው መላ ብልሃቱን ፣ ጉልበቴን አበርታው ስለው ብርታቱን ፣ ቅን ልቦና ስጠኝ ስለው ርህራሔውን እና የፈለግኩትን ሁሉ አያጓድልብኝም! እናም ዘወትር ተመስገን እለዋለሁ !
ገና ከአልጋየ ሳልነሳ ከአፊ ውስጥ አንድ ቃል ይመላለሳል ፣ ቃሉ ወደ አረፍተ ነገር ሺር በሎ ተቀየረ ! በጨለማ የማያይ አይኔን ወደ ድቅድቁ ጨለማ የመኝታ ክፍል ጣራ አፍጥጦ በምናብ አነበንበዋለሁ … በጀርባየ ተኝቸ ወደ ጣራ ካፈጠጥኩበት ወደ ጎን ግልበጥ እልና እጆቸን ጭንቅላቴ ስር ወሸቅ አድርጌ ከአፊ የማወጣውን አረፍተ ነገር ደጋገምኩ ” ተመስገን ተመስገን ተመስገን አልልም !” … እል ይዣለሁ!
የጋዜጠኛ ተመስገን ድብደባ ሰሞነኛው መነጋገሪያ …
ለምጀዋለሁና እንደቀሩት ቀናት በአርቡ የሳውዲ የእረፍት ቀን መዳረሻ በድቅድቁ ጨለማ ሌሊት ላይ ነቅቸ የሚነበብ የሚታይ ካለ ዳሰስ ዳሰስ አደረግኩ። የሚሞነጫጨር የማለዳ ወግ መነሻ የሚሆነኝ ጉዳይ ከአንድ የፊስ ቡክ ወዳጀ በኩል በውስጥ መልዕክት ደርሶኛል ። ይህው መልዕክት የደረሰኝ የኢቲቪ ዜና አንባቢ ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ በተባለ ቅጽበት ነበር ። መረጃው ሲሰራጭ እኔም በጅዳ ቆንስል ከድብደባ ያላነሰ ግፍ ተፈጽሞብኝ ነበር ። በደል እየተፈጸማቸው ፡ እየታመሙና እያበዱ ስላሉ ወገኖቸ ጉዳይ መፍትሔ ፍለጋና ምክክር ስብሰባ “አትሰበሰብም ፣አትመክርም!” ተብየ የታገድኩበት አጋጣሚ ነበርና የሰማሁትም የሆነብኝም አበሳጭቶኝ አዘንኩ ! የቆንስሉን እገዳ መረጃ በጻፈ እጀ በተመስገን ላይ የተቃጣውን ድብደባ የተሰማኝን ስሜት ሳላንዛዛ በተሰራጨው መረጃ ስር አስተያየቴን እንዲህ በማለት አስቀመጥኩ ” እርምጃው በማንም ይወሰድ በማን ፣ አላስደሰተኝም! ” በማለት …
ይህ ከሆነ በኋላ በውስጥ መልዕክት መቀበያ ሳጥኔ ብዙ የተቃውሞና ድጋፍ መልዕክት ደረሰኝ! የለመድኩት ነበርና ሁሉንም በጥንቃቄ እያነበብኩ አለፍኩት ። ከትናነት በስቲያ ከደረሱኝ መካከል ከላይ የጠቀስኩት መልዕክት እንዲህ ይላል” ሰላም ነብዩ በኢባሲ የደረሰብህ በጣም አሳዝኖኛል አሁን የሰማሁት መረጃክ ስለተመስገን መደብ እጅግ አዝኛለው አንተም ሀቅን እንናገር ስላልክ ከኢባሲክ ከተከለከልክ እደተመስገን አንዳያደርጉህ ተጠንቀቅ ” ይላል መልስ የሚያሻው አስተያየት!… እርግጥ ነው ባለኝ ትርፍ ሰአት መረጃ በማቀበሌ እና ሃሳቤን ባንሸራሸርኩ ፣ ከተቃዋሚ ጽንፈኛ ተብየ እስከ መንግስት ጽንፈኛ ደጋፊዎች የሚሰነዘርብኝ የማስፈራሪያ የዛቻና የ”እንገድልሃለን !” ፉከራ እኔ ለምጀው ባልፍም ብዙዎቹን ያሳስባቸዋል! ከእኒህ ወዳጆቸ መካከል ምክር ለለገሱኝ ወዳጀ ምስጋና ካቀረብኩ በኋላ በሰጠሁት ምላሽ ከጋጠዎጦች ባልተናነሰ እኔንም ሆነ የዜጎች መብት መገፈፍ ያገባናል የምንልን ወገኖች መብት የማያከብሩ ፣ ሰላም የነሱን ፣ መብት ማስከበሩ ቀርቶ የሚገፉን የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ናቸው የሚል መልሴን ሰጠሁ … በዚህ ዙሪያና በተመስገን በምንም ሚዛን ተቀባይነት የሌለው ድብደባ ዙሪያ የማለዳ ወግ አምዴ ልሞነጫጭር ባስብም ድካም የመጻፍ ፍላጎቴን ጎድቶት እንቢ አለኝ !
ዛሬ ሌሊት ….
በድቅድቁ ጨለማ በነቃሁ ሰአት ይህንን እያሰላሰልኩ መረጃዎችን መፈተሽ ይዣለሁ … በኢቲቪ ጋዜጠኛ በተመስገን በየነ ላይ ደረሰበት የተባለውን ድብደባ ተከትሎ የቅርብ ወዳጆቹ ፣ አድናቂዎቹና የኢቲቪ ጋዜጠኞች የሰጧቸው አስተያየቶች ተበራክተዋል ። ይህን ሁሉ ቃኝቸ ተመልሸ ገደም እንደልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ !
በማለዳው ግን ተነሳሁ … እናም ሰሞነኛው ተመስገን አልለቀቀኝም “ተመስገን አልልም ” እያስባለ ያሚያንሰላስለኝን ሃሳብ ከተጋደምኩበት ቀና ብየ መጻፍ ጀመርኩ ! ግጥም ሆነ …
ተመስገን ማለቱ ክፉ ነው ባልልም
ስጋቱ ተገፎ ስላላየሁ ዛሬም
ተመስገን ተመስገን ተመስገን አልልም !
የቱ ነው እውነቱ የዝብርቅርቁ አለም ?
ሰው ያለ ሃጢያቱ ከቶ አይወነጀልም ?
ወህኒ አይወረወር አይደበደብም ?
ፍትህን ተነፍጎ ከቶ አይገደለም ?
ለዚህ የሚያስደስት ዛሬ መልስ የለኝም!
ስል በስሜት መነጫጨርሙ … ቀጠልኩ …
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ባልልም
ድብደባ ግድያን ፍጹም አልደግፍም !
… አልኩና አንገቴን አቅንቸ በኩራት ተሞልቸ ተመስገን ተመስገን አልልም ስል የቅርብ ሩቁን ፣ ግራ ቀኙን የነፍስ ማጥፋት እኩይ ምግባር አጠየቅኩ … ምክርም መክሬ ፍላጎት ምኞቴን እንካችሁ አልኩ …
በጠራራ ጸሃይ በሚንቀለቀለው
“ኢትዮጵያዊ ክብሬ” ስላለ ቢከፋው
ቆፍጣናውን መምህር ያን አሰፋ ማሩን ከቶ ማን ገደለው ?
ያንን ጋዜጠኛ ተስፋየ ታደሰን ማነው ያጋደመው?
በምሽት ጨረቃ ድምቅ ፍንትው ባለው ?
ጀኔራል ሃየሎም ማነው የደፈረው ?
በጥይቱ ባሩድ ከእኛ የለያየው ?
ማለዳው ጸሃይ ጸጥ ረጭ ባለው
የደህንነቱን ሰው ክንፈን ገብረ ማን አጠፋው ?
አመት እንኳ ቀርቶ መንፈቅ ባልደፈነው
ወሎ ሰማይ ስር ረግቶ በሚታየው
በምሽት ጨረቃ ሸሁን በጭካኔ ማነው ገዳያቸው?
አልኩና ውጋት ህመም የምለውን ፣ ምክር ዝክር ይሆናል የምለውን ገጣጠምኩትን ! ከሙሉው ግጥም ግጥሜን በቀነጨብኳት ስንኝ ውጌን ልቋጭ …
ችግሩን ለማጥፋት ከሆነ የምናልም
ለድብደባ ፣ እስራት ፣ ለተበራከተው የሰው ልጅ ግድያም
መፍትሄ ፍለጋ ከሆነ ምንሻው እንዳይደጋገም
“ምንድነው ሰበቡ ” ብሎ ማጠየቁ ሳይጠቅም አይቀርም !
ህግ ባለበት ሃገር ግፉ ተበራክቶ ፣ ልዩነቱ ከሰፋ
ችግሩን እንመርምር ያለ መቁረጥ ተስፋ
ፍርድን አናዛባ ፣ ግፉንም አናብዛ ሰውን አናስከፋ
ሃገር አናሰድብ ሰሟን አናስጠፋ
ሰላምን አናውርድ ልዩነቱ ይጥበብ እንድንኖር በተስፋ
ይህን ሳናሟላ ፣ በልዩነት ሰበብ ሰውን አንበድለው
ሰው ከሃገሩ በምድሩ ክብሩን አናሳጣው
መብት በጠየቀ አሸባሪ አንበለው !
ይህን ካደረግ ሰውን ካከበርነው
ማግለልን ካቆምን በዘር በቀለሙ ብሎም በእሳቤው
ያኔ ነው ቀናችን ድብደባ ግድያ የሚጠፋውማ
ያኔ ነው ቀናችን ተመስገን መባያው
እልል የሚባለው ሰለም የሚኖረው!
ጥላቻን አጥፍተን ፣በእርቅ በይቅርታ ደምቀን ስንታይ ነው
ተመስገን ፣ ተመስገን ፣ ተመስገን የምንለው !
ከእንቅልፍ አንቅቶ ያብተከተከኝን ሙሉ የስንኝ ቋጠሮ በወግ አሰናድቸ እስካቀርበው ለዛሬ የማለዳ ወግ ይህችን ታክል ካወጋን አይከፋም ! ለእናንተ ለወዳጆቸ መልካም ቀንን ተመኝቸ አንድየን አመስግኘ እንለያይ ! ፈጣሪ ሆይ አንተን አልፋና ኦሜጋ እናመሰግንሃለን ! ተመስገን !
ሰላም
ነቢዩ ሲራክ
ከወይና ደጋው ሳውዲ በአንዷ ከተማ
http://www.goolgule.com/

በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በስነልቦና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን ተገለጠ

po
ኢሳት ዜና :-ከኢትዩ -ኤርትራ ግጭት እና ኢትዮጵያ ከሶማሊያው አልሸባብ ጋር ካደረገችው ጦርነት ጋር በተያያዘ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች በስነልቦና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን የጦር ሃይሎች ሆስፒታል የስነ ልቦና ህክምና ቡድን መረጃ አመለከተ

ከመዝገብ ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ፤ በጦርነቱ ስዓት በተከሰተ ምንነቱ ባልታወቀ የሞራል እና የስነ ልቦና ችግር ከ3 ሺ 500 በላይ ወታደሮች እስከ እብደት በሚያደርስ በሽታ ተጠቅተዋል።

ሪፖርተራችን በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ እንደተመለከተው አንዳንድ ወታደሮች በአሰቃቂ የእብደት ደረጃ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ከማህበረሰቡ ተገልለው ተገቢው ህክምና ሳይሰጣቸው በስቃይ ላይ ይገኛሉ።

ዘጋቢያችን አንዳንድ የወታደር ቤተሰቦችን አነጋግሮ ባጠናከረው መረጃ መንግስት አካላቸውን ላጡ ሰዎች የ5000 ብር ክፍያ ከመፈጸም ባሻገር ለአዕምሮ ተጎጅዎች ምንም ዐይነት ክፍያ አላዳረገላቸውም።

የኢሳት ዘጋቢ እንደሚገልጸው ትክክለኛ የመረጃ አያያዝ ዘዴ ቢቀየስ የስነ አእምሮ ተጎጂ ወታደሮች ቁጥር ከተገለጸው አሀዝ በብዙ እጅ ሊልቅ ይችላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሐት ነባር ታጋዮችን የሚያሰባሰብ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ ህወሐትን አሰናፊ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ የሰሩ በተለያዩ የትግራይ እና በሐገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ታጋይ የህወሐት ተወላጆችን ለመደገፍ በማሰብ የህይወት ታሪካቸውን የሚሞሉበት ፎርም በሐገሪቱ ባሉ የፖለቲካ ቢሮዎች መበተኑ ታውቋል።

ESAT

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡- በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ (ከተ/ሚካኤል አበበ)

nn
ከተክለ ሚካኤል አበበ

1- ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው። የአንድነት ምሽት በቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል። የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስም መከሰስም የለበትም። ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስት ወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።

የፖለቲካ ተንታኝና የፖለቲካ መሪ

2- የፖለቲካ መሪ ከፖለቲካ ተንታኝ መለየት አለበት። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ የጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ተንታኞችን/የምሁራንን ስራ ይጋፋል። ያ ብቻም አይደለም። መምራት አቅቶት፤ ወይም መምራት ጠፍቶት፡ በአካልና በስም የፖለቲካ መሪነቱን ወንበር ተቆናጦ፤ በግብር ግን የፖለቲካ ተንታኝነትን ቦታ ይዞ፤ የፖለቲካ መሪነትን ስራ በፖለቲካ ትንታኔ ሊያካክስ ይሞክራል። ያም ብቻ አይደለም፡ የፖለቲካ መሪነት ሚናን ከፖለቲካ ተንታኝ ጋር ያደባለቀ መሪ፤ የያዘውን የፖለቲካ መሪነት ሀላፊነት ከተንታኝነት ሲለሚቀይጠው፤ ትንታኔው ንጹህ አይሆንም። ስለዚህ የፖለቲካ ትንታኔውን መቀበል ይከብዳል። ባይከብድም ትንታኔው ጎዶሎና ወደሁዋላ የሚጎትት፤ ወይንም ወደፊት የማያራምድ ይሆናል። ወይም ትንታኔው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የሚደረግ ጥልቅ ያልሆነ ትንታኔ ይሆናል።

3- ለምሳሌ ብርሀኑ ነጋ ባለፈው የኢሳት ስብሰባ ላይ ያቀረበውን የንግግሩን ገጽ 16 መጨረሻና ገጽ 17 መጀመሪያ ብንመለከት ሀሳቡ ጥልቅ ወይም ሀቀኛ አለመሆኑን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/6563 ለዚህም ነው ምሁር ፖለቲከኛ መሆንን ከመረጠ፤ ምሁርነቱን ቀንሶ መሪነቱን እንዲያጠብቅ ግድ ነው የምንለው። ኦባማን ውሰዱ። ኦባማ ሲመረጥ ምሁር ነበር። ከአራት አመት በሁዋላ ግን ምሁርነቱ እየቀነሰ፤ ወደቡሽነት እየተጠጋ መጥቷል። የኦባማ የሶሪያ አቋም፤ ከቡሽ የኢራቅ አቋም ብዙ አይለይም። አሳድን እንበለው ወይም እንብላው እያለ ነው። ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) ያንን መለየት ነው የተሳነው። በፖለቲካ መሪነት መጥቶ (በግንቦት ሰባት ሊቀመንበርነት) የፖለቲካ መሪነቱን ግን ትቶ፤ ምሁር ለመሆን ሞከረ። ተንታኝ። የፖለቲካ ተንታኝ በመሆን የጋዜጠኞችንና የምሁራንን ስራ መሻማት ብቻ ሳይሆን፤ ሁለቱንም ሳይሆን ቀረ። በዚህ ረገድ ጃዋር ይሻላል። እንደተንታኝ በደንብ ይተነትን ነበር። የተንታኝነቱን ሚና ትቶ ባለፈው ሰሞን የራሱን የፖለቲካ አቋም ሲያንጸባርቅም፤ ብዙ ሰዎችን ቢያበሳጭም፤ እቅጩን ነው ያስቀመጠው። ብሬ አድበሰበሰው። በእስር ላይ የሚገኙትም ይሁኑ በነሱ የተተኩትን ከነሱም የቀደሙትን ሙስሊሞች አካሄድና እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩ ካሉ፤ ጥርጣሬያቸው በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ነው የተፈጠረው ለማለት ይከብዳል። በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የማይበገሩም ከተጠራጣሪዎቹ ተርታ ውስጥ አሉበትና።

4- የዲባቶ ብርሀኑ ነጋ ያልጠራ ትንታኔ የመነጨው፤ ፖለቲካዊ መሪ መሆንና ፖለቲካዊ ምሁር/ተንታኝ መሆንን አጣምሮ ለመሄድ ከመሞከር ነው። የፖለቲካ ተንታኝ የምለው፤ በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ በአድራጊ-ፈጣሪነት ሳይሳተፍ ወይም መሳተፍ ሳይጠበቅበት፤ የአንድን ፖለቲካዊ ስብስብ/ማህበረሰብእ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየቃኝ፤ ከአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ሁነቶች ጋር እያጣቀሰ፡ የሁነቶቹን ምክንያት የሚያብራራ፤ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን የሚጠቁም፤ አደጋዎችን የሚተነብይ፡ ተመልካችና ተናጋሪ ማለት ነው። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ አደናጋሪ ነው የሚሆነው። የፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ተንታኝ መሆን የለባቸውም እያልኩ አይደለም። እኔ የምለው፤ አንደኛ ፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ትንታኔ ችሎታቸው የሚገለጸው በፖለቲካዊ አመራራቸው በሚወስዱት ፖለቲካዊ እርምጃ ውስጥ መሆን አለበት ነው። ሁለተኛ፡ ፖለቲካን መተንተን የፖለቲካ መሪዎች ዋና የአደባባይ ስራ መሆን የለበትም ነው። እዚያው ድርጅታቸው ውስጥ እንደፍጥርጥራቸው። ይፋዊ ፖለቲካዊ ስራቸው ግን፤ መምራት እንጂ መተንተን አይደለም። አቶ መለስ ከሞቱ በሁዋላ ብቻ ያለውን ሁኔታ እንኳን ብንለመከት ግን፤ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ብርሀኑ ነጋ፤ ከሲሳይ አጌና ጋር ያደረጋቸውን ቃለምልልሶች ወይንም ያለፈው ሰሞንን የኢሳት መድረክ ጨምሮ፤ በቀረበባቸው መድረኮች ላይ የሚናገራቸወን ስንለመከት አድራጊ የፖለቲካ መሪ ሳይሆን፤ ተንታኝ ጋዜጠኛ ወይንም እዚህ አገር እንደሚሉት ጠቢብ ምስክር ለመሆን ነው የጣረው።

5- ያ ብቻም አይደለም፤ አሁን በእመ-ብርሀን፤ ሰላሳ ድርጅቶች የኢትዮጵያን እጣፈንታ ከህዝብ ጋር ሊመክሩ በተሰበሰቡበት መድረክ ላይ ለመነሻ የሚሆን የአስር ደቂቃ ንግግር አድርጎ የተቀረውን ሰዓት ለህዝብ ውይይት መተው እንጂ፤ የ55 ደቂቃ ድርሳን ማንበብ ምን የሚፈይደው ነገር አለ? ብርሀኑ ነጋ ባለፉት ሶስት ወራት በኢሳትም ይሁን በተለያዩ መድረኮች ያገኘውን እድልና ሰዓት ስንመለከተው ደግሞ የንግግሩ መርዘም ስህተትነትና አበሳጭነት ይጎላል። ያ ብቻም አይደለም፤ ሶስት ሺህ ምናምን አመት፤ መጀመሪያ በጸሀዩም በጨረቃውም በማምለክ፤ ከዚያ ብሉይን በመቀበል፤ ከዚያ ክርስትናን፤ ከዚያ እስልምናን፤ ከዚያ ካቶሊክን፤ ከዚያ ፕሮቴስታነንስዝምን፤ በመቀበልና በማቻቻል ለኖረች አገር፤ የሊበራሊዝምና ዴሞክራሲ መፍትሄ ለሀይማኖት ነጻነት የሚል የአንድ ሰዓት ስብከት ያስፈልጋታል? ቢቀርብንስ?

6- በዚህ ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ ግንቦት ሰባትን ወክሎ ንግግር ካቀረበው ብርሀኑ ነጋ ይልቅ፤ የሽግግር ምክርቤቱ እጥር ምጥን ባለች ባለአራት ገጽ ወረቀቱ፤ የተሻሉ የሽግግር ሀሳቦችን አቅርቧል። http://etntc.org/ENTC/wp/wp-content/uploads/ESAT-Presentation-0818.pdf። እነሱ የሚመኟት ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለበት፤ ሽግግሩ ምን እንደሚመስል፤ የሽግግር ሰነድ የሚያረቅ ኮሚቴ ስለማዋቀራቸው፤ አለማቀፍና አገርአቀፍ የእምቢተኝነት ቡድን ስለማቋቀም፤ ድርጅታቸው ምን እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል። ከሽግግር ምክርቤቱ አራት አመት ቀደም ብሎ የተቋቋመው ግንቦት ሰባት ግን ጥምረት ከተቋቋመ ከሶስት አመት በሁዋላ፤ የከማል ገልቹ ኦነግ ከተመለሰ ከሁለት አመት በሁዋላ፤ ገና ስለድርጅቶች አንድነት፤ በጋራ ትግል ወያኔን ስለማስወገድ አጣዳፊነት ይሰብካል። የዛሬ አመት፡ የዛሬ ሁለት አመት፡ የዛሬ ሶስት አመት ከነበርንበት ብዙም ፈቀቅ አላልንም።

7- ኢሳት ይሄንን ስብሰባ ማዘጋጀቱ ይደነቃል። ይሁን እንጂ፤ የኢሳት አስተዳዳር የሆነው ወዳጄ ነአምን ዘለቀ የዛሬ አመት አካባቢ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ስብሰባ ሲዘጋጅ፤ (ያኔ ስብሰባው የተዘጋጀው በኢሳት ሳይሆን በግንቦት ሰባትና በነኑሮ ደደፎ (ዲባቶ)/ከማል ገልቹ ኦነግ ነበር)፤ እባክህን መሪዎቹ ንግግር ያሳጥሩና ለሰዉ እንዲተነፍስ ግዜ ይስጡት ብዬ አሳስቤው ነበር። ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም። እነሆ፤ ባመቱ፤ ሌላ ውድ መድረክ ባከነ። የብርሀኑ ነጋ ጽሁፍ፤ የመጀመሪያው አስራሶስት ገጽ ለዚያ መድረክ አስፈላጊ አልነበረም። ነገር መቁረጥና ማሰጠር፤ እንዲሁም መድረክ ላይና ምድር ላይ የምናቀርበውን መምረጥ አለብን። ያለበለዚያ ትክክለኛና ውጤታማ ሚናችንን መለየት አለብን።

ተስፋ፡ አድናቆትና፤ ግብዣ

8- መቼም ተቃጥላችሁ አትሙቱ ያለን ፈጣሪ መጽናኛ አያሳጣንም፤ በግንቦት ሰባት ሊቀመንበር አቀራረብ ብንበሳችም፤ አላህ የሚያጽናናን አላሳጣንም። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ እኛ በምናደርገው ነገር ምንም ቀስቀስ በማይልበት፤ ፖለቲካዊ አየሩ ጸጥ ረጭ ባለበት ሁኔታ ነው፤ የዛሬ ሶስት ወር አካባቢ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተሳካ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ላለፉት ስምንት አመታት ሰልፍ አይታ ለማታውቀው አዲስ አበባ ሀያ መቶም የሁን ሀያ ሺህ ሰው ያስወጣ ሰልፍ ተከሰተ። ያ ያጽናናል። እነሆ ያኔ በያዙት ቀጠሮ መሰረት፤ ሁለተኛው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በመጪው እሁድ ይቀጥላል። መቼም ብዙዎቻችን ፈሪዎችና ሸሺዎች በሆንበት ሁኔታ፤ ጥቂት ዠግኖች አልጠፉምና፤ የሰማያዊ ፓርቲዎች ድፍረትና ቁርጠኝነት የሚያስደንቅ ነው። የህወሀት ኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር በኩል ሰልፉ ህገወጥ ነው ቢሉም፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ግን ሰልፉ ህጋዊ ነው፤ እንገፋበታለንም እያሉ ነው። የመጪው እሁድ ትልቅ ተጋድሎ ዋዜማ ላይ ነን።

9- እንዲህ ያለውን ትእይነት ቆሞ መመልከት ብቻ ግን ነውር ነው። መቼም አንዴ ሸሸተን ወጥተናል፤ በወጣንበትም ቢሆን ግን፤ የምንችለውን እንኳን በማድረግ ተዋናይ መሆንም አለብን። የኛ የተቀናቃኙ/ተፎካካሪው/ተቃዋሚው ጎራ፤ በተለይ በውጪ የምንኖረው ተቃዋሚዎች ትልቁ ችግር፤ ማድረግ የምንችለውን እንኳን ማድረግ አለመቻላችን ነው። በሰላማዊም ይሁን ደማዊ መንገድ፤ በአመጽም ይሁን በጸሎት ለሚታገሉት ስንቅና ትጥቅ ማቀበል። ስንቅና ትጥቅ ላለማቀበል ብዙ ምክንያት መደርደር ይቻላል። ምንም ምክንያት ግን አጥጋቢ አይሆንም። ቅዳሜና እሁድ የዱለትና የቁርጥ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ እያብራራ የሚተነትነው፤ የምእራባዊያንን ሴራ የሚመሰጥረው ወዳጄ፤ የኢሳት ዝግጅትን የ20 ብር ትኬት ስሰጠው ፊቱን እንዳጨፈገገው መሆን የለብንም። ለሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፍ መሳካት እንጸልያለን። በጸሎት ብቻ አናበቃም። በግብርም እንከተላለን።

10- መቼም በየከተማው ብዙ የማይደክማቸው ሰዎች አሉ። እነሆ በመጪው ቅዳሜ ማታ፤ በዚህ በኛ ከተማ ትንሽ ተንፈስ እንላለን። ተሰብስበን ኢህአዴግን ከመዘልዘል ባሻገር፡ የትግሉ በረከት እንጥፍጣፊ ይደርሰን ዘንድ የአንድነት ምሽት ያዘጋጁ አሉ። “የአእላፋት ድምጽ ለነጻነት” የተሰኘውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ዘመቻ በመደገፍ እዚህ ቶሮንቶ ከተማ፤ እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር፤ ቅዳሜ ኦገስት 31 ማታ ከ6ሰኣት ጀምሮ’፤ 2050 ዳንፎርዝ ጎዳና በሂሩት ሬስቶራንት የቤተሰብ አዳራሽ የእራት ምሽት ተዘጋጅቷል። በሰሀን $ 50 ብቻ። ለጥንዶች $ 60። ለኔቢጤው ደሀ ደግሞ $ 30 ብቻ። ገቢው፤ ከወጪ ምላሽ ለአንድነት ፓርቲ የሚሄድ ነው።

11- እነሆ፤ በአካል ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ጋር ላንዘምት እንችላለን። በአካል ከሰማያዊ ፓርቲም ጋር አንሰለፍ ይሆናል። ከአንድነት የነጻነት ድምጾች ጋር ለመጮህ ግን አይሳነንም።ለሚጮሁት ጉልበት፤ ለሚሰለፉት ብርታት፤ ለሚዘምቱትም ጽናት ልንለግስ እንችላለን። በያለንበት አካባቢ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች እንርዳ። እዚህ ቶሮንቶ ያለን፤ ቅዳሜ ሂሩት ሬስቶራንት ብቅ እንበል። ቅዳሜ እንኩዋን፤ ላሊበላና ብሉናይል፤ ዞብልና ራንዴቩ ይቅሩብን። ቅዳሜ ማታ፤ ሂሩት ጋር እንገናኝ።

እኛው ነን። ከቶሮንቶ። ነሀሴ፡ 2005/2013።

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡ ክፍል 13

በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6908

የሰማያዊ ፓርቲ የነገው ሰልፍ ህገወጥ ነው – ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ

hh
ማሳወቅ ባለብን ሰዓት አሳውቀናል፤ ለሚፈጠረው ችግር መንግስት ሀላፊነቱን ይወስዳል- ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ሰማያዊ ፓርቲ ሳያስፈቅድ በሚያካሂደው ሰልፍ ለሚፈጠር ችግር ሀላፊነት ይወስዳል- አቶ ሽመልስ ከማል
የሰማያዊ ፓርቲ የነገው ሰልፍ ህገወጥ ነው – ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ
በነገው እለት ሰማያዊ ፓርቲና የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ፅ/ቤት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ህገወጥ ነው ብሏል
ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የሚመለከተውን አካል አሳውቄአለሁ ያለው ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ፤ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በፊት ማሳወቁን ገልፆ፤ በሁለት ሰልፎች ምክንያት ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂው መንግሥት ነው ብሏል፡፡
“ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉ አልተፈቀደለትም ያሉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፤ ፓርቲው ይህንን ተላልፎ በሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር ሀላፊነቱን ይወስዳል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የሚፈልግ አካል ሰልፉን ያደራጀውን ሰው፣የሰልፉን አላማ ይዘት፣ የሚወጣውን የሰው መጠን ግምት፣የሚካሄድበትን ጊዜና ቦታ መግለፅ እንዳለበት የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ማስፈቀድም እንደሚያስፈልግ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡ “ማሳወቅ ማለት ማስፈቀድ አይደለም” ያሉት አቶ ሽመልስ፤ ካሳወቁም በኋላ ፍቃድ መጠየቅ የግድ ነው ብለዋል፡፡ “በበኩሌ የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፅህፈት ቤት እሁድ የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እንቅስቃሴን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማስፈቀዱን አውቃለሁ” ያሉት አቶ ሽመልስ፤ በየትኛውም አገር በአንድ ቀንና በአንድ ቦታ ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች ማካሄድ ስለማይፈቀድ፣ ፈቃድ ሰጭው አካል ይህን እያወቀ ለሰማያዊ ፓርቲ ፈቃድ ይሰጣል የሚል እምነት የለኝም ብለዋል፡፡ “በመሆኑም ሰልፉን የሚያካሂደው የተፈቀደለት አካል ነው” ብለዋል፡፡ አቶ ሽመልስ አክለውም፤ “በየትኛውም አገር ፍቃድ ሳይገኝ ሰላማዊ ሰልፍ አይወጣም፣ማሳወቅ ብቻ በቂ ነው ብሎ ህግን በመናቅ የትም አይደረስም፣ይህን ተላልፎ ቢገኝ ለሚፈጠረው ችግር ፓርቲው ሀላፊነት እንደሚወስድ ራሱም ያውቀዋል” ብለዋል፡፡ “በአንድ ቀን ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች የማይፈቀዱት የተለያዩ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠርና የፀጥታ ሀይሎች ወደተለያዩ ስራዎች ሊሰማሩ ስለሚችሉ የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት ነው” ሲሉ አቶ ሽመልስ ገልፀዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤ ፓርቲያቸው ከሶስት ወር በፊት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ያነሳቸው የህዝብ ጥያቄዎች ካልተመለሱ፣ ከሶስት ወር በኋላ ሁለተኛውን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ በተደጋጋሚ መግለፃቸውን አስታውሰው፤ ይህም ጊዜ ነገ መሆኑንና አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸውን ተናግረዋል፡፡ “እኛ የማሳወቂያ ደብዳቤውን ያስገባነው ከሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፅ/ቤት በፊት ነው” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ መንግስት በእኛ ላይ የተደረበውን ሰላማዊ ሰልፍ መሰረዝ እንዳለበት በመግለጫ ማሳወቃቸውንና ሰልፉን ከማካሄድ የሚገታቸው እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ “ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ ለሚፈጠረው ችግር መንግስት ሀላፊነቱን ይወስዳል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ፅ/ቤት የማሳወቂያ ደብዳቤውን ካስገቡ በኋላ ፅ/ቤቱ የስብሰባውን አላማ፣የትና መቼ እንደሚያካሂዱ፣የሰው ብዛት ምን ያህል እንደሚገመት ፓርቲው እንዲያሳውቀው በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ለጥያቄዎቹ ሁሉ በደብዳቤ ምላሽ መስጠታቸውን ኢ/ር ይልቃል አስታውሰው፤ ነገር ግን ማሳወቂያ ፅ/ቤቱ በ48 ሰዓት ውስጥ ምላሽ ባለመስጠቱ እንደተፈቀደ ቆጥረን ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ከሰማያዊ ፓርቲ በኋላ መጥቶ ሰልፍ የሚያካሂደውን አካል በማስቆም፣ መንግስት ሀላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል – የፓርቲው ሊቀመንበር፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ፤ “እኔ የማውቀው አንድ ሰላማዊ ሰልፍ ነው፤ የሰማያዊ ፓርቲ ህገወጥ ነው” በማለት መልሰዋል፡፡ ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ በዕለቱ ስለመካሄዱ ለፓርቲው አሳውቀው እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ማርቆስ፤ “ደብዳቤ ፅፈን ስንሰጣቸው የፓርቲው ሰዎች አንቀበልም በሚል ወርውረውት ሄደዋል” ብለዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን የጠየቅናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል፤ “ፅ/ቤቱ በቃልም በደብዳቤም ያሳወቀን ነገር የለም፤ እኛም በነገው ዕለት ሰልፉን እናካሂዳለን” በማለት የፅ/ቤቱን ምላሽ አጣጥለውታል፡፡ ትናንትና ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠርቶ እንዳነጋገራቸው የገለፁት ኢ/ር ይልቃል፤ “ሰላማዊ ሰልፍ እንደምታካሂዱ የደረሰን መረጃ የለም” መባላቸውን ጠቁመው፤ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት እንዳሟሉ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ አሳውቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ በስልክ ያነጋገርናቸው ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ከሚመለከተው አካል ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው ገልፀው፣ ሰማያዊ ፓርቲም ሰልፉ የተፈቀደበትን ማስረጃ ማቅረብ እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡ “በመሆኑም የነገው የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ህገ ወጥ ነው” ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

ሰበር ዜና በአሁኑ ሰዓት የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ተከቧል

mmm
በአሁኑ ሰዓት የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ተከቧል
በፓርቲው ጽ/ቤት ውስጥ ወደ 100 የሚጠጉ አባላት የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ወደ 60 የሚሆኔ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ በግቢው ውስጥ ይገኛል ማንም መውጣትም ሆነ መግባት አይችልም፡፡ ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን እንገልጽላችኋለን፡
ፓርቲው ከሰላሳ ደቂቃዎች በፊት ባደረሰን መረጃ፤ የሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ከባድ መሳሪያ በታጠቁ ፖሊሶች ተከቧል፡፡ ወደ መቶ የሚጠጉ አባላት በፅ/ቤቱ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የሚፈጠረውን እየተከታተልን እንነግራችኋለን ያለን ቢሆንም ከአስራ አምስት ደቂቃ ቆይታ በኋላ ደግሞ ይህንን መግለጫ አውጥቷል፡፡
ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል!
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ለሕዝብ ቃል በገባነው መሠረት በድጋሚ ተቃውሞ ሰልፍ አቅዶ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ሥራ መሳካት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ነሐሴ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፣ መጀመሪያ ባቀረብነው ደብዳቤ ላይ ያልተካተቱ ጉዳዮችን እንድናካትት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈልን ደብዳቤ ተጠይቀን አስፈላጊውን መልስ አሟልተን ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀናል፡፡
በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግሥታዊ መብት እንደሆነና ማንም ሊከለክለን እንደማይችል በማያሻማ መንገድ ተገልጿል፡፡ ሰልፉን የማሳወቁ ዓላማ የጥበቃ አገልግሎትና አንዳንድ አስተዳደራዊ ድጋፎችን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ መንግሥት የጥበቃና የቦታ ችግር ካለ ሰልፉን ለሌላ ጊዜና ቦታ እንዲያደርግ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ በፅሑፍ መልስ ይሰጣል የሚል ድንጋጌ አለ፡፡ ነገር ግን በመንግሥት በኩል ላቀረብነው የመብት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት ሲገባው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በመጠቀምና ዜጐችን አስገድዶ ሰልፍ እንዲወጡ በማስፈረም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ በተደራቢ በሃይማኖት መቻቻል ስም ህገ መንግሥቱን በመጣስ የሃይማኖት ተቋማትን ለራሱ የድርጅት ፖለቲካ መጠቀሚያና የሰማያዊ ፓርቲን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ይህ አሰራር እንዲስተካከል መንግሥትን በመግለጫ ብንጠይቅም የተሰጠን ምላሽ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የሀገሪቱን ህገ መንግሥትና የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ እንዲሁም ሰልፍ ጠሩ በተባሉ አካላት ግልፅ የሆነና የተቀነባበረ ህገ ወጥ ሴራ ሆኗል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. የምናደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ከዚህ ቀደም ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረብ ከመሆን አልፎ የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር አድጓል፡፡ በመሆኑም በመንግሥት የሚደረገው ዓይን ባወጣ ሁኔታ ህግን የመጨፍለቅ ተግባር እንዲቆም ለምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከጐናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ምንጊዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!
ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

የሰማያዊ ፓርቲ ስጋት እና መግለጫ!

bb
የሰማያዊ ፓርቲ ስጋት እና መግለጫ!

ፓርቲው ከሰላሳ ደቂቃዎች በፊት ባደረሰን መረጃ፤ የሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ከባድ መሳሪያ በታጠቁ ፖሊሶች ተከቧል፡፡ ወደ መቶ የሚጠጉ አባላት በፅ/ቤቱ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የሚፈጠረውን እየተከታተልን እንነግራችኋለን ያለን ቢሆንም ከአስራ አምስት ደቂቃ ቆይታ በኋላ ደግሞ ይህንን መግለጫ አውጥቷል፡፡

ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል!
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ለሕዝብ ቃል በገባነው መሠረት በድጋሚ ተቃውሞ ሰልፍ አቅዶ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ሥራ መሳካት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ነሐሴ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፣ መጀመሪያ ባቀረብነው ደብዳቤ ላይ ያልተካተቱ ጉዳዮችን እንድናካትት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈልን ደብዳቤ ተጠይቀን አስፈላጊውን መልስ አሟልተን ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀናል፡፡
በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግሥታዊ መብት እንደሆነና ማንም ሊከለክለን እንደማይችል በማያሻማ መንገድ ተገልጿል፡፡ ሰልፉን የማሳወቁ ዓላማ የጥበቃ አገልግሎትና አንዳንድ አስተዳደራዊ ድጋፎችን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ መንግሥት የጥበቃና የቦታ ችግር ካለ ሰልፉን ለሌላ ጊዜና ቦታ እንዲያደርግ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ በፅሑፍ መልስ ይሰጣል የሚል ድንጋጌ አለ፡፡ ነገር ግን በመንግሥት በኩል ላቀረብነው የመብት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት ሲገባው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በመጠቀምና ዜጐችን አስገድዶ ሰልፍ እንዲወጡ በማስፈረም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ በተደራቢ በሃይማኖት መቻቻል ስም ህገ መንግሥቱን በመጣስ የሃይማኖት ተቋማትን ለራሱ የድርጅት ፖለቲካ መጠቀሚያና የሰማያዊ ፓርቲን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ይህ አሰራር እንዲስተካከል መንግሥትን በመግለጫ ብንጠይቅም የተሰጠን ምላሽ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የሀገሪቱን ህገ መንግሥትና የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ እንዲሁም ሰልፍ ጠሩ በተባሉ አካላት ግልፅ የሆነና የተቀነባበረ ህገ ወጥ ሴራ ሆኗል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. የምናደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ከዚህ ቀደም ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረብ ከመሆን አልፎ የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር አድጓል፡፡ በመሆኑም በመንግሥት የሚደረገው ዓይን ባወጣ ሁኔታ ህግን የመጨፍለቅ ተግባር እንዲቆም ለምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከጐናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ምንጊዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!
ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

Post Navigation