addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “August 3, 2013”

ከጉራፈርዳ እስከ ጋምቤላ – የሥርዓቱ ሰለባዎች

xz
‹‹የአማራ ብሔር ተወላጆች ዳግም ከጉራፈርዳ እየተፈናቀሉ ናቸው›› የሚለውን የሪፖርተር ጋዜጣ ዜና አንብበው እየተገረሙ አንድ ትዝታ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ሙሉ ስማቸው እንዲገለጽ ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ አቶ ታደሰ ይባላሉ፡፡ አሁን የ56 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡

በተለይ የሰሜኑ ኢትዮጵያ በድርቅ በተደጋጋሚ በተመታበት 1977 ዓ.ም. ቀጣይ ዓመት በአሁኑ የደቡብ ክልል ቤንቺ ማጂ ዞን ልዩ ስሙ ጉራፈርዳ ወደተባለ አካባቢ ተጉዘው ነበር፡፡ ‹‹ጥቅጥቅ ያለ ጫካ›› ነበር ወዳሉት ወደዚህ አካባቢ የተጓዙበትን ሁኔታ በትዝታ መልክ ይተርኩልኝ ጀመሩ፡፡ በደርግ ጊዜ ጋዜጠኛ ነበሩ፡፡ በወቅቱ በ20ዎቹ ዕድሜ መጨረሻ ላይ ነበሩ፡፡ ከሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በወቅቱ የትግራይና የወሎ ክፍለ ሀገሮች በግድ ታፍሰው ለሚመጡ ሰፋሪዎች ቦታ ለማመቻቸት ወደአካባቢው ያመራውን አንድ የመንግሥት ቡድን ሥራ ለመዘገብ ነበር አብረው የተጓዙት፡፡

ከአዲስ አበባ እስከ ሚዛን ቴፒ በመኪና ተጉዘዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በወቅቱ በመኪና መጓዝ አይታሰብም፡፡ በሔሊኮፕተር ለመጓዝ ተገዷል ቡድኑ፡፡ ‹‹ጥቅጥቅ ካለ ጫካ ውጪ ምንም ነገር አልነበረም፡፡ መሬቱ ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ እርሻ የሚባል አያውቅም፡፡ በጠቅላላው ምንም ዓይነት ጥቅም ላይ አልዋለም፡፡ እንደተፈጠረ ነበር፤›› ይላሉ፡፡

አቶ ታደሰ ትረካቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ‹‹ሰው ብሎ ነገርም የለም፡፡ አልፎ አልፎ ብቅ ጥልቅ የሚሉ ጦር የያዙ ራቁታቸውን የሆኑ ሰዎች ይታያሉ፡፡ ሆኖም ልብስ የለበሰ ሰው ሲያዩ የሚሸሹ ናቸው፤›› የሚሉት አቶ ታደሰ፣ በወቅቱ የተመለከቱት በትምህርት የሚያውቁት ‹‹የጋርዮሽ ማኅበረሰብ›› አኗኗርን ነበር ያስታወሳቸው፡፡

ሰፋሪዎች ወደ አካባቢው ከመንቀሳቀሳቸው በፊት የዩኒቨርሲቲ ዘማች ተማሪዎች የራሳቸውን መጠለያዎች ጨምሮ፣ ለሰፋሪዎች ጎጆ ቀለሱ ይላሉ የተመለከቱትን ሲያስታውሱ፡፡ በአካባቢው ከሁለት ሳምንታት በላይ የቆዩት አቶ ታደሰ በብዙ መኪኖች (መንገድ ተጠርጎ) በአካባቢው የተራገፉ የወሎ ሰፋሪዎችን ተመልክተዋል፡፡ ‹‹በቁጥር ብዙ ነበሩ›› ከማለት ውጪ በእርግጥ ቁጥራቸውን በውል መገመት አይችሉም፡፡

የማይተገበር ቃል
አቶ ታደሰ ትዝታቸውን የጫረው ይኼው ዜና ቀደም ሲል በጉራፈርዳ ወረዳና በሌሎች ወረዳዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጉዳይ የመደበኛውም ሆነ የሶሻል ሚዲያ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡

የሚዲያዎችን ቀልብ የሳበው በተለይ ቁጥራቸው በርከት ያለ (ከ22 ሺሕ በላይ) የአማራ ተወላጆች ለሦስት አሥርት ዓመታት ከነበሩበት፣ ካለሙት መሬትና ንብረት ካፈሩበት አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ መፈናቀላቸው ነው፡፡ በቅርቡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ሲፈናቀሉ የበለጠ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፡፡ ይህ የአካባቢ አስተዳደሮች እጅ አለበት ተብሎ የሚታመንበት የማፈናቀል ዕርምጃን በተመለከተ ከፓርላማ አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም፣ ቁርጥ ያለ የፖለቲካ ውሳኔ የሚመስል ምላሽ ሰጥተው ነበር፡፡

መንግሥት በነዋሪዎቹ ላይ በተፈጸመው ድርጊት እጅግ ማዘኑን ገልጸው፣ ተፈናቃዮቹ ወደቀያቸው ተመልሰው የሚሰፍሩበትና በዚህ ድርጊት ላይ የተሳተፉ የአስተዳደር አካላትም ሕግ ፊት ቀርበው እንደሚጠየቁ አጽንኦት ሰጥተው ነበር፡፡ በኪራይ ሰብሳቢነትም ፈርጀዋቸው ነበር፡፡ በቅርቡ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የወቅቱ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ‹‹አንዳንድ ሚዲያዎች ያጋነኑት›› በሚል ጉዳዩን የሚያሳንስ ምላሽ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ ሆኖም ይህንን ወንጀል ፈጸሙ በተባሉ ግለሰቦች ላይ የተወሰደውን ዕርምጃ መንግሥት ዛሬ ነገ ለሕዝብ ያሳውቃል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ነዋሪዎቹን ከቀያቸው የማባረርና የማፈናቀል ድርጊት ደግሞ ተጠናክሮ መቀጠሉ እየተዘገበ ነው፡፡

በዚህ የማፈናቀል ድርጊት ሰማያዊ ፓርቲና መኢአድም የተቃውሞ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይም ክስ ለመመሥረት ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ በቅርቡ ቁጥራቸው በርከት ባለው በጉራፈርዳ ተፈናቃዮች ምክንያት ቀደም ብሎ አጀንዳ መሆን የቻለው ይኼው የመፈናቀል አደጋ፣ ሌሎች ጥያቄዎችንም የሚጭር ነው፡፡ ምናልባትም የጉዳዩ ስፋት በአስተዳደራዊ (ፖለቲካዊ) ውሳኔዎችና በፍርድ ቤት ክትትል ብቻ እንደሚፈታ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡

ጉራፈርዳ – ከግዳጅ ሰፈራ ወደ መፈናቀል
በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያካሄደ ድርጅት ወይም ግለሰብ ማግኘት ባይቻልም፣ አንዳንድ ከደቡብ ክልል መንግሥት የተገኙ መረጃዎች ሁኔታውን ለመረዳት የሚጠቅሙ ናቸው፡፡

በጽሑፉ መግቢያ ላይ የሰፈራ አጀማመሩን የተረኩልን አቶ ታደሰ እንዳሉት፣ የአማራ ብሔር ተወላጆች ወደ አካባቢው የተወሰዱት በ1978 ዓ.ም. በፈቃደኝነት ላይ ባልተመሠረተ የደርግ የሰፈራ ፕሮግራም ነበር፡፡

የቀድሞው መንግሥት እጅግ ከሚተችባቸው ድርጊቶች አንዱ በሆነው የግዳጅ ሰፈራ ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተለይ ደግሞ ከወሎ አካባቢ (የአማራ ተወላጆች) የመጡ ዜጎች በቤንች ማጂ ዞን፣ በጉራፈርዳ ወረዳና በሰሜን ቤንች ወረዳ ሰፍረው ይኖሩ ነበር፡፡

የደርግ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ የተወሰኑት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው ቀድሞ ወደመጡበት ይመለሳሉ፡፡ ሌሎች ግን እዚያው ይቀራሉ፡፡ አካባቢውን ለቀው ወደመጡበት አካባቢ ተመልሰው የነበሩትም ቢሆኑ፣ ከአሥር ዓመት በኋላ ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ የአካባቢውን ለምነትና አጠቃላይ የተፈጥሮ ሁኔታ ያውቁ ስለነበር ተመልሰው መስፈሩን ተያያዙት፡፡ ይህ እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ የቀጠለው የመንግሥት ‹‹ዕውቅና›› ያልነበረው መልሶ የመስፈር ሁኔታ፣ በተለይ የጉራፈርዳ ወረዳን የሚመለከት ነው፡፡ ከቀድሞ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ቃለ ምልልስ መረዳት እንደሚቻለው፣ በወቅቱ ወደ አካባቢው የመጡት ሰዎች በአካባቢው የመንግሥት አካላት በሕጋዊ መንገድ ስምሪት አግኝተው ወደ ልማት የገቡ አልነበረም፡፡

ሰፈራው በተፈጥሮ ሀብት አጠባበቅ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩና በአካባቢው ‹‹ነባር›› ነዋሪዎች ላይ ጫና ፈጥሯል የሚለው የክልሉ መንግሥት አቋም ነው፡፡ የክልሉ መንግሥት ከ2000 እስከ 2001 ዓ.ም. ባደረገው ጥናት በደን ምንጠራና ሰው ያልሰፈረበትን ክፍት ቦታ በመቆጣጠር ሦስት ወረዳዎች ላይ ነዋሪዎቹ ሰፍረዋል፡፡ እነሱም ጉራፈርዳ፣ ሜኤኒት ጎልዲያና ሜኤኔት ሻሸ ይባላሉ፡፡

በጥናቱም መሠረት በጉራፈርዳ ወረዳ ብቻ 22,046 ሰዎች የሰፈሩ ሲሆን፣ በተቀሩት ሁለት ወረዳዎች ወደ ሦስት ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች ሰፍረዋል፡፡ በጉራፈርዳ ከሰፈሩ ሰዎች መካከል ቁጥራቸው ወደ አንድ ሺሕ የሚጠጋውን ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር በመነጋገር በባህር ዳር ማስፈር መቻሉ ይነገራል፡፡ የተቀሩትም ለእርሻ ሁለት ሔክታር፣ ለመኖርያ ቤት መሥሪያ አንድ ሺሕ ካሬ ሜትር እንዲሰጣቸው መደረጉን የክልሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

መሠረታዊ መብቶች
በቀድሞ ሥርዓቶች የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ለዘመናት ‹‹ብሔራዊ ጭቆና›› ደርሶባቸዋል የሚለው ብዙም የሚያከራክር አይደለም፡፡ በመሆኑም በ1986 ዓ.ም. በፀደቀው የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አማርኛ የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ሆኖ ተወስኖአል፡፡ ክልሎች ቋንቋን ጨምሮ የሚተዳደሩበት የራሳቸው ሕገ መንግሥትም እንዲያፀድቁ ጭምር ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡

በአገሪቱ የሕጎች ሁሉ ሕግ (እናት) የሆነው ይኼንን የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥትና ሌሎች የክልል ሕገ መንግሥቶችንም ለማስፈጸም በየጊዜው የሚደነገጉ ሌሎች ሕጎች፣ አዋጆችና ድንጋጌዎች የሕገ መንግሥቱን ዋነኛ መርህ ሊጥሱ አይችሉም፡፡ ከሕገ መንግሥቱ ንፍቀ ክበብ ውጪም መተርጎምም የለባቸውም፡፡

የሕገ መንግሥቱ የመሠረት ድንጋይ የሆኑት የብሔር ብሔረሰቦች መብትና የሰብዓዊ መብቶች ቃል ኪዳን ናቸው፡፡ በአንቀጽ 39 ላይ የሰፈረው የብሔር ብሔረሰቦች መብት እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ማንነቱን የማክበር፣ ቋንቋውን የመጠቀም (በአፍ መፍቻ ቋንቋውን የመማር)፣ ታሪኩንና ባህሉን የማሳደግና የመግለጽ፣ እንዲሁም የመጠበቅ መብት ሰጥቶታል፡፡

ይህ በቡድን መብት የሚጠቃለል ሲሆን፣ አንድ ዜጋ ሕገ መንግሥቱ ከሰጠው ዋስትና አንዱ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተዘዋውሮ የመሥራት፣ የመኖርና ንብረት የማፍራት ይገኝበታል (አንቀጽ 32)፡፡

ይህንን ንብረት የማፍራት፣ የመጠቀምና የመገልገል መብቶች በአንቀጽ 40 በስፋት የተዘረዘሩ ሲሆን፣ በሌሎች አንቀጾች የአገሪቱን የተፈጥሮ ሀብትና መሬት የኢትዮጵያ ዜጎችና የመንግሥት ንብረት መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በአንቀጽ 44 እንደተደነገገውም፣ መንግሥት በሚያካሂደው ልማት ምክንያት በቂ ካሳ አግኝተው ከቦታ ቦታ የሚፈናቀሉ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም ዜጋ የሕይወቱና የንብረቱ ደኅንነት ተጠብቆ የመኖር መብቱ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገ ነው፡፡

ሕገ መንግሥታዊ ጥሰቶች
የሚዲያ ትኩረት ያገኘው የአማራ ተወላጆች በደቡብ ክልል የጉራፈርዳና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሰፋሪዎች የመፈናቀል ጉዳይ ቢሆንም፣ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ችግሮች እየተስተዋሉ ነው፡፡ በኦሮሚያ ክልል ኦሮሚኛ ቋንቋ የማይችሉ ሰዎች የመሥራት መብታቸው እየተገደበ እንደሆነ በስፋት ይነገራል፡፡ በመሆኑም በአካባቢው የሚገኙት ቁጥራቸው ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ የአማራ ተወላጆችና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የትግራይ ተወላጆች ቋንቋውን ባለመናገራቸው ምክንያት ከፍተኛ ችግር እየገጠማቸው መሆኑንና መኖሪያቸውን ጥለው የሚወጡ መኖራቸው ይነገራል፡፡

በተለያዩ አጋጣሚዎች አሁን የአማራ ክልል ወደሆነው አካባቢ የተንቀሳቀሱ የኦሮሞ ተወላጆች የራሳቸውን ዞን መሥርተው ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እየተጠቀሙ ቢሆንም፣ በኦሮሚያ አካባቢ የሚገኙ በርካታ የአማራ ተወላጆች ይህንን መብት አልተጎናፀፉም በማለት ወቀሳዎች ይቀርባሉ፡፡

ከዚህ ውጪ በቀደሙት ሥርዓቶች በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ጭምር በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚገኙ ደገኞች (ትግራይና አማራ) በአካባቢው አስተዳደራዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተወስኖ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ በተለይ የመመረጥና የመምረጥ ሕገ መንግሥታዊና ፖለቲካዊ መብት እስከመከልከል የሚደርሰ ድንጋጌ የነበረ ሲሆን፣ ይህ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጣልቃ ገብነት በተወሰነ መልኩ ሊስተካከል ችሏል፡፡

ሕገ መንግሥቱ የአናሳዎች መብት (Minority Right) እስከ ዞን ደረጃ የራሳቸውን አስተዳደር የመመሥረት መብት ያጎናፅፋቸዋል፡፡ ሆኖም በአጠቃላይ በክልላቸው ባላቸው ቁጥር ብዙኃን (Majority) የሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ግን በተለያዩ ‹‹የታሪክ›› አጋጣሚዎች በሌሎች አካባቢዎች አናሳ ሆነው የሚገኙበት ሁኔታ አለ፡፡ የኦሮሞ ተወላጆች በአማራ ክልል አናሳዎች ሲሆኑ፣ የአማራና የትግራይ ተወላጆች ደግሞ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች አናሳ ሆነው ይገኛሉ፡፡

ቀደም ሲል እ.ኤ.አ. በ2007 ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ የቀረበው አንድ የባለሙያዎች ጥናት ይህንን የሚመለከት ነው፡፡ በመሆኑም አገራዊ ኮንፈረንስ ተደርጎ ውይይት እንዲደረግበትና በኅብረተሰቡ መካከል ግልጽነት እንዲፈጠር ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡

‹‹Report of the Independent Expert on Minority Issues፡ Mission to Ethiopia›› በሚል ሚስስ ጋይ ማክ ደጋል አደንዱም በተባሉ ባለሙያ የቀረበው አንድ ሰፊ ጥናታዊ ሪፖርት፣ ሕገ መንግሥቱ የብሔር ብሔረሰቦች መብትን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ስለሚገኙ ንዑሳን የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጠው ምንም የሕግ ከለላ የለም ይላል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ጨርሶ የፖለቲካ ተሳትፎ የተነፈጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የመኖራቸውን ያህል፣ አንዳንድ አናሳ ብሔረሰቦች ደግሞ ቋንቋቸው በመጥፋት ላይ መሆኑን ሪፖርቱ ያሳስባል፡፡ በመሆኑም ሕገ መንግሥቱ በአጠቃላይ የከፋ ችግር ባይኖረውም በብሔር ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ያላግባብ እየተተረጎመ የራስን መብት ከመጠበቅ አልፎ የሌሎችን መብት ለማፈን ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ በስፋት ትችት ይቀርባል፡፡ ቀደም ሲል በተጠቀሱት ሕገ መንግሥታዊ አንቀጾች ማናቸውም ዜጋ በአገሪቱ ተዘዋውሮ በነፃነት የመሥራትና የመኖር መብት ያለው ቢሆንም፣ ይህ መብት በተግባር ሲጣስ እየተስተዋለ መሆኑም እንዲሁ፡፡

ምናልባትም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሕገ መንግሥቱ ከዚሁ በፊት ብሔራዊ ጭቆና ለደረሰባቸው ብሔረሰቦች ሙሉ መብት ያጎናፀፈ ቢሆንም፣ እነዚህን ወገኖች የሚመለከት ግን ግልጽ የሆነ የሕግ ከለላ የለም፡፡

አቶ ታደሰ እንደተመለከቱት፣ ‹‹ደገኞች›› በግዳጅም ሆነ በውዴታ ኑሮአቸውን ለማሻሻል በተንቀሳቀሱበት አካባቢ ከመጡበት ማኅበረሰብ ባመጡት በእርሻ፣ በቤት አሠራር፣ የተለያዩ ምርቶችን በማምረትና በተለየ አኗኗር ዘይቤ ጠቃሚ ልምድ ያበረከቱ ናቸው፡፡ ይህንን በታሪክ አጋጣሚ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ መዘንጋት እንደሌለበትም አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በቀደሙት መንግሥታት አስገዳጅነት የተፈናቀሉ ወገኖች፣ የአካባቢዎቹ አስተዳዳሪዎች ሕገ መንግሥቱን አዛብተው በመተርጎማቸው ምክንያት ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን፣ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ካላደረገበት ችግሩ መቆሚያ እንደሌለው የሕግ ምሁራንም ያስረዳሉ፡፡

ከጉራፈርዳ እስከ ጋምቤላ – የሁለት ሥርዓቶች ሰለባዎች

ሪፖርተር መነሻ ገፅ

Silvio Berlusconi loyalists warn of ‘civil war’ if tax-fraud sentence not lifted, call for mass protest in Rome Sunday

የ “ድምፃችን ይሰማ” ሰልፍ በአዘጋጆቹ ተሠረዘ …VOA

21
ፌደራል ፖሊስ ትናንት ሐሙስ ሐምሌ 25/2005 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “… አክራሪዎች በመስጊዶች ውስጥ የሚያካሂዱትን የጥፋት ድርጊት ለማስቆም …” በሚል “ተገቢውን እርምጃ እና አስፈላጊውን እርምጃ” የሚወስድ መሆኑን በማስታወቅ አስጠንቅቋል፡፡

“የሮመዳን ፆም ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ሰላምን ለማወክ እና በየመስጊዶቹ ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ አክራሪዎች ሕገወጥ ቅስቀሣዎችን እያደረጉ ይገኛሉ” ብሎ በ “አክራሪዎቹ” ላይ “እወስዳቸዋለሁ” ላለው “እርምጃ” ኅብረተሰቡ እንዲተባበረው ጠይቋል፡፡

የሠልፉ አዘጋጆች በተለያዩ መንገዶችና በብዝኃሚድያ ባሠራጩት ጥሪ በሮመዳን የመጨረሻ ጁምዓ ዕለት በአዲስ አበባው ፍልውኃ ተውፊቅ መስጂድ እና ከአርባ በላይ ከተሞች ውስጥ ሰዉ የተቃውሞ ድምፁን በሰላማዊ ሁኔታ እንዲያሰማ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኢሳት፡ አማራጭ ወይስ ምላጭ? ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

1111111111111
ምዕራባዊያን መንግስታት በአንድም በሌላም መንገድ ምድራቸው ለተጠለለ ሕጋዊ የውጭ ዜጋ ራሱን ችሎ ይቆም ዘንድ ከሚሰጡት ዕድል መካካል አንዱ ክፍት የስራ በር ሲሆን ይኸውም ስራ ሳያማርጥ፥ ሳይንቅና ማንኛውም ዓይነት ስራ የመስራት ፍላጎት እንዲሁም የልብ ተነሳሽነት ላለው የምድር ዜጋ ሁሉ እንደ ደረጃው ማለትም ትምህርት ያለው በተማረው የትምህርት ደረጃ መሰረት፥ ሞያ ያለው በሞያው፥ ሌላው ደግሞ እንዲሁ አቅሙ በፈቀደው የስራ መስክ ተሰማርቶ ራሱንና ቤተሰቡን ያስተዳድር ዘንድ በሮቻቸው ክፍት ነው። የሚያሳዝነው ግን አንዳንድ ወገኖች የሞት ያክል ዋጋ ከፍለው: ተላልጠውና ተሸራርፈር አሜሪካና አውሮፓ ደርሰው ሲያበቁ አገሮቹ የሚሰጡት ዕድል ለመጠቀም ፍላጎትም ሆነ ተነሳሽነት ሳይኖራቸው ሲቀሩ እጅግ ያሳዝናል። ሰው ስራ ሰርቶ ሙሉ ሰው በሚሆንባቸውና ራሱን በሚለውጥባቸው አገሮች ተቀመጦ ሲያበቃ የዕድሉ ተጠቃሚ ሳይሆን መቅረቱ ብቻ ሳይሆን ስንፍናው ለሌላ ታታሪ ሰራተኛ ዜጋ ጭምር የሚተርፍ በሽታ/ጦስ ሆኖ ከማየት በላይ የልብ ስብራት የለም።
ያለ ምክንያት ስለ ስራ ክቡርነት አንስቼ አልሞገትኩም። ስራ ክቡር ነው። ምን ይሁን ምን ሰውን ሰው የሚያደርገው፥ የሰው እጅ ከመጠበቅም የሚያተርፈው ስራ ነው። በአንጻሩ ግን ከለንደን እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ጸብ፥ ጥፋት፥ እልቂትንና መለያየትን እንጂ አንዳችም የሰውን ህይወት የሚገነባ፥ የሚለውጥ፥ መልክ ያለው፥ የሚያንጽና የሚረባ መልእክት የማይወጣቸው በአንጻሩ አፍራሽ አጥፊና አውዳሚ የነገር መስመር ዘርግተው ወሬ ሲፈትሉና ሲያቀጥኑ ጸሐይ የምትጠልቅባቸው ግለሰቦች የዕለት ዕለት ድርጊቶቻቸው ስመለከት በሰልቃጭ ማላሶቻቸውና መንታ አንደበቶቻቸው የሚሰለበውን ንጹሕ ዜጋ እየታየኝ እያሳሰበኝም በርካታ ጥያቄዎች ወደ አእምሮዬ ስለሚመላለስ ነው።

አንዳንድ ጊዜም እንዲህ እላለሁ: በእውነቱ ነገር ሰዎቹ ዋጋ የሚያወጣ አእምሮ ካላቸው እንዲህ ባለ በታሪክ የሚያስጠይቅና ትውልድ የሚያፍርበት ስራ ተሰማርተው ሀገራቸውን ከሚበድሉና ሕዝባቸውንም ለጊዚያዊ ጥቅም ሲሉ ብቻ የፈጠራ ዜናዎችና ሐተታዎችን በማሰራጨት ሕዝብ ወዳልሆነ አቅጣጫ እንዲያመራ በማድረግ እርስበርስ እንዲተላለቅና እንዲጨራረስ ከማድረግ ይልቅ ምን አለበት አቅማቸው በፈቀደው የስራ መስክ ተሰማርተው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ቢረዱ እላለሁ። ከተሳሳትኩ ከስህተቴ ለመታረም ዝግጁ ነኝ! በተረፈ ግን ጋዜጠኝነት ሞያ መሆኑ ቀርቶ ስራ ሰርተው ኑሮአቸውን መግፋት የማይፈልጉ የስራ ፈቶች መደበቂያ ዋሻ ከሆነና መስራት የማወድ ተለላ ሁሉ በጋዜጠኝነት ስም ያለ እውቀት ምክርን የሚያጨልም ከሆነ ሀገርንና ሕዝብ እስከ መቼ በነፈዞች ይታወካሉ? በማለት የመጠየቅ መብቴ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያ ለመበታተን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አብረው ሲያበቁ ኢትዮጵያውያን፤
የግል አጀንዳ ያላቸው በምኞት የተቃጠሉ ጥመኞች ሳሉ የሕዝብ (ሕዝባውያ)፤
ምድሪቱ የደም መሬት ሕዝቦችዋንም በደም ለመቃባት አፋቸው የከፈቱ የበልዓም ምክር አስፈጻሚዎችና ተራጋሚዎች ሆነው ሳሉም ነጻ: ገለልተኛና ፍትሐዊ የሚሉ የሸቀጥ ታፔላዎች ግንባራቸው ላይ ለጥፈው የተሰለፉ ስተው የሚያስቱ የምላስ አርበኞች በኢሳት ቅጥረኞች ላይ ያለኝ ጥያቄ እንደቀጠለ ነው።

ይህ ራሱን “ነጻ፥ ገለልተኛና ፍትሐዊ ኢትዮጵያዊ ሚድያ ነኝ” በማለት የሚጠራ አፈ ለምጽ ለበርካታ ጊዜያት ሀገር ወደ አላስፈላጊ ትርምስና ብጥብጥ ለመክተት ያደረገውና የሚያደርገውን ዘመቻ እንድያቆም ከድርጊቱም እንዲቆጠብ በተደጋጋሚ ጊዜያት በግልም በአደባባይም የቀረበለትን ጥያቄ አሻፈረኝ በማለት በሕዝቦች መካከል ጥላቻንና አመጻን መዝራት እንደገፋበት ይገኛል።

ኢሳት ምንም እንኳ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይንና ጆሮ ነኝ” ከማለት ባይመለስም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ተቋሙ የኢትዮጵያውያን ዓይንና ጆሮ ለማጥፋት ብሎም ለማደንቆር ያሰፈሰፈ የኢትዮጵያ መልካምነት ማየት የማይሆንላቸው ሃይሎች ክንፍ ለመሆኑ ለብዙዎቻችን ግልጽ ነው ብዬ አምናለሁ።

ሌላ የዚህ ተቋም ጉራማይሌ ገጽታው እንደሚከተለው ይመስላል። የራሱ ማንነትና የተገለጠ ጸረ ዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ አሰራር ለማድበስበስ ኢቲቪ: ፋና ሪድዮ: አዲስ አድማስና ሪፖርተር እያነሳ ሲጥል ኢሳት ማለት ግን በአንጻሩ ቀዳሚና ተከታይ የሌለው ብቸኛ የነጻ ፕሬስ ተሟጋችና ጠበቃ አድርጎ ለማቅረብ የሚያደረው ጥረት ነው። ኢሳት ስለ ነጻ ፕሬስም ሆነ የዜጎች ሃሳብህን በነጻ የመግለጽ መብት በተመለከተ አፉን የመክፈት፥ የመናገር የሞራል ብቃት የለውም። ይህ ብቻም አይደለም ኢሳት የሚወቅሰው አካል የለም! ሊኖርም አይችልም! አይኖርምም። የዜጎችን ሃሳብ በነጻነት የመግለጽ መብት በመገደብና በማሳጣት እንዲሁም የነጻ ፕሬስ አፈና በተመለከተ ከኢሳት የከፋ አፋኝ ጸረ- ነጻነት አለ ብለው ራስዎ አያታልሉ። አለ ብለው የሚያምኑ ከሆነም መቀመጫው ሲዖል ያደረገ ስለ ናዚ (Nazi) ሊቀ መንበር እየተናገሩ እንደሆኑ እርግጠኛ ይሁኑ።

ለመሆኑ ነጻ: ገለልተኛና ሚዛናዊ ሚድያ ማለት ዜጎች በዜግነታቸው (ያለምንም ቅድመ ሁኔታ) ሃሳባቸውን ያለገደብ በነጻነት የሚያነሸራሽሩበት የሕዝብ መድረክ መሆኑ ቀርቶ ግለሰቦች በፈላጭ ቆራጭነት ሌላውን የሚሳለቁበት ማለት ነው ያለ ማን ነው? ማን ነው ኢሳት ነጻ: ገለልተኛና ሚዛናዊ ሚድያ ብሎ ለመናገር የሚደፍር? አእምሮውን ያጣ ግለሰብ ካልሆነ በስተቀር። እንግዲያውስ ኢሳት ማለት ሌላ ማንም ሳይሆን ሀገርንና ሕዝብን ለመበተን አፉ የከፈተ የዘንዶ ምላስ ነው!

ኢሳት ቅንጣት ታክል ኢትዮጵያዊ ራዕይና ዓላማ የሌለው ይልቁንስ የኢትዮጵያ ጠላቶች አፍ እንደሆነም ጭምር በተጨባጭ ከዚህ ቀደም በበርካታ ጽሑፎቼ በስፋትና በጥልቀት ግንዛቤ ማስጨበጤ የሚታወስ ነው። በእርግጥ የኤርትራ መንግስት ጦር አዝምቼ ኢትዮጵያን እገጥማለሁ አፈራርሳለሁ ብሎ በህልሙም ጭምር እንደማያስበው የሚጠራጠር ኢትዮጵያዊ አለ ብዬ አላምንም። ኩሽታ ያሰማ ዕለት እንደሆነ ያለቀባሪ በቆፈረው ጉድጓድ ራሱን እንደሚጨምር የአስመራ ባለስልጣናት ለአፍታ አይስቱትም። ታድያ “ኢትዮጵያዊ አማራጭ ሚድያ” በማለት ራሱን የሚጠራ ኢሳት በመባል የሚታወቀው የሳይበር ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ የአቶ ኢሳይያስ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሕልም ተለዋጭ ምላጭ ለመሆኑ የሚጠራጠር ማን ነው?

ምላጭ የሚቆርጥ፥ የሚያደማ፥ የሚለያይ፥ የሚከፋፍል፥ የሚቀድና የሚበሳሳ ስለታም መሳሪያ ሲሆን ኢሳት ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብና ምድር ክብር፦

ለመግፈፍ፥
ለመላጨት
ለማራቆት፥
ለማርከስ፥
ለማድማት፥
አንገት ለማስደፋት፥
ለማሸማቀቅ፥
ለማዋረድ፥
ለማለያየትና ለመከፋፈል በእደ ግንቦት 7 ወኢሳይያስ/ህግደፍ የተዘረጋ ምላጭ ነው። ጥያቄ ያለው ማቴ 7፥ 17 በማንበብ መልሱን ያገኘዋል።
“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።” (ማቴ 7፥ 17)

ወገን፡ መጽሐፍ ሲናገር እውነት ነው! መጽሐፍ ሲናገር ግልጽ ነው! መጽሐፍ ሲናገር ትክክል ነው! ኢሳቶችም ፍሬአቸው፥ ምኞታቸውና ግብራቸው ነው ሞራለ ቢሶች ግብረ አረማውያን ወአስመራውያን እንጅ መልካቸው: ቋንቋቸውና ዜግነታቸውማ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰ የኤርትራ መንግስት እንደሆነ ቃኘው ቁጭ ብሎ በድምጺ ሐፋሽ ኤርትራ የሬድዮ ጣቢያና በERTV በኩል በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የፈለገውን ዜና እየሰራ ሲለፈልፍ ውሎ ቢከርም ማንም የሚሰማው የለም። ማን ይሰማዋል? ማንስ ጆሮ ይሰጠዋል? ማንም። ለምን? የኤርትራ መንግስት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ጥይት አንጂ ዳቦ እንደማይመኝልን ዜጋ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነውዋ። ምንስ እንዲል ይጠበቃል? የኤርትራ መገናኛ ብዙሐን ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን መልካም ነገር ይዘግባሉ ብሎ የሚጠብቅስ ማን ያበደ ነው? የኤርትራ መንግስት ግን በዚህ ሁሉ ተስፋ አልቆረጠም። ይህ መንገድ አልሆነልኝም አልተሳካልኝም ብሎም እጁና እግሩ አጣጥፎ አልተቀመጠም። ይልቁንስ በልኩ ያሰፋው አፍ በኢሳት በኩል ሀገራችን ሲወጋ: ሲያደማ: ልዩነትንና ጸብን/ሁከት ሲዘራ እየተመለከትነው ነው። እስከ መቼ? ለሚለው ጥያቄ “ለሀገሪቱ ባለ ስልጣናት” (ለኢትዮጵያ ባለ ስልጣናት) የሚተው ጥያቄ ይሆናል።

እኔምለው ሰው እንዴት ይህን ያህል ይጨልምበታል? እንዴት ይህን ያህል አእምሮ ቢስ ይሆናል? በነጋ በጠባ ቁርጥ እንዴት ሁከትና ረብሻን ለመቀስቀስ እንቅልፍ ያጣል? አንዳንዱማ በህወሐት የውሃ ጥምቀት የተጠመቀ ነው የሚመስለው። ያለ ህወሐት ሌላ አፍ መውጫ ቋንቋ የለውምና። አረ መቼ ነው ኢሳት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያን የሚረባ: የሚገነባ: አንድ የሚያደርግና የሚያንጽ ቃል ከአፉ የሚወጣበት? መቼ ነው ኢሳት ስለ ኢትዮጵያ መልካም ነገር የሚናገረው? አንዲት ቀን ተሳስቶም ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ የሚያሳርፍ፥ ሰላማዊና መልካም ዜና ላለመዘገብ ሰዎቹ በልጅ ልጆቻቸው ተማምለዋል ልበል? እንዴት በ 1100 ቀናት ውስጥ አንዲት ቀን አንዲት መልካም ነገር መናገር ይሳናቸዋል? ለነገሩ መጽሐፍ “ከእሾህ ወይን ከኩርንች በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።” ብሎ የለም። ለነገሩ ኢሳቶች ተሳስተው ስለ ኢትዮጵያ መልካም ነገር የተናገሩ ዕለት ነው የሚደንቀኝ።

ይቀጥላል …

የዛሬ ሳምንት:

ሰውም ሰይጣንም የሚያውቀው የአስመራ መንግስት በሀገራች በኢትዮጵያ ላይ ያለው አጀንዳ፤
ትናንት የሰው ነፍስ አንደ ድንች በዘይት ሲቀቅሉ የነበሩ የዛሬ “የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች”፣ “ጋዜጠኞች”፣ “የነጻ ፕሬስ ጠበቆችና የዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመገለጽ መብት ጠባቂዎች” በቀድሞ የደርግ ወታደራዊ መንግስት የስራ ድርሻ እንዲሁም

ሦስት ዋና ዋና የኢሳት የስራ ድርሻዎችና ግዴታዎች አንስተን በጨለማ ላይ ብርሃን እናበራለን ይጠብቁኝ!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Biting back: Taking the sting out of spider venom

By Ben Tavener
São Paulo, Brazil
sa
The brown recluse spider has a nasty bite

Brown recluse spiders bite more than 7,000 people in Brazil every year causing serious skin lesions and even death. The anti-venom used as treatment comes at the expense of many animal lives. But could a breakthrough in synthetic spider venom lead to a more humane solution?

“The first time I was bitten, I nearly died,” says Adelaide Fabienski Maia, a school assistant from Curitiba.

“I put my shorts on in the morning and felt a bite but didn’t realise what it was. It wasn’t until the evening that my face started burning up. I looked at the bite area and it was red.”

Adelaide was soon rushed to hospital with the classic target-shaped lesion caused by the venom eating away at her skin.

It was only thanks to a dose of anti-venom that she’s still around to tell the tale.

But the anti-venom currently available comes with its own risks – mostly to the animals involved in the production process.

Venom is milked from thousands of brown spiders before being injected into horses. This triggers an immune response that creates life-saving anti-venom for humans – while drastically reducing the horses’ own lifespan.

Now scientists in Brazil have come up with a synthetic venom alternative that could save many of those lives.

Not so incy-wincy
The Loxosceles family of venomous brown and recluse spiders is found in North and South America, Africa, Australia and some parts of Europe.

At 6-20mm long, they are by no means the world’s biggest spiders. Even their bite is almost painless. But their venom can cause large sores and lesions through dermo-necrosis – literally “death of the skin”.

It is the only family of spiders in the world to cause the skin to die in this way. Scientists have linked it to a rare enzyme in the venom called sphingomyelinase D, which damages and kills skin tissue.
22
Brown spider venom kills the skin and leaves horrific wounds
In a small percentage of cases where anti-venom is not administered quickly enough, people can die through organ failure.

But many more deaths – of spiders and horses – are caused through the anti-venom production itself.

“We milk the spiders once a month for three to four months,” says Dr Samuel Guizze, a biologist at the Butantan Institute, Sao Paulo’s pioneering centre for anti-venom production.

It involves one technician gingerly picking up a spider and giving it an electric shock while a second scientist rushes to draw the venom into a syringe.

As only a tiny squirt of venom is surrendered each time, it means that tens of thousands of individuals must be bred for milking.

“The amount of venom obtained per spider is very small,” says Dr Guizze. “We then inject the venom into horses and after 40 days the horses are bled and the antibodies [anti-venom] separated from the blood.”

Unsurprisingly, being injected with brown spider venom has an effect on the horses’ health over time. Their lifespan is reduced from around 20 years to just three or four.

Sadly, the spiders fare even worse – dying after just three or four venom extractions.

Alternatives to animals
Six hundred miles away at the Federal University of Minas Gerais, a breakthrough in venom technology promises to greatly reduce the anti-venom industry’s reliance on animals.
For see http://www.bbc.co.uk/news/health-23408949

“ሰማያዊ ፓርቲ፣ግንቦት ሰባት እና አክራሪዎች ጋብቻ ፈፅመዋል”

qq
ሙሉጌታ ውለታው፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ
ሰማያዊ ፓርቲ፤ ግንቦት ሰባት እና አክራሪዎች ህገመንግስቱ ከሚፈቅደው ውጪ ሀይማኖትና ፖለቲካን በማደባለቅ ለመስራት ጋብቻ ፈፅመዋል ሲሉ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታው ተቹ፡፡
ከነሐሴ 21-23 ቀን 2005 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የሀይማኖት ኮንፈረንስ በማስመልከት በአዳማ ከተማ ለሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እየተሰጠ ባለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ የተገኙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ “መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገባ ማለት በእሳት ተጫወተ ማለት ነው፤ አሁንም ሆነ ወደፊት ጣልቃ አይገባም” ብለዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሙስሊሙ ህብረተሰብ የሀይማኖት ነፃነት አልተከበረም በሚል ተቃውሞ ማሰማታቸው እንዴት ይታያል? በሚል የተጠየቁት ሚኒስትር ዴኤታው፤ “በክርስቲያንም ሆነ በሙስሊሙ ያልተመለሰ የሀይማኖት ጥያቄ የለም፤ ያልተመለሰም ካለ የሰማያዊ ፓርቲ እና የግንቦት ሰባት ጥያቄ ነው” ያሉት ሚንስትር ዴኤታው፤ የነዚህ አካላት ጥያቄም ሀይማኖትን ሽፋን ያደረገ የፖለቲካ ጥያቄ እንጂ የሀይማኖት አለመሆኑ ግልፅ ነው ብለዋል፡፡
“በዚህ ጉዳይ ላይ አጥፊና አፍራሽ ጉዳዮችን አብሮ ለመፈፀም ሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት ሰባት እና አክራሪዎች ጋብቻ ፈጽመዋል፤ ጋብቻቸውም ግልጽ ያልሆነ እና “ኦድ ኬሚስትሪ” (ያልተለመደ ቁርኝት) ነው” ብለዋል፡፡ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ ነው በሚል የሚነሳውን ወቀሳ በተመለከተ ሲናገሩም፤ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገባ ማለት በእሳት ተጫወተ ማለት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ሙሉጌታ፤ አክራሪዎች በሚያነሱት ረብሻ ሰላማዊ ህዝብ እንዳይበጠበጥ መንግስት ሠላም የማስከበሩን ሃላፊነትን ሲወጣ ጣልቃ ገባ ማለት አግባብ አለመሆኑንና አንዲትም ኢንች ጣልቃ እንዳልገባና ወደፊትም እንደማይገባ ገልፀዋል፡፡
አክራሪዎች ጥቂት ናቸው ከተባለ ለምን ጉዳዩ እንዲህ አንገብጋቢ ሆነ ተብሎ ለተነሳው ጥያቄም “ጉዳዩ አለምአቀፍ ስጋት ነው፤ ችላ ከተባለ የዕንቁላሉ ስርቆት ወደ በሬ ስርቆትነት ስለሚሸጋገር በእንጭጩ መቀጨት አለበት”ያሉት ሚንስትር ዴኤታው፤ መንግስት እየሰራ ያለው በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ አይነት እርምጃ እንደሆነም አስምረውበታል፡፡
የሼሁን ግድያ በተመለከተ፤ ተጠርጣሪዎች ፍ/ቤት ቀርበው ሳይፈረድባቸው በመንግስት መገናኛ ብዙሃን አሸባሪ መባላቸውን በተመለከተ ሲመልሱ፤ “መገናኛ ብዙሃኑ ተጠርጣሪ እንጂ አሸባሪ አላሉም” ሲሉ በማለት አስተባብለዋል፡፡
በእስር ላይ የሚገኙት “የሙስሊሞች ችግር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ” አባላት ቀደም ሲል ከመንግስት ጋር ሲደራደሩ የነበሩ ከመሆኑ አንፃር፣ እነሱን “አሸባሪ” ብሎ ማሰሩ ጉዳዩን አክርሮታል ይባላል በሚል ስለ ጉዳይ የተጠየቁት ሚኒስትር ዴኤታው፤ “የሀይማኖት ጥያቄ አንስቶ የታሰረ የለም፤ ያጠፉትም ቢሆኑ ሁሉም አልታሰሩም” ካሉ በኋላ በተመረጠ አካኋን ከሀይማኖት ውጪ ችግር ሲፈጥሩ በፖሊስ የተያዙ ጥቂት ሰዎች ብቻ መታሰራቸውን እና ስለጥፋተኝነታቸውም ፖሊስ ተጨባጭ ማስረጃ እንዳለው አብራርተዋል፡፡
“የሀይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴትን በማጎልበት እና ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን ህዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን” በሚል መሪ ቃል ከነሀሴ 21-23 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ለሚደረገው አገር አቀፍ የሀይማኖት ኮንፈረንስ፣ ጋዜጠኞች ሊኖራቸው በሚችለው ሚና ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና ትላንት አመሻሽ ላይ ተጠናቋል፡፡
Written by ናፍቆት ዮሴፍ (ከአዳማ)

Post Navigation