addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “August 29, 2013”

ፓሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ነገ ሊያነጋግር ነው

77
ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡

ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡

ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ፀሐፊን፣ ሊቀመንበሩንና የሰልፍ አስተባባሪዎችን ለማነጋገር ጥሪ እንዳቀረበላቸው ታውቋል፡፡

በፀጥታ ዙሪያ ልናነጋግራችሁ እንፈልጋለን የሚለው የፖሊስ መጥሪያ ፓርቲው የእሁዱን ስብሰባ እንዲሰርዝ ለማግባባት ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፓርቲያቸው የእሁዱን ስብሰባ ለማካሄድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ተናግረው፤ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ ከያዙት አቋም እንደማያስቆማቸው ለኢሳት ተናግረዋል፡፡
በታሪክ፣ በሞራልም ሆነ በህግ ተጠያቂ የሚያስደርገን ነገር ስለሌለ ሰላማዊ ሰልፉ የማይቀር መሆኑን የፓርቲው አመራር ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማህበራት ፍቃድ ጽ/ቤት የፓርቲውን ሰልፍ ህገወጥ ነው ማለቱን አስመልክቶ የተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ‹ሕጋዊ ወይም ህገ ወጥ› የሚባል ሰልፍ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

የፓርቲው የሰልፍ አስተባባሪ ዝግጅት ክፍል ለእሁድ ሰልፍ የሚያደርገው ዝግጅት ከገዥው ፓርቲ የተለያየ ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

መብራት በተደጋጋሚ የመጥፋት ተግባርና በመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ የተደረገ እንቅስቃሴ በፀጥታ ሀይሎች ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

የኢህአዴግ አባላት ቤት ለቤት በመሄድ ህዝቡ ለእሁድ የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ እንዲወጣ ቅስቀሳ ማድረግ ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

መንግስት እያስተባበረ የሚገኘው የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ ህዝቡ አክራሪነትን እና ጽንፈኝነትን ለማውገዝ በሚል የተጠራ ቢሆንም እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ ያለመ እንደሆነ የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

ሁለት ቀን ብቻ የቀረው የእሁዱ የመንግስትና የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ ከብዙ ዓመታት በኋላ ያጋጠመ ክስተት ተደርጎ ታይቷል፡፡

ወታደራዊ ትጥቅ ማ ምረቻ ፋብሪካ በቃጠሎ ጉዳት ደረሰበት

qa
ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በተነሳ የእሳት አደጋ ቃጠሎ በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ፡፡

ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው የተለያዩ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን የደረሰው አደጋ መንስኤ ሊታወቅ አልቻለም፡፡

በፋብሪካው ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት ከአዳማ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ባለመኖሩ ደብረ ዘይት ከሚገኘው አየር ሀይል እሳት ማጥፊያ እስከሚደርስ ድረስ የተነሳውን እሳት ማጥፋት አለመቻሉን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየው የእሳት አደጋ ግምታቸው ከፍተኛ የሆነ ማሽኖች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ሲሆን ከአራት ቀናት በፊት መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ማሽኖች በፋብሪካው ገብተው እንደነበረ ታውቋል፡፡

የኢህአዴግን አክራሪነት ተቃውመን እንጂ ደግፈን ሰልፍ አንወጣም!!!

4444
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱበት ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎ ነበር፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ስለሙስሊሙ የሐይማኖት ጥያቄ፣የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችና የፖለቲካ እስረኞች ባፋጣኝ እንዲፈቱ፣ስለኑሮ ውድነት ወዘተ ነበር በሰልፉ ላይ የተስተጋባው፡፡ በሰልፉ ማብቂያ ላይ እንደተነገረው እነነዚህ ጉዳዮች በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የማይመለሱ ከሆነ እንደገና የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠሩ በእለቱ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናገረው ነበር፡፡ እንደቀልድ ሶስት ወሯም አልቃ የተጠየቁትም ጥያቄዎችም ሳይመለሱ ነሃሴ 26, 2005 ቀን ደረሰች፡፡

ከፋፋዩ ኢህአዴግ የተጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ፋንታ በማን አለብኝነት ዜጎችን ማሰሩን፣ማንገላታቱን አልተወም፡፡ አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ›› በሚለው ዘመቻው በርካታ ሰልፎች ከ አዲስ አበባ ውጪ ማደረጉ ተጨማሪ እንቅልፍ የነሳው ይመስላል፡፡ ለዚህ ነው ከአንድ ገዢ ፓርቲ የማይጠበቅ በየእንቅስቃሴያቸው ላይ እየተከተለ ጎማ ሲያተነፍስ የነበረው፡፡ የነፃነትን በዚህ ሁኔታ ማስቆም የሚቻል መስሏቸው እንዲሁ ይደክማሉ፡፡ አንባገነኖች እንዲህ ናቸው፡፡ ከስህተታቸው መማርን አያውቁም ጦሩ አጠገባችን ነው ብለው በጦር ይመካሉ፡፡ ይህ ደግሞ ያየነው ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን ብንጀምር እንኳን ደርጉ ምን እንደነበር ምን እንደሆነ እናስታውሳለን፡፡ ከዚህ ከቅርቧ እንኳ መማር አልቻሉም፡፡ የጉልበት መንገድ( ፕሮፍ መስፍን ህገ አራዊትነት ይላታል፡፡) የት እንደሚያደርሳቸው የምናየው ይሆናል፡፡ ሆነም ቀረም አምባገነኖች አምባገነኖች ናቸው፡፡

በየእንቅስቃሴዎች መርበትበት የያዘው አምባገነኑ ስርአት በተለይም አክራሪነት ለመዋጋት ብሎ የጀመራት ዘመቻ እንዲሁም ከሼህ ኑር ይማም ሞት ጋር ተያይዞ በፓርቲዎች ላይ ጨምሮ በሙስሊም የሃይማኖት ጥያቄ ጠያቂዎች ላይ ዘመቻ ከፍቶ ነበር፡፡ ሃገር በውሸት ትመራ ይመስል ነጋ ጠባ ውሸትን ማዝነብ ይዘዋል ሚዲያዎቹ፡፡ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል የሚለው ለዚህ ግዜ የሚሰራ አይደለም ፡፡ በእጅ ስልካችን እንኳ የሚደርሰን መረጃ ቀላል አይደለም፡፡ ይህም ቴክኖሎጂው እየተስፋፋ ሲሄድ ከዚህ በላቀ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አሁንም የነፃነት ጉዞው አቅም በፈቀደው ሁሉ ይቀጥላል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ ነሃሴ 26 ሰልፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ እንደሰማነው ገዢው ፓርቲ ‹‹ፀረ አክራሪነት ትግል›› በሚል ከተለያዩ የሓይማኖት ተወካዮች ጋር በመተባበር በሚመስል መንገድ ለስምም ‹‹የሐይማኖቶች ጉባኤ›› ተሰባስበው ሰልፍ ለመውጣት እንደወሰኑ ተናግረዋል፡፡ መቼም ለወጉ ብዬ እንጂ የሓማኖት ተወካይ ያልኩት፤ ተወካይ ነን ያሉት ሁሉም ሓይማኖታቸውን የሚወክሉ ሳይሆኑ ለስርዐቱ ያደሩ ናቸው፡፡ የሐይማኖት አክራሪነት ምናምን የሚሉትት ፍረጃ ሰላማዊ የሆነውን እና ለ 18 ወራት ያህል ሲጠይቁት የነበሩትን የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄ አፈር ለማስበላት ያቀደ ነው፡፡ ይህም የሚሳካ አይደለም፡፡የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄ መልስ ሊያገኝ ይገባል፡፡

አምባገነኑ ኢህአዴግ በጣም በሚያስቅ እና በሚያሳዝን መልኩ ሰዎች በሰልፉ ላይ እንዲወጡ እያስገደደ ይገኛሉ፡፡ በየቤቱ እተዞረ ቅስቀሳው ተጧጡፏል፡፡ በየክፍለ ከተማው ባሉ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ በየክፍለ ከተማው ያሉ ወረዳዎችም በወረዳዎቻቸው ውስጥ ለሚገኙ ተቋማት ባለ ሁለት ገፅ መልእክት በትነዋል፡፡ በጣም የሚያስቀው እጄ ከገባው ባለ ሁለት ገፅ ፅሁፍ ውስጥ ሰልፉ ነሃሴ 26 እንደሚደረግ ወዘተ ይገልፅና ቀጥሎ እንዲህ ይለናል ‹‹ስለሆነም በወረዳችን የምትገኙ የመንግስትና የግል ተቋማት በስራችሁ ያሉ አጠቃላይ ሠራተኖችን በማነቃነቅ ነሃሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንዲሳተፉ እንድታደርጉልን እያሳሰብን ለዚህም ስራ ይረዳችሁ ዘንድ ለባነርና ለመፈክር የሚሆኑ መልዕክቶችን አያይዘን የላክን መሆኑን አሳውቃሉ፡፡›› ይልና በሁለተኛው ገፅ ‹‹በሰላማዊ ሰልፍ መተላለፍ ያለባቸው ዋና መልዕክቶች›› በሚል ይዘረዝራል፡፡ የአንድነትና የመከባበር፣የሰላም እሴቶቻችን በአክራሪዎችና ፀረ ሰላም ሃይሎች እንደማይናጋ›› እያለ ቅዠት የተሞላበትን ዲስኩር ያወራል፡፡ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ሰልፍ የሚወጡ ዜጎችን እንኳን በሰልፉ ላይ የሚያስተጋቡትን የሚመርጥላቸው ኢህአዴግ ነው፡፡ ከዚህ በላይ መውረድ ምን አለ? እንደዚህ አይነት ፓርቲስ በየትኛው አገር ነው የሚገኘው? ኢህአዴግ በፍፁም አይመጥነንም አራት ነጥብ

ስለሆነም ይህን ሰልፉ ማለትም ስርዐቱና የስርዐቱ ሎሌዎች በሚያዘጋጁት ሰልፉ ላይ መገኘት ሙስሊም ወገኖቻችን ለ18 ወራት ያህል ሲጠይቁት የነበረውን ፍፁም ሰላማዊ የሆነ የሐማኖት ጥያቄ ስርአቱ አለባብሶ ለማለፍ በሚያደርገው ሴራ ላይ ተባበሪ መሆን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ለከፋፍለህ ግዛ፣ለኢ-ዴሞክራሲያዊነት፣ ለብልጣብልጥነት፣ለአምባገነንነት በአደባበይ እውቅና መስጠት ነው፡፡ ስለሆነም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን አካሄደም አላካሄደም ስርአቱ እራሱ በጠራው ሰልፍ ውርደትን ልናከናንበው እንችላለን፡፡ ለዚህም ከስርዐቱ ሴራዎች ለማምለጥና የተሳካ ስራ እንድንሰራ በእለቱ ለምናካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች ልንመክር ይገባል፡፡

አንድነት ፓርቲ በአሜሪካ ኤምባሲ ቅር መሰኘቱን ገለፀ

11
አንድነት ለዲሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ቅር መሰኘቱን ገለፀ። ፓርቲው በኤምባሲው ላይ ቅሬታውን የገለፀው የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆነው ወጣት ዳንኤል ተፈራ ለፓርቲው የስራ ጉዳይ ለአንድ ወር ወደ አሜሪካ እንዳይሄድ በመደረጉ ነው።
የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳና ወጣት ዳንኤል ተፈራ በጋራ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት ኤምባሲው ቪዛ በመከልከሉ የፓርቲውን ስራ መስተጓጎሉን ተናግረዋል።
ወጣት ዳንኤል ወደ ዋሽንግተን ለማቅናት ግብዣ የቀረበው አሜሪካን ሀገር በሚገኙ የፓርቲው ድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮች አማካኝነት ሲሆን በቅርቡ ፓርቲው የጀመረው ‘‘የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት’’ የተባለውን ሕዝባዊ ንቅናቄ በአሜሪካን ተገኝቶ ገለፃ እንዲያደርግና ድጋፍ የማሰባሰቡን ተግባር ለማጠናከር ነበር።
ይሁን እንጂ ኤምባሲው የዳንኤል ተፈራን ወጣት መሆን በማየት ብቻ ቪዛ መከልከሉ የኤምባሲው የስራ ኃላፊዎችን የአመለካከት ችግር ማሳያ መሆኑን ወጣት ዳንኤል የገለፀ ሲሆን በቀጣይም ፓርቲው በዚሁ ጉዳይ ላይ ኤምባሲውን ማብራሪያ እንደሚጠይቅም አመልክቷል። ወጣት ዳንኤል ቪዛ ከማግኘቱ በፊት ደመወዙን፣ የቤት መኪና እና የቤት ካርታ በቅድመ ሁኔታ እንዲያቀርብ መጠየቁ አሳዛኝ መሆኑን ገልጿል።
‘‘እኔ ቤተሰብ ያለኝ ሀገሬን የምወድና ከፓርቲው ተልእኮ ውጪ አንድም ቀን በአሜሪካን ሀገር የመቆየት ፍላጎት የለኝም’’ ያለው ወጣት ዳንኤል በኤምባሲው ድርጊት ማዘኑን ገልጿል።
ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ ተብሎ ዕድሜ ልክ የተፈረደበት አቶ አንዱአለም አራጌ ቪዛ መከልከሉ አይዘነጋም።
ጉዳዩን በማስመልከት የኤምባሲውን የህዝብ ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ሮበርት ፖስትን ለማነጋገር ብንሞክርም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ባለመስራቱ ልናገኛቸው አልቻልንም።

የእሁዱ ሰልፍን ሳንሰላስለው…

21
እንኳንስ ሌላው ቀርቶ፤ አዲስ አበባ ስታድየም የከተማው ደርቢ እግር ኳስ ጨዋታ ሲኖር የቡና ልጆች ሚስማር የሳንጃው ልጆች ደግሞ ዳፍ ነው የሚገቡት፡፡ ጥላ ፎቁንም ግራ እና ቀኝ ብለው ይካፈሉታል፡፡

ይህንን የሚያደርጉት ሁለቱም ቡድኖቻቸው በአንድ ሜዳ ስለሚጫወቱ ማዶ ለማዶ ሆነው መሀል ላይ የሚጫወተውን ቡድናቸውን ለማበረታታት ነው፡፡ እንጂ ለብሽሽቅ ብለው አይቀጣጠሩም… ኳስ ጨዋታ በሌለበት እስቲ እናንተም ውጡ እኛም እንውጣ እና እናደበላልቀው ብለው ሲጠራሩ ሰምቼ አላውቅም፡፡

ነሀሴ 26 በመስቀል አደባባይ ሁለት ሰልፎች ተጠርተዋል፡፡ አንደኛው ሰማያዊ ፓርቲ ከሶስት ወር በፊት ላደረገው ሰልፍ ምላሽ ካላገኘሁ እመለስበታለሁ ብሎ ሲዘጋጅበት የከረመው ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ድንገት ከየት መጣ ከየት ሳንለው የተከሰተው የሀይማኖት ተቋማት የጠሩት ሰልፍ ነው፡፡ ይህ ሰልፍ በተዘዋዋሪ መንግስታችን የጠራው ሰልፍ መሆኑን ያወቅነው ቤት ለቤት እየቀሰቀሱ ያሉትን ቀበሌ ቀበሌ የሚጫወቱ ሴቶች ከማየታችን በፊት በኢቲቪ ዜና አንባቢው ጮክ ብሎ ሲናገር የሰማን ጊዜ ነው፡፡

እሁድ ነሀሴ 26 መንግስት፤ ተቀናቃኙ ሰማያዊ ፓርቲ ቀድሞ በጠራው ሰልፍ ላይ ሌላ ሰልፍ መጥራቱ ባስበው ባስበው አሁንም ባሰበው ምክንያቱ አልገለፅልህ ብሎኛል፡፡

ሰልፍን ደጋግሜ ሳንሰላስለው ሳንሰላስለው…. መንግስታችን ኢህአዴግ ይህንን ሰልፍ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀን ላይ ደርቦ ሲጠራ እንደው በደረቁ ሰልፍ ብሎ ከሚጠራ ለሰማያዊ ፓርቲ ሰዎች አንዳች ሆነ ግብዣ ቢያደርግ እና…

መሀል መስቀል አደባባይ ከሁለቱም ወገን የሚገኙ አመራሮች የሚሳተፉበት አይደል ሾው ነገር ወይም ደግሞ ድሮ ጊዜ እንደሚደረገው ሁለቱም ወገኖች አሉ የሚሏቸውን አዋቂዎቻቸውን አቁመው ርስ በርስ የሚሟገቱበት እና በህዝቡ ዘንድ የሀሳብ ብልጫ ለመያዝ ሙከራ የሚያደርጉበት የክርክር ውድድር ካልሆነ ካልሆነ ደግሞ የሆነ የቁንጅና ወድድር ነገር ቢያሳዩን ብዬ በማሰብ ላይ እገኛለሁ… ሸግዬ አሳብ አይደለም ትላላችሁ…!

የምር ግን ኢህአዴግ የጠራው ሰልፍ የምሩን ነው ማለት ነው…

እኔ የምለው የሀይማኖት ተቋማቱ መንግስት ይሄንን እንዲያደርጉ ሲያዛቸው ዝም ብለው እሺ ከሚሉት ሰብሰብ ብለው ፀልየው ከህመሙ እንዲፈወስ ቢያደርጉልን ምናለ… እውነቴን ነው ምላችሁ መንግስቴ ታሟል!
Abe Tokichaw

በይዘቱ ወቅታዊ የቴሌ-ኮንፍረንስ ስብሰባ – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ደጋፊ ግብረ ኃይል

ጋባዥ: የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ የሰሜን አሜሪካ አንድነት ፓርቲ ደጋፊ ግብረ ኃይል
ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ በስብሰባው ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፥ 1) የፓርላማ አባል የተከበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ 2) የአንድነት ፓርቲ ፍኖተ ነፃነት ቦርድ ሰብሳቢ እና አቶ በላይ ፈቃዱ በረዳ በኢትዮጵያችን በአቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እእንዲሁም በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ትግላችን ላይ እነዚኽ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ባልደረቦች በቴሌ-ኮንፍረንስ ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ስለሚያደርጉ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ግብረ ኃይል በአክብሮት ጋብዞዎታል። የአንድነት ፓርቲ መሪዎችን ጥያቄዎች መጠየቅ ይችላሉ። በዚኽ ቴሌ-ኮንፍረንስ ከተጋበዙት ሚዲያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፥ 1) ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች፥ የአሜሪካ ድምጽ (አማርኛ፣ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራሞች)፣ ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ፣ የዲሲ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሬዲዮኖች በሰሜን አሜሪካ በሙሉ 2) ድረገጾች፥ ዘሐበሻ፣ ኢትዮሚዲያ፣ ኢትዮሚዲያ ፎረም፣ አቦጊዳ፣ ኢትዮሪቪው እና ሌሎች 3) ፓልቶክ ሚዲያዎች፥ ቃሌ፣ ሲቪሊቲ እና ከረንት አፌር ቴሌ-ኮንፍረንሱ የሚደረገበት ቀን እና ሰዓት፥

ቀን፥ ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. (Saturday, August 31, 2013) – ከሁለት ቀኖች በኋል!
ሰዓት፥ ከቀኑ 1፡00 ሰዓት (1:00 PM Estern Time)
በቴሌ-ኮንፍረንሱ ለመሳተፍ፥ 267-507-0240 ይደውሉ እና 201820 ኮድ ይጠቀሙ
ውድ የድረገጾች አስተናጋጆች፥ የጊዜ እጥረት እየተፈታተነን ነው። ስለዚኽ ይኽን ጥሪ በድረገጾቻችሁ ላይ በማውጣት የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ወገናችን ሁሉ ስለቴሌ-ኮንፍረንሱ እንዲያውቅ እንድታደርጉልን በአክብሮት ትብብራችሁን እንጠይቃለን። ለቴሌ-ኮንፍረንሱ ሁለት ቀኖች ብቻ ስለቀሩን ጥሪው እንደደረሳችሁ በድረገጾቻችሁ እንደምታሰፍሩልን ተስፋ እናደርጋለን።

እስከዚያ በአክብሮት መልካሙን እንመኛለን!

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5489#sthash.3jeutKPL.dpuf33

የሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱም አሉ።

hj
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል። በተለይ ደግሞ « በትግራይ ተወላጁ ዘንድ ሕወሐት የለም፣ ተከፋፍሏል፣ ተዳክሟል፣ ፓርቲው ሰው የለውም፤» የሚለውን እራሱ ቡድኑ በማንሳት ለገዛ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ « ሕወሐት አሁንም ሃይል አለው፤ አልተዳከመም» በማለት አድራጊ- ፈጣሪ በመሆን ስልጣኑን በበላይነት ተቆጣጥሮ እንደያዘና ቡድኑ የመጣውም “አይዟችሁ” ለማለት እንደሆነ መገለፁን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አስታውቀዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ፥ « ልማት አልምተናል፤ ትግራይ እየለማ ነው፤ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገነው ነው» ከማለቱ ባሻገር « በትግራይ ተወላጁ ላይ አደጋ ተደቅኗል፤ የሙስሊሙ፣ የትምክህተኞችና የሽብርተኞች አደገኛ እንቅስቃሴ እያንዣበበ መሆኑን፣…የተደቀነብህን አደጋ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤ ያለበለዚያ ግን ሊያጠፉህ ነው፤» ሲሉ መናገራቸውን የገለፁት ምንጮች አክለውም፣ « አባላት የሆናችሁ ተወደደም ተጠላ መሬትና መኖሪያ ቤት እንሰጣችኋለን፤ ለዚህም ከእኛ ጎን መሰለፍ አለባችሁ» በማለት ሊሸነግሉ መሞከራቸውን ጠቁመዋል።
ከዋሽንግተን ስብሰባ (ለሁለት ተከፍሎ ነው የተካሄደው) በኋላ ወደ ሶስቱ ከተሞች ተከፋፍለው እንደሄዱ ሲታወቅ፥ ሲያትል አቶ ብርሃነ ማረት፣ እንዲሁም ላስቬስጋስ አባይ ወልዱና ተክለወይኒ አሰፋ መሄዳቸው ታውቋል። በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው እነአባይ ስብሰባው ከቀኑ 2፡00 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ አመሻሽ ላይ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባው ሲጀመር ከላይ የተገለፁትን ጉዳዮች ያደመጠው ተሰብሳቢ ተከታዮቹን ጥያቄ አቀረበ፤ « ዴሞክራሲ አለ ትላላችሁ፣ ነገር ግን ዴሞክራሲ የለም፤ በሃሳብ የሚቃወማችሁን ታስራላችሁ፣ ታንገላታላችሁ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ታካሂዳላችሁ፤ ከእናንተ የተለየ ሃሳብ ያለውን ትፈራላችሁ፤ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምታደርጉት?….በማ.ረ.ት.abay-weldu(ማህበር ረድኤት ትግራይ) በትግራይ ሕዝብ ስም የምትሰበስቡትን ገንዘብ ለአራጣ ብድር እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ በመሳሪያነት እያዋላችሁት ነው። ለምን?….ትእምት (ኤፈርት) ማነው ባለቤቱ?..በማን ነው የሚመራው?..ማነው የሚቆጣጠረው?..ለመሆኑ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል ወይ?..እነማናቸው እየተጠቀሙበት ያለው?» የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች እንደነበሩ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን፣ አባይ ወልዱ « እኔ አልመልስም፣ ተ/ወይኒ መልስ ይስጥበት» ቢሉም ነገር ግን ግልፅና አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማመናጨቅና ቁጣ ያመሩት ተ/ወይኒ በዚህ ድርጊታቸው በርካታ ተሰብሳቢዎችን እንዳሳዘኑ አስረድተዋል። በዚህ የተበሳጨው ተሰብሳቢ « ጥያቄያችን አልተመለሰም» በማለቱና ሁከትና ያለመደማመጥ በማየሉ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች፣ የጥያቄና ተቃውሞው መብዛት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናቱ የመረጡት ማምለጫ በላስቬጋስ ተወካያቸው በሆነውና መድረክ ሲመራ በነበረው አቶ ተወልደ በኩል፥ « አዳራሹን የተከራየንበት ሰአት አብቅቷል፤ ስለዚህም ስብሰባው አብቅቷል » በማለት በአስቂኝ ሰበብ መቋረጡን አያይዘው ገልፀዋል። እነአባይ ከአዳራሹ ሲወጡ ቀድሞ ውጭ ሆኖ ይጠብቃቸው በነበረው ተሰብሳቢ ውግዘትና ስድብ እንደደረሰባቸው ያስታወቁት ምንጮች « ሌባ..ሌባ…ሙሰኞች..» የሚሉ ተቃውሞዎች ጎላ ብለው እንደተሰሙ አመልክተዋል።
ስብሰባዎቹን የታዘቡ ወገኖች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል፤ « በአንድ በኩል ልማት እያካሄድን ነው፤ እያሉና ገንዘብ እየጠየቁ በሌላ በኩል “ትግራዋይ አደጋ ተደቅኖብሃል፣ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤” ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭና ድጋፍ የማግኛ የፖለቲካ የፖለቲካ ቁማር ነው። ያልተጠየቁትን የፓርቲውን ህልውና (ስለ ሕወሐት) አንስቶ መነገሩም አስገራሚና አጠያያቂ ነው።» ሲሉ ትዝብታቸውን የጀመሩት እነዚህ ወገኖች በማያያዝም፥ « እነዚህ ሰባት ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ የመጡት ከነዘመዶቻቸው፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ የመንግስት ወኪሎች እንደመሆናቸው – በማን ገንዝብ ነው የሚንቀሳቀሱት?..የሚለው መጠየቅ አለበት። በሕዝብ ገንዝብ እየተንፈላሰሱ እንደሆነ ግልፅ ነው። የትግራይ ተወላጁን ብቻ ለይተው ስብሰባ የሚጠሩት ለምንድነው?…በእርግጥ ስላሰቡለት ነው?…የሚሉት ሲፈተሹ .መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው። አላማቸውና ትኩረት የሰጡት የትግራይ ተወላጁን እየተንከባከቡት እንደሆነና ተጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት በመፈለግ፣ እግረ-መንገዳቸውን ከቀሪው ኢትዮጲያዊ ወገኑ ጋር በመነጠል..ድጋፍ ለማግኘትና በውስጣቸው የተፈጠረውን ቀውስ በዚህ በኩል ቀዳዳውን ለመድፈን የሚደረግ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት ነው። ..ደግሞስ ሕወሐት “አጋር” ከሚላቸው ብ.አ.ዴ.ን፣ ኦ.ህ.ዴ.ድ.፣ ደቡብ ሕዝቦች ተለይቶ፣ በሕዝብ ገንዘብ ስብሰባ የሚጠራበትና ያሻውን የሚያደርግበት አግባብ ምንድነው?..የሚለው ከዚህ ጋር መታየት ያለብት ነው። ፖለቲካዊ ፍጆታና ማንአለብኝነት በፓርቲው በመነገሱ እንደሆነ ደግሞ ግልፅ ነው።» ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አሜሪካ ከመጡት ሰባት የሕወሐት ባለስልጣናት መካከል- ማለትም አባይ ወልዱ፣ ብርሃነ ኪ/ማሪያም፣ ተ/ወይኒ አሰፋና ዳንኤል አሰፋ በዋነኛነት ሲጠቀሱ፣ ከሰባቱ ሶስቱ ስብሰባውን ሳያካሂዱ ከቡድኑ ተገንጥለው በአሜሪካ መቅረታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው (ልጆቻቸውን ጭምር) በመምጣት አሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀው መቅረትን የመረጡት ባለስልጣናት ውስጥ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባላት እንዳሉ ያረጋገጡት ምንጮች በቅርቡ ዝርዝሩን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰልፍ የሚያደርግ ከሆነ፤ሰልፉ ህገወጥ ነው አለ።

oo
ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው።
ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “የቀደምኩት እኔ ነኝ” በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።
ስለጉዳዩ ተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፤ ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ፤ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።
እንደ ሊቀመንበሩ ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባቱን ተናግረዋል።
በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል።
ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ከጽ/ቤቱ እስካሁን ደረስ ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል።
ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፤ በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2005 በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ ፤ በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ለሰልፉ ሲዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።
ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ የሃይማኖት ጽ/ቤቱ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያሳወቀበትን ቀን ለመናገር አልፈለጉም።
ከዚህም በላይ ሰንደቅ እንዳለው፤ የርዕሰ ደብር በሪሁን መግለጫ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ሰልፉን ለማካሄድ ጥያቄ ያቀረበው ከነሐሴ 15 እና 16 በኋላ መሆኑን የሚያመለክት ነው። በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ የማሳወቂያ ደብዳቤ፡ያስገባው ግን ነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ/ም ነው።
ሀቁ ይህ ቢሆንም፤የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ፦” የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚ የነበሩት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በመሆናቸው ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንዲያካሂድ አልተፈቀደለትም” ብለዋል።
አክለውም፦”ፓርቲው ሰልፍ የሚያካሄድ ከሆነም ህገወጥ ነው” ብለዋል።
ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ስላሳወቁበትን ቀን እና ስለ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

ድሬዳዋና ሞቃዲሾ ሁለት የኢትዮጵያ አውሮፕላኖች ተከሰከሱ

kj
የኢትዮጵያ ሚሊታሪ አቪየሽንና የኢትዮጵያ ኤየር ሀይል ከሁለት ሳምነት በፊት ድሬዳዋና ሞቃዲሾ የወደቁትን ሁለት አውሮፕላን አደጋዎችን እየመረመሩ እንደሆነ ለሪፖርተር የውስጥ አዋቂወች አስታዎቁ፡፡ ከኢትዮጵያ ሚሊታሪ አቪየሽንና ከኢትዮጵያ አየር ሀይል የተመረጡ የአደጋው ምክንያት አጣሪዎች አደጋው ወደተከሰተበት ቦታ መላካቸውም ተጠቅሷል፡፡
የመጃመሪያው አደጋ ኦገስት 6 ሲ130(ኤል100) የተባለ የጦር አውርፕላን ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር መንገድ ላይ ሲከሰት ሁለቱ ተሳፋሪዎችም ቀላል አደጋ አጋጥሟቸዋል፡፡ የአውሮፕላኑ ፓይለት የነበሩትም ኮሎኔል ሰለሞን ሲሆኑ የተጎዱት ሁለቱ ተሳፋሪዎች አዲስ አበባ በሚገኘው ጦር ሁይሎች ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
የዩኤስ ማንግስት ሁለት ሄርኩለስ ሲ130 የጦር አውሮፕላኖች ለኢትዮጵያ ኤየር ሀይለ በ1998 እ.ኤ.አ. በእርዳታ እንደሰጠ ይታወቃል፡፡ የዩኤስ ማንግስት በእርዳታ ሊሰጥ የነበረው አራት ሄርኩለስ ሲ130 የጦር አውርፕላኖች ቢሆንም ሁለቱን አውሮፕላኖች እንደሰጠ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በሜይ 1998 በመነሳቱ ሀሳቡን ቀይሮ የቀሩትን ሁለቱን የጦር አውሮፕላኖች ከልክሏል፡፡
ሁለተኛው አንቶኖቭ 12 አውሮፕላን ደግሞ ኦገስት 9 በሶማሊያ ሞቃዲሾ አየር መረፊያ ላይ ተከስክሶ በእሳት ሲቀጣጠል ከስድስቱ ተሳፋሪዎች ውስጥ አራቱ ሞተው ተገኝተዋል፡፡ ሁለቱ የተረፉት ተሳፋሪዎች ደግሞ ወደ ሞቃዲሾ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ይህ አውሮፕላን የሙስሊም ታጣቂዋች ጋር ለሚዋጉት የአለም አቀፍ ሀይሎች መሳሪያ ጭኖ ነበር፡፡
የሄው የጦር እቃ ጫኝ አንቶኖቭ 12 አውሮፕላን ኦገስት 9 ከጠዋቱ 12፡00 ሰአት ከድሬዳዋ ተነስቶ ከሁለት ሳታት በኋላ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ላይ ጠዋት 2፡00 ተከስክሷል፡፡
ለሪፖረተር የታመኑ የዜና ምንጮች አንደዘገቡት የኢትዮጵያ ሚሊታሪ አቪየሽንና የኢትዮጵያ ኤየር ሀይል ኤክስፐርቶች በሶስት ቀን ልዩነት የተከሰቱትን የአውሮፕላን አደጋዎች ምርመራ እያካሄዱ ነው፡፡ የአደጋዎቹ መንስኤ ገና እንዳልታወቀና መረጃዎች እየተሰበሰቡ እንደሆነ ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡ ምነጮች ጨምረው እንደተናገሩት ‘‘ ሁለት አደጋዎች ባአንድ ሳምንት ማለት ብዙ ነው፡፡ አደጋው የተከሰተው ባጋጣሚ ወይም ታቅዶበት ሊሆን ይችላል፡፡’’ ብለዋል፡፡
የበረራ ኤክስፐርቶች እንዳሉት አንቶኖቭ አውሮፕላን ደካማ አደጋን የመከላከል ብቃትና የደህንነት መጠበቂያዎች እንዳሉት መዝገቦቹ ያረጋግጣሉ ብለዋል፡፡ ብዙ ያረጁ አንቶኖቭ አውሮፕላን አደጋዎች በአፍሪካና በተለያዮ የአለማች ክፍሎች ተከስተዋል፡፡ እንደ ኤክስፐርቶቹ ገለጻ ሲ130 አውሮፕላኖች በአንጻራዊ ሁኔታ የተሸሉ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ኤክስፐርቶች እነዳሉት ማንኛውም አውሮፕላን በደካማ ሁኔታ ከተጠገነ የመከስከስ አደጋ ሊያጋጥመው ይችላል ፣ ነገር ግን ያረጁ አውሮፕላኖች የመከስከስ አደጋ ከየትኛውም አውሮፕላኖች በተለየ ሁኔታ ይጨምራል፡፡

http://sodere.com/

የዱርየው ወያኔ መንግሥት የውሸት አምራች ፋብሪካዎች ይዘጉ

mn
ተሾመ ደባለቄ

‘የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ’ ሲል የሀገሬ ሰው ሀገር ያወቀውን ፀሐይ የሞቀውን ሌባ ጨዋ ለማስመሰል የሚያጋጋው ውሸት ሲያሰለች ነው። እንደዚሁም መንግሥት ነኝ ተባዩ ወያኔም የውሸት ጋጋታው ሰውን አሰልችቶት እውነትም ቢናገር እነኳን የሚያምነው አጥቶ ሙጥኝ የያዛቸው መዋቅሮች ‘ውሸታም’’ ና ‘ሌባ’ የሚል ስም አትረፈዋል።

ውርደት ያተረፈው ወያኔ የውሸት ጋጋታው አልበቃ ብሎት ለምን እውነት ተነገረ ብሎ ድርጅት መዘጋት ባልደረቦችን ማሳደድ፣ ማሰርና እስከመግደል ደረጃ ደርሷል። በራሱ ውሸት ያበደው ወያኔ በአካባቢው ከሚያጎበድዱለት ጉጅሌዎቹ መሃል አብደሃል በሙስና ተዘፍዝፈሃል የሚለው ጠፍቶ እንደመሸበት ሰካራም ቤቱ ጠፍቶት በየሰዉ ቤት እያንኳኳ በራሱ ውሸት ተሸብሮ ህዘብን ማሸበሩን ቀጥሎበታል።

በመሰረታዊ ውሸት ላይ የተመሰረተው ወያኔ ‘ድንጋዩ ዳቦ ነው’ ብላችሁ ተቀበሉ እያለ መከራውን ሲያይ አዝለውት የሚዞሩት ጉጅሌዎቹ የውሸቱ ሸክም በዝቶባቸው ሲዘላበዱና በህዘብ መሳለቂያ ሲሆኑ ማየት ያሳፍራልም ያሳዝናል።

በዕውነቱ ውሸቱ በዝቶ የራሱ ነፍስ ፈጥሮ ወያኔን ማስተዳደር ከጀመረ ሰንብቷል ማለት ሀሰት አይሆንም። ይህ ከመሰረቱ በውሸት የተገነባው መንግስት ነኝ ባዩ ቡድን ወደሃላ መመለስ ስለማይችል የባሰ እያበደ ይሄዳል አንጂ እውነትን ለመቀበል ችሎታም አቅምም ሊኖረው አይቻልም። ስለሆነም እራሱን ወጥመድ ውስጥ አግብቶ ለማምለጥ ሲፈራገጥ ወገን እያቆሰለና አገር አያደማ መሆኑ ሊያስገርመን አይገባም።

ሆዳቸውን በውሸት የሞሉት ጉጅሌዎቹም ቢሆኑ ሆድን ከእውነት መርጠው እየቃዡ ምላሰቸው ተቆላልፋል። እውነት መናገርም የሚያጎርሳቸውን እጅ መንከስ ስለሆነባቸው እውነት የሚናገረውን መናከስ የሚረዳቸው መስሏቸው ሲዘላብዱ በህዘብና በሀገር ሲያፌዙ ይገኛሉ።

የቸገረው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ቀንደኛው የውሸት መሪ ካለፈ ጀምሮ ውሸቱን ማስተዳደር አቅቷቸው ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ሲዘባርቁ ለተመለከታቸው አብደው ሊያሳብዱ የተነሱ እንደሆኑ ግልጽ ነው። በእርግጥኝነት ሊባል የሚቻለው እብድ ማበዱን ካላመነ ጤነኛ ነኝ ብሎ እራሱን ስለሚያሳምን በእብዶች መሀል አንድ ጤነኛ ቢኖር እንኳን እንደ እብድ ስለሚቆጠር ያበዱትን ባልደረቦቹን ሊረዳቸው አይችልም።

የብዙሃን መገናኛ ላይ ያሰፈሰፉት ካድሬዎችን ብናስተውል የወያኔ ውሸት የራሱን ነፍስ እንዳላው ያረጋግጥልናል። እነዚህ የብዙሃን መገናኛ ተባዮች የውሸት ፋቢሪካ ሆነው በሶስት ፓኬጅ እያሸጉ ውሸትን ሊሸጡ ሲሯሯጡ ይታያሉ።

አንደኛው ፋብሪካ የውሸቱ ጥሬ ዘር የሚያመርተው በወያኔ የሚተዳደሩት መዋቅሮች ሲሆን የውሸት ምሶሶና በምንጭነት ፊት ቀዳሚ ሲሆን የህዋዓት ዋና መሳሪያ ነው። ሆኖም መንግሥት ነኝ የሚለው ወያኔ ስለተቆጣጠራቸው የሚያምናቸው አጥተው ወንዝ እንደሚያከራትተው ግንድ ይወዛወዛሉ።

woyane propaganda machine

በሁለተኛ ደረጃ ያሉት የውሽት ፋብሪካዎች ወያኔ በካድሬዎቹ ያደራጃቸው መዋቅሮችና የብዙሃን መገናኛዎች (በተለይም በስደት ላይ ያለውን ወገን ለማወናበድ) የተዋቀሩ ናቸው። እነኝህ መዋቅሮች በወያኔ ጥሬ ወሸትና ገንዘብ የሚታገዙ ስለሆኑ አላማችው በግል ስም ወያኔ በመንግሥት ስም መሸጥ ያቃተውን ውሸት ዳግም ማሸግና መሸጥ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ወያኔ ከመጣ ጀምሮ ማንነታቸው የማይታወቅ (ጎሬላዎች) ናቸው። ከተጋለጡት መሃል የአይጋ-ፎረም ባለቤት ኢሳያስ አፅብሃ ከሳኖዜ ካሊፎሪኒያና የትግራይ-ነት ባለቤት ሚካኤል አባይ ከዴንቨር ኮለራዶ ይገኙበታል።

በሶስተኛ ደረጃ ያሉት የውሸት ፋብሪካዎች ደግሞ በነጻ ፕሬስ ስም የሚነግዱ መዋቅሮች ሲሆኑ እነሱም በሁለት ይከፈላሉ። አንዱ በወያኔና ባልደረቦቹ የሚተዳደሩ የውስጥ ሚስጥረና ድጋፍ ያለቸውና ዜጋ ለማወናበድ የተደራጁ የብዙሃን መገናኛ መዋቕሮች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በተቃዋሚ ስም የተደራጁ አስመሳይ መዋቅሮች ናቸው። የሁለቱም አላማ አንድ ቢሆንም የውሸትን ማሸግና መሸጥ መንገዳቸው ይለያያል። ነገር ግን ሁለትም የወያኔን ሥርዓት በተወሰነ ደረጃ ይገስጻሉ ግን አላማቸው ወያኔን ማቆየት ስለሆነ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እነዳይነኩ የታዘዙ ይመስላሉ። ሁሉቱም ከውጭ ሚዲያ የመጣን ወያኔን የሚያሞግስ ዜና አያመልጣቸውም ወይን ይፈጥራሉ። ሁለቱም ህዘብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና ዘረፋ ለመሸፈንና ለማደናገር ዘመቻ ላይ የተሰማሩ ናቸው። ሁሉቱም በጋዜጣ ስም አሰመስለው የፐሮፖጋነዳ ሥራ ለመስራት ውስጥ ለውስጥ የተደራጁ የሥርዓቱ ጉጅሌዎች ናቸው።

በውሸት ላይ የተሰማሩት የወያኔ ባልደረባና አስመሳይ ጋዜጠኞች ሥራዓቱ እየፈራረሰ ሲመጣ የሚያደርጉት ስለጠፋባቸው ወያኔን ለማዳን ያላቸው ብቻ ምርጫ የእስላም አሸባሪ መጣባችሁ እያሉ ማስፈፈራራት አዲሱ ሞያቸው ሆኗል። እሱንም ጉዳይ በተለያየ የውሸት ማቀነባበር መንገድ እያዘጋጁ ህዘብን በማተራመስና ለወያኔ ጊዜ ሊገዙለት እየጣሩ ነው።

ለምሳሌ ቀንደኛዎቹ የወያኔ የዜና መዋቅሮች የውሸት ቲያትር እያሰሩ ሲያሰራጩ በግል የዜና መዋቀር ስም የሚቀሳቀሱት ደግሞ ቲያትሩን እውነት ለማስመሰል የውጭ አከራሪዎችን ዜና በማነፈስ ህዘብን ቢያንስ እንዲጠራጠር አልያም እንዲያምን ይጥራሉ። ከዚህ በፊትም በአማራው ህብረተሰብ ላይ ያወረዱበት የውሸት ዘመቻ ስኪ ሆነ ብለው ስለሚያምኑ በእስልም ተከታዮች ወገኖቻችን ላይ እየመከሩት መሆኑ በግልጽ ይታያል።

ወገንም የነፃ ብዙሃን መገናኛዎችም የፖሎቲካና የሲቪክ መዋቅሮችን እነኚህን የውሸት ፋበሪካዎችንና የሚያንቀሳቅሷቸውን የውሸት መልክተኞች ማወቅ ማጋለጥና ከዛም አልፎም ማዘጋትና ተጠያቂ ማድርግ ግድ ይላል።

ትግሉ ማንንም ግለሰብንና ቡድን የውሸት ፋበሪካ ሰለባ እንዳይሆን የመከታተልና የመቅታት ዋናው ስራው መሆን ይኖርበታል። የወያኔ ሥርዓት እየገማ በመጣ ቁጥር ባልደረቦቹ እያባሱ መግማታቸው አይቀሬ ስለሆነ እያናዳንዱ ዜጋ እነኝህን የውሸት መልክተኞች መከታተል ሀላፊነት አለበት። የውሸት ፋብሪካ መዘጋትና ሥራ አስኪያጂዎች መቅጣት የዲሞክራሲ ትግል ዋናው ምሶሶ ስለሆነ ፋብሪካዎቹም ሆነ ሥራአስኪያጆቹ ዕውነት ያመርታሉ ማለት የህልም እነጀራና ሞኝነት ነው።

የኢትኦጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ከመጣ ጀምሮ እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ካደሬዎችና ተጠቃሚዎች የገዢውን ቡድን ውሸት እያሰራጩ ኢሳትን የሚያጋልጠውን እውነት ሊነኩት አቅቷቸው አይናቸውን ጨፍነው ጆሯቸውን ደፍነው ቅዠት ውስጥ እንዳሉ እራሳቸው ይመሰክራሉ። ኢሳት አንዱ ትልቁ ሥራው እንኝህን የወያኔን ውሸት ፋብሪካና ቸርቻሪ ባለቤቶችን ለህዘብ ማጋለጥና ማንነታቸውን ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረግ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን በቶሎ የሚጎናፀፈውና የወደፊት ሰላምና ብልጽግና የሚያገኘው የውሸት ፋብሪካዎች ሲዘጉና የእውነት ፋብሪካዎች ሲስፋፉ ነው። ይህ መሰረታዊ መፍቴህ የውሸት ፋበሪካ ባለቤቶችን እያሳበዳቸው ጨርቃቸውን ጥለው እየሮጡ እነዳሉ ግልጽ እየሆኑ መጥተዋል። ሆኖም በቂ ትኩረት ተሰጥቶት ስላልተሰራ ተደብቀው ውሸትን ማምረትና መቸርቸር ሥራቸውን ቀጥለዋል። በድርጅት ከመስራት በግለሰብ መሥራት የባህል ድክመት ብዙዎቹን የነፃ ሚዲያዎችን ያዳከመና የውሸት ፋብሪካዎችን እድል ከፍቶላቸዋል ማለት ይቻላል።

የውሸት ፋብሪካዎችን ለማዘጋት ባለቤቶቹንም ለመቅጣት እንዘጋጅ እንደራጅ

ድል ለኢትዮጵያ ህዘብ

Post Navigation