addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “August 25, 2013”

Breaking News: በሚኒሶታ ለአባይ ቦንድ ሽያጭ የተጠራው ስብሰባ ሳይጀመር ተበጠበጠ

21
(ዘ-ሐበሻ) በሴንት ፖል ሚኒሶታ የአባይን ቦንድ ለመሸጥ የኢትዮጵያ መንግስት አዳራሽ ተከራይቶ ለዛሬ ኦገስት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከ ቀኑ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት ስብሰባ የጠራ ሲሆን ስብሰባው ከመጀመሩ አንድ ሰዓት በፊት ብጥብጥ ተነሳ።

በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን “ወያኔን አናምንም፤ 2 ሰዓት ብሎ ጠርቶ ስብሰውን ቀድሞ ሊጀምርና ሊነሳበት የታቀደውን ተቃውሞ ሊያከሽፍ ይችላል” በሚል ገና ከጠዋቱ ስብሰባው ይደረግበታል የተባለበት አዳራሽ በር ላይ ሲጠባበቁ ቆይተዋል። ልክ ስብሰባው ሊጀመር 1 ሰዓት ሲቀረው አንድ የስርዓቱ ደጋፊ የሆነ ሰው ካሜራ ይዞ “ከአባይ በፊት ሰብአዊ መብት ይከበር፤ የታሰሩት ይፈቱ” በሚል ለተቃውሞ የተሰባሰበውን ሕዝብ ሊቀርጽ ሲጠጋ ሕዝቡ “ሃገር ቤት ቪድዮ የቀረጻችሁት ሳያንስ እዚህ ልትቀርጹ ነው ወይ?” በሚል ልጁን ክፉኛ ከደበደቡት በኋላ ካሜራውን ሰባብረውበታል ያሉት የአይን እማኞች ወዲያውም ከ20 የሚበልጡ የሴንት ፖል ከተማ ፖሊስ መኪናዎች አካባቢውን በመክበብ ብጥብጡን አርግበውታል።

የሴንት ፖል ፖሊሶች መቃወም ትችላላችሁ፤ ሆኖም ግን ሰውን መደብደብ አግባብ አይደለም በሚል ለተቃውሞ የተዘጋጁትን ሲበትኑ ሕዝቡም “በአባይ ስም የሚደረገው ሕገወጥ ስብሰባ ነው” በሚል ለፖሊስ በማመልከታቸው ፖሊስም የቦንድ ሽያጩ አይደረግም ሲል ቃል ገብቷል።

ሕዝቡ ፖሊስ የቦንድ ሽያጩ ተሰርዟል ቢላቸውም ማረጋገጫ የለንም በሚል በአካባቢው የሚገኝ ሲሆን ብጥብጡን ተከትሎ በሴንት ፖል ፖሊስ ታስረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን ወዲያው ተለቀዋል።

የኢሕአዴግ መንግስት በሚኒሶታ የአባይ ቀን በሚል ቦንድ ለመሸጥ የተከራየው የላኦ ኮምዩኒቲ አዳራሽ አድራሻ 320 University Ave W St Paul, MN 55103 ነው።

ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ከፎቶ ግራፍ እና ቪድዮዎች ጭምር ይዛ ትመለሳለች።

ይጠብቁን፤ ይመለሱና ይመልከቱን።

Short URL: http://www.zehabesha.com

በኢትዮጲያ የተምሳሳይ ጾታ ተጋቢዎች መብት እንዲከበር እሰራለው

sa
ፕሬዘዳንት ኦባማ አዲስ አምባሳደር በኢትዮጲያ ሾመዋል። ፓትሪሻ ሀስላች ሲባሉ እኚሁ አምባሳደር ልዩ የዲፕሎማሲያዊ ስራዎች እንደሚያከናውኑ ይጠበቃል።

እናም ከመምጣቷ በፊት አሳካቸዋለው ብለው ለጋዜጠኞች ከገለጻቸው ነገሩች ውስጥ አንዱ ትኩረት ስቧል።

ትምህርት እንዲስፋፋ ትምህርት እሰጣለው ወይም የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል አረጋለው እንዳይመስልህ።

እሳቸው ያሉት በኢትዮጲያ የተምሳሳይ ጾታ ተጋቢዎች መብት እንዲከበር መቀነቴን ጠበቅ አድርጌ እሰራለው ነው ያሉት።

ቁም ነገር መፅሄት

ሰበር ዜና ከፍቼ

33
አንድነት ፓርቲ በፍቼ ከተማ እያካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በአማርኛ በኦሮሚኛ መፈክሮች እየተስተጋቡ ነው ፡፡ “የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ” ፣ “መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቁም” ፣ “ሙስና ስርአቱ መገለጫ ነው”፣ “ውሸት ሰለቸን” “የፀረሽብር ህጉ የህገመንግስት ጥሰት ነው” የሚሉና ሌሎችም ይገኙባል፡፡ – See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5454#sthash.nYMicm5k.dpuf

ሰበር ዜና ከባሌ ሮቤ

33
የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መንግስት በባሌ ሮቤ ያሰበውን የደም ማፋሰስ ሴራ አክሽፈዋል፡፡የአከባቢው ባለስልጣናት ያደራጇቸው ሀይሎች ሰልፉ በሚካሄድበት ወቅት ግጭት ለፈጥሩ ተዘጋጅተው እንደነበር ታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ አመራሮች በሳል ውሳኔና ሀገር ወዳድ የባሌ ዞን የፖሊስ አካላት ለፓርቲው በሰጡት መረጃ መንግስስታዊ ውንብድና ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ – See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5452#sthash.ZTx7iJYR.dpuf

የባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አፈና ተፈፀመበት

33
አንድነት ፓርቲ ዛሬ በባሌ ሮቤ የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኦህዴድ ባለስልጣናትና በደህንነት ሀይሎች አፈና ተፈፀመበት፡፡ ሰልፉን ለማደናቀፍ የአካባቢው ባለስልጣናት ትላንት ምሽት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ካረፉበት ታይታኒክ ሆቴል ንብረታቸውን ሳይዙ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጉም በላይ አብዛኞቹ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ታግተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ደህንነት አደጋ ላይ እንደሆነም ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መንግስት ያደራጃቸው ሀይሎች ሁከት ለመፍጠር መዘጋጀታቸው በመታወቁ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ሰልፉ እንዲሰረዝ ወስኗል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UD – See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5450#sthash.kPEOp5su.dpuf

Oromo rights activist dies in Kaliti jail

bbb
Sunday, August 25, 2013
OPride) – Engineer Tesfahun Chemeda, a fierce Oromo rights advocate and a former UNHCR recognized refugee, died yesterday of undisclosed cause at Kaliti prison, where he was serving a life sentence under concocted charges of plotting to overthrow government, reports said.

Chemeda was nabbed along with a close friend Mesfin Abebe in 2007 from Nairobi, where they lived as refugees since 2005, by Kenyan anti-terrorism police and was later deported to Ethiopia, according to Oromia Support Group (OSG), a UK-based human rights organization.

“The two men were picked up in a restaurant by Kenyan anti-terrorist police on 27 April 2007 and taken to Kamukunji police station, where they were held overnight before being transferred to Giriri police station,” OSG wrote in 2010 press release.

The duo were subsequently visited by UNHCR and members of the FBI in Kenya who assured them that “they would not be deported,” according to OSG reports and activists who were advocating for their release at the time.

“I had an opportunity to meet with Kenyan anti-terrorism head, inspector Francis Wanjiru, and an FBI agent,” wrote Raajii Gudeta, 31, in an email to OPride from Edmonton, Canada where he now lives. “Both the FBI and Kenyan official told me that they [Chemeda and Abebe] were not terrorists. We don’t have any business with them but the Ethiopia government need them badly.

On May 9, 2007, during a court hearing, Kenyan officials told a local judge the two were already “sent back to Ethiopia to face terrorism charges,” citing a doctored “Laissez Passer from the Ethiopian embassy, dated 1 May, which had obviously been backdated as that day was a public holiday,” according to OSG.

Efforts by members of the Kenyan Oromo community, Kenyan Human Rights Commission, and the UNHCR to prevent their refoulement went to no avail, according to Sori Fengor, 43, of Minnesota, who knew and lived with Chemeda at the time. Chemeda and Abebe were held incommunicado until December 2008 when they were formally charged in Ethiopian court.

“The last time I saw Chemeda was on May 10 2007 at Muthaiga police station,” wrote Gudeta, who worked as a Community Development Officer for the International Rescue Committee at the time. “After I dropped off food and water for them, Tesfahun saw me crying and grabbed a copy of the Daily Nation newspaper and slapped me saying, ‘we will be handed over to the Woyane [Ethiopian] regime, forget about us and focus on organizing the Oromo youth so that the Oromo struggle can reach its final destination.’”

Chemeda was accused of being an activist with the outlawed Oromo Liberation Front (OLF), an organization formed in 1973 to fight for self-determination of Oromo people in Ethiopia. A three-judge panel at Ethiopia’s federal court latersentenced Chemeda to life in prison without parole in April 2011.

Fifteen other Oromo co-defendants received stiff prison terms while Abebe was sentenced to death. The Oromo are Ethiopia’s single largest ethnic group, comprising more than 40 percent of the country’s population. There are an estimated 20 to 30,000 Oromo political prisoners in Ethiopia.

Chemeda was born in the East Wollega zone of Oromia region near Guduru district. He attended Shambu High School before joining Addis Ababa University’s School of Civil and Environmental Engineering. Following his graduation in 2001 from Addis Ababa University, Chemeda, a civil engineer, worked for Ethiopian Road Transport Authority.Chemeda sought asylum in Kenya sometime in 2005 following harassment and intimidation at the hands of Ethiopian security and road transport administration officials, his acquaintances said.

Early Saturday afternoon when the news of Chemeda’s death broke on social media, activists changed their profile pictures to his photo and wrote to express their grief and condolences. Many remembered Chemeda as a humble, soft-spoken rational thinker, and strategic leader.

Other acquaintances reached by OPride remembered Chemeda for his relentless advocacy and commitment to Oromo people’s freedom. Many Oromo refugees in Kenya knew him in 2005 and 2006 through his role in the now defunct East African Oromo Students’ Association and efforts to organize Oromo refugees in Kenya.

Chemeda’s involvement in Oromo student activism dates back to early 2000. “I went to Menelik Hospital with Chemeda to collect the corpse of Simee Tarafa, an Oromo student who was mysteriously killed in 2001 while attending Mekelle University in Ethiopia’s Tigray region,” recalled Geresu Tufa.

“Before that I worked closely with Chemeda in a 12-member Oromo students committee set up to organize a nationwide campaign to extinguish a forest fire in Bale and Borana regions.” Chemeda was instrumental in signing up over 3000 volunteers and about 480 students dispatched to put out the forest fire, according to Tufa.

Chemeda has been in solitary confinement at Kaliti prison for nearly two years after he was transferred there from Ziway, according to family sources. Early reports about the circumstances of his death are unclear. Some suggest that Ethiopian officials murdered him because they could not break his spirit even after years of torture. Others say authorities are unofficially claiming that he committed suicide.

Chemeda’s sister, the only visitor he had seen for years, was denied the body on Saturday pending “further medical examination,” according to Gudeta. She had seen him earlier this week and reported no changes in his attitude or demeanor.

source,,,http://addisvoice.com/2013/08/ormo-rights-activist-dies-in-kaliti-jail/

Eyob Mekonen Biography – Facts, Birthday, Life Story

111

አሠሪዎችና ዳያስፖራዎች በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይስተናገዱ ታዘዘ

23
-እስካሁን 72 ማኅበራት ብቻ ተመዝግበዋል

ለሠራተኞቻቸው የመኖሪያ ቤት ለመገንባት ፍላጎት ያላቸው የግል ድርጅቶች፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችና በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝርዝር መመርያ ከመውጣቱ በፊት፣ በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ፕሮግራም ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይስተናገዱ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ የግል ድርጅቶችና ዳያስፖራዎችን ለማስተናገድ ራሱን የቻለ ዝርዝር መመርያ ያስፈልጋል በማለት ነው ሰሞኑን ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው፡፡

መንግሥት የነዋሪዎችን የመኖርያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ካቀረባቸው ፕሮግራሞች አንዱ የመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር ነው፡፡ ለዚህ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የወጣው መመርያ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችና የግል ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው የጋራ መኖርያ ቤት ለመገንባትና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በማኅበር ተደራጅተው ቤታቸውን እንዲሠሩ ይፈቅዳል፡፡ ነገር ግን ከሁለት ሳምንት በፊት የከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በከተማው ውስጥ የራሳቸውን ቤት የመገንባት አቅም ያላቸው ተደራጅተው እንዲቀርቡ የተዘረጋውን መርሐ ግብር ይፋ ሲያደርግ ችግሮች መታየት ጀምረው ነበር፡፡

በወቅቱ አሠሪ መሥሪያ ቤቶች ለሠራተኞቻቸው መኖርያ ቤት የሚያስገነቡላቸው ከሆነ፣ በአሠሪ ድርጅቶች የተረጋገጠ የአባላት ዝርዝርና የግንባታውን 50 በመቶ ክፍያ በዝግ ሒሳብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ ቀሪውን 50 በመቶ ማኅበሩ መሬት ሲያገኝ አሠሪ ድርጅቶች ክፍያ የሚፈጽሙ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ያቀርባል ይላል መመርያው፡፡

ከዚህ ባሻገር አሠሪው ለእያንዳንዱ ሠራተኛ ወይም የማኅበር አባል ለቤቱ የሚከፈል የገንዘብ መጠን፣ የመረጠውን የቤት ዓይነት፣ ስፋት፣ የመኝታ ቤት ብዛትና ጠቅላላ ዋጋ የያዘ ሰነድ፣ እንዲሁም አሠሪው 50 በመቶ የከፈለበትንና ቀሪውን 50 በመቶ ማኅበሩ መሬት ሲረከብ የሚፈጽም መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ አሠሪው መሥርያ ቤት በሚገኝበት ክፍል ከተማ በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ስም ለኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

እነዚህ ሁለት የመመርያው አንቀጾች በአሠሪው መሥርያ ቤትና በሠራተኛው መካከል የመኖርያ ቤቱ ካርታ በማን ስም ሊሆን ነው የሚል ጥያቄና ውዝግብ እንዲነሳ አድርገዋል፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር ምንጮች እንደሚሉት፣ በመኖርያ ቤት ፕሮግራሙ መመርያ ላይ አሠሪ መሥርያ ቤቶችና ሠራተኞች እንዴት እንደሚተሳሰሩ የተቀመጠ ነገር ባለመኖሩ፣ የከተማው አስተዳደር ጉዳዩ በድጋሚ መታየት አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

ዳያስፖራን በተመለከተ መንግሥት ዳያስፖራው በኅብረት ሥራ ማኅበራት ተደራጅቶ መኖርያ ቤቱን የሚገነባበት አሠራር ለመንደፍ በቅድሚያ ዝርዝር መመርያ ማውጣት ማስፈለጉ ታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰሜን አሜሪካ ለሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ማስታወቂያ እያስነገረ ነው፡፡

ማስታወቂያው በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የግል አፓርታመንትና በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት የመኖርያ ቤት ፈላጊዎች የማስፈጸሚያ መመርያ እየተዘጋጀ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በዚህ መሠረትም መመርያው ሲጠናቀቅ በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር ለሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ምዝገባው በተቀናጀና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ እንዲከናወን ውሳኔ ተላልፏል ብሏል፡፡ ይህም በመሆኑ በኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘው የዳያስፖራው ምዝገባ ቆሞ በአገርም ሆነ በውጭ በሚሲዮኖች አማካይነት የሚደረገው ምዝገባ በተመሳሳይ ጊዜ ከጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለነዋሪዎች ይፋ ያደረገው የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ እየተገባደደ ቢሆንም፣ የማኅበር አደረጃጀቱ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ በካቢኔው እየታየ የመመዝገቢያ ቀን እንዲራዘም መመርያ ሰጥቷል፡፡ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም በማኅበራት የተደራጁ ግለሰቦች በድጋሚ በአዲሱ መመርያ መሠረት 16 እየሆኑ እንዲደራጁ፣ አዳዲስ ማኅበራት ደግሞ 24 እየሆኑ እንዲደራጁ አስታውቋል፡፡

ምዝገባው ከተጀመረ ሦስት ሳምንት ቢሆነውም የተመዘገቡት 72 ማኅበራት ብቻ መሆናቸውን የከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽሰማ ገብረ ሥላሴ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፕሮግራም ከአሥር ሺሕ ሰዎች በላይ በማኅበር ይደራጃሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ በ72 ማኅበራት ውስጥ የተደራጁ 1,680 ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ እስካሁን ነባር ማኅበራት መደራጀት አለመቻላቸው ታውቋል፡፡ ምንጮች እንደሚገልጹት፣ ቀደም ሲል በማኅበር ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት በነፍስ ወከፍ የሚፈለገው ስምንት ሺሕ ብር ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ቤት የመገንቢያው ገንዘብ በቅድሚያ ባንክ ገቢ የሚደረግ በመሆኑ የቀድሞ ተመዝጋቢዎች ወደኋላ እያፈገፈጉ ነው ተብሏል፡፡

ethiopian reporter

ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በቃሊቲ እስር ቤት ሕይወቱ አለፈ

bbb
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የሰብአዊ መብት ታጋይና መንግስትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል ሕይወቱን በሙሉ በእስር ቤት እንዲያሳልፍ የተፈረደበት ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በቃሊቲ እስር ቤት ሕይወቱ ማለፉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገቡ።
እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ኢንጂነር ተስፋሁን ሕይወቱ ያለፈው ትናንት ሲሆን ለሕይወቱ ማለፍ የተገለጸ ምክንያታዊ በሽታም ሆነ ሌላ ነገር አልቀረበም።
በኬንያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስደተኛ አድርጎ ወረቀት የሰጠው ቢሆንም የኢሕአዴግ መንግስት ከኬንያ ድረስ ስደተኛውን ኢንጂነር ተስፋሁን ወደ ሃገር ቤት አምጥቶ ያሰረው ሲሆን ሕይወቱን ሙሉ በ እስር ቤት እንዲያሳልፍ ተፈርዶበት ላለፉት 6 ዓመታት በ እስር ቤት መቆየቱ ታውቋል።

በዚህ ዜና ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ይዘን እንቀርባለን።

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6664

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

jk

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በስተጀርባ በበቀለኝነታቸውና የጥፋት ሴራ በማቀነባበር የሚታወቁት ስብሃት ነጋ እንዳሉበትና ከኤፈርት ስልጣናቸው ያስነሷቸውን አዜብ ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ ባለፈ በሙስና እንዲጠየቁ በየአቅጣጫው ጫና እያሳደሩ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል። በአዜብ ተፈፀሙ ተብለው ከተነሱት የሙስና ወንጀሎች በኤፈርት ስም 200 ከባድ ተሽከርካሪዎች አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ቀረጥ ሳይከፍሉ እንዲያስገቡ ማድረጋቸውን፣ በሚሊዮን የሚገመት ቀረጥ ሊከፈልባቸው የሚገቡ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ በኤፈርት ገንዘብ ሶስት መርከብ ስሚንቶ የፍራንኮ ቫሉታን ሕግ በመተላለፍ ቀረጥ ሳይከፈልበት አገር ውስጥ መግባቱ፣ ክሶች እንዲቋረጡ ትእዛዝ በመስጠት..የሚሉት በዋነኛነት መነሳታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ( አዜብ ከኤፈርት እንደሚነሱ ከዚህ ቀደም በወጡ ዘገባዎች ምንጮችን በመንተራስ መገለፁ ይታወሳል)
ይህ በእንዲህ እንዳለ – በአዜብ ቦታ የተተኩት ብርሃነ ኪ/ማርያም (በቅፅል ስማቸው ብርሃነ “ማረት”) ሲሆኑ፣ ከመለስ በፊት የአዜብ ፍቅረኛ የነበሩና ከሱዳን ተያይዘው በመምጣት ሕወሐትን እንደተቀላቀሉ ምንጮች አስታውሰዋል። ድርጅቱን ከተቀላቀሉ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለቱ (አዜብና ብርሃነ) የፍቅር ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ ከበላይ አመራር መወሰኑን፣ አዜብ ከመለስ ጋር ግንኙነት መቀጠላቸውን ይገልፃሉ። ፓርቲው ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ብርሃነ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ተመድበው ሲሰሩ «ለመንገድ ስራ ከተመደበ ገንዘብ አምስት ሚሊዮን ብር ተዘርፏል» በሚል በሙስና እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል። አዲስ አበባ የመጡት ብርሃነ ብዙ ጥረት አድርገው አዜብ ዘንድ (ቤተ መንግስት) የመግባት አጋጣሚ ያገኛሉ። ባቀረቡት አቤቱታና ተማፅኖ መሰረት ሲቪል ሰርቪስ እንዲገቡ አዜብ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። ከኰሌጁ እንደወጡ የማ.ረ.ት. ሃላፊ ተደርገው በመለስ የተሾሙት ብርሃነ፣ በተለይ ከ1993ዓ.ም በኋላ የመለስ ቀኝ እጅ በመሆን በአውሮፓና አሜሪካ ያለውን የፓርቲውን መዋቅርና ስለላ በመምራት፣ አምባሳደሮችን በማስፈራራት፣ በማዘዝና ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ በማሳለፍ ታማኝ አገልጋይ ሆነው እንደቆዩ ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሞት በኋላ ግን የስብሃት ነጋ ተከታይና አስፈፃሚ በመሆን አሰላለፋቸውን ቀይረው እንደቀጠሉ አያይዘው ገልፀዋል። ስብሃትና ብርሃነ ዝምድና እንዳላቸው የጠቆሙት ምንጮች፣ አዜብን በማስነሳት ብርሃነ እንዲቀመጡ ያደረጉት ስብሃት መሆናቸውን አመልክተዋል።

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6659

Post Navigation