addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “October 12, 2013”

ወያኔ በእሳት የተቃጠሉ አብያተ ቤተክርስቲያናት ለፖለቲካ ፍጆታ አየተጠቀመ ነዉ

33
ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ አዋበልና አነደድ በሚባሉ ወረዳዎች የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ ባለው የአምስት ወር ጊዜ ዉስጥ በእሳት ተቃጥለው መዉደማቸዉንና በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳትና መጽሐፍትም የእሳቱ ሰላባ መሆናቸዉን ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ የሚገኙ የዜና ወኪሎቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። በቃጠሎዉ እጅግ ያዘኑት የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል የቃጠሎዉ ምክንያት ባስቸኳይ ተመርምሮ በወንጀለኞቹ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ ጆሮ እንዳላገኙ ዘጋቢዎቻችን አክለዉ የላኩልን ዜና ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱ ታዉቋል፡፡

በአንድ አካባቢ ብቻ በተለያየ ጊዜ አብያተ ክርስትያናት በተደጋጋሚ ሲቃጠሉና ንብረት ሲወድም በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኋን አንድም ቀን አለመዘገቡ ወንጀሉ የመንግስት እጅ እንዳለበት በግልጽ ያሳያል ሲሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። ይህንን ጉዳይ በሚመለከት ዘጋቢያችን ያናገራቸዉ አንድ የምስራቅ ጎጃም የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ሰራተኛ አብያተ ቤተክርስቲያናቱ መቃጠላቸውን አረጋግጠዉ በቃጠሎው የተነሳ በህዝብና በመንግስት በኩል እንዲሁም በህዝቡና በቱሪዝም ኮሚሽን በኩል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን ተናግረዋል። መንግስት ድርጊቱን የፈጸሙት የሙስሊም አክራሪዎች ወይም የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው ሲል፣ ህዝቡ ደግሞ አክራሪዎች አይደሉም በማለት እየተከራከረ መሆኑን ሰራተኛው ጨምሮ ገልጿል። የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤትም የችግሩ መነሻ በውል ባይታወቅም በአክራሪዎች ምክንያት እንዳልሆ በውል እንደሚያምን አክለው ገልጸዋል።

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አክራሪነትና ሽብረተኝነት ላይ ስልጠና እንዲወስዱ እያስገደደ ነዉ

33
እሱ እራሱ ሽብርተኛ የሆነዉ የወያኔ አገዛዝ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት ስለ አክራሪነት፤ ሽብርተኝነትና ጸረ ሰላም እያለ ስለሚጠራቸዉ ኃይሎች መስጠት የጀመረዉን ስልጠና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ለመስጠት ማቀዱ ተሰማ። የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ዘረኝነት፤ ሙሰኝነትና የሰብዓዊ መብቶች መደፍጠጥ መሆኑን በዉል ለሚረዳና የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ምንጭ ደግሞ ወያኔ መሆኑን ለተገነዘበ ህዝብ ወያኔ አክራሪነትና ሽብርተኝነት በሚል ስልጠና መስጠት መጀመሩ ህዝቡ ልቡ እንዲሸፍት ከማድረግ ዉጭ ምንም ዉጤት የማይኖረዉ ከንቱ ድካም መሆኑን አንዳንድ የወያኔ አባላትን ጨምሮ ብዙዎች ይስማሙበታል። በተለይ እንዲህ አይነት ስልጠና ለህጻናት ጭምር መሰጠቱ ብዙዎችን አስቆጥቷል። ለምሳሌ ከሁለት ሳምንት በፊት በክልል ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችና መምህራን ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት፣ በርካታ ተሳታፊዎች እድሜያቸው ከ15 አመታት በታች የሆኑ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዳይወስዱ ጠይቀው ነበር።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ተማሪዎች ባለፈው አርብ እና ቅዳሜ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ወደ ግቢ በገቡበት ሰአት፣ ምዝገባ ቆሞ ተማሪዎች ስድስት ኪሎ ወደሚገኘው የስብሰባ ማእከል እንዲያቀኑ ከታዘዙ በኋላ በአዉቶቡሶች እየተጫኑ ወደ ስልጠና ቦታ ተወስደዉ ያለፍላጎታቸዉ ቀኑን ሙሉ ስልጠናዉን ሲከታተሉ ዉለዋል። በስልጠናዉ ወቅት የወያኔ ካድሬዎች ለአገዛዙ አደጋ ይፈጥራሉ ብለዉ ያመኑባቸዉን እንደ ግንቦት7፣ ኦነግና ኦብነግ የመሳሰሉትን ድርጅቶች በጸረ ሰላምነትና በአሸባሪነት እንደምሳሌ ተጠቅመዉባቸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ ለሚሰጠው ስልጠና የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ለ10 ቀናት ተዘግተዋል። በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው።

አገልግሎት ፈላጊዉ ህዝብ ጉዳዩን ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ ባለስልጣናቱ ስልጠና ላይ ናቸው የሚል መልስ እየተሰጠ ነው። መንግስት በዚህ ስልጠና ምን ለማግኘት እንዳሰበ በግልጽ ባይታወቀም ስልጠናው ወደ ወረዳዎች ሁሉ ይዘልቃል ተብሎአል። እስካሁን ድረስ በስብብሰባው ላይ የሚቀርቡት አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛው ተሰብሳቢ በኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት አለ ብሎ አያስብም። ይህ ደግሞ ወያኔን ክፉኛ እንዳስደነገጠዉ ለማወቅ ተችላል።

መብቱን ለማስከበር ታስሮም እንደማያጎበድድ በእስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አረጋገጠ

33
ፋሽስት ወያኔ ባቀነባበረው የውሸት ክስ በሽብርተኝነት ተከሶና በወያኔ አሻንጉሊት ዳኞች እድሜ ልክ ተፈርዶበት ቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዳለም አራጌ ዛሬም በእስር ቤት ለመብቱ እየታገለ እንደሆነ ተገለጸ። በውጭ ያሉት የተቃውሞ ሃይሎች መሰባሰብና እየተጠናከሩ መምጣት ሰላም የነሳው ፋሽስት ወያኔ በሀገር ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባለው የፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ ላይ ዛቻ እንዲያሰማ እንዳደረገው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው እንግዲህ ፋሽስት ወያኔ ለአቶ አንዷለም አራጌ ሰላም በማሰብ በሚል በእስር ቤት የሚጠይቁትን ሰዎች ቁጥር ለመወሰን የፈለገው።

ፋሽስት ወያኔ ከሌሎች የቆዩ እስረኛ ጓደኞቹ ጋር እንዳይገናኝ በማሰብ እስካሁን ድረስ አቶ አንዷለም አራጌን በጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ማሰሩ ሳያንስ ይህን የነጻነት ታጋይ የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር ለመገደብ በመወሰን እነማን እንዲጎበኙት እንደሚፈልግ ስም ዝርዝር እንዲያቀርብ ጥያቄ ማቅረቡ አንዷለምን አበሳጭቷል ተብሏል። በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለመብቱ እንደቆመ አስረግጦ በማሳየት ላይ ያለው አንዷለም ግን “መጎብኘት ሕገመንግስታዊ መብቴ ነው ። የስም ዝርዝርም አልሰጥም” በማለቱ የተነሳ ከመስከረም 29 2006 ዓ/ም ጀምሮ ማንም ሰው እንዳይጎበኘው ክልከላ መጣሉን ፓርቲው አንድነት አሳውቋል።

ፖለቲከኛና ሚስማር ሲመታ ይጠብቃል የሚሉ ወገኖች የነጻነት ታጋዩ የሞራል ፅናትና ጥንካሬ ከመቼውም በላይ መድረሱን አድንቀው፤ ፋሽስት ወያኔ የደረሰበት የወረደና የዘቀጠ የፍርሃት ደረጃ ግን በእስር ቤት አጉሮ እያሰቃያቸው ያሉትን የነፃነት ታጋዮች እስካለማመን አድርሶታል ያላሉ። እውነት አስፈሪ ናት የሚሉት እነዚሁ ወገኖች ሕገመንግስታችን የሚሉትን ተረት ተረት እንኳ ሳይቀር ከፋሽስት ወያኔ በተሻለ ሁኔታ የነጻነት ታጋዩ አንዷለም አራጌ አሳምሮ እንደሚያውቀውና እያከበረው መሆኑን የሚያውቀው ሕሊናቸው ጫፍ ከሌለው ፍርሃት ውስጥ እንደከተታቸውም ጨምረው ጠቁመዋል።

በወያኔው ብአዴን ውጥረት የነገሰበት ግምገማ ከ 170 በላይ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ እንዳስገቡ ተጠቆመ

33
ሁልጊዜም በያመቱ የአባላት ግምገማ (በሂሳብ ሰዎች አጠራር የሰዎች ኢንቬንተሪ) የሚያካሂደው ፋሽስት ወያኔ፤ የታመመ፣ የደከመ፣ ተነሳሽነት የጎደለው እንዲሁም ሌላል ሌላም በሚል ሰበብ፤ የፖለቲካ አቋም መስመራቸውን ያላስተካከሉ የሚላቸውን እንደሚቀጣ ይታወቃል። በዚህ መሰረትም ብአዴን የሚባለው የወያኔው አንዱ አንጃ ኪራይ ሰብሳቢነት በሚል አጀንዳ የጀመረው ግምገማ ከፍተኛ ውዝግብና መተረማመስ ከመፍጠሩም በላይ በስብሰባው የተገኙ አባላት በብአዴንና በወያኔው አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

“ባይናችን እያየነውና እየሰማነው ካለው በአገዛዙ ሹመኞች የሚከወን ንቅዘት አንጻር እኛን እስክርቢቶ ወሰዳችሁ እያሉ መገምገም ፌዝ ነው” ያሉት የግምገማው ተሳታፊዎች “በሚሊዮን ዶላር በሚቆጠር መጠን ወደ ውጭ ሀገራት ባንኮች የሚወጣውን ሃብት መቆጣጠር የተሻለ ነበር” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል። አክለውም “ልጆቻችንን በቅጡ ለመመገብና ለማሳደግ ካቃተን አባላት ላይ የአባልነት ክፍያ እያለችሁ ትሰበስባላችሁ ሌላው ግን አገዛዙ የቸረውን የአገዛዝ ቦታ ተጠቅሞ ከሕዝብ በዘረፈው ሃብት ሶስትና አራት ሕንጻዎችን ሲገነባ የሚናገረው የለም፤ እኛም መረረን መኖር አቃተን በዚሁ ሳቢያም አባላት መልቀቂያ እያስገቡ ነው ብለዋል።”

ከ15 ሺ በላይ የኢህአዴግ አባላት መልቀቂያ አስገቡ

1111111111111
ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ እያካሄደ ባለው የአባላት ግምገማ ወቅት ከ15 ሺ በላይ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማስገባታቸው ይፋ ተደርጓል።

ስራቸውን ከሚለቁበት ምክንያቶች መካከል በድርጅቱ አመኔታ ማጣት ፣ ተገቢውን አገልግሎት ክፍያ አለማግኘት፣ ለድርጅቱ የሚከፍሉት ገንዘብ ከፍተኛ መሆን እና የድርጅቱ አባላት ሹመት በወገን መሆኑ የሚሉት ተጠቅሰዋል።

ከፍተኛ የአባላት መልቀቂአ ቁጥር ከተመዘገበባቸው ክልሎች መካከል ኦሮሚያ በ9 ሺ 4 መቶ 56 አንደኛ ሲሆን ፣ አማራ፣ ደቡብ ክልል እና ትግራይ በተከታታይ ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል። በትግራይ በ2005 ዓ/ም 1 ሺ 1 መቶ 13 ሰዎች የህወሀት አባላት መልቀቂያ አስገብተዋል።

ኢህአዴግ 5 ሚሊዮን አባላት እንዳሉት ቢነገርም ፣ በንቃት የሚሳተፉት 2 ሚሊዮነቹ ብቻ ናቸው ተንብሎአል። ከእነዚህ መካከል 20 ሺ የሚሆኑት በስም ብቻ አባላት ተብለው ቢመዘገቡም፣ በአካል የሌሉ መሆናቸውም ተገልጿል።

በስብሰባው አብዛኞቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለደሞዝና ለስራ ሲሉ አባል እንደሚሆኑ የተገለጸ ቢሆንም በአለፉት አመታት ድርጅቱን ከተቀላቀሉት ተማሪዎች መካከል ስራ አገኙት ሩብ አይሆንም ተብሎአል።

በክልል ዋና ዋና ከተሞች በአዋሳ፣ ባህርዳር፣ እና መቀሌ ውጤት ያላቸው ተመራቂዎች ስራ ሳይዙ፣ ውጤት የሌላቸው የድርጅቱ ነባር አባላት በተቃራኒው ስራ መቀጠራቸው በአባላቱ ላይ ቅርታ እንዲፈጠር አድርጎአል ተብሏልም ።

ዛሬ ስራ ማግኘት የህልም እንጀራ ነው ያሉት አባሎች፣ ዲግሪ ይዘው ስራ ለማግኘት ከሶስት እስከ 4 አመታት የሚጠብቁ ተመራቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ኢህአዴግ መልቀቂያ ያቀረቡ አባላቱን ጥገኞች ሲል ሰይሞአቸዋል። የድርጅቱ አባላት ለኢሳት እንደገለጹት አብዛኞቹ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች በሙስና የተዘፈቁ ናቸው። ኢሳት በሚቀጥለው ሳምንት <> በሚል የብአዴን የአመራር አባላት ሙስናን በተመለከተ የላኩትን ደብዳቤ ይፋ እንደሚያደርግ ለመግለጽ ይወዳል።

በተመሳሳይ ዜናም አክራሪነትና ጽንፈኝነትን አስመልክቶ ስልጠና ለመስጥት የፈዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ትናንት ያደረገዉ ስብሰባ ያለዉጤት ተበትኗል።

መንግስት ንጹሀንን ያለምንም መረጋገጫ አክራሪ አሸባሪ ብሎ መፈረጁ ግዜ ያለፈበት ነው”ያሉት የስብሰባው ተሳታፊዎች፤”በመንግስት እየተባለ ያለውን ነገር+ እንኳን የዩንቨርስቲዉ ማህበረሰብ ፤ሳይማሩ እያስተማሩ ያሉት እናት አባቶቻችንም አይቀበሉትም “ብለዋል።

ተማሪዎችና መምህራን በማከልም፦”የመረጃ ምንጫችን ኢቲቪ ብቻ ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችሗል” በማለት የመንግስት ባለስልጣናትን ሞግተዋቸዋል።

“ጽንፈኛ” የሚለዉ ቃል በባርያ ፍንገላ ግዜ በባሪያ አሳዳሪዎች ላይ ያምጹ ለነበሩ ግለሰቦች የተሰጠ ስያሜ ነው በማለት የተናገሩት አንድ ክርስቲያን የሆኑ የስብሰባው ታዳሚ፤ “መንግስት የእስልምና ሐማኖት ተከታዮች በክርስቲያኑ ላይ ጦርነት ሊያዉጁ ነው ብሎ ቢናገር ፤ህዝበ ክርስቲያኑ አይቀበለውም”ብለዋል።

ግለሰቡ አስተያየታቸውን ሲያጠቃልሉም፦ኢትዮጵያ ዉስጥ አክራሪ አለ ማለቱ አለማቀፋዊ እዉቅናን ያላገንኘና ተዓማኒት የሌለዉ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ቢ.ቢ.ኤን ዘገባ፤በስብሰባው ላይ በዩንቨርሲቲዉ ሶላትና ሂጃብን አስመልክቶ እገዳ ለማድረግ እቅድ እንዳለ የቀረበው ሃሳብ በሁሉም ተሳታፊዎች ከፍ ያለ ተቃውሞ ገጥሞታል።

“ኢትዮጵያን ልክ እንደ አፍጋኒስታንንና ፓኪስታን ችግር ያለባት ማስመሰሉ ተገቢ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎ ያለ በመሆኑ ያንዱ ወገን ሐይማኖት መከበር ለሌላዉ ስጋት አይደለም፤”ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ ሰዎችአለባበሳቸዉን ከቀየሩ አመለካከታቸዉን ይቀይራሉ ማለቱ ስህተት ስለሆነ “ሀይማኖታዊ አለባበስ ከዩኒቨርሲቲ በር መልስ”የሚለው ሃሳብና እቅድ ተቀባይነት የለውም”ብለዋል።

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሐረማያ ዩኒቨርስቲ” አክራሪነትንና አሸባሪነትን” አስመልክቶ ባዘጋጀዉ በዚህ ስልጠና ላይ እስከ አስራ ሁለት ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

ይሁንና በርካታ ተማሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀርቡትን ሐሳብ ፊት ለፊት በንግግር ከመቃወማቸውም በላይ ስብሰባዉን ረግጦ ወጥተዋል።

በጎጃም ሶስት ወረዳዎች የሚኖሩ ሕዝቦች መንግስትን አስደነገጡ

ff
(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ጎንቻ ሲሶ፣ ሁለት እጁ እነብሴ እና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ሰሚ ያጣ ህዝብ በሚል መንግስት ጥያቄዎቻችንን ባስቸኳይ ካልመለሰልን የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡ በተለይ ነዋሪዎቹ ቢቸና፣ደጀን፣ሞጣ ባህርዳር ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ለማስራት ከዚህ ቀደም የሞቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ቃል ቢገቡም እስካሁን አልተሰራም፤ አሁን ደግሞ የመንገድ ግንባታው ተሰርዟል ተብለናል በሚል መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ማታ በወረዳዎቹ ከተሞች ላይ በራካታ መፈክሮች ያሉት ፖስተሮችን ለጥፈው አድረዋል ሲል የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ዘግቧል።

በደል የወለደው ቁጭት በሚል ርዕስ ግብር ያለልማት ብዝበዛ ነው፣አንድ መንግስት መንገድ ለመስራት ስንት ዓመት ይፈጅበታል፣ የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በርካት ጥያቄዎችንም ማንሳታቸው ታውቋል፡፡ይህንም የአካባቢው አመራሮች መስከረም 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት አይተው በመደናገጥ ፖስተሮችን ያስቀደዱ ሲሆን፤ ህዝቡ አሁንም ጥያቄያችን ካልተመለሰ በአካባቢያችን ያሉ ትምህርት ቤቶች፣ ሶቆችና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተዘግተው የተቃውሞ ሰልፍ እንወጣለን ሲሉ በማስጠንቀቃቸው እስካሁንም በአካባቢው ውጥረቱ አይሏል፡፡ በዚህ ጉዳይ የአካባቢውን ባለስልጣናት ዘሐበሻ ለማናገር ያደረገችው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኝት ጸሎት አደረጉ

ff
(አንድ አድርገኝ ጥቅምት 2 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ነገ ጥቅምት 3 2006 ዓ.ም ከናይጄሪያ ብሐየራዊ ቡድን ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ትላንትና አርብ አመሻሹ ላይ ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመሄድ አምላክ ድሉን እንዲያጎናጽፋቸው ጸሎት አድርገው ወደ ማረፊያቸው ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ተመልሰዋል ፡፡ ከሳምንት በፊት ዴቪድ ማርክ የተባሉ የናይጄሪያ ሴናተር መላው ናይጄርያዊ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን ጨዋታ ለማሸነፍ እንዲያበረታታ በካቶሊክ አማኞች ለ9 ቀናት የሚዘልቅ የፀሎት ስነስርዓት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካቶች በአዲስ አበባ እና በበርካታ ክልል ከተማዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ማሊያ ፤ ስካርፍ እና እጅ ላይ የሚደረጉ ማጌጫዎችን በመግዛት ቡድኑን ለመደገፍ ከፍተኛ ዝግጅቶችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ባሳለፍነው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ቡድን አንዲት ጎልን ብቻ አግብቶ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጎሏ መገኛ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጅ 19 ቁጥር በመልበስ የሚጫወተው አዳነ ግርማ መሆኑ አይረሳም፡፡

የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ

andadirgen.org

በአረብ አገራት፣ ኢትዮጵያውያን ቦንድ ለመግዛት እንደተገደዱ ገለፁ

በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች እና በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የኤምባሲና የቆንፅላ ፅ/ቤት አገልግሎቶችን ለማግኘት የሕዳሴ ግድብ ቦንድ እንድንገዛ እየተገደድን ነው አሉ፡፡ “ሁሉም ስደተኛ ተሰብስቦ ያሳለፈው ውሳኔ ስለሆነ የግድ ቦንድ መግዛት አለባችሁ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ስደተኞቹ ተናግረዋል፡፡ በአባይ ወንዝ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተስማማበት ፕሮጀክት እንደመሆኑ፣ እኛም ድጋፋችንን በተለያየ መንገድ በመስጠት ላይ ነን የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ የገንዘብ መዋጮውና የቦንድ ግዢው የግዴታ መሆኑን ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
የቦንድ ግዢም ሆነ መዋጮ በዜጎች ፈቃደኝነት የሚፈፀም እንደሆነ መንግስት በተደጋጋሚ እየገለፀ መመሪያ ሲያስተላልፍ እንደነበር ያስታወሡት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ይሁን እንጂ በዱባይ እና በሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲዎች ወይም የቆንፅላ ፅ/ቤቶች ግን ፓስፖርት ለማሣደስና ሌሎች አገልግሎቶች ለማግኘት ስንሄድ፣ ቦንድ እንድንገዛ እንገደዳለን ብለዋል፡፡ ለ10 አመታት ከሚኖርበት ከሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ሣምንት ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን የሚናገረው ጀማል አረቦ ኢስማኤል፤ ቢያንስ በ500 ሪያል (ወደ 3ሺ ብር ገደማ) ቦንድ መግዛት አለብህ እንደተባለ ገልጿል፡፡ ቅሬታቸውን ለኤምባሲዎችና ለቆንስላ ፅ/ቤቶቹ አቅርበው እንደሆነ ተጠይቆ ጀማል ሲመልስ፤ ብዙ ስደተኞች በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውን ጠቅሶ፣ መፍትሄ ግን አልተሰጠንም ብሏል፡፡
“ቃል ስለገባችሁ በቃላችሁ መሠረት የቦንድ ግዢውን ፈፅሙ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው አቶ ጀማል ገልጿል፡፡ የቦንድ ግዢ በእያንዳንዱ ሰው ፈቃደኝነትና ውሳኔ እንጂ፣ የተወሰኑ ሰዎች ተሰብስበው ወስነዋል ተብሎ በሁሉም ሰው ላይ ግዴት የሚጫን መሆን የለበትም ብሏል – ጀማል፡፡ “ስንቸገር ዞር ብሎ ያላየንና በችግራችን ጊዜ ያልደረሠልን ኤምባሲ፤ የዜጐችን የላብ ውጤት በአስገዳጅ ሁኔታ መቀማቱ ተገቢ አይደለም” የሚለው ጀማል፤ ሁሉም ነገር በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ይላል፡፡ በሳዑዲ አረቢያ ለ6 አመት የኖረው ሌላው ወጣት በበኩሉ፣ በርካቶች ለቦንድ ግዢ የሚጠየቁትን ክፍያ በመሸሽ ወደ ኤምባሲው አገልግሎት ለማግኘት መሄድ እንደማይፈልጉ ተናግሯል፡፡
“እያንዳንዱ ዜጋ ቦንድ ግዢውን በፍቃደኝነት ብቻ ነው የሚሣተፈው፤ በምንም ሁኔታ አይገደድም” የሚለውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ቃል አስታውሶ፣ አሁን ግን ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም ብሏል፡፡ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ በዱባይ የምትኖር ሌላዋ አንዲት ወጣት፤ ፓስፖርት ለማሣደስ ወደ ቆንፃላ ፅ/ቤቱ ብታመራም 1000 ድርሃም ካልከፈልሽ አገልግሎት ማግኘት አትችይም መባሏን ገልፃለች። 500 ድርሃም ለቦንድ ግዢ ሲከፈል ቀሪው 500 ደግሞ ይህን ጉዳይ ለማስፈፀም ለተቋቋመው ኮሚቴ ተብሎ ይከፈላል የምትለው ኢትዮጵያዊቷ፤ ክፍያው ካልተፈፀመ ከማንኛውም የቆንስላ ፅ/ቤት አገልግሎት ማግኘት አይቻልም ብላለች፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ አግኝተን ያነጋገርናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ “ይሄ ስለመፈፀሙ የተጨበጠ መረጃ የለንም፣ ነገር ግን ማስገደድ ተቀባይነት የሌለውና ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡ ተገቢ እንዳልሆነ ከዚህ በፊትም ተነግሯል” ብለዋል፡፡ አክለውም “ይሄ ድርጊት ተፈፀመብን የሚሉም ጥቆማውን ለመስሪያ ቤታችን ማሣወቅ ይችላሉ” ብለዋል፡፡
Source/www.addisadmass.com

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በብራዚል ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ዘፈን እንዲያቀርብ፣ በውድድሩ ዋና ስፖንሰር በኮካኮላ ኩባንያ ተመረጠ፡፡

cx
ታዋቂው የአገራችን ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በብራዚል ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ዘፈን እንዲያቀርብ፣ በውድድሩ ዋና ስፖንሰር በኮካኮላ ኩባንያ ተመረጠ፡፡
እ.ኤ.አ በ2014 ለሚካሄደው የአለም እግር ኳስ ጨዋታ ከሚከናወኑ ዝግጅቶች መካከል ውድድሩን የሚያደምቁ ሙዚቀኞችን መምረጥ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠው ምንጮቻችን የገለፁ ሲሆን፤ ቴዲ አፍሮ መመረጡ ለዘፋኙና ለአገሪቷ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡
ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል ይሆናል ተብሎ እንደሚገመት የገለፁልን እነዚሁ የመረጃ ምንጮች፤ የሙዚቃው ሙሉ ቀረፃ የሚከናወነው በኬንያ እንደሆነ ተናግረዋል። የሙዚቃ ስራው መቼ በይፋ ለሕዝብ ጆሮ እንደሚደርስ በእርግጠኛነት አልታወቀም፡፡ በቅርቡ ዝርዝር መግለጫ ይሰራጫል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው የ2010 የአለም ዋንጫ ዝግጅት ሶማሌያዊው ድምፃዊ ወጣት ኬናን በኮካኮላ ተመርጦ የሙዚቃ ስራውን እንዳቀረበ የሚታወስ ሲሆን፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅናን እንዳተረፈ ይታወቃል፡፡

addis admas

በውኃ ላይ የታነፀው ይምርሐነ ክርስቶስ የ“ወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ የ2014 ተመራጭ መካነ ቅርስ” ሆነ

xx
ከዛጒዌ ስመ ጥር ነገሥታት አንዱ በነበሩት በንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስ ዘመነ መንግሥት ከተሠሩት ኪነ ሕንጻዎች አንዱ የኾነው ይምርሐነ ክርስቶስ፤ የወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ የ2014 ተተኳሪ መካነ ቅርስ (2014 World Monuments Watch) ሆኖ ተመረጠ፡፡
ፈንዱ መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ዋና ጽ/ቤቱ በሚገኝበት በኒው ዮርክ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው÷ እ.አ.አ በ2014 ዓለም በትኩረት ሊያውቃቸው፣ ሊጠብቃቸውና ለትውልድ ሊያስተላለፍላቸው ይገባል ካላቸው የ41 አገሮች ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች መካከል ልዩ የኪነ ሕንጻ ጥበብ የሚታይበት የይምርሐነ ክርስቶስ መካነ ቅርስ አንዱ ኾኖ መመረጡ ተገልጧል፡፡
“ወርልድ ሞኑመንትስ ዎች” በተሰኘው ፕሮግራሙ ለአደጋ የተጋለጡና ዝነኛ የቱሪስት መስሕብ የኾኑ ታሪካዊ ኪነ ሕንፃዎችንና ባህላዊ መካነ ቅርሶችን በማስተዋወቅ፣ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ በመለገሥ ዘመን ተሻጋሪ እንዲኾኑ ዓለም አቀፍ ቅስቀሳ የሚያደርገው ወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ፣ በዝርዝሩ ያካተታቸው የተመረጡ ቅርሶች ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኙና በአግባቡ እንዲጠበቁ በዓለም ዙሪያ ያሉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በዩኔስኮ የተመዘገቡ በርካታ የዓለም ቅርሶች የፈንዱ ተጠቃሚ ሲኾኑ ከእኒህም መካከል ፈንዱ እ.ኤ.አ በ1966 ሲቋቋም የክብካቤና ድጋፍ ሥራውን የጀመረባቸው የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ መቅደስ እንደሚገኙበት በመግለጫው ተመልክቷል።
የይምርሐነ ክርስቶስ መካነ ቅርስ በዓለም አቀፍ ፈንዱ ተመራጭ እንዲኾን በመጠቆምና ለምርጫው የሚያግዙ መረጃዎችን በማቅረብ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ለአዲስ አድማስ የገለጸው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ክብካቤና ልማት ማኅበር፤ መካነ ቅርሱ የ2014 የወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ ተመራጭ መኾኑ ኪነ ሕንጻውን የበለጠ ለማስተዋወቅና ለማልማት ዕድል ይሰጣል ብሏል፡፡ ቅርሶች ዘላቂ ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ያበረክቱ ዘንድ ራእይ የሰነቀው ሀገር በቀል ማኅበሩን ጨምሮ በቅርስ ክብካቤ ዙሪያ የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ የሥራ ሓላፊዎችና ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የብዙኀን መገናኛና ሌሎች አካላት ጋራ በመተባበር እንንዲንቀሳቀሱም ምቹ ኹኔታ ይፈጥራል ተብሏል፡
ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት በሰሜን ወሎ ወግረ ስኂን በሚባል ቦታ ሰፊና ግርማ ሞገስ ባለው የተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ በውኃ ላይ እንደታነፀ የሚታመነውና ልዩ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የሚታይበት ይምርሐ ክርስቶስ÷ በአገራችን ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረውን የቤተ መንግሥት ሕንጻ፣ በድንቅ ጥንታዊ ሥዕሎችና ንድፎች ያሸበረቀ ቤተ መቅደስ አሰናኝቶ የያዘ መካነ ቅርስ ነው፡፡ በተጨማሪም ልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች፣ ያልፈረሱና ዕድሜ ጠገብ የሰው ዐፅሞች፣ የሀገር በቀል ዕፀዋት ጥቅጥቅ ደንና ማራኪ መልክአ ምድር የሚገኙበት ነው፡፡
Source/addisadmass.com

Post Navigation