addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “October 13, 2013”

ስብሃት ነጋን አጅበው አክቲቪስት መስፍን ላይ ድብደባ የፈጸሙት ግለሰቦች ማንነት ታወቀ

sibsha
(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው ዕለት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና ባቀረበቸው ቪድዮ ላይ አክቲቪስት መስፍንን በቡጢ የተማቱትና የቆሙ መኪናዎችን ገጭተው ያመለጡት ግለሰቦች ማንነትን ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አረአያ ማወቁን ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ፡፡

የሕወሓት መንደርን ከቃረምኩት በሚል በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ የሕወሓት ምስጢሮችን በሚያጋልጠው ጽሁፎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ አረአያ ተስፋማርያም (ኢየሩሳሌም አረአያ) በትናንትናው እለት በአክቲቪስቱ ላይ ድብደባ የፈጸሙትን በሕግ የሚጠየቁት ግለሰቦች ሶስቱም የሕወሓት አባላት መሆናቸውን ጠቅሶ ማንነታቸውን ዘርዝሯል።

1ኛው. የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ወንድም ታምራት ገ/መድህን፣

2ኛው. የወያኔ ኪነት አባልና ጊታሪስት ወዲ ሰቦቃ (በአሜሪካ ፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ)፣
3ኛው ሃይሌ በአሜሪካ – የኢትዮጲያ ኤምባሲ የብርሃነ ገ/ክርስቶስ ሹፌር የነበረና በአሁኑ ወቅት በቪዛ ክፍል የሚሰራ ናቸው።

አክቲቪስት መስፍን ለደረሰበት ድብደባ ሕክምና የተከታተለ ሲሆን ጉዳዩን በሕግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። በሌላ በኩል የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አንድ የቨርጂኒያ ጠበቃ አነጋግሮ ባቀረበው ዘገባው ስብሃት ነጋን ጨምሮ እነዚህ ግለሰቦች ሰውን በመደብደብና የሰው መኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀሎች ከተከሰሱና ፍርድቤትም ጥፋተኛ ካላቸው በ እያንዳዱ ክስ እስከ አንድ አመት የሚያስቀጣ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። ስብሃት ነጋም የወንጀል ተባባሪ፣ እንዲሁም የሰው መኪና ገጭቶ ባመለጠ መኪና ውስጥ በመሄዳቸውና ወንጀልን በመተባበር ክስ በአሜሪካ ህግ በወንጀል ተባባሪነት ሊከሰሱ የሚችሉበት ህግ አለ።

14 ዓመታት ተፈርዶበት እስር ቤት የሚገኘው ውብሸት ታዬ የሲኤንኤንን ሽልማት አሸነፈ

webishet
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የሚዲያ ተቋም ሲኤንኤን (Cable News Network) በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የመልቲ ቾይዝ የአፍሪካ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሄደ። በዚህ የሽልማት ስነስርዓት ላይ በ እስር ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ አሸናፊ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ሽልማቱን በትዊተር በመከታተል ካገኘችው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ ዘርፎች ሲኤን ኤን የአፍሪካ ጋዜጠኞችን በየዓመቱ የሚሸልም ሲሆን ከዚህ ዓመት ተሸላሚዎች መካከል ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሽልማቱን ያገኘው Free Press Africa Award በሚለው ዘርፍ ነው።

በእስር ቤት ከ2 ዓመት ከ4 ወር በላይ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ይሰራበት በነበረው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ ጽሁፍ ጽፈሃል በሚል 14 ዓመታት ተፈርዶበት እስር ላይ ይገኛል። የዛሬውን የሲኤን ኤን ሽልማት እርሱ እስር ላይ በመሆኑ ባለቤቱ መምህርት ብርሀን ተስፋዬ እና ልጁ ፍትህ ውብሸት በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር በመገኘት መቀበላቸውን ዘ-ሐበሻ በትዊተር በመከታተል ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

ለጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መታሰር ለሕወሓት/ኢሕአዴግ ደህንነቶች ጥቆማውን በመስጠት ደረጃ ማንን ትጠረጥራላችሁ? እኛ እያጣራነው ያለነው ጉዳይ አለ፤ እናንተ ግን አስተያየታችሁን በአስተያየት መስጫው ያስቀምጡ።

http://www.zehabesha.com/

Breaking News: Sebhat Nega and his bodyguards attacking peaceful Ethiopian activists in DC (watch the video)

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው
ከኢየሩሳሌም አርአያ

በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። መስፍን የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል።

Post Navigation