addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “October 26, 2013”

የጀነራል መኮንኖች የምደባ ለውጥ ተካሄደ

et.
ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ የአየር ሀይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውንና የአዛዥ ጄነራሎች ላይም የምደባ ለውጥ መደረጉን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ በአየር ሀይል አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም ምትክ የተሾሙት ሜጀር ጀነራል አደም የአየር ሀይል ፓይለት የነበሩና በሱዳን አቢዬ ግዛት የሠላም አስከባሪ ሀይል ምክትል አዛዥነት ያገለገሉ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ነበሩ፡፡
በሌሎች የመከላከያ የስራ ምድብ ቦታዎች ላይ የአዛዦች የምደባ ለውጥ መደረጉን የተናገሩት ምንጮች፣ አዲስ የሀላፊነት ምደባ ከተሠጣቸው ውስጥ ሌተናል ጀነራል ሠአረ መኮንን፣ ሌተናል ጀነራል አበባው፣ ሜጀር ጀነራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ባለፈው አመት እና ዘንድሮ ከ60 በላይ ለሚሆኑ መኮንኖች የጀኔራልነት ሹመትና እድገት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

addis admas

ታንኮች የህዝብን ጤንነት አይጠብቁም የወያኔን ስልጣን ዘመን እንጂ

Elias Abayneh Lema

ከጥቂት ቀናቶች በፊት 12 October 2013(እአአ) በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ስር የሚገኘው የአገሪቱ ብቸኛ የአስክሬን ምርመራ ክፍል የምርመራ አገልግሎቱ እንዳቋረጠ ሰምኤተናል ደግሞም ከተለያዩ ድህረ ገጾች አንብበናል የገዥው ፓርቲ ልሳን እንደሆነ የሚታወቀው ፋና FM ሬዲዮ ደግሞ ጥቅምት 132006 በቀትር የዜና እወጃው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከትናንት 10 ሠዓት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ የሆስፒታሉ ታክሚዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አረዳን፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ በመቋረጡ የቀዶ ጥገናና ጽኑ ህሙማን ታካሚዎች፣ ጠቅላላ ቀዶ ጥገና እና ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጥባቸው ክፍሎች እንዲሁም ያለ ጊዜያቸው የተወለዱና ሙቀት የሚፈልጉ ህጻናት ሙቀት የሚያገኙባቸው ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመው እንደነበር እና የኤሌትሪክ ሃይል በመቋረጡ የተነሳ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ለነዚህ ከሞት አፋፍ ለደረሱና በተፈጥሮ መተንፈስ ላልቻሉ ህሙማን የህክምና ባለሙያዎቹ ዓየር በእጃቸው እየጨመቁ እንደሰጡ ተነገረን::

በሌላ ዜና ድግሞ 17 October 2013 (እአአ) የአስትሪየም ሳተላይትና HIS የተባለ የባህር ላይ መርከብ ጥምር መረጃ ሰብሳቢ እንዳመለከተው በመስከረም ወር ከዩክሬን ኦክታያብርስክ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ…

View original post 330 more words

በኢትዮጵያ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ የቆየማንዴላን የተመለከተ የደህንነት ሚስጥር ዛሬ ይፋ ሆነ።ሚስጥሩን ማንዴላም እስካሁን ድረስ አይውቁትም።(Audio)

MANDELA GARDኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል።ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በወቅቱ ለማንዴላ ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።

ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት የግድያ ሙከራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል።

ሻምበል ጉታ ዲንቃ በንጉሡ ዘመን የፖሊስ መኮንን ነበሩ። ማንዴላን በከፍተኛ ሚስጥር እንዲጠብቁ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ በወቅቱ ኮ/ል የነበሩ)፣ኮ/ል ፍቃደ እና ሻምበል ፈቃደ ውስጥ ነበሩ።ዛሬ የ76 አምቱ የእድሜ ባለፀጋ ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሸገር ሲናገሩ እንዲህ አሉ።

” ማንዴላን እንድጠብቅ ኃላፊነት የተሰጠኝ እኔ ነበርኩ።ማንዴላ የሚያድሩበት እና ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱበት የኮልፌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቦታ በተለይ እርሳቸው የሚገኙበት ቦታ ‘የፈንጅ ወረዳ’ ነበር የሚባለው።ከአራታችን በቀር ማንም ወደ እርሳቸው ቦታ ዝር ማለት አይችልም። ሲተኙ መስኮት ከፍተው ነው የሚተኙት።አንድ ቀን ታድያ አብሮኝ ከሚሰራው የፖሊስ ባልደረባዬ በጥብቅ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ።ጣይቱ ሆቴል ተቀጣጠርን እና ሃሳቡን ገለፀልኝ።” ካሉ በኃላ አሁን አዲስ አበባ ላፍቶ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ሻምበል ጉታ በመቀጠል እንዲህ ብለዋል-

”ጣይቱ ሆቴል የወሰደኝ ሰው ለጊዜው 2000 ፓውንድ በወቅቱ አስቡት 2000 ፓውንድን እና ሰጥቶ እንዲህ አለኝ- ‘ሁለት ዕድል ከፊታችን ተቀምጧል።ሊያመልጠን አይገባም።ከፍተኛ ገንዘብ እናገኛለን።ቀጥሎም ወደ ውጭ ሀገር የመሄድ ዕድል አለን።ከአንተ የሚጠበቀው ማንዴላ በተኛበት ዛሬ ሌሊት በመስኮት ገብተህ በገመድ አንቀህ ግደል እና ውጣ እንደወጣህ መኪና ተዘጋጅቶ ይጠብቅሃል ከእዚህ የውትድርና ሕይወት እንገላገላለን’ አለኝ። እኔም ጉዳዩን ከሰማሁ በኃላ በጉዳዩ የተስማማሁ መስዬ ቀጥታ ለጀኔራል ታደሰ ነገርኩኝ። ጉዳዩ በሚስጥር ተይዞ ይህንን ያደረጉት ሰዎች ተደረሰባቸው እና ከሀገር እንዲወጡ(እንዲባረሩ) ተደረጉ ይህ ሚስጥር ለዘመናት ከእኔ ጋር የኖረ ነው።ጉዳዩን ማንዴላም አያውቁትም።” ብለዋል።

ኔልሰን ማንዴላ በወቅቱ እንደ ሻምበል ጉታ ዲንቃ አይነት ታማኝ የኢትዮጵያ የፖሊስ መኮንን ባይገጥማቸው ኖሮ የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታሪክ ሂደትም ሆነ የነፃነት ትግሉ ታሪክ ሌላ መልክ በያዘ ነበር።ይህ ጉዳይ እጅግ ትልቅ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ ያደረገው አስተዋፆ የሚያጎላ፣ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪክ ያደረገችው ትልቅ አስተዋፆ በመሆኑ በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎቶች ሁሉ ትኩረት ተሰጥቶት የዓለም አቀፍ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ለኢትዮጵያ ፋይዳው ብዙ ይመስለኛል።

በመሆኑም ቢያንስ ለሻምበል ጉታ ዲንቃ የኢትዮጵያ ፖሊስ ጠርቶ ከማዕረግ እስከ ሽልማት ከእዚህ ባለፈም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት እና ማንዴላ በሕይወት ዘመናቸው ሳሉ ሻምበል ጉታ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄደው እንዲያገኙዋቸው ማድረግን ሁሉ ይጠይቃል።ጉዳዩ የደህንነት ሚስጥር የነበረ በመሆኑ በወቅቱ ግድያውን ሊፈፅም የሞከረው አካል ወይንም ሀገር (ማንነቱን ሻምበል ጉታ አልገለፁም (የተባረሩት ዜጎች የየት ሀገር እንደነበሩ አልገለፁም) ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ጥላ እንዳያጠላ ስጋት ስለሚሆን ዜናው በተፈለገው ደረጃ ለዓለም ሕዝብ እንዳይደርስ የሚደረጉ ስውር ስራዎች እንደማይጠፋ ማጤን ሌላው ሥራ ሊሆን ይችላል።

በመጨረሻም ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሕዝብ ወጥተው ዛሬ ላይ ምንም ምስጢርነት የሌለውን ጉዳይ ለሕዝብ በመንገራቸው ሊመሰገኑ ይገባል።

ምንጭ-http://gudayachn.blogspot.no/2013/10/blog-post_25.html

Post Navigation