addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “October 20, 2013”

በኦጋዴን የነዳጅ ጉድጉድ ቁፋሮ ተጀመረ

kk
ኒው ኤጅ የተሰኘው የእንግሊዝ ኩባንያ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኦጋዴን ቤዚን፣ ኤልኩራን በተባለ ሥፍራ የነዳጅ ጉድጓድ ቁፋሮ ጀመረ፡፡ ኒው ኤጅ በኦጋዴን ብሎክ ሰባት፣ ስምንትና አዲጋላ በተባለ ድሬዳዋ አቅራቢያ በሚገኙ የነዳጅ ፍለጋ ቦታዎች አፍሪካ ኦይል ከተሰኘ የካናዳ ኩባንያ ጋር በነዳጅ ፍለጋ ሥራ የተሰማራ ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ኤልኩራን በተባለ በሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ አካባቢ የነዳጅ ጉድጓድ ቁፋሮ ጀምሯል፡፡
ታማኝ የዜና ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኩባንያው የመቆፈሪያ ማሽኑን ተክሎ የቁፋሮ ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ሳለ የቁፋሮ ባለሙያዎች በማሽኑ ላይ የቴክኒክ ችግር በማግኘታቸው የቁፋሮ ሥራውን ሳይጀምሩ አዘግይተውታል፡፡ ባለሙያዎቹ በማሽኑ ላይ ያገኙትን የቴክኒክ ችግር አስወግደው የቁፋሮ ሥራውን ባለፈው ሳምንት መጀመራቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የሚቆፈረው ጉድጓዱ ጥልቀት 2,800 ሜትር እንደሆነና የቁፋሮውን ሥራ ለማጠናቀቅ ሦስት ወራት ያህል እንደሚፈጅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከሦስት ወራት በኋላ በጉድጓዱ ውስጥ ነዳጅ መኖርና አለመኖሩን የሚጠቁም የሙከራ ሥራ እንደሚሠራ ታውቋል፡፡
አፍሪካ ኦይል በቅርቡ በድረ ገጹ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ከኒው ኤጅ ጋር በመተባበር በኦጋዴን ላይ አተኩሮ እንደሚሠራ ገልጿል፡፡ አፍሪካ ኦይል በኤልኩራን የነዳጅ ክምችት እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ መገኘቱን ጠቅሶ፣ አሁን በሚቆፈረው ጉድጓድ በአካባቢው የሚገኘውን የነዳጅ ክምችት መጠን ለማወቅ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡
‹‹በኤልኩራን ነዳጅ መኖሩ ይታወቃል፡፡ አሁን ዋናው ሥራ የሚሆነው በሚቆፈረው ጉድጉድ ውስጥ የነዳጅ ፍሰት እንዲከሰት በማድረግ በአካባቢው የሚገኘውን የነዳጅ ክምችት መጠን ማወቅ ነው፤›› ብለዋል ምንጮች፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፔትሮሊየም ባለሙያዎች በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ቴኔኮ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ በኤልኩራን በቆፈረው የመጀመሪያ የነዳጅ ፍለጋ ጉድጓድ የተፈጥሮ ዘይት ፍሰት ማግኘቱን አስታውሰው፣ በወቅቱ ኩባንያው ክምችቱ በቂ አይደለም በሚል ትቶት ሄዷል ብለዋል፡፡ አክለውም አሁን ባለው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው አፍሪካ ኦይልና ኒው ኤጅ በኤልኩራን ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ክምችት ሊያገኙ እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ዜናው የሪፖርትር ነው።

ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

የህውሃት ኢሃደግ መንግስት በልጆቼ ለምን ዘመተ? (ከኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል)

12
ሁለተኛ ልጄ ክብሮም እንደ ወንድሞቹ የእስር ሰለባ ሆነ፡፡እኔ ለኢትዮፕያ ህዝብ ጠላት ሳልሆን ፍፁም ወዳጁ ነኝ መጀመርያ ደርግን 17 ኣመት በመታገል ፋሽሽታዊ ደርግ በማስውግድ ኣስተዋፅኦ ነበረኝ፡፡ ህውሃት ኢህኣደግ ስልጣን ከያዘ በሃላም ለንሮየ ለደሞወዝ ሳላስብ 17 ኣመት ሙሉ የታገልኩበት ኣላማ ስለተቀለበሰ በተጨማሪ የህውሓት መሪዎች ለኢቲዮፕያ ሉኣላዊነትና ኣንድነት ታማኝነት ስላጎደሉ የኢትዮፕያ ሕገመንግስት በሚፈቅደው መሰረት በግልም በፓርቲ ተደራጅቼ እየታገልኩ ቆይቼ ኣሁንም እታገላለው ታድያ እኔ በሃገራችን ሕ/መንግስት በሚፈቅድልኝ መሰረት መታገሌ እንደ ሃጠያት ተቆጥሮ የቂም በቀል ፖለቲካ ወደ ልጆቼ ምን ኣመጣው ይህ ለማለት የፈለጉኩት፡፡

1.የማነ ኣስገደ ልጄ ምንም ሳይፈፅም በገጠር ቤተሰብ ለመጠየቅ ሄዶ ታስሮ ብዙ ግፍ ተፈፅሞበታል በተፈፀመበት ግፍ ጠንቅ ታሞ እናቱ የመከላክያ ኣባል ስለሆነች በመከላክያ ሚኒስተር ሆስፒታል ብዙ ጥረት ተደርጎ ሊያድኑት ስላልቻሉ ወደ መቀሌ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከስልጣን በላይ ብለዉት ሂወቱ ተርፎ ኣሁንም በቤቱ ታሞ የኣልጋ ቁራኛ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተማረው መሰረት ለሃገሩ እንዳያገለግልም እንደማይሰራ ኣካል ጉዳተኛ ኣድርገዉታል ወደ ውጪ ወስድን እንዳናሳክመው ኣቅም የለም፡፡

2.ኣሕፈሮም ኣስገደ ልጄም ከስራ ገብታው ኣፍነው ወስደው ታስሮ በፖሊስ ጣብያ 6 ወር ታስሮ ክስ ሳይመሰረትበት በቀዳማይ ወያኔ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ከ 15 ጊዜ በላይ ቀጠሮ ጊዜ እየተባለ ሲመላለስ ከርሞ በመጨረሻ ክሱ የዋስ መብት የሚከልክለው የፀረ ሙስና ኣንቀፅ በሙስና የተከሰሰ የዋስ መብት ኣይፈቅድም የሚል ሽፋን ልጄን ከእሱር ላለማውጣት ክሱ ወደ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በማዞር የፀረ ሙስና ጉዳይ ደግሞ በወረዳ ስለማይታይ 6 ወር ሙሉ ሲያንገላቱት ከርመው ክሱ በመቀሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደ ኣዲስ ተመስርቶ በ 28/1/2006 ዓ.ም በዞኑ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ደግሞ ሌላ ተጠርጣሪ ስላለና ስለታጣ በጋዜጣ ኣሳውጀን እስከ ምንፈልግ ኣሕፈሮም በወህኒ ቤት ይግባ በማለቱ ልጄ ያለ ፍርድ በወህኒ ቤት ተወርውሮ ይገኛል የጊዜ ቀጠሮ እየተባለ 7 ወሩ በስቃይ ይገኛል፡፡

ሌላ ያሁኑ ይባስ ክብሮም ኣስገደ የሚባል የ 10ኛ ክፍል ተማሪ የስብእና መሳት ስነ ኣእምሮ ችግር ያለው ይህም በሃኪም ክትትል ላይ ያለ በፍርድ ቤትም ታይቶ ያደረ በካስ ሜዳ እየተጫወተ እያለ ፖሊሶች ይዘው በእስርቤት ኣግብተው በኣንድ ጨለማ ቤት ለብቻው ኣስረው ከወላጆቹ ከሃይማኖት ኣባት ከህግ ኣማካሪ እንዳይገናኝ ኣድርገው ኣፍነዉት ይገኛሉ የምንሰጠው ምግብ ለማን እንደሚሰጥ ኣናውቅም ለፍትህ ቢሮ ፖሊስ ኣዛዞች ኣመለከትን ፍትህ ኣልተገኘም ዳኛ እንድያገናኙን በስልክ ነግሮዋቸው ፖሊሶች ኣልተቀበሉትም ኣሁን 80 ሰኣት በላይ ታስሮ ቤተሰብ ልናገኘው ኣልቻልንም ይህ ዘመቻ በእኔ የጀመረው ልጆቼም የግፍ ሰለባ ሆነዋል የኔ ጉዳይም የህውሓት የ17 ኣመት ታሪክ በመፃፌ ከኣንድ ዜግነቱ ኣሜሪካዊ ትውልድ ኢትዮፕያዊ በሰዎች የተቀናበረ ሴራ ተከስሼ 3 ኣመት ባስቆጠረ ክስ ላይ ነኝ ገና መቃጫ ኣላገኘም፡፡

ይህ ጉዳይ የእኔና የልጆቼ ብቻ ችችግር ኣይደለም ብዙ የሚናገርላቸው ያጡ ዜጎች በስቃይ ላይ ይገኛሉ ስለሆነ ሁሉም ዜጎችና ለፍትህና ለዲሞክራሲ ለሰብኣዊ መብት የምትታገሉ ያላችሁ ተቃዋሚ ሃይሎችም ዝምታ ከመምረጥ ብትነጋገሩበትና ብትቃወሙት ጥሪየን ኣቀርባለው፡፡

በተለይ በኣሁኑ ጊዜ ኣንድ ኣንድ የፖሊስ ከፍተኛ መኮነኖች በታሰረው ልጄ ኣሕፈሮም ኣስገደ ከታሰረበት የእስር ቦታ ሄደው ኣባትህ ኣስገደ ተው ኣርፈህ ተቀመጥ ትእግስት ኣድርግ እስከማለት ሄደዋል ለዚሁ አንደ ምሳሌ ኮማንደር ገ/ሂወት ካሕሳይ የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ዋና ኣዛዠ ይጠቀሳል በዛ በሰጠው ማስፈራርያ ታድያ ልጄ ኣሕፈሮም በትልቅ ስጋት ላይ ይገኛል ታድያ ከዝሂች ኣገር ኣገሬ የት ልሂድ ንፁህ ዜጋ ነኝ እና በዚህች ኣገር የዳኝነት እና የህግ የበላይነት መረጋገጥ ኣለበት ወተደራዊ ኣገዛዝ እንዳይደገም እንጠንቀቅ ፡፡

እባካችሁ የቂም በቀል ፖለቲካ ለልጆቻችን ኣናውርሳቸው ሰላም ፍትህን ዲሞክራሲን እናውርሳቸው፡፡

http://abrahadesta.wordpress.com/

“በ15 ቀን ውስጥ ከወልቃይት ጠገዴ ሁለት ሺ ተማሪዎች ተፈናቅለዋል”መአህድ

ff
የመላው አማራ ህዝብ (መዐህድ) በአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ፡፡ መአህድ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የአማራ ተወላጆችን መፈናቀል በተመለከተ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማሳወቁንና መፈናቀሉ እንዲቆም መጠየቁን ጠቁሞ፤ ጉዳዩ እስካሁን እልባት አለማግኘቱን ገልጿል፡፡
መፈናቀሉ ሊቆም ቀርቶ ተጠናክሮ መቀጠሉንና በቅርቡም ከጉራፈርዳ፣ ከቤኒሻንጉል እና ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች መፈናቀላቸውን የጠቆመው መዐህድ፤ ድርጊቱ በአገሪቱ ስርዓት አልበኝነት መንሰራፋቱን ያሳያል ብሏል፡፡
ከተማሪዎች በተጨማሪ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮችንም ለይቶ ማፈናቀሉ ለመሪር ሀዘን እንደዳረገው መአህድ ገልፆ፤ አንድን ብሄር ማዕከል ያደረገ ማፈናቀል እንዲቆም ጠይቋል፡፡
ባለፉት 15 ቀናት ብቻ “አካባቢያችሁ አይደለም” በሚል ከወልቃይት ጠገዴ ሁለት ሺህ ተማሪዎች መፈናቀላቸውን የገለፁት የመአህድ ፕሬዚዳንት አቶ ሸዋንግዛው ገብረስላሴ፤ ከጉራፈርዳም ተማሪዎች ተፈናቅለው ከትምህርት መስተጓጐላቸውንና ለጊዜው ቁጥራቸው በውል አለመታወቁን ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ “ከጉራፈረዳ ምን ያህል ተማሪዎች እንደተፈናቀሉና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የሚያጣራ ቡድን ልከናል” ያሉት አቶ ሸዋንግዛው፤ አጣሪ ቡድኑ ሁኔታውን አጣርቶ ሲመለስ መዐህድ በድጋሚ የአቋም መግለጫ እንደሚያወጣም ተናግረዋል፡፡
“ተማሪዎች የወደፊት አገር ተረካቢ ሲሆኑ አርሶ አደሮችም የአገር ህልውና ምሰሶ ስለሆኑ በአገራቸው የትኛውም ቦታ የመማርና የመስራት መብታቸው ተከብሮ፤ ተማሪዎችም ወደ ትምህርት፣ አርሶ አደሮችም ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ እንጠይቃለን” ብለዋል፤ ፕሬዚዳንቱ፡፡
የአማራ ተወላጆችን ከተለያዩ አካባቢዎች ከማፈናቀል በተጨማሪ የአማራውን ክልል ለማጥበብ ወደ አጐራባች ክልሎች የሚደረገው የመሬት ሽንሸና ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም መዐህድ በመግለጫው የጠየቀ ሲሆን በአማራ ህልውና ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ስልታዊ እንቅስቃሴ እና ትንኮሳ ሊገታ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡ ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማህበራትም ይህንን ኢ-ሰብአዊ ድርጊትና መብት ረገጣ እንዲያወግዙ ጠይቋል፡፡
source Addisadmas

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት አይሏል::

ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ተቃውሞ ገጥሞታል:: ከፍተኛ ጄኔራሎች ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አብዝተዋል::የምስጢራዊ ስብሰባ ቃለ ጉባዬ የምትይዝ የሆነችው የአንድ ከፍተኛ ጄነራል ጸሃፊ
dd
ትክዳ ወይም ትገደል አልታወቀም::ለሜ/ጄ ዮሃንስ ethiopian_troops_pickupገብረመስቀል የተሰጠው የሌ/ጄ ማእረግ የታሰበው ሌ/ጄ ሳሞራን ይተካሉ ተብለው ለነበሩት ለሜ/ጄ አበባው ታደሰ የነበረ ቢሆንም በምን ምክንያት እንደተዘዋወረ አልታወቀም::

በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በከተማ እና በሌሎች የእዝ መምሪያዎችም መቀጠሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየኡ መሆኑ ተጠቁሟል::

ሰራዊቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሳው ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው:: በቅርቡ ከስልጣን ይነሳል የሚባለው ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የብኣዴን ታጋይ መኮንኖች የተቃወሙት ሲሆን እኛም ከማንም ያላነሰ የታገልን ስለሆነ ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ብኣዴን እያለው ለምን እንዲህ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አንስተዋል::

ከፓርቲ አጣብቂኝ ያልተላቀቀው የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ አመራር ህገመንግስታዊ መዋቅር እንዲይዝ ለማድረግ ምንም አይነት ስራ አለመሰራቱ በሰራዊቱ አዳዲስ መኮንኖች ዘንድ አቤቱታ ቢያስነሳም ጄኔራሎቹ የሚያደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ እንዴት መፍታት ሳይሆን ማክሸፍ እንደሚቻላቸው እየመከሩ ሲሆን አዳዲስ ወታደራዊ ደህንነቶችን በየእዙ አስርጎ በማስገባት እንዲሁም የሰራዊቱን አቤቱታ ያስተባብራሉ የሚባሉትን በስራ ምክንያት በየማእዘኑ በመበተን ለመስራት የታቀደ ሲሆን የአበታተኑን ሁኔታ በማስጠናት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በተጨማሪ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ይረዳቸው ዘንድ ኮማንዶዎችን እና ንቁ የደህንነት ጠባቂዎችን ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ለመመደብ ተነጋግረዋል::

መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ምዽር ጦር መምሪያ እንዲሁም ደብረዘይት እና አስፈላጊም ሲሆን በመኖሪአ ቤቶቻቸው የሚያደርጉትን ስብሰባ ቃለጉባዬ የምትይዘው የአንድ ጄኔራል ጸሃፊ ከድታ ይሁን ተገድላ ሳይታወቅ ካለፈው ሳምንት ጀምራ በስራ ገበታዋ ላይ ያልተገኘች እና የት እንዳለች የማይታወቅ ሲሆን ስልኳም መዘጋቱን ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል::

ምንሊክ ሳልሳዊ

አቶ ስብሃት ነጋ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ልዩነት እንደነበራቸው አመኑ

“ህወሓት መለስ ከነበረበት በጣም የጠነከረ ድርጅት ይሆናል” አቶ ስብሃት ነጋ
22
Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Nov. 20, 2013)፦ ሰሞኑን በአሜሪካ ለሚገኙት የህወሓት መስራችና የቀድሞ ሊቀመንበር ለአቶ ስብሃት ነጋ የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ደረጀ ደስታ እስከዛሬ ተጠይቀው የማያውቋቸውን ጥያቄዎች አቅርቦላቸዋል። ቃለምልልሱን ጋዜጣው ላይ በቅርብ ይዞት የሚወጣ ሲሆን፣ ይኸንኑ ቃለምልልስ ለኢትዮጵያ ዛሬ በድምፅ ልኮልናል። ከተጠየቋቸው ጥያቄዎ ውስጥ ከህወሓት ማዕከላዊ አባልነት እንዴት ወደ ተራ አባልነት እንደተሻገሩ፣ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ያላቸውን ጠብ፣ ከአቶ መለስ ጋር የነበራቸውን አለመግባባት፣ የአቶ መለስ ደካማ ጎን፣ ሙስኝነትን፣ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ላይ ያላቸውን ውግዘት፣ ስለፕሬሱ፣ … ይገኙበታል። (ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

http://www.ethiopiazare.com/interview/interview/3089-sibhat-nega-with-zethiopia

Eritrean Norwegian 23 Left a Wife and a Newborn to Fight a Jihad War in Syria

Islamic Jihad militants take part in the funeral of their comrade Mahmoud Shaath in Khan Younis, in the southern Gaza Strip
Eritrean Norwegian 23 Left a Wife and a Newborn to Fight a Jihad War in Syria
How did 23-year-old’s life from pike fishing to holy war
As a youth he loved pike fishing. Now he is fighting in Syria.
By kadafi Zaman | http://www.tv2.no
According to the Police Security Service (PST) has at least 30 to 40 people traveled from Norway to fight in Syria. Now, TV2 tell the story of one of them, 23-year-old “Ali”.

He came from Eritrea to Norway as an unaccompanied migrant on September 9th 2003. When he was only 13 years.

The first residence was a reception center just outside Oslo. After a short time he had a Norwegian foster family in Bærum. Tor Bach in the multicultural outdoor organization Wild X was often visited by Norwegian-Eritreans.

– I remember him as a happy, well-adjusted and securely boy who got along with everyone, says Bach.2223-year-old “Ali” came to Norway as an unaccompanied asylum seeker in 2003. © Private
He says that the boy was with several fishing trips arranged by leisure organization.

– We were ice fishing and pike fishing. He got one six-pound pike. He was brilliant bland and very proud to have received the pike is, says Bach.

– Talked about shooting Jews
For five years the boy lived with his Norwegian foster family. He played football and got good grades from high school.

TV 2 has spoken to several sources familiar with Norwegian-Eritreans. They will not stand up, but describes him as a dutiful and kind person.

In 2010 he worked as a nursing staff member at an institution in Bærum. He worked for a time as well as a student assistant at a school in Drammen.

Right after high school he moved to Volda to study.

According to TV2’s sources, he changed himself after he left home. They say that he came back shortly with a more conservative approach to the religion of Islam.

Spring 2012 called Norwegian-Eritreans to Tor Bach and asked if he could take hunting test with three friends. Bach welcomed him, but said he was surprised when they met.33
According to TV2’s sources changed the 23-year-old “Ali” after he left home. © Private
– I saw a completely different boy. Then I saw a guy with a long beard and angry eyes, and friends who talked about shooting Jews, says Bach.

Do you have tips about this matter? Contact us attips@tv2.no

Radicalized in a short time
TV 2 is known that the three individuals Norwegian-Eritreans had with them are key figures in the extreme grouping Prophet’s Ummah.

– They would have access to weapons and thought that hunting proficiency test course was a great way to arrange it. We managed to sabotage so that none of them had access to weapons, says Tor Bach.

From January 2011 to September 2012 worked the then 22 year old man as a parking guard in Oslo. During this period he also married a Norwegian-Eritrean woman.

According to TV2’s sources were Norwegian-Eritreans radicalized within a very short time. He was greatly inspired by jihadist propaganda films from Syria.

In December 2012 left the 23-year-old Norway and headed for Syria. Back set one wife and one just a few weeks old baby.

Deleted Facebook account
For the first time tells the Police Security Service about how many people have traveled from Norway to fight in Syria.

– We assume that there may be between 30 and 40 people, but it is unrecorded and figures may be higher, says the PST-head Benedicte Bjørnland to TV 2

For ten months, the 23-year-old fought in Syria. TV2 know that he is alive and that he is in jihadistbrigaden, Kataib al-Muhajereen. It is associated with the so-called al-Nusret-front.

– We are seeing a worrying increase in traveling from Norway to conflict areas. Previously we have not seen so many go at once so adapted to the same place, says Bjørnland.

– Where do they travel?

– It is primarily Syria, says PST boss.

Norwegian-Eritreans deleted a short time ago his Facebook account and there is almost no trace of him on the internet. It has not succeeded TV 2 to get in touch with the man.

Software Translation from Norwegian
http://eastafro.com/

ቴዲ አፍሮ በማርፈዱ ሸራተን እንዳይገባ ተከለከለ

tedo
ሰሸዋንዳኝ የአልበም ምርቃት የተጋበዙት ሠራዊት ፍቅሬና ሰይፉ ፋንታሁንም ተከልክለዋል

በሸራተን አዲስ ጋዝ ላይት ክለብ ከትናንት በስቲያ ሰተካሄደው የድምፃዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ “ስጦታሽ” አልበም ምርቃት በክብር እንግድነት የተጠራው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፤ ሰዓት አርፍዶ በመድረሱ እንዳይገባ ተከልክሎ ከበር ተመለሰ፡፡
ቴዲ አፍሮ ከምሽቱ 5፡30 ላይ የምርቃት ስነስርዓቱ ወደሚካሄድበት ጋዝ ላይት ክለብ ሊገባ ሲል የጥበቃ ሰራተኞች “ጥሪው 4 ሰዓት እንጂ 5፡30 ሰዓት አይደለም” በማለት እንዳይገባ እንደከለከሉት ለማወቅ ተችሏል። አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬና ሰይፉ ፋንታሁንን ጨምሮ በርካታ ያረፈዱ እንግዶች ወደ ጋዝ ላይት ክለብ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የዓይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ ሸዋንዳኝ፤ ቴዲ አፍሮ እንዳይገባ መከልከሉን የሰማው መድረክ ላይ ሆኖ እንደሆነ የገለፁት ምንጮች፤ በዚህም ማዘኑን ተናግረዋል። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች፤ ሁለቱ እንዳላቸው ቅርበት ቴዲ አፍሮ በፕሮግራሙ ላይ ቀድሞ መገኘት ነበረበት ብለዋል፡፡ ድምፃዊ ሸዋንዳኝን ስለ ጉዳዩ በስልክ ጠይቀነው፣ መልስ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡
ከትላንት በስቲያ ምሽት በተካሄደው የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ሸዋንዳኝ ከአዲሱ አልበም አስር ዘፈኖችን የተጫወተ ሲሆን የተዘጋጀለትን አዲካ እና ኤም ጂ ፕሮሞሽን ያዘጋጁለቱንም ኬክ በዚያው ፕሮግራም ላይ ቆርሷል፡፡ ሸዋንዳኝና ቴዲ አፍሮ በአንድ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ ለረጅም አመታት አብረው የሰሩ ሲሆን ቴዲ አፍሮ ሲያገባ ሸዋንዳኝ ሚዜው ነበር፡፡
ማርፈድ የስንፍና ምልክት መሆኑን የተናገረው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፤ሸራተን ስንደርስ የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ በሩን ዘግተው እንደሄዱ ተነግሮናል ብሏል፡፡ “በሌሎች አገሮችም የተለመደ ነው፤ናይት ክለብ ከሞላ ሰው እስኪቀንስ መግባት አይቻልም” ያለው ሰራዊት፤ “እኛ ታዋቂ ስለሆንን ለምን ተከለከልን የሚል ቅሬታ አላደረብንም” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
http://www.addisadmassnews.com/

Post Navigation