addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

መንግስት የተቃጠሉትን አብያተ ቤተክርስቲያናት ለፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀምባቸው ነው ተባለ

መንግስት የተቃጠሉትን አብያተ ቤተክርስቲያናት ለፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀምባቸው ነው ተባለ
cd
ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል።

ፓርቲው እንዳለው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ ጆሮ አላገኙም፡፡

ጉዳዩንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱን አትቷል፡፡

በአንድ አካባቢ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ በቤተክርስትያን ላይ የማውደም ተግባር ስምንት ጊዜ ሲፈፀም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አንድም ቀን አለመገለፁና በመንግስት በኩል መፍትሔ አለመስጠቱ ፓርቲውን እንዳሳሰበውም ተገልጿል፡፡
አንጋጫ ኪ/ምህረት ፣ ዳገት ሚካኤል ፣ የደርበን ሚካኤል ፣ ዋሻ መድሀኒዓለም ፣ መንክር ማሪያም ፣ ቀዝቀዝ ገብርኤል፣
ደማም እየሱስ እና ምስለ ዋሻ ጊዮርጊስ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መውደማቸውን ከፓርቲው መግለጫ ለመረዳት ተችሎአል።

ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት በኩል ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት የቃጠሎው ምክንያት ተጣርቶ ድርጊቱን የፈፀመው አካል በህግ ተጠያቂ እንዲሆንና ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገለፅ እንዲሁም በሕዝብ አመኔታ የሚጣልባቸው ተቋማትን የማውደም ተግባር ወደፊትም እንዳይደገም በመንግስት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ በአፅንኦት ጠይቋል።

ጉዳዩን በማስመልከት ለምስራቅ ጎጃም የባህልና ቱሪዝም አንድ ሰራተኛ በመደወል ያነጋገርናቸው ሲሆን እሳቸውም አብያተ ቤተክርስቲአናቱ መቃጠላቸውን አረጋግጠውልናል። ስማቸው እንዲገለጽ ፣ ድምጻቸውም እንዳይወጣ የፈለጉት እኝህ ሰራተኛ፣ በቃጠሎው የተነሳ በህዝቡና በመንግስት በኩል እንዲሁም በህዝቡና በቱሪዝም ኮሚሽን በኩል ውዝግብ ተነስቷል።

መንግስት ድርጊቱን የፈጸሙት የሙስሊም አክራሪዎች ወይም የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው ሲል፣ ህዝቡ ደግሞ አክራሪዎች አይደሉም በማለት እየተከራከረ መሆኑን ሰራተኛው አብራርተዋል። የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤትም የችግሩ መነሳ በውል ባይታወቅም በአክራሪዎች ምክንያት እንዳልሆ በውል እንደሚያምን አክለው ገልጸዋል። የመንግስት አካሄድ ትክክል አይደለም ያሉት ሰራተኛው፣ ህዝቡ መንግስትን አናምንም ባይል ኖሮ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችሉ ነበር ብለዋል።

አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ጉልላታቸው አካባቢ እንደተቃጠለ፣ ታሪካው ቅርሶች ሳይወድሙ በህዝቡ ጥረት እንደተረፉ እኝሁ ሰራተኛ በዝርዝር አስረድተዋል።

Single Post Navigation

Leave a comment