addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 2, 2013”

በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የቦንድ ምንተፋ በተቃዋሚዎች የድምጽ ማእበል እየታመሰ ነበር

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን የሚያዉለበልቡ ብቻ ሳይሆን የለበሱም ነበሩ።የኢትዮጽያ መንግስት አባይን ለመገደብ በሚል ስም ቦንድን ለመመንተፍ የሚያደርገዉን ሴራ እንቃወማለን አባይ ከመገደቡ በፊት ነጻነት፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህ ለመላዉ ኢትዮጵያን ያሻል በማለት በዘር በሃይማኖት ሳይለያዩ እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች ድምጻቸዉን ያሰማሉ።
dsa
ቁጥራቸዉ የተመናመነ ግለሰቦች ሃፍረት በተሞላበት መልኩ ወደ አዳራሹ ቢያመሩም ከመካከላቸዉ አንዳንዶቹ አንዳንዶቹ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የሟቹን መለስ ዜናዊ ቲሸርት በመልበስ ቢንጎማለሉም በፍርሃት እየነፈሩ መሆናቸዉ ግን ያስታዉቅ ነበር። “ተከብረሽ የኖርሽዉ ባባቶቻን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም” በማለት ኅብረ-ዜማን የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን “ተመልከቱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዝግጅት ቢያዘጋጁም የኢትዮጵያን ባንዲራን ለማዉለብለብ ግን ፍላጎቱ የላቸዉም! እኛ ግን በአባይ ስም አትነግዱ ስንላችዉ የኢትዮጵያን ባንዲራ እያዉለበለብን ነዉ” ይላሉ።
xz
“እኛ ኢትዮጵያዉያን ነን ወደ አዳራሹ ለመግባት የዘር መለዮ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ የሚያሻን” ብሉዉ ለመደራደር ቢሞክሩም አዘጋጆቹ የአባይ ጉዳይ በዘር የተደለደለ እንዲመስል አድርገዉታል። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ከሰላሳ የሚያንሱ የቦንድ ተመንታፊዎች በሰአት 400 ዶላር በሚከፈልበት አዳራሽ ዉስጥ ሲገቡ ተስተዉሏል። በአዳራሹ ዉስጥም መዝጋቢ ሰዉ እንደሌለ ፣እንኳን ደህና መጣቹ ባይ እንዳልነበረ አንድ በተክለ ሰዉነቱ የስብሰባዉን አዘጋጆች የዘር መስፍርት የሚያሟላ ልቦናዉ ግን ለኢትዮጵያዊነቱ የጸና ግለሰብ ዉስጥ ገብቶ የታዘበዉን ገልጿል።
saተገቢዉ መልኩ ጥናት ያልተደረገበት አባይን የመገደቡ ሙከራ የዲፕሎማሲና የደህንነንት አደጋ አለዉ፤ ስልጣንን ለማራዘምና አቅጣጫን ለማስቀየር በሚደረግ ደፋ ቀና ነዉ አባይን መገደብ በሚል ስም የኢትዮጵያ መንግስት የሚንቀሳቀሰዉ የሚሉ ተቺዎች ብዙ ናቸዉ። ባንጻሩ አባይ አሁን አይገደብ የሚሉት ፖለቲካውዊ ክፋት የተጠናወታችዉ ናቸዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ለማጣጣል ይሞክራል። አንድ የጋራ እዉነታ ግን አለ በአባይ የመገደብ ጉዳይ ኢትዮጵያዉያን የተለያየ ሃሳብ የላችዉም! ህዝባዊ ዉክልና የሌዉ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ያላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃግድቡን አያርገዉ ባዮች ቢኖሩ እንጂ…

ጁን 30 በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የአትላንታ ጆርጂያ የቦንድ ምንተፋ ሂደት ክዉ ድንግጥም ያለ ነበር።

ሳዲቅ አህመድ
ECADF

ግብጦች ምን ነካቸው…!?

cd
ግብጦች ምን ነካቸው…!?

እስቲ ጠይቁልኝ ግብጦች ምን ነካቸው…

ኡኡታ ሚያሰሙት ካደባባይ ወጥተው…

ከፍቷቸው ነው አሉ ከመንግስት ተኳርፈው…

ታድያ ለምንድን ነው… ካገር የማይወጡ…

“ከነገሩ ጦም ይደሩ” ብለው የማያመልጡ…

ምን አሟገታቸው

ምን አስጨነቃቸው

ምንስ አስጮሃቸው

ዝም ብለው አይሄዱም ሀገሪቱን ጥለው…

እሺ እርሱም ይቅር ሀገር ጥሎ መሄድ እንደ አፍ አይቀልም፡፡

ለምን ዝ…….ም አይሉም ለበጎ ነው ብለው… ለምን ፀጥ አይሉም

“…ካለፈው ይሻላል የባሰ አታምጣ

አምላኬ ተመስገን አናበዛም ጣጣ…”

ብለው …ጫ! አይሉም ምን አስጨነቃቸው….

አደባባይ ወጥተው እንዲህ መጮሃቸው

እስቲ ጠይቁልኝ ግብጾች ምን ነካቸው…!
http://www.abetokichaw.com

ዶ/ር ብርሃኑ ከኢሳት ጋር በማገናኘት፣ኢሳትና ያገር ቤት ህዝብ ሊቆራረጡ ነው? የኢህአዴግ አዲሱ አዋጅ!!!

ImageImage

ዶ/ር ብርሃኑ ከኢሳት ጋር በማገናኘት፣ኢሳትና ያገር ቤት ህዝብ ሊቆራረጡ ነው? የኢህአዴግ አዲሱ አዋጅ!!!

ከኢሳት ጋር ማናቸውም ግንኙነት ያደረገ መረጃ የሰጠ ቃለ መጠይቅ ያደረገ እና ሌሎችንም ለመክሰስ ወያኔ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው

በኢትዮጵያ ምድር እንደ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የኢህአዴግን ስነልቦና የተረዳ ሰው የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ከቀድሞ መለስ ዜናዊ ጋር እኩል በእኩል ሊወዳደር፣ እንደውም አንዳንዴ የሚበልጥብኝ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ስለ ዶ/ር ብርሃኑ ሳስብ ብቅ የሚልብኝ እኔ የምታገለው ለልጆቼ ነው፣ልጆቼ በነጻነት የሚኖሩባትን ሀገር ለመፍጠር ነው ያላት ነገር ዛሬ በብዙ አባቶቻችን ልብ ውስጥ አለች፡፡
በርግጥ ዛሬ ዶ/ር ብርሃኑን ለማሞገስ አይደለም ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ ምንም እንኵ ማሞገስ ቢገባውም፡፡ ዋናው ዛሬ ለመጻፍ የተገደድኩበት ምክንያት በኢህአዴግ እጅ በገባ ማስረጃ የዶ/ር ብርሃኑ የተጠለፈ ንግግር ምክንያት ገዢው መንግስት አዲስ አዋጅ አዘጋጅቶ ኢሳት ላይ ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉትን ያገር ቤት ፖለቲከኞችና እንግዶችን እንዲሁም በኢሳት ላይ ከዚህ በኋላ የሚናገሩትን በሙሉ ከሽብርተኛው ቡድን ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ኢሳትን ካገር ቤት ህዝብ ጋር ለማቆራረጥ አስፈላጊውን ማስረጃ እያሰባሰበ መሆናቸውን ስመለከት ካልጻፍኩ ይቆጨኛል ብዬ ነው፡፡

በኢትዮዽያ በጉጉት የሚታየውና እየተደመጠ ያለው ኢሳት ለወያኔ ስጋት ከመሆኑ የተነሳ በተደጋጋሚ ጃም ቢደረግም ፈተናውን አልፎ በሚያጋልጣቸው የወያኔ መሰሪ አካሄድ የተነሳ ከህዝቡ ከፍተኛ ድጋፍ ማግኘቱ ስጋት የሆነበት የወያኔ መንግስት ኢሳትን ከህዝቡ ጋር ለማራራቅ ኢሳት አሸባሪ ከተባለው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በማዛመድ በፀረ ሽብር ህግ ለማስቀጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየሰሩ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡

መንግስት ኢሳትን የግንቦት 7 ንብረት ነው በማለት በርካታ ማስረጃዎችን አሰባስቦ እያጠናቀቀ ይገኛል፡፡ በነገራችን ላይ ባለፈው በአውራምባ ታይምስ የተለቀቀው የድምጽ መረጃ እስከ ክፍል አራት ድረስ ቀስ እየተባለ በመልቀቅ በተለያዩ ወገኖች የሚሰጡትን አስተያየቶችን በመሰብሰብ ለአዋጁ ዝግጅት ለመጠቀም ታስቧል፡፡ ይህንንምና ሌሎችን ማስረጃ በመያዝ ኢሳት የሽብርተኛ ሚዲያ ነው በማለት ከኢሳት ጋር ማናቸውም ግንኙነት ያደረገ/መረጃ የሰጠ/ቃለ መጠይቅ ያደረገ እና ሌሎችንም በማካተት እስከ 2007 ዓ.ም ምርጫ ድረስ ሚዲያውን ከህዝብ ለመነጠል እየተዶለተ ይገኛል፡፡ ስለዚህም ኢሳትና ማኔጅመንቱ አስፈላጊውን ዝግጅትና ሌሎች እርምጃዎችን እንዲወሰዱ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ በመቀጠልም ዶ/ር ብርሃኑ ገንዘቡን የተቀበለው ከኤርትራ ነው በማለት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኤርትራ በአለም አቀፍ መንግስት ማዕቅብና ሌሎች መገለሎች የደረሰባት በመሆኑ የዶ/ር ብርሃኑን እንቅስቃሴ ለመግታት ያተቀደ ተግባር ነው፡፡
ኢሳትን እንወደዋለንና!!!!!!
Source http://freedom4ethiopian.wordpress.com/

Post Navigation