addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 22, 2013”

የካድሬው የፍቅር ደብዳቤ (አቤ ቶኪቻው )

cccc
የካድሬው የፍቅር ደብዳቤ
(አቤ ቶኪቻው ) funny,8-)

መሠረት ገና ስምሽን ስጠራው የአገራችን የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ የደረሱበትን የላቀ ደረጃ እያስታወስኩ…

ልቤ ሃሴት ታደርጋለች፡፡ በዚህ ጊዜ፣ “እንኳንስና ከእርሷ፣ ከስሟ ፍቅር ቢይዘኝ ምን ይገርማል”?! ስል አስባለሁኝ፡፡
መሲ ከሁሉ አስቀድሜ አንቺን የፈለግኩሽ ለጊዜያዊ መሳለጫ ሳይሆን ቀጣይነት ላለው ፍቅር መሆኑን ልገልጽልሽ እወዳለሁ፡፡

የኔ ቆንጆ ከመሬት ተነስቼ እንደ ማንም ጎረምሳ ዳሌሽን፣ ፀጉርሽን እና አጎጠጎጤሽን አይቼ ብቻ የወደድኩሽ አይምሰልሽ፡፡
እንዲያ ስል ደግሞ አካላዊ ውበትሽ አይማርከኝም ለማለት አይደለም፡፡

ዓይኖችሽ ውስጥ ቅንነት፣ ታማኝነት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ በሥልጣን ያለአግባብ አለመበልፀግ በአጠቃላይ አስሩንም
የሥነ ምግባር መርሆዎች ይነበቡበታል፡፡

የጥርሶችሽ አቀማመጥ እና አደራደር በአገራችን ያለውን የብሔር ብሔረሰብ እና ሕዝቦች በመፈቃቀድ እና በመቻቻል
እንዲሁም በእኩልነት አብሮ መኖርን ይመስላል፡፡

ገበያ ተኮር በሆነው ግብርናችን የሚመረተው፣ በማዳበሪያ ብቻ ሳይሆን በግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ልዩ እገዛ በቅሎ
የሚዘናፈለውን የምርጥ ዘር ሰብልን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተከታተለ ሰው ፀጉርሽን ሲመለከት “የት ነው የማውቀው?”
ብሎ ግር ሳይለው አይቀርም፡፡ አንድ ናቸዋ”

ጡቶችሽ የሽብር ጥቃት እና ሕገ መንግሥታዊውን ሥርዓት ለማፍረስ የሚሞክሩ የጎዳና ላይ ነውጠኞችን ለመከላከል ዘብ እንደቆሙ መንታ ፌዴራል ፖሊሶች ቀጥ ብለው ላያቸው ከአሁን አሁን ተኮሱ የሚል ድንጋጤን ይፈጥራሉ፡፡
(አበበ ቶላ፤የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች፣2002)

ከመምህር ግርማ ይልቅ የሕዝብ መፈተኛ የሆነው የሰሞኑ ድርጊት

za
በተላያዩ ብዙ ፈተናዎች መሀከል አልፈው መምህሩ ዛሬ ያሉበት ደረጃ ደረሱ፡፡ ዛሬ እንደድሮው የሚታለል ሕዝብ እያነሰ በእሳቸው ትምህርሕርት ራሱን እያወቀ ለእግዚአብሔር የሚንበረከክ ሕዝብ እየበዛ መጣ፡፡ ፈታኞቹ ግን ዛሬም ተስፋ አልቆረጡም፡፡ ፈተናው ግን የአንዱ የመምህር ግርማ ሳይሆን የሕዝብ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም ፈተናውን መወጣት የሕዝብ ድርሻ ነው፡፡ እስከዛሬ ሕዝብ እስከሚገባው በሚል መምህሩ ብቻቸውን ፈተናዎችን ሁሉ በመጋፈጥ መስዋዕት ሆነው ሕዝቡን ለዚህ አብቀተውታል፡፡ ይሄው ሰሞኑን በሰማንው ድርጊታቸው በገሃድ ማንነታቸውን ነገሩን፡፡ እሳቸው ባሉበት ቢሆን ጥሩ ነበር አስለፍልፈው ውደ ሲኦል ይሸኙላቸው ነበርና፡፡ በእስጥፋኖስ ቤተክርስቲያን መምህር ያስተምሩበትን የነበረውን መድረክ አፈረሱ፣ በመደረኩ ላይ ተደርድረው የነበሩ የቅዱሳን ስቀላትን ቀዳደዱ፣ አላማቸው ነበርና የእግዚአበሔር ቃል የሚነገርበትን አጋንንት የሚነዱበትን ጉባዔ አስታጎሉ፡፡ እና እነዚህ “ሰዎች” ማን ናቸው? በመጨረሻም ደብዳቤ ፅፈው ቤተክርስቲያኒቷ ግድግዳ ላይ ለጠፉ፡፡ መምህር የነበሩት በቅድስት አገር እየሩሳሌም ነበር፡፡
የተጻፉት ደብዳቤዎችና ይዘታቸው
የመጀመሪያው ደብዳቤ በ28/08/2005 የተጻፈ በቅዱስ እስጥፋኖስ የደብሩ አስተዳዳሪ በአባ ሚካኤል ታደሰ የተፈረመ ነው፡፡ ለመምህር ግርማ ወንድሙ ይላል፡፡ የዚያን ያህል ባይካበድም እንደ እንድ ማህተብ ያለው ደብዳቤ ሥህተቱ እዚሁ ይጀምራል፡፡ ደብዳቤው ሕጋዊ ፕሮቶኮል እስከጠበቀ ድረስ ስማቸውና ማዕረጋቸው በትክክል መጻፍ አለበት፡፡ እኔም አዚህ መምህር እያልኩ የሚጸፈው የተለመደውንና በሕዝብ የታወቀውን ብዬ እንጂ የመምህሩ የአሁኑ ማዕረግ ከላይ የጠቆምኩት መለአከ መንክራት ነው፡፡ ይዘቱ በ2003 ዓ.ም. በአቡነ ቀውስጦስ በተጻፈ ደብዳቤ መምህር መታገዳቸውን ያትትና በአለታወቀ ምክነያት ግን እስከዛሬም መምህር እያስተማሩ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሆኖም ብዙዎቻችሁ ከቀድሞው የደብሩ አስተዳዳሪ መለአከ ሰላም ዘላለም አሴይ እንደሰማችሁት መምህር እዛ ቦታ ላይ የሚያስተምሩት ሕጋዊ በሆነ ደብዳቤ ተጋብዘው ነው፡፡ ከቀድሞው የቤተክርስቲያኒቷ ፓትሪአርክ ብፁዕ አቡነ ጰውሎስም ሕጋዊ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው የደብዳቤውም ቀጅ በእጃቸው እንደሚገኝ መልአከ ሰላም ዘላለም እሴይ ተናገረዋል፡፡ እንደው እሳቸውን ማጣቀሱ አግባብ ስለሆ እንጂ እኔ ራሴ ያ ደብዳቤ መድረክ ላይ ሲነበብ ሰምቻለሁ፡፡ ደብዳቤው የተጻፈውም በሕዝብ ጥያቄ እንጂ መምህር ጠይቀው አይደለም፡፡ ደብዳቤውም የትም ሄደው ማስተማር የሚያስችላቸውን ፍቃድ የሚገልፅ ነበር፡፡ የተጻፈውም አቡነ ቀውስጦስ እገዳ ጻፉ በጸባለበጽ በ2003 ዓ.ም፡፡ እውን የተባለው የአቡነ ቀውስጦስ ደብዳቤ አለ? ከአለስ በምን አግባብ ነው? ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ ይህ የደብሩ አስተዳዳሪ የጻፉት ደብዳቤ ተጨባጭ ምክነያትን ከማቅረብ ይልቅ በተደጋጋሚ ሕገ-ወጥ በሚል ቃል ታጭቋል፡፡ በአጻጻፍ ቀርጹና ሥርዓቱ ግን ከዚህ በታች ከምገጸው ከመንበረ ፓትሪአርክ ጸ/ቤት ተጻፈ ከተባለው ደብዳቤ የተሻለ ነው፡፡ ለመንበረ ፓትሪአርኩ ጸ/ቤትና ለሌሎችም አካላት ግልባጭ ይላል፡፡
ሁለተኛው ደብዳቤ በ08/09/2005 የመንበረ ፓትሪአርእ ራስጌ (heading paper)ወረቀት የተጻፈ፣ የመንበረ ፓትሪአረኩ ጽ/ቤት የሚል ማህትም ያለበት፣ ፊርማ ያለበት ግን የፈራሚው ሥም የሌለበት ነው፡፡ ይዘቱ በብዛት ከመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ይወጣል ተብሎ ለማመን የሚያዳግት፡፡ ቃላቶቹ ያለታረሙና በየተኛውም ሕጋዊ ደብዳቤ መታየት የሌለባቸው፤ ለምሳሌ ሥርዓተ-አለበኛ፣ ሕገ-ወጥ፣ የመሳሰሉት፡፡ ሲጀምር ጉዳዩ ይልና በአስቸኳይ በደብሩ በተባለው ቀን፣ የደብዳቤው ቁጥር ተጠቅሶ የተደረገው አገዳ የጸደቀ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ የጻፈው ለደብሩ ነው፡፡ ለመምህሩ ግልባጭ የለውም፡፡ ባለጉዳይ እሰከሆኑ ድረስ በግልባጭ እንዲያውቁት መደረግ ነበረበት፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያው ደብዳቤ የተጻፈው ለመምህር ግርማ ነው፡፡ በሌላላ የተለየ ደብዳቤ ካልሆነ በስተቀር የፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የላኛው ደብዳቤ የደረሰው በግልባጭ ነው፡፡ እንደ ደብዳቤዎች አጻጻፍ ሥርዓት ከላይ የተጻፈውን ደብዳቤ ለማጽደቅ የፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ሌላ ደብዳቤ መጻፍ የለበትም፡፡ ከደብዳቤው ጋር የሚቃረንና እርምት የሚያስፈልገው ነገር ኖሮ ኃላፊነቱን ካለበት እንጂ፡፡ ውሳኔው ቀድሞውኑ ተወስኗል፡፡ ለመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የተደረገው እንዲያውቀው ግልባጭ ነው፡፡ እዚህ ላይ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ደብዳቤ አጽፍም አይደለም ግን የሚጽፈው ኃላፊነት ስላለበት ማስተካከያ/እርምት ነው እንጂ ድጋፍ ሊሆን አይገባም፡፡ እንዲህ ያሉ ውሳኔውች ሌሎች ከውሰኑ በኋላ ማጽደቅ ሳይሆን ባይሆን ራሱ ወስኖ ለሌሎች ማስተላለፍ ነውና የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ድርሻ፡፡ ደግሞ ስንት ዘመን በግልፅ የነበረውን መድረክ አስቸኳይነቱ ለምን? ይዘት በዋናው ንባብ አጥማቂና ፈዋሽ ነኝ በማለት (መምህርን መሆኑ ነው) ይላል፡፡ መምህር አጥማቂም ፈዋሽም ነኝ ብለው አይደለም ሰው የአገልግሎቱ ተጠቀሚ የሆነው፡፡ አኛ ራሳችን የሚካሄደውን የፈወስና ወንጌል አገልግሎት በአይናችን ስላየን በጆሮአችን ስለሰማን እንጂ፡፡ እሳቸው ከሁላቸው በተሻለ የአምላካቸውን ክብር ያውቁታል፡፡ የሚያድነው የእግዚአበሔር የስሙ ኃይል ነው እኔ አገልጋዩ ነኝ ከማለት በቀር እኔ ፈዋሽ ነኝ ሲሉ ሰምተናቸው አናውቅም፡፡ ደብዳቤው እንደምንም ተንገዳግዶ ሌላ ፖለቲካ የሚመስል ነገር ለመጥቅስ የሞክራል ቤተክርስቲያናችን ከተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት፣ ቤተ መንግስት፣ ትላልቅ ሌሎች ተቋማት አቀሪያቢያ መሆኑንና በአካባቢውም የመምህር ጉባዔ የጸጥታ ችግር እንደፈጠረ የከሳል፡፡ በመጨረሻም ለፖሊስና ለጸጥታ ኃይሎች ትብብርን ይጠይቃል፡፡ እንዚህ ኃይሎች ግን እንዲያወቁበት የተደረገ ነገር የለም፡፡ ይህን ምንአልባትም አዛው በደብሩ አስተዳዳሪ የተፈበረከ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ባላወቀው መልኩ በሥሙ ወንጀል እየተሰራ ሊሆን ስለሚችል ማጣራቱ ወሳኝነት አለው፡፡ ከመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤትም እውን የወጣ ከሆነ ፈራሚው ማነው? ይዘቱስ የዚህን ያክል ጽ/ቤቱን በሚያስገሚት ሁኔታ እንዴት ሊወርድ ቻለ፡፡ አግባብነቱስ እንዴት ይታያል? በመጀመሪያ ላለተጠየቀው መልስ መስጠቱ (የመጀመሪያው ደብዳቤ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ለመጠየቅ ሳይሆን ለማሳወቅ ነበርና)፣ ለመምህሩ ግን እንዲያወቁት አልተደረገም፡፡ የሕዝብስ ጉዳይ በመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የሚታየው እንዴት ነው?ሕዝብን ወይም ተወካዩቻቸውን ሳያናግሩ?
ምን ይሁን፡በየትኛው ደረጃ ያለ የቤተክርስቲያኒቷ መሪም ይሁን አካል የምዕመንን እንጂ የተሿሚዎችን ብቻ ድምጽ እሰማ በቤተክርስቲያኒቱ እንደፈለገው የመሆን መብት ሊኖረው አይገባም ማንም ቢሆን አግባብ ያሌለው ነገር ሰርቶ እነደሆነ በሕግ እንዲጠየቅ፣ መንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤቱ በእዚህ ነገር እውን ካለበት በሕዝብና በሕግ አግባብ ሊጠየቅ ይገባዋል መምህር ግርማ ለሕዝብ ጠቃሚ ናቸው እስከተባለ ድረስ ጉባዔያቸውን የሚያውኩ ግለሰቦች በሕግም በቤተክርስቲያኗ ደንብም እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡
እግዚአብሔር መልካሙን ሁሉ ያሳስበን!
Source: http://memhirgirma.wordpress.com/page/2/

ሀገራችን ኢህአዴግ አክራሪነትን እንደሚያሰሰጋት ተሰጋ!

mn
ሀገራችን ኢህአዴግ አክራሪነትን እንደሚያሰሰጋት ተሰጋ!

ይቺ ጨዋታ ፍትህ ጋዜጣ አዲስ ታምስ መጽሄት ከዛም ልዕልና ጋዜጣ ባደረጉት መተካካት አሁን ተራውን ለተቀበለችው አዲሲቱ ፋክት መፅሄት የተላከ ነው፡፡ እስቲ የድረ ገፃችን አንባቢዎች ደግሞ ከተመቻቸው ያንበቧት ተብላ የተለጠፈች ናት!

ርዕሴ እንዳይረዝምብኝ ሰግቼ ነው እንጂ፤ “ሀገራችን ኢህአዴግ አክራሪነት እንደሚሰጋት ተሰጋ (ድርብ ሰረዝ) ሁላችንም ይሄንን ጉዳይ እንዋጋ (አሁንም ድርብ ሰረዝ) ኋላ ይቆጨናል ሲያስከፍለን ዋጋ…(ቃል አጋኖ) ብለው ደስ ይለኝ ነበር፡፡

እንግዲህ ጥናት አትኚዎች እና ምርምር አድራጊዎች ከፈለጉ ተመራምረው የምለውን “ፉርሽ” ያድርጉት እንጂ የእኔ አነስተኛ ጥናት ግን በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቷን በጣም እያሰጋት ያለ አንድ አደገኛ ነገር እንዳለ አመላክቶኛል፡፡ እርሱም ኢህአዴግ አካራሪነት ነው፡፡

በተደጋጋሚ ኢህአዴግዬ እንደነገረችን ሀገራችን የኃይማኖት አክራሪነት ያሰጋታል ተብለናል፡፡ አረ ምን መባል ብቻ በዚህ የተነሳ የተለያዩ እርምጃዎች እና እርግጫዎች እየተወሰዱብን አይደል እንዴ…

እኔ ሳስበው (አረ ምን እኔ ሳስበው ብቻ ሁላችንም እንደምናውቀው … የሀይማኖት አክራሪነት ለአንድ ማህበረሰብ ከባድ ችግር ነው፡፡ ሀይማኖተኞች እምነታቸውን ለራሳቸው በቅጡ ማመናቸው ብቻ አልበቃ ብሏቸው “ሌላ እምነት የሚያምን የተረገመ ነው” ብለው ማሰብ ሲጀምሩ ጦሱ ያኔ ይጀምራል፡፡ ይህ ችግር እጅግ ሲበረታ ውጤቱ በአለማችን ላይ ያየናቸውን በርካታ አሰቃቂ ጉዳቶች መንስኤ ወደ መሆን ያመራል፡፡ ይሄ ደግሞ ያማርራል፡፡ ይደብራልም፡፡ እዝች ላይ ምልክት ያድርጉልኝ….

አረ ቆይ ወዳጄ እስቲ በቅጡ ሰላምታ እንሰጣጥ … እንዴት አሉልኝ… ጤናዎ እንዴት ነው… ከዶክተር ቴውድሮስ ወዲያ የመጡት ጤና ጥበቃ ሚኒስትር እንዴት ናቸው… ምንውሳ ድምጻቸው ብዙ አይሰማም…! አንገታቸውን ደፍተው እና ድምፃቸውን አጥፍተው ለእኛ ጤና እየደከሙ ስለሆነ ነው… ይበሉ እና እስቲ ያስደስቱኝ በሞቴ!

ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ካነሳን አይቀር እኒህ ሰውዬ “ፖዘቲቭ” ሆነው ተገኙ የሚባለው ነገር እንዴት አዩት…

ይሄን ጊዜ እርስዎ በልብዎ …ታድያ ለአንድ የኢህአዴግ አባል ፖዘቲቭ መባል ብርቅ ነው እንዴ… ብለው፤ አምባ ገነንነት ፖዘቲቭ፣ ሙስና ፖዘቲቭ፣ ኢመልካም አስተዳደር ፖዘቲቭ፣ ጉራ መቸርቸር ፖዘቲቭ፣ መሬት መቸርቸር ፖዘቲቭ፣ ትዕቢት ፖዘቲቭ፣ ማን አለብኝነት ፖዘቲቭ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት ፖዘቲቭ… አባል ሰብሳቢነት ፖዘቲቭ ኡ ኡ… ደከመኝ… ፖዘቲቭ… እያሉ ሲደረድሩት ታየኝ፡፡

እኔ እንኳ በግሌ የኢህአዴግ አባላት እና አባታት ከዚህ ሁሉ ችግር አብረው የሚኖሩ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ ያላመኑ ብጹሃን ናቸው እንዲል አብዮታዊ ዴሞክራሲ ስለ ድርጅታችን የሚወራውን ክፉ ባለማመን ለእናት ድርጅቴ ያለኝን ታማኝነት ማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

እና ዶክተር ቴውድሮስ ከሌሎች የኢህአዴግ አባላት ተለይተው “መልካም ስብዕና ፖዘቲቭ” ናቸው ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ ይህንን ነገር ያወጋሁት አንድ ወዳጄ መጀመሪያ በጥርጣሬ አያየኝ “…አንተ ሰውዬ እኒህን ሰውዬ ማመስገን አበዛህ ሀገርህ ናፈቀችህ መሰለኝ…” ብሎኛል፡፡ እንደርሱ አባባል ከውጪ ጉዳዩ ሰውዬ ጋር ጠጋ ጠጋ ያበዛሁት ከውጪ ወደ ውጫሌ ወይም ወደ ሰላሌ ወይም ወደ ጉለሌ ለመመለስ ባለኝ ፅኑ ፍላጎት ነው… (ለዚህ ወዳጄ አስተያየት ትንሽ ፈገግ እንበልለት እና እንቀጥል…)

እውነቱን ለመናገር ሰውየውን “መልካም ስብዕና ፖዘቲቭ” ያልኳቸው ትዊተር ስለሚጠቀሙ የመሰለው ካለ “ኤክስ” ነው የሚያገኘው፡፡ በእርግጥ እርሱም አንድ ቁምነገር ነው… በማህበራዊ ደረ ገጽ በኩል ለማህበረሰቡ ቀረብ ብሎ ትችቱንም ሙገሳውንም መስማት ጥሩ ነገር ነው፡፡ በነገራችን ላይ በዚህ በዚህ ጎላ ካሉት ተቀናቃኝ ፓርቲ ሰዎች አቶ ግርማ ሰይፉ እንደ ዶክተር ቴውድሮስ ሁሉ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አሁንም በነገራችን ላይ ባለፈው ጊዜ ብሄራዊ ቡድናችንን ለማበረታታት እነዚሁ ሁለት ሰዎች ጎን ለጎን ቆመው በማየቴ በአራዶቹ ቋንቋ “አቦ ሙድ አለው” ብዬ አድንቄያለሁ፡፡

የሆነ ሆኖ ባለፈው ጊዜ የእኔን ሀሳባዊ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ዝርዝር ለማስቀመጥ ስሞክር ዶክተር ቴውድሮስን በሶስተኛ ደረጃ አካባቢ ነበር ያስቀመትኳቸው፡፡ በእግር ኳስ “ድሪም ቲም” የሚባለው አይነት ነው ነገርየው፡፡

ቆይ እስቲ ይሄንን ነገር ድጋሚ ጊዜ ወስጄ እሰራውና፤ የራሴን ካቢኔ ለማደራጀት እሞክራለሁ፡፡ ከአሸባሪውም ከተሸባሪውም ቀላቅዬ ለዛች ሀገር ሁነኛ እና “የሰው ማኛ” የምላቸውን በየሙያ መስካቸው አደራጅና ለኢትዮጵያ ህዝብ አቀርባለሁ፡፡ ከዛ… ከዛማ… በቃ እነበብን እንስቃለን…! ማን ያውቃል አንድ ቀን ሁሉም በፖለቲካ አሰላለፉ ሳሆን በችሎታው የሚሾምባት በየእውቀቱ የሚቀመጥባት ሀገር ትኖረን ይሆናል፡፡

እኔ የምለው አቶ ሃይለማሪም ደሳለኝ አዳዲስ የሚኒስቴሮች ሹመት አንበሻበሹ አይደለም እንዴ….! በዛ ሰሞን “አዲስ ካቢኔ የሚቋቋምበት ምክንያት የለም… የእርሳቸውን ራዕይ ለማስቀጠል እርሳቸው የያዙትን ይዘን እንጂ አዲስ ጥንስስ አንጠነስስም አዲስ መጠጥም አናመርትም” ብለውን አልነበር እንዴ…!

ታድያ አሁን ይሄ ሁሉ አዳዲስ የካቢኔ ሹመት እና ሽረት አዲስ ጠጅ የመጥመቅ ያክል አይደለም አንዴ… ይሄ በአዲስ መልክ የሚያሰክሩ አዳዲስ ጥንስሶችን ማበጀት አይደለም እንዴ…! አንዳንዶቹን ሹመቶችማ ልብ ብለን ስናያቸው ማስከር ብቻ ሳሆን “ጢንቢራ” የሚያዞሩ እንደሆኑ ከወዲሁ ያስታውቃሉ፡፡ (ጢንቢራ ምን ነበር…!) እውነቴን እኮ ነው እስቲ አሁን የፖሊስ ሹመኛን መንገድ ትራስፖርት ሚኒስትር ማድረግ ምን ይሉት ሹመት ነው…

አረ ሳልጠይቅዎ ወዳጄ ክረምቱ እና የባቡር መንገድ ግንባታው አንድ ላይ ሆነው እንዴት አደረጉዎት… የአዲሳባ መንገድ እንኳንስ ለባቡር፣ ለቴሌ ሲቆፈር፤ እንዴት እንደሚመር… አወቀዋለሁ፡፡ እና ገና የመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስትር ብዬ ስል በአዕምሮዬ የመጣው እሱ ነው… እና እንዴት አደረግዎት… ብሎ መጠየቅ ወገኛ ደንቡ ነው… እሱን ተወው ብሎ መመለስም የአንባቢ ደንብ ነው፡፡ እንግዲህ ጽናቱን ስጠን ብሎ መመረቅስ ሌላው የወገና ደንብ አይደል እንዴ…

የእኔ ነገር አንዱን ስጥል ሌላውን ስቀጥል ዋና ጨዋታችን ተቆርጣ ልትቀርኮ ነው… እስቲ አዲስ መስመር ላይ እንውረድና እንቀጥላት…

ሀገራችን ኢህአዴግ አክራሪነት እንደሚሰጋት ተሰጋ… አልኩዎ አይደል…!ማን ሰጋ… ብለው የጠየቁኝ እንደሁ እኔ እልዎታለሁ፡፡

ከላይ እዝችጋ ምልክት ያድርጉልኝ ያልኩዎትን ቦታ አስታወሷት…

…የሀይማኖት አክራሪነት ለአንድ ማህበረሰብ ከባድ ችግር ነው፡፡ ሀይማኖተኞች እምነታቸውን ለራሳቸው በቅጡ ማመናቸው ብቻ አልበቃ ብሏቸው “ሌላ እምነት የሚያምን የተረገመ ነው” ብለው ማሰብ ሲጀምሩ ጦሱ ያኔ ይጀምራል፡፡ ይህ ችግር እጅግ ሲበረታ ውጤቱ በአለማችን ላይ ያየናቸውን በርካታ አሰቃቂ ጉዳቶች መንስኤ ወደ መሆን ያመራል፡፡ ይሄ ደግሞ ያማርራል፡፡ ይደብራልም፡፡ እዝች ላይ ምልክት ያድርጉልኝ…

ብዬዎት ነበርኮ… የሀይማኖት አክራሪነት ኢትዮጵያን ያሰጋታል ብሎ መንግስታችን በንጹሀን ዜጎቻችን ላይ ሳቀር እርምጃ፣ እርግጫ፣ ግልምጫ፣ ቡጥጫ፣ ጡጫ… ሲወስድ አይተነዋል፡፡

እኔ ግን እላለሁ ሀገራችን ከሀይማኖት አክራሪነት ይልቅ ኢህአዴግ አክራሪነት ያሰጋታል፡፡ በኢህአዴግ አክራሪነትም ከእኛ የባሱቱ ካድሬዎች ለራሳቸው የከደሩት አንሷቸው ከኢህአዴግ ሌላ ፓርቲ (የጭፈራ እንኳ ቢሆን)፣ ከኢህአዴግ ሌላ ግንባር (የቴስታ እንኳ ቢሆን)፣ ከኢህአዴግ ሌላ ድርጅት (የንግድ እንኳ ቢሆን)፣ ከኢህአዴግ ሌላ እናት (ወላጅ እንኳ ብትሆን) አለኝ ብሎ የሚመካ ካለ እርሱ የተረገመ ነው ብለው ያወግዛሉ፡፡ ማውገዝ ብቻ ደግሞ አይደለም ያግዛሉም እንጂ….

በዚህ የተነሳ ስማቸውን ጠቅሰን የማንጨርሳቸው ወዳጆቻችን እስር ቤት የገቡት፡፡ በዚህ የተነሳ ነው ቁጥራቸውን ቆጠረን የማንጨርሳቸው ሰዎች ከሀገር የተሰደዱት፡፡ በዚህ የተነሳ ነው ስንትና ስንት የሀገረሰብ ድረ ገፆች ለሀገራቸው ባዳ የተደረጉት፡፡ በዚህ የተነሳ ነው ስንት እና ስንት ሰዎች ከሀገር ተሰደዱት በዚህ ተነሳ ነው…

እስቲ የሚሰማ ካለ ድምጻቸ ጮክ አድርገን እንናገር፤

ከኢህአዴግ ውጪም ፓርቲ ከኢህአዴግ ውጪም ድርጅት ከኢህአዴግ ውጪም ግንባር አለ፡፡ እኔ ብቻ ነኝ ትክክል ከእኔ ውጪ ሌላው የተረገመ ነው ማለት አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት ደግሞ ለማንም አይበጅም፡፡ እንኳንስ ለሌላ ለራሱ ለአክራሪውም አይበጀው፡፡ ስለዚህ ውድ የኢህአዴግ ወዳጆቼ ኢህአዴግ አክራሪነትን በጋራ እንከላከል!

ወዳጄ ግድየሎትም የዛሬ ወጋችንን እዝች ላይ እንቋጨው…

abe tokichaw

በቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን አሉ

1111111111111
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል።

እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ፍርድ ቤት በቀጠሮአቸው ቀን እንዳይቀረቡ መከልከላቸውን ለመቃወም ለበላይ አካላት ደብዳቤ በመጻፋቸው ምክንያት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የገለጹት እስረኞቹ ፣ ጉዳዩን ለቂሊንጦ ዋና አስተዳዳሪ ኦፊሰር አምባየ ስናመለክት ” እስከ መግደል ድረስ እርምጃ ለመውሰድ መብት አለን፣ አርፋችሁ ካልተቀመጣችሁ በጥይት እንቆላችሁዋለን፣ የምግብ ማቆም አድማ እናደርጋለን ብትሉም ለእኛ ደንታችን አይደለም” በማለት እንደመለሱላቸውና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እየተዛተባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። ለ4 ቀናት ምግብ ማቆማችንን ተከትሎ ማንም ስላልጠየቀን በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን ያሉት እስረኞቹ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ እገዛ እንዲያደርግላቸውም እስረኞቹ ተማጽነዋል።

ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ህክምና ከተከለከሉት መካከል ቀጀላ ገላና ገቢሳ፣ በላይ ኮርሜ ባይሳ፣ መንግስቱ ግርማ አየሳ፣ ተፈራ ቀበኔ ገመቹ፣ ሙላት ሽመልስ እጀታ፣ ኢብሳ አህመድ ሙሀመድ እና ሸምሰዲን የተባሉት ሲገኙበት ፣ ድብደባ ከተፈጸመባቸው መካከል ደግሞ ሌሜሳ ዲሴሳ፣ አለሙ ተሾመ ቦኬ፣ ዘርፉ መልካ አባይ፣ ቀበታ ገቢሳ ነባራ፣ ቀበና ነጋሳ ነገራ፣ መልካሙ መገርሳ፣ አዳሙ ሽፈራው፣ ቡልቻ ሱሪሳ ጌታቸው አብራ ቶሎሳ፣ ስለሺ ሶሬሳ፣ የፓርላማ አባል የነበረው ጉቱ ወልዴሳ፣ አለማየሁ ቶሎራ፣ በርሲሳ ሊሙ፣ ብርሀኑ እምሩ፣ ኡርቄና አጀማ፣ አህመድ አብደላ ጎዳ እና ለማ በዳዳ ይገኙበታል።

በኦነግ ስም በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት እስረኞች ያቀረቡትን ተማጽኖ ተከትሎ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ቀይ መስቀል ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግ የድርጅቱ ስልክ አይነሳም። የታራሚዎች ፍትህ አስተዳዳር ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ ብርሀኔ ሀይለስላሴ ስልክ ብንደውልም፣ ስልካቸው ቢጠራም አይነሳም።

ኢሳት በእስረኞች ላይ የደረሰውን ድብደባ ተከትሎ አካባቢው በደም በመበከሉ እንዲታጠብ መደረጉን መዘገቡ ይታወቃል። የቂልንጦ እስር ቤት ዋና ሃላፊ በቅጽል ስሙ ሻቢያ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በእሰረኞች ላይ መፈጸሙን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሰማያዊ ፓርቲ ሌላ ሰልፍ ጠራ

ከሣምንታት በፊት ባካሄደው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ አላገኙም ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26 / 2005 ዓ.ም ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን አስታውቋል።
9999
ከሣምንታት በፊት ባካሄደው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ አላገኙም ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26 / 2005 ዓ.ም ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን አስታውቋል።

ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ መንግሥት ለጥያቄዎቹ ትኩረትም አለመስጠቱን ገልጿል።

ሰማያዊ ፓርቲ ከ1997ቱ ምርጫ ወዲህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የተባለውን የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄደው ግንቦት 25/2005 ዓ.ም እንደነበር ይታወሣል፡፡
አቶ ይልቃል ጌትነት – የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
አቶ ይልቃል ጌትነት – የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

በዚሁ ሠልፍ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲስተካከሉ፣ የፖለቲካ እና የሕሊና እሥረኞች እንዲፈቱ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ መግባት እንዲቆም እና የተፈናቃሉ ዜጎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ ጠይቆ መንግሥት ለጥያቄዎቹ ምላሽ ካልሰጠውም ከሦስት ወራት በኋላ ሌላ ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ ነበር፡፡

የሰማያዊ ፓርቲን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለው እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ ያደረሰን ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት።

Source http://amharic.voanews.com/content/blue-party-call-for-a-new-demo-07-19-13/1705518.html

በወረባቡ የአንድነት አባላትን ጨምሮ 45 ወጣቶች ታስረዋል

09
በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ አይሰጣችሁም፣ ዘርና ማዳበሪያም አታገኙም የሚል ማስፈራሪያ በካድሬዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በተለይ ከታሰሩት 45 ወጣቶች መካከል 3ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ የእድሜ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እና ወጣቶቹ ከመስኪድ ውጭ በአካባቢው ሜዳ ላይ ሲሰግዱ ስለተወሰዱ አብዛኞቹ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁና እስካሁንም እየፈለጓቸው መሆኑ ታውቋ፡፡ ወጣቶቹም ከታሰሩ ከሳምንት በላይ የሆናቸው ሲሆኑ እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህን ዜና እስክናሰራጭ ድረስ ከታሳሪዎች መካከል ከፊሉ በደሴ ቀሪዎቹ ደግሞ በሐይቅ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እስር ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም ከወረዳውና ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደርና የፀጥታ ክፍል ስለጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ አይሰጣችሁም፣ ዘርና ማዳበሪያም አታገኙም የሚል ማስፈራሪያ በካድሬዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በተለይ ከታሰሩት 45 ወጣቶች መካከል 3ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ የእድሜ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እና ወጣቶቹ ከመስኪድ ውጭ በአካባቢው ሜዳ ላይ ሲሰግዱ ስለተወሰዱ አብዛኞቹ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁና እስካሁንም እየፈለጓቸው መሆኑ ታውቋ፡፡ ወጣቶቹም ከታሰሩ ከሳምንት በላይ የሆናቸው ሲሆኑ እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህን ዜና እስክናሰራጭ ድረስ ከታሳሪዎች መካከል ከፊሉ በደሴ ቀሪዎቹ ደግሞ በሐይቅ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እስር ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም ከወረዳውና ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደርና የፀጥታ ክፍል ስለጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5043#sthash.Qb0GWFJe.dpuf

በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

122
በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት በፕሬዘዳንቱ ቢሮ አካባቢ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ፡፡ ሰልፉን ያካሄዱት የዚህ ዓመት የክረምት የተፈጥሮ ሳይንስ የድግሪ መርሃ ግብር የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱበት ምክንያት ቀደም ሲል ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ትምህርቱን የሚከታተሉት ለ 6 ዓመታት እንደሆነ እና 4 ዓመቱን ከተከታተሉ በኋላ የባችለር ኦፍ ሳይንስ ድግሪ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው፤ ቀሪው 2 ዓመት ደግሞ መምህር ለመሆን የሚያስችላቸውን የስነ ትምህርት ዘዴ(ፔዳጎጂ) እንደሚወስዱ መዋዋላቸው ተጠቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት 4 ዓመት የክረምት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችም በተዋዋሉት መሰረት ድግሪያቸው እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የዪኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ክንዴ በበኩላቸው ተማሪዎቹ ሰልፉን እንዲበትኑ እና ከተወካዮቻቸው ጋር መነጋገር እንደሚቻል በገቡት ቃል መሰረት እንዳናገሯቸው ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም የተማሪዎቹ ተወካዮች ከፕሬዘዳንቱ ጋር ከተወያዩ በኋላ ፕሬዘዳንቱ አሰራሩን እንደማያውቁና በሌሎች የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎችም ተመሳሳይ አሰራር ካለ አጣርተው ከ3 ቀናት በኋላ ምለማጣራትላሽ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም የዪኒቨርስቲው ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እና ፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት ስለ ጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5045#sthash.LkcI1r2B.dpuf

Post Navigation