addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 16, 2013”

በቂልንጦ እስርቤት የእሰረኞች ደም በድብደባ እንደጎርፍ መፍሰሱን የአይን እማኞች ተናገሩ

ኢሳት ዜና :- አርብ ፣ ሀምሌ 6 2005 ዓም በእነ አቶ ተሻለ ኮርኔ መዝገብ : የተከሰሱ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ፍርድ ቤት የሚወስዳቸው ፖሊስ ያጣሉ። በቅጽል ስሙ ሻእቢያ እየተባለ የሚጠራውን የእስር ቤቱን ሀላፊ ሲጠይቁት ቀጠሮአቸው ለ4 ወር መራዘሙን ይነግራቸዋል..
BODIES
እስረኞቹም ” ከ2 አመታት በላይ የላፍትህ ታስረን በመጨረሻ ብይን በሚሰጥበት ወቅት ለ4 ወራት ተራዝሟል መባሉ ተገቢ አይደለም” በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የሚላክ ፊርማ ማሰባሰብ ሲጀምሩ ማረሚያ ቤቱ መረጃው ይደርሰውና 69ኙ እሰረኞች በ20 ተከፋፍለው ወደ ተለያዩ የማረሚያ ክፍሎች ወይም ዞኖች እንዲበተኑ ይደረጋል።

አርብ ጧት ሌሎች እስረኞች ወደ ውጭ እንዳይወጡ ከተደረገ በሁዋላ ፣ ሻእቢያ በሚባለው የእስር ቤቱ ሀላፊና ከውጭ በመጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲደበደቡ ይደረጋል። አስተባባሪ ናቸው የተባሉትን 18 እስረኞችን እንደገና በማውጣት በሰደፍና እና በዱላ ከቀጠቀጡዋቸው በሁዋላ 8ቱ ራሳቸውን ሲስቱ ወደ እስር ቤቱ የህክምና ክፍል ይወሰዳሉ። ችግሩ ከአቅሙ በላይ መሆኑን የእስር ቤቱ የህክም ክፍል በመግለጹ፣ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

የአይን እማኞች ለኢሳት እንደገለጹት እስረኞቹ የተደበደቡበት ቦታ በደም በመጨቅየቱ አርብ እለት በውሀ ሲታጠብ አርፍዷል።

ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል በላይ ኮርሜ ፣ ተፈሪ ቀብኔሳ እና መንግስቱ ግርማ የሚባሉ ይገኙበታል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአህኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና እሰረኞቹ መደብደባቸውንና የተወሰኑት ሆስፒታል መግባታቸውን መረጃው እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

ዶ/ር መረራ “ድርጊቱን በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተን መልስ በማጣታችን መንግስት ሆን ብሎ በፖሊሲ ደረጃ ይዞ የሚያካሄድ ይመስላል” ሲል አክለዋል።

የእስር ቤቱን ሀላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

ሰበር ዜና ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ታገቱ

09
Hanna Metasebia
ሰበር ዜና
————–
ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ታገቱ
——————————

————————————————–
በጎንደርና በደሴ በደረሰበት ፖለቲካዊ ኪሳራ የተበሳጨው ኢህአዴግ ዛሬ ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላትን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች አግቷል፡፡ የታጋቾቹን ስም ዝርዝርና የታሰሩባቸውን አከባቢዎች ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ እናደርጋለን፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም ጠየቁ


የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች አመጽ እንደቀጠለ ነው። ደቀመዛሙርርቱ (ተማሪዎቹ) ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም በመጠየቅ በዛሬው የሥላሴ ክብረ በዓል ላይ የሚከተሉትን መፈክሮች አሰምተዋል።
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!
ልጆቹን የማይጠይቅ አባት አለን?
ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!
የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ!
ጢሞቴዎስ ሆይ፣ አደራህን ጠብቅ፡፡ (፩ኛጢሞ. ፬÷፳)
ችግራችንን የሚሰማንና መፍትሔ የሚሰጠን አባት ዐጣን!
የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ትኩረት ይስጡን!
ሙስናን በቃል ሳይኾን በተግባር እንዋጋ!
ተማሪዎች ሙስናን በመዋጋታቸው ሊበረታታቱ እንጂ ሊባረሩ አይገባም!
ከአየህጉረ ስብከቱ ቤተ ክርስቲያንን አምነን ወጥተን ለረኀብ ተጋለጥን፡፡
ኮሌጁ በመዘጋቱ ከተመገብን ሰባተኛ ቀናችን ነው፡፡
አቤቱ የኾነብንን አስብ፡፡
ኮሌጁን የሚዘጋው የከፈተው ሲኖዶስ ነው፡፡
ኮሌጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የግለሰቦች አይደለም!
እውነትን ሙስና አይደለም መቃብር አያሸንፈውም!
ጌታ ሆይ፣ ከመቅደሳችን ውስጥ የሙስናን እሾኽ ንቀል!
እየሞትንና እየተራብን ሙስናንና ዘረኝነትን እንቃወማለን!
ሙስና ከቤተ ክርስቲያናችን ይወገድ!
ከሓላፊነት መሸሽ በራሱ ሙስና ነው!

ሐራ ተዋሕዶ ድረ ገጽ እንደዘገበው በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚያካሂዱት ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ምእመኑ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
አቡነ ጢሞቴዎስ ደቀ መዛሙርቱን በፖሊቲከኝነት መወንጀል ጀምረዋል
የተማሪዎች መማክርት የኮሌጁን አስተዳደር በሕግ ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው
St Trinity College Disciples demonstrating at the gate of the Patriarchate
ደቀ መዛሙርቱ በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር በተቃውሞ ትዕይንት ላይ

ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ከመሳለምና ገንዘብ ከመስጠት/ከመመጽወት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ በመጠየቅ ቀጥተኛ ተሳታፊ መኾን እንደሚገባቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አሳሰቡ፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ማሳሰቢያውን ያስተላለፉት፣ በዛሬው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል አጋጣሚ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለተገኘው ምእመን የኮሌጁ አስተዳደር በትምህርት አመራሩና በአካዳሚያዊ መብቶቻቸው ላይ ስለሚፈጸመው በደል በገለጹበት ወቅት ነው፡፡

አንጋፋው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ÷ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የመምሪያ ሓላፊዎችን፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችን፣ የዩኒቨርስቲ መምህራንን፣ ተመራማሪዎችን፣ በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልኾኑ ድርጅቶች በከፍተኛ ሓላፊነት ላይ የሚገኙ ቀደምት ምሩቃንን ያፈራ መኾኑን ደቀ መዛሙርቱ ለምእመናኑ አስታውሰዋል፡፡

ኮሌጁ አገልግሎቱን የሚያከናውነው ‹‹በእናንተው ገንዘብ ነው›› ያሉት ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹የምእመኑ ሥራ ገንዘብ መስጠት ብቻ አይኹን፤ ስለ ቤተ ክርስቲያናችኹ ጠይቁ፤ ይህ ኮሌጅ የሕዝብ ነው፤ ነገር ግን የገጠር አብያተ ክርስቲያን እየተዘጉ፣ መናፍቃን እንደ አሸን ፈልተው ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደ ቅርጫ ሥጋ ሊከፋፍሏት ባሰፈሰፉበት ወቅት በግለሰቦች እየተዘጋ ነው›› በማለት ከአስተዳደሩ ጋራ ሙስናን፣ ኑፋቄንና ብልሹ አሠራርን በመቃወም የገቡበትን ውዝግብ በሰፊው አብራርተዋል፡፡

ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ ከዐሥር ጊዜያት በላይ በጋራና በተወካዮቻቸው በመመላለስ ጥያቄዎቻቸውን ሲያቀርቡ መቆየታቸውን የገለጹት ደቀ መዛሙርቱ በጥበቃ እየተገፈተሩ ያለውጤት ከመንገላታት በቀር ያገኙት ነገር ባለመኖሩ ምእመኑን፣ ‹‹በየብሔረሰቡ በተለያየ ቋንቋ ቤተ ክርስቲያንን የምናገለግል ልጆቻችኹ ነን፤ ሙሰኞቹ ኀያላን ናቸውና ርዱን! ነገ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በሁለት ሰዓት በምናደርገው እንቅስቃሴ አብራችኹን ቁሙ!!›› ሲሉ በከፍተኛ አጽንዖት ተማፅነዋል፡፡

Short URLhttp://www.zehabesha.com/amharic/?p=5271

Post Navigation