addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 7, 2013”

Ethiopian Torture Victim Speaks Out video

cc

በመንግስት ጥያቄ የጎንደርን ሰላማዊ ሰልፍ ለሐምሌ ሰባት አዘዋውረናል!!

ssከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት ህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልት በመንደፍ የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡… ሁልጊዜም የሀገሪቱን ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ 30ና የሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ 50ኛ ዓመት ቁጥር 4 በሚደነግገው መሰረትም ከህዝቡ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ማወቅ ለሚገባው አካልና ለዞኑ አስተዳደር አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ በመግባት ከ80 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በማሳተም ከ20 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በጎንደር ከተማ አሰራጭቷል፡፡ በመዋቅራችን አማካኝነትም የቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን እንዲያሰማ እያደረግን ባለንበት ወቅት በክልሉ መንግስት የማደናቀፍና የማሰር ርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡

በክልሉ መንግስት አባሎቻችን ላይና አመራሮቻችን ላይ በሕገ ወጥ መንገድ ህገ መንግስታዊ መብታቸው እየተገፈፈ፤ ሰብዓዊ ክብራቸውን በመጣስ ላይ ነው፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ የፓርቲያችን አባላት የሆኑት አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ የፓርቲውን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለምን በተናችሁ ተብለው ከሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ ከሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ፣ አቶ አምደማሪያም እዝራ እና አቶ ስማቸው ዝምቤ ከሰኔ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው፡፡ እንዲሁም በወገራ አቶ ጀጃው ቡላዴ ሰኔ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ታስሮ ተለቋል፡፡ አቶ ጋሻው ዘውዱ ላይ ጥይት በመተኮስ የመግደል ሙከራ የተደረገ ሲሆን ሮጦ ለማምለጥ ችሏል፡፡ በአልፋ ጣቁሳ ወረዳ መምህር አዋጁ ስዩም ከሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ሲሆን ሁሉም የታሰሩት ለምን ቀሰቀሳችሁና ወረቀት አሰራጫችሁ በሚል ነው፡፡ ፓርቲያችንም የዞኑን መስተዳድር አፋኝነትና ህገወጥነትን እያወገዘ የታሰሩ አባሎቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በፅኑ እንጠይቃለን፡፡ የታሰሩ አባሎቻችንም ህገወጥ እስሩን በመቃወም ከትናንት ጀምሮ የርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡

የዞኑ አስተዳደርና የከተማው ም/ከንቲባ በአንድ በኩል ሰላማዊ ሰልፋችንን ለማፈን ርምጃ እየወሰዱ በሌላ በኩል የህዝቡ ሰላማዊ ትግል ወዳድነት ስላስደነገጣቸው የእንነጋገር ጥሪ በ25/10/2005 ዓ.ም አቀረቡ፡፡ በተለይም የከተማው ም/ከንቲባ የሆኑት አቶ ጌትነት አማረ ከሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር በ27/10/2005 ዓ.ም 2 ሰዓት የፈጀ ድርድር ካደረጉ በኋላ ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ዕለት በጎንደር የተማሪዎች ምረቃ ስላለና የመንገድ ምረቃ ስላለ እንዲሁም ፖሊስ ግምገማና ስልጠና ላይ በመሆኑ በቂ የጥበቃ ኃይል አይኖረንም በሚል ቀኑን አዘዋውሩልን የሚል ጥያቄ በማቅረባቸውና ይህም ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በጎንደር የሚደረገውን ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ እሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ተዘዋውሮ እንዲደረግ ፓርቲያችን ወስኗል፡፡

በዚህም መሰረት ህዝባዊ ንቅናቄያችን የቆመለትን ዓላማ በምንም ህገ-ወጥነት የማይቀለበስ መሆኑን እየገለፅን ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን፡፡ ሰላማዊ ትግል የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የቆምንለት ክቡር አላማ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንን በመረዳት አሁንም እንደበፊቱ ሁሉ በቁርጠኝነት ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን፡፡ የጎንደርና አካባቢው ሕዝብም ይህንን አፋኝ ስርዓት በማውገዝ ከጎናችን በመቆም ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሀገራዊ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አበባ

‹አዲስ አበባ ውስጥ ግብረ ሰዶማዊነት ተስፋፍቷል፡፡ reporter

mm‹‹አዲስ አበባ ውስጥ ግብረ ሰዶማዊነት ተስፋፍቷል፡፡ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎችና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በየመንደሩ፣ በየሥርቻው፣ በየጓዳውና ጉድጓዳው ራሳቸውን ደብቀው ያደፈጡ ሁሉ ቢቆጠሩ ብዛታችን ያደላል፡፡ መጠሪያ ስማችን ጌይ ወይም ግብረ ሰዶማዊ የሚል ሳይሆን ‘ዜጋ’ የሚለው ነው፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ያልገቡ ሌሎች ወገኖችን ደግሞ ‹‹ቀጥ›› በሚል እንጠራቸዋለን፡፡››

ይህንን የተናገሩት ከሰባት እስከ 32 ዓመት ድረስ ሕይወታቸውን በግብረ ሰዶማዊነት ያሳለፉት ግብረ ሰዶማውያንና ግብረ ሰዶማውያት (ወንዶችና ሴቶች)፣ ‹‹ዝምታው ይሰበር ትውልድ ይዳን በእኛ ይብቃ›› በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ዶክሜንተሪ ፊልም (ቪሲዲ) ውስጥ ባካሄዱት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው፡፡

በቸርችል ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ ‹‹ስለኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሠራር›› የሚል ታካይ ርእስ ባለውና ለምረቃ በበቃው በዚሁ ፊልም ውስጥ ይህንኑ ቃለ መጠይቅ ካካሄዱት ከእነዚህ ግብረ ሰዶማውያን ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው ሕጋዊና መደበኛ ሚስት አግብተው፣ ትዳር መስርተውና ልጆች ወልደው በሽምግልና ዕድሜያቸው ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ አዛውንቶች አሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹‹አባባ መሽቷል እባክዎን ወደ ቤትዎ ሂዱ›› እያሉ ወጣት ግብረ ሰዶማውያን ይቀልዱባቸዋል፡፡ ይሳለቁባቸዋል፡፡ እነዚህም አዛውንቶች ታዋቂነታቸው በ‹‹ዜጎች›› ዘንድ ብቻ ስለሆነና በአካባቢያቸው ማኅበረሰብ ዘንድ የሚታወቁት ባለትዳርና የልጆች አባት ስለሆኑ ከማኅበረሰቡ ዘንድ እንዳይገለሉና ተከብረው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፡፡

የእምነት ቃላቸውን ከሰጡት ግብረ ሰዶማውያን መካከል በቅጽል ስሙ ‹‹ኤሊያና›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ወጣት፣ ግብረ ሰዶም መጀመርያ የተፈፀመበት በሐዋሳ ከተማ የሰባት ዓመት ሕፃን ሳለ ነበር፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ መኖር ከጀመረ 32 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ እስካሁን ባሳለፈው ሕይወት ውስጥ ለወሬም የማይመች፣ ከባህል ውጭ የሆነ፣ ሕይወትን እስከመጥላት የሚያደርስና አሰቃቂ የሆነ ወሲብ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ሲፈጸም እንደኖረ ነው የተናገረው፡፡

ግብረ ሰዶማውያን የሚፈልጉትን ቆንጆ ወንድ አንዲት ሴት ይዛባቸው ከሄደች ወይም ካወጣችው ‹‹ዓይነጥላ›› ወሰደችብን እያሉ እንደሚያማርሩ ያወሳው ኤሊያና፣ በድሬዳዋ፣ በጅቡቲ፣ በየመንና በሳዑዲ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ይህንኑ የግብረሰዶም ሥራ ያከናውን እንደነበርም አልሸሸገም፡፡ ጅቡቲ የገባው ከድሬዳዋ እስከ ደዋሌ ድረስ በባቡር ከዚያም እስከ ጅቡቲ ደረስ በእግሩ ለአምስት ቀን ያህል ከተጓዘ በኋላ ነው፡፡ ከጅቡቲም በአንድ የሞተር ጀልባ ተደብቆ ወደ የመን እንደተሻገረና በመቀጠልም ሳዑዲ እንደገባ አመልክቷል፡፡

‹‹በአገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የአምስት ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው የግብረ ሰዶማውያን ሠርጎችን አይቻለሁ፡፡ ይህን ዓይነቱንም ሠርግ መንግሥት ወይም ማዘጋጃ ቤትና ባህል አያውቀውም፡፡ እኛው ራሳችን ነን የምንፈጽመው፡፡ ይህም ሆኖ ፍቅርን ስለማናውቅ በጋብቻ ፀንተን አንቆይም፡፡ ጋብቻው ግፋ ቢል የሚቆየው ለሦስት ወራት ያህል ብቻ ነው፤›› ብሏል፡፡
ሚስት የሚሆን ወንድ በሠርግ ሥነ ሥርዓቱ ቀን ቅንድቡን ተቀንድቦ፣ ቻፕስቲክ ተቀብቶ፣ ፊቱ ላይ ማድረግ የሚገባውን ሜክአፕ ሁሉ አድርጎ፣ ፀጉሩን ተሠርቶና ቬሎ ለብሶ ይቀርባል፡፡ በሥነ ሥርዓቱም ላይ ኬክ እንደሚዘጋጅ ነው የተናገረው፡፡

ሠላሳ ሁለት ዓመታት ያህል በግብረ ሰዶም ሕይወት የቆየ፣ ስምንት ጊዜ ድል ባለ ሠርግ አግብቶ የወንድ ሚስት የነበረና በቅጽል ስሙ ‹‹አጠለል›› እየተባለ የሚጠራው ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ግብረ ሰዶማዊነትን መተዳደሪያው አድርጎ የያዘው ሲሆን፣ ይህንንም የጀመረው የስምንት ዓመት ሕፃን ሳለ ነው፡፡ የሴት ሚስት ላለውና በዚህ ላይ ደግሞ 17 የወንድ ሚስቶች ካሉት ግብረ ሰዶማዊም ጋር ትዳር ለመጀመርያ ጊዜ ‹‹17ኛ የወንድ ሚስት ሆኜ ነው ያገባሁት›› ሲል አጠለል ይናገራል፡፡

የግብረ ሰዶማውያን መለያቸው ከአለባበሳቸው እንደሚጀምር ይናገራል፡፡ ሁልጊዜ ቁምጣ ሱሪ እንደሚያደርጉ፣ ጠባብ ስኪኒ እንደሚያዘውትሩ፣ ጠልጠል ያለ ቦዲ ቲ ሸርት በመልበስ እምብርት እያሳዩና ያለ ካልሲ ጫማ እያደረጉ እንደሚሄዱ፣ ፀጉራቸውን ሊሞዚ መቆረጥ፣ ጆሯቸውን በተለየ ቦታ ላይ በመበሳት ጌጣ ጌጥ ማስገባትና ሎቲ ማንጠልጠል ናቸው፡፡ ከውጭ አገር የሚረዷቸውም ሰዎች አሉ፡፡ በተለይ ዳያስፖራዎች የጠለልን አድራሻ ይዘው ነው የሚመጡት፡፡ ሲጠሩት ይቀበላቸዋል፡፡ በኢንተርኔትም የሚገናኙበት መንገድ አለ፡፡ በዚህም የተነሳ ደንበኞቻቸው ሲመጡ አይቸገሩም፡፡ በሚፈልጉበት ቦታ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

‹‹ሪች›› በመባል የምትጠራዋ ሌላው ግብረ ሰዶማዊት (ሌዝቢያን) ወደዚህ ሕይወት ውስጥ የገባችው በጓደኛዋ ግፊት እንደሆነ፣ በዚህም ሕይወት ከገባች ስምንት ዓመት እንደሆናትና መተዳደሪያዋም ይኸው እንደሆነ ገልጻለች፡፡ ሁለት ቋሚ የሴት ደንበኞችም እንዳሏት ተናግራለች፡፡ አንደኛዋ ደንበኛዋ አዲስ አበባ ውስጥ ኦሎምፒያ አካባቢ፣ ሁለተኛዋ ደንበኛዋ ደግሞ በሐዋሳ ከተማ ይኖራሉ፡፡ በጠሩዋት ቁጥር ትሄድላቸዋለች፡፡፡ ጠሪዎቿም በጣም ሀብታሞች እንደሆኑ ነው የተናገረችው፡፡ በዚህም እርካታ እንደምታገኝ፡፡ ከተመሳሳይ ጾታዋ ጋር ካልሆነ በስተቀር ለወንድ ወይም ለተቃራኒ ጾታ ፍላጎት እንደሌላት አስረድታለች፡፡

ብሩክቱ ሌላዋ ግብረ ሰዶማዊት ናት፡፡ ሪታ የምትባል ክልስ የልጅነትና አብሮ አደግ የሆነች ጓደኛ ነበረቻት፡፡ በልጅነታቸው ትምህርት ቤት ሲገናኙና ከትምህርት መልስ ወደየቤታቸው ለመሄድ ሲለያዩ ይሳሳማሉ፡፡ ይህን ዓይነት ሁኔታ ቢያዘወትሩም የልጅነት ነገር እንጂ ወደ ሌላ ስሜት አይመራቸውም ነበር፡፡ ከዓመት ዓመት እያደጉና ነፍስ እያወቁ ሲመጡ በመካከሉ ሪታ ወደ ኢጣሊያ አቀናች፡፡

ሪታ ከሄደችበት ወደ ኢትዮጵያ ስትመለስ ግን ተለውጣ መጣች፡፡ የመሳሳማቸው ሁኔታ ወደ ልጅነት መንፈስ መሄዱ ቀርቶ ወደ ወሲብ ቀስቃሽነት ተሻገረ፡፡ በዚህም የተነሳ ውለው ሲያድሩ ፍቅር መሠረቱ፤ ‹‹እወዳታለሁ ትወደኛለች፣ ከእሷ ጋር ግንኙነት ሳደርግ ታስደስተኛለች፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ከገባሁ ሰባት ዓመት ሆኖኛል፤›› ብላለች ብሩክቱ፡፡

ሁሉም ወንዶችና ሴቶች ግብረ ሰዶማውያን ኤችአይቪ ፖዘቲቭ እንደሆኑ፣ በዚህ ላይ ደግሞ የሥነልቡና ችግርና የአአዕምሮ ጭንቀት እንዳጋጠማቸው፣ በተለይም ኤሊያና የኪንታሮት በሽታ እንዳደረበት፣ ሁሉም ከዚህ አስከፊና አስነዋሪ ሕይወት ለመውጣት እንደሚፈልጉ በየተራ በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል፡፡

ሰኔ 23 ቀን 2005 ዓ.ም. በተከናወነው የዶክመንተሪ ፊልሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የሁሉም እምነቶች ተከታዮች፣ አባት አርበኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በዚህም ጊዜ መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) የማኅበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት ሊቀመንበርና የፊልሙ ዋና አዘጋጅ ዓላማውን ሲገልጹ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለው ግብረ ሰዶማዊነት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ትውልድንም ምን ያህል እየጎዳ እንዳለ ለማስገንዘብ ነው ብለዋል፡፡

ሦስት ዓመት በፈጀው ጥናታቸው የተገነዘቡት ነገር ቢኖር ከግብረ ሰዶማውያን መካከል አንዳንዶቹ ይህን ድርጊት ሕጋዊ እናደርገዋለን ብለው የሚዝቱና፤ ከፊሎቹ ደግሞ በተቃራኒ ድርጊቱ ለሕይወት ጎጂ በመሆኑ መውጣት አለብን ብለው የወሰኑ መኖራቸውን ነው፡፡

የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 6/29 ግብረ ሰዶም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፡፡ አንቀጽ 6/32 ደግሞ በዚህ ተግባር የተገኘ ከቀላል እስከ እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ያስቀጣል ይላል፡፡ መምህር ደረጀ እንደሚሉት፣ የወንጀል ሕጉ ግብረ ሰዶምን ቢከለክልም ግብረ ሰዶማዊነት በአገሪቷ በድብቅ እየተስፋፋ ነው፡፡ ራሳቸውን አጋልጠው የሚወጡ ሰዎች ቢኖሩም ራሳቸውን ባላጋለጡት ተፅዕኖ ያደርስባቸዋል፡፡

ዶክመንተሪ ፊልሙ በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነት መኖሩን በግልጽ በሚመሰክሩ ሰዎች አማካይነት ለመንግሥትና ለኅብረተሰቡ ማሳወቅና ከድርጊታቸው ይወጡና ይታቀቡ ዘንድ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ ለማቅረብ ነው፡፡

በፊልሙ ወቅታዊ ሞቅታን ፈጥሮ መለያየት እንደማያስፈልግ የሚናገሩት መምህር ደረጀ፣ በሕፃናት ላይ ግብረ ሰዶማዊ ጥቃት የመፈፀም አካሄድ የሚከተሉትን ግብረ ሰዶማውያን ከወዲሁ ለማቆም በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በሥነ ምግባር ማኅበር ተደራጅቶ በቀጣይነት መሥራት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

በግብረ ሰዶም ሕይወት ለብዙ ዓመታት ማሳለፋቸውን በመጥቀስ የሕይወታቸውን እውነታ ለገለጹት የቀድሞ ግብረ ሰዶማውያን ከችግር የተነሳ መልሰው እንዳይገቡበት ኅብረተሰቡና መንግሥት ሊረዷቸው እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነት እየተስፋፋና ግብረ ሰዶማዊ ጥቃትም እየተፈጸመ ስለሆነ ድርጊቱ ከመስፋፋቱና ‹‹ለኛም መብት ይሰጠን›› የሚል ጥያቄ ከመነሳቱ በፊት መንግሥት ከእንጭጩ ሊገታው ይገባልም ብለዋል፡፡

የምረቃውም ታዳሚዎች ይህ ዓይነቱን እኩይና ትውልድ ገዳይ የሆነውን ድርጊት ለመግታት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ሲሆን፤ ከታዳሚዎቹም መካከል አርቲስት ተስፋዬ አበበ ግብረ ሰዶማዊነትን ለመግታት የሚያስችል በአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጠይቀው፣ ለኮሚቴውም ሥራ ስኬታማነት ቀስቃሽና ትምህርት አዘል መልዕክት ያላቸውን ልዩ ልዩ መዝሙሮች ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል፡፡
ethiopian reporter

Officials eye lack of landing tool in San Francisco crash that killed two

ሰበር ዜና ———— ኢህአዴግ ደንግጧል!! በአዲስ አበባ የአንድነት አባላትን ማሰር ተጀምሯል

09በአዲስ አበባ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት የበተነ የአንድነት አባል በአደራ ታሰረ፡፡
አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ መንግስት የማደናቀፍ ተግባሩን በአዲስ አበባም ጀምሯል፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ሙሉጌታ ተፈሪ የተባለውን የአንድነት ፓርቲ የወረዳ 15 አባል ካዛንችስ አካባቢ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስሯል፡፡ ሙሉጌታ ካዛንችስ አካባቢ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጭ መታሰሩን ፖሊስ ተናግሯል፡፡
የአባሉን መታሰር የሰሙት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ ግርማ ሰይፉና አቶ በላይ ፍቃዱ ካዛንችስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው ሙሉጌታ በህገወጥ መንገድ መታሰሩን በማስረዳት ተከራክረዋል፡፡ የጣቢያው ፖሊሶች ግን “ሙሉጌታን ያሰረው ፖሊስ ስለሌለ እሱ ሳይመጣ አይፈታም” በማለት “የአደራ እስር” ከጎንደር በተጨማሪ በአዲስ አበባም መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ አመራሮቹም “እኛም ወረቀቱን እየበተንን በመሆኑ እሰሩን” በማለት ተሟግተዋል፡፡
ዘግይቶ በደረሰን ዜና የአንድነት አመራሮች የታሳሪውን ጉዳይ መከታተላቸውን ተከትሎ ሙሉጌታ ተፈሪ ክቤ በተባለች ፖሊስ “ተመርምሮ” ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሊወሰድ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን አባላት ዛሬ ጠዋት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በመገኘት ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ህዝባዊ ንቅናቄውን በአዲስ አበባ ተደራሽ የማድረግ ተልዕኮ ተቀብለው ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ100ሺ በላይ የሆነ በራሪ ወረቀትም በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡
# millionsofvoice sforfreedom # Ethiopia # udj
ምንጭ ፍኖተ ነፃነት

Post Navigation