addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 9, 2013”

ወጣቶች በብዛት በዲሲዉ የአንድነት ስብሰባ ላይ ተገኙ !

zzzzበሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር፣ ጁላይ 5 ቀን ሕዝባዊ ስብሰባ በዋሺንገትን ዲሲ አካባቢ ባደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ከሕዝብ ጋር ተወያየ። በስብሰባዉ በአካል ተገኝነተዉ፣ አንጋፋዉ የቀድሞ የሰሜን አሜሪካ ቅንጅት ድጋፍ ማህበር አመራር አባል የነበሩት አቶ ብርሃን መዋ፣ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ የዉጭ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ተመስገን ዘዉዴ፣ ለሕዝቡ ንግግር አድርገዋል። አቶ ተመስገን የአንድነት ፓርቲ ስለጀመረዉ የሶስት ወራት የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴ ገለጻ የሰጡ ሲሆን ኢትዮጵያዉያን የተዘጋጁ ፔትችኖችን በመፈረም የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። በአገር ቤት የሰማያዊ ፓርቲ በጠራዉ ስብሰባ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች እንደተባበሩ፣ የአመራር አባላቱን በሰልፉ እንደተገኙ የገለጹት አቶ ተመስገን፣ አንድነት ትግሉን እስከረዳ ድረስ፣ ማንም ጠራ ማንም፣ በማናቸዉም ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ጎን እንደሚቆም አስረድተዋል። ብዙዎች እየታሰሩ፣ እንግልትና መከራ እየደረሰባቸው እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ተመስገን፣ ትግሉ ከመቼዉም በበለጠ ወሳኝ ደረጃ ላይ እንዳለም ገልጸዋል። xxአቶ ብርሃነ መዋ በበኩላቸው፣ የአንድነት ፓርቲ፣ በተለይም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ያለዉን ግንኙነት በጣም እንዲያጠክር፣ የመከሩ ሲሆን ኢትዮጵያዉያን በአንድነት እንጂ በተናጥል ከሰሩ ብዙ ዉጤት ማምጣት እንደሚያስቸግራቸው አስረድተዋል። በተለይም በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መብዛትና እርስ በእርስ መጠላለፍ ትግሉን እንደጎዳው የተናገሩት አቶ ብርሃነ መዋ ከተቃዋሚው ወገን ያለውን ያለመተባበር ችግር አስረግጠው ከነመፍትሄው አስረድተዋል። ሁሉም የራሱን ሕልውና ማ ዕከል የመሠረተ ድርጅት ስለሚመሰርት ትግሉ ውጤት እንዳላመጣ በንግግራቸው ላይ የጠቀሱት አቶ ብርሃነ መዋ “ተቃዋሚው አቶ መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ 18 ዓመት ተቀመጡ ብሎ ይተቻል። ራሳቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ስልጣኑ ላይ ለተመሳሳይ አመታት ቁጭ ብለውበታል። ስልጣን መቀያየርን ሁሉም መልመድ ይኖርበታል።” በማለት ተናግረዋል።

ትግሉን ወጣቶች እንዲመሩት መደረግ እንዳለበት አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ብርሃነ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለመመስረት ሁሉም ተቃዋሚ ኃይል በአንድነት ቆሞ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
ccበሌላም በኩል ይህን የዚህ ስብሰባ ሌላ ገጽታ ከኢትዮጵያ በቀጥታ ለተሰብሳቢዉ ንግግር ያደረጉ ወጣት የአንድነት አመራር አባላት መኖራቸው ነበር። አቶ በላይ ፍቃዱ የአንድነት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና የፍኖት ኤዲቶሪያል ሰብሳቢ እንዲሆም የአንድነት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊዉ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራ፣ በስካይፕ በአገር ቤት እየተደረገ ስላለዉ አገረ ሰፊ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴ በስፋት አብራርተዋል። ይሄም ፓርቲዉ በጣም የበሰሉ፣ የሰከኑና መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጁ በርካታ ወጣት አመራሮች እንዳሉት ለብዙዎች ያሳየበት ሁኔታ ነዉ የነበረው። – zxcከስብሰባው ተሳታፊዎቹ ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆኑቱ ወጣቶች መሆናቸው፣ የድጋፍ ድርጅት አመራር አባላትን በእጅጉ እንዳስገረመም አንዳንድ የውስጥ አዋቂዎች ጠቁመዋል። «የአንድነትን እንቅስቃሴ በፌስቡክና በሌሎች የማህበረሰብ ሚዲያዎች ብዙዎች እንደሚከታተሉትና በርካታ ለቴክኖሎጆ ቅርብ የሆኑት ወጣቶችን አንድነትን ለመደገፍና የትግሉም አካልን ለመሆኑ ከመቼዉም በላይ ፍላጎት እያደረባቸው መሆኑን የሚያሳይ ነዉ» ሲሉ አንዱ የቆዩ የአንድነት ድጋፍ ማህበር አባል ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ሲሆን በመቀጠልም በመቀሌ፣ በደሴ ተከታታይ ህሕዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚያደርግ ካወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል። ፓርቲዉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችንም እያደረገ ከሁለት ወራት በኋላ ለሚያደርገዉም የጠቅላላ ጉባዔ እየተዘጋጀ መሆኑ ሲታወቅ ጠቅላላ ጉባዔዉ ሲደረግ በርካታ ወጣቶች ወደ አመራሩ ይመጣሉም ተብሎ እንደሚታወቅ የውስጥ አዋቂ ምንጮች መረጃውን ሰጥተውናል።

በሌላ ዜና፦
በአዲስ አበባ የአንድነት አባላትን ማሰር ተጀምሯል-

ከዳግማዊ ቴዎድሮስ

የአንድነት ፓርቲ በስፋት የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል ህዝባዊ እንቅስቃሴ አዉጁ በሁሉም ክልሎች በተለያዩ ማኤዠናት ትልቅ ሥራ የተስራ ነዉ። በዚህም እንቅስቃሴ ከፍተኛ ዋጋም እየተከፈለ ነዉ። በአዲስ አበባ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት የበተነ የአንድነት አባል በአደራ ታሰሯል።

አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ መንግስት የማደናቀፍ ተግባሩን በአዲስ አበባም ጀምሯል፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ሙሉጌታ ተፈሪ የተባለውን የአንድነት ፓርቲ የወረዳ 15 አባል ካዛንችስ አካባቢ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስሯል፡፡ ሙሉጌታ ካዛንችስ አካባቢ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጭ መታሰሩን ፖሊስ ተናግሯል፡፡

የአባሉን መታሰር የሰሙት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ ግርማ ሰይፉና አቶ በላይ ፍቃዱ ካዛንችስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው ሙሉጌታ በህገወጥ መንገድ መታሰሩን በማስረዳት ተከራክረዋል፡፡ የጣቢያው ፖሊሶች ግን “ሙሉጌታን ያሰረው ፖሊስ ስለሌለ እሱ ሳይመጣ አይፈታም” በማለት “የአደራ እስር” ከጎንደር በተጨማሪ በአዲስ አበባም መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ አመራሮቹም “እኛም ወረቀቱን እየበተንን በመሆኑ እሰሩን” በማለት ተሟግተዋል፡፡

ዘግይቶ በደረሰን ዜና የአንድነት አመራሮች የታሳሪውን ጉዳይ መከታተላቸውን ተከትሎ ሙሉጌታ ተፈሪ ክቤ በተባለች ፖሊስ “ተመርምሮ” ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሊወሰድ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን አባላት ዛሬ ጠዋት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በመገኘት ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ህዝባዊ ንቅናቄውን በአዲስ አበባ ተደራሽ የማድረግ ተልዕኮ ተቀብለው ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ100ሺ በላይ የሆነ በራሪ ወረቀትም በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=4773#sthash.wzJ84xvR.dpuf

we have to help daniel Norway can forcibly deport him to dictatorships.

unity is power

 

  • Target: http://une.no/ UNE Grete Faremo Minister of Justice and Public Security
  • Sponsored by: Yared Elias

720120-1373328305-mainIt gives an impression when a person after 10 years in Norway detained for deportation to a dictatorship and crimes are to have stayed in the country following the rejection, and to have worked. How else will a paperless survive? Food must have, and it costs money. Roof over head costs. So clearly working. I can not fathom that there should be a criminal offense. I can not fathom that Norway has signed a deportation agreement with the Ethiopian intelligence servicesEthiopian secret agents and the regimes supporters,systematically placed with in Ethiopian community here in Norway,have been carefully montering,potografing and filming our poltical activites and oppostion movementes and reporting back to their superiors for years so please norway don’t send daniel to dictator regimes.

View original post

ዋይታ በደቡብ ነግሷል የብሄር ጥያቄ ተመልሷል በተባለ ማግስት ጥያቄው አገረሸ

1122በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጋሞጎፋ ዞን የምትገኘው ቁጫ ወረዳ ሰላም በር ከተማና አካባቢዋ ላለፉት ሁለት ቀናት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ስትታመስ መቆየቷን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ከስፋራው አጋልጠዋል፡፡

እንደ ምንጮቻችን ዘገባ በቁጫ ወረዳ የሚገኙ ከ200.000የሚልቁ ነዋሪዎች ያለ ፍላጎታቸው በጋሞጎፋ እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ሲቃወሙ ቆይተዋል፡፡‹‹እኛ ጋሞ ወይም ወላይታ አይደለንም››በማለት የማንነት ጥያቄ ያነሱት ቁጫዎች የራሳችን ቋንቋና ከጋሞም ሆነ ከወላይታ የሚለየን ባህል ያለን በመሆኑ ልጆቻችን በራሳችን ቋንቋ እንዲማሩ ይደረግ በማለት የማንነት ጥያቄ ሲያነሱ አመታት ተቆጥረዋል፡፡

የደቡብ ተወላጅ የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር ከተረከቡ በኋላ በመለስ አስተዳደር ምላሽ ያላገኘው ጥያቄያቸው መልስ ሊያገኝ እንደሚችል ተስፋ በማድረግ ሽማግሌዎችን በመምረጥ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰድደዋል፡፡አዲስ አበባ የመጡት መልእክተኞች ጥያቄያቸው በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካኝነት ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ ተገብቶላቸው ወደ መጡበት እንዲመለሱ ቢደረጉም መኖሪያ ቀዬአቸው ከደረሱ በኋላ ለእስር መዳረጋቸው የአካባቢውን ማህበረሰብ አስቆጥቷል፡፡

ፖሊስ ሽማግሌዎቹን በማሰር ሳይቆጠብ ቅዳሜ ምሽት ሌሎች ሰዎችን ከየቤታቸው በመለቃቀም ለእስር ዳርጓል፡፡ለፍኖተ ነጻነት በደረሰ መረጃ መሰረት ለእስር የተዳረጉ ሰዎች 15 የሚደርሱ ሲሆን ሙሉ ስማቸው የታወቀው ግን የአስሩ ብቻ ነው፡፡

1ኛ. አቶ ደፋሩ ዶሬ (የፋይናንስ ቢሮ ኦፊሰር)

2ኛ. አቶ ሻምበል ሻዋ (የፋይናንስ ቢሮ የሰው ኃይል ሥራ ሂደት ባለቤት)

3ኛ. አቶ አማኑኤል ጎቶሮ (የፋይናንስ ቢሮ ኦፊሰር)

4ኛ. አቶ ባንትይርጉ ሄባና (የፋይናንስ ቢሮ የገቢ አወሳሰን ኦፊሰር)

5ኛ. መሸሻ ዜማ (መምህር)

6ኛ. ባሻ ፋንታሁን ታደሰ (የማይክሮ ፋይናንስ ሠራተኛ)

7ኛ. ዶለቦ ቦንጃ (የመሰናዶ ትም/ቤት መምህር)

8ኛ. አቶ ቲንኮ አሻንጎ (የኅብረት ሥራ ማህበራት ኦፊሰር)

9ኛ. አቶ አበራ ገ/መስቀል (የትም/ት ኤክስፐርት)

10ኛ. አቶ ጴጥሮስ ሀላላ (ነጋዴ) ናቸው፡፡

እሁድ ማለዳ የተወካዮቹንና የወረዳውን ታዋቂ ሰዎች መታሰር የሰማው ህዝብ ከያለበት በመሰባሰብ ታሳሪዎቹ ወደ ሚገኙበት ፖሊስ ጣብያ በማምራት ፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ ያሰራቸውን እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡ፖሊስ እስረኞቹን ለመፍታት ፈቃደኛ ባለመሆኑም ከ5000 የማያንስ ህዝብ ፖሊስ ጣብያውን በመክበብ ‹‹እነርሱን በመወከል የማንነት ጥያቄያችንን እንዲያቀርቡ የወከልናቸው እኛ ነን ከፈለጋችሁ እኛን ልታስሩ ይገባል››በማለት የወኪሎቻቸውን መታሰር ተቃውመዋል፡፡

ፖሊስ ወኪሎቼን ፍታ በማለት የጠየቀውን የቁጫ ነዋሪ ከጣብያ ገለል ለማሰኘት በወሰደው የሃይል እርምጃ ብዙዎች መጎዳታቸውን የፍኖተ ነጻነት ምንጭ አጋልጧል፡፡ምሽት ላይ በወታደር ካሚዮን የተጫኑ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ወረዳው በመግባት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር መሞከራቸውንና ሺዎችን ለእስር መዳረጋቸውን ምንጫችን ጨምሮ ገልጻል፡፡

ስለ ሁኔታው ማብራሪያ የተጠየቁት የወረዳው ፓሊስ ጣብያ አዛዥ ‹‹ምንም አይነት የሃይል እርምጃ ፖሊስ አለመውሰዱን ከመናገር ውጪ ተጨማሪ ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ስልካቸውን ዘግተዋል፡፡

ኢህአዴግ የብሄር ጥያቄን እንደመለሰ በመግለጽ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ማክበር የጀመረ ቢሆንም ጥያቄው ተገቢውን ምላሽ አለማግኘቱ በቁጫ ወረዳ የተነሳው የማንነት ጥያቄ ማሳያ እንደሚሆን ፍኖተ ነጻነት ያነጋገረቻቸው ባለሞያዎች ገልጸዋል፡፡

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=4789#sthash.BjDJq0F0.dpuf

Breaking News: የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ ከግርማ ብሩና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ተወያየ

as
(ዘ-ሐበሻ)የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአቶ ግርማ ብሩና ከሌሎች የኤምባሲው ሃላፊዎች ጋር ረጅም ሰዓት የፈጀ ውይይት ማድረጉን ከኤምባሲ አከባቢ የተገኘ መረጃ አጋለጠ።

የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች እንዳጋለጡት ዛሬ ጁላይ 8 ከቀኑ 4pm ጀምሮ ዳዊት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ተገኝቶ ውይይት ያደረገው ስለምን እንደነበረ ባይታወቅም በድምጻዊ ሰለሞን ተካልኝ ምትክ ወያኔ ለመክፈት ላቀደው ሬዲዮ እንዲያዘጋጅ ሊሆን እንደሚችል የኤምባሲው ምንጭ ያለውን ግምት ገልጿል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም የገዢውን ፓርቲ የሚያስደስቱ ቪድዮችን በመልቀቅ ከትግራይ ኦንላይን እና ከአይጋ ፎረም የማይተናነስ ገዢውን ፓርቲ የሚያስደስቱ ሥራዎችን እየሰራ ነው በሚል የሚተቸው ዳዊት ከበደ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ከአቶ ግርማ ብሩ ጋር ከመገናኘቱ አስቀድሞ በቅርብ ወደ አሜሪካ ለአባይ ግድብ ጉዳይ መጥተው ያልተሳካ የገንዘብ ማሰባሰብ ካካሄዱት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎሮስ አድሃኖም ጋርም በስልክ መገናኘቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ በዲያስፖራው የሚገኙ የነፃው ፕሬስ ሚዲያዎችን በማጥቃት እየተወነጀለ እንደሚገኝ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ከሚሰጡ አስተያየቶች መረዳት ተችሏል።

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=5097

Post Navigation