addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 30, 2013”

ETVዬ፤ ይሄኛው መንገድ የት ያደርሰ ይሆን!?

AETVዬ፤ ይሄኛው መንገድ የት ያደርሰ ይሆን!?

አንድነት ፓርቲ ፤

“የፀረ ሽብር ህጉ ከሀገሪቱ ህገ መንግስት ጋር የሚፃረር በመሆኑ” ሊሰረዝ ይገባዋል አሉ፡፡

የኢቲቪው ጋዜጠኛ፤

ተቃዋሚዎች የሽብርተኞች ህግ ይሰረዝ እና ሀገራችን በሽብረኞች ትሞላ እንደ ሴሪያ እና እንደ ግብጽ ትበጣበጥ ይላሉ… እርስዎ በዚህ ላይ ምን የሚሰጡን አስተያየት አለ…?

አስተያየት ሰጪ፤

(ድንግጥ ብለው) “እንዴ… እንዴት እንደዚህ ይላሉ ነውር አይደለም አንዴ… መበጣበጥ ለማን ይጠቅማል… ይሄ ከአንድ ሀገር ሊመራ ካሰበ የፖለቲካ ፓርቲ አይጠበቅም…”

ድምፃችን ይሰማዎች፤

“የሼክ ኑሩ ግድያ የተቀነባበረ ድራማ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሟችንን የምናሰማው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ የምንሞትለት እንጂ የምንገድልበት ሀይማኖት የለንም፤ ስለዚህ የሼሁ ግድያ መንግስት ነው የፈፀመው” ሲሉ ይከሳሉ…

የኢቲቪ ጋዜጠኛ፤

ፅንፈኞቹ የሼህ ኑሩ ግድያ ድራማ ነው እንጂ አልሞቱም ይላሉ እርስዎ ይሄንን እንዴት ያዩታል…?

አስተያየት ሰጪ፤

(ግራ ተጋብተው) “እንዴ… እንዴት እንደዚህ ይባላል… ይሄ ጭካኔ ነው፡፡ ለእነርሱ ድራማ ቢመስላቸውም እኛ ግን የቀበርነው አባት ነው፡፡”

አንድነት ፓርቲ፤

“የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ደላሎችን ማሰር ብቻ መፍትሄ አይሆንም ስር ነቀል የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል” አለ፡፡

የኢቲቪ ጋዜጠኛ፤

ተቃዋሚዎች በቅርቡ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳታፊ የሆኑ ደላሎች መታሰራቸውን እንቃወማለን ብለዋል፡፡ እርስዎ በዚህ ላይ ምን የሚሰጡን አስተያየት አለ…?

አስተያየት ሰጪው፤

(ተደንቀው) “ይገርማል… እንግዲህ የህገ ወጥ ዝውውር ደላሎቹ ራሳቸው ናቸው ማለት ነዋ… ሰው እንዴት ወንጀለኛ አይታሰር ይላል… ወገኖቻችን ለከፋ አደጋ እየተጋለጡ ደላሎቹ አይታሰሩብን ካሉ ራሳቸውም ወንጀለኞች ናቸው ማለት ነው”

በጁምዓው ተቃውሞ፤

አንድ ሰውዬ ያረጀ ባንዲራ ይዞ ታየ፡፡ ልብ አድርጉልኝ አንድ ሰውዬ ነው፡፡ ሰውዬው ምናልባትም በቤቱ ያገኛትን አሮጌ ባንዲራ ይዞ ወጥቷል ወይ ደግሞ…. (ወይ ደግሞውን እንተወው… ብቻ ግን አንድ ሰውዬ ብቻ ነው ይሄ ሰውዬ በፍፁም ሚሊዮኖቹን ሊወክል አይቻለውም፤ ተቃውሞ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች የተሳተፉበት ነው)

የኢቲቪው ጋዜጠኛ፤

አክራሪ ሀይሎች ባለፈው አርብ ባንዲራውን ሲቀዳድዱ ነበር ይሄ የሀገር ክህደት አይደለም ይላሉ…

አስተያየት ሰጪ፤

እንዴ የሀገራቸውን ባንዲራ መቅደድማ አይገባም… ኢትዮጵያ እኮ ሀገራቸው ናት…ነውር አይደለም እንዴ…

ሌላም ሌላም…

ልብ አድርጉልኝ ኢቲቪ ይሄንን ድራማ የሚሰራው ሊዝናናን አይደለም፡፡ የምሩን ነው፡፡ ኮስተር ብሎ ነው፡፡ እየቀለደ አስደለም እየቀለደብን ነው እንጂ…

እና የምሬን ልጠይቅ ETVዬ፤ ይሄኛው መንገድ ግን የት ድረስ ያስኬድ ይሆን!?
http://www.abetokichaw.com/

ለ ኦቦ አዩ ቀናቴ ኖርዌዬ፤ ጉዳዩ… ቪዲዮዎትን መመልከቴን ስለመግለፅ



ለ ኦቦ አዩ ቀናቴ ኖርዌዬ፤ ጉዳዩ… ቪዲዮዎትን መመልከቴን ስለመግለፅ

እኔ አቤ ቶኪቻው የተባልኩ ግለሰብ፤ በነገራችን ላይ አቤ ቶኪቻው የሚለው ስም ከየት የመጣ መሰልዎ… አባቴ ብዙ ጊዜ ሲተርት፣ ሲያንጎራጉር፣ ሲፎክር፣ አንዳንዴም ሲሳደብ፣ እንዲሁም ሲወድ… የሚጠቀመው ኦሮምኛ ነበር፡፡ ታድያ እኔን ሲወደኝ ቶኪቻው አለኝ፡፡ ቶኪቻው ማለት አንዱ ማለት ነው፡፡ እናልዎ እኔ ደግሞ እሱን ስወደው እርሱ እንደሚጠራኝ ራሴን ጠራሁ፡፡ ይሄን ያዩ ሁሉ (ነሚቺ ኩኒ ኦሮሞ ዳ) ይሉኛል፡፡ ታድያ እንዴት ደስ እንደሚለኝ ባዩ!

ለማንኛውም ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው፤ ባለፈው ስለ እኔ ያሰናዱትን አንድ ቪዲዮ ተመልክቼው በድረ ገፄም ያየ ሰው ይፍረደኝ ብዬ አጋርቼው ነበር፡፡

በመጀመሪያ “አክብረው” ስለተቹኝኝ አመሰግኖታለሁ፡፡ ትችትዎ የመጣው በበስጭት ምክንያት፤ ብስጭትዎ ደግሞ የመጣው ያልኩትን በትክክል ባለመረዳትዎ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ነገሩን ለማስረዳት አንድ በአንድ እየዘረዘርኩ መልስ መስጠት ፈልጌ ነበር፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ከዚህ ቀደም በፃፍኳቸው ማብራሪያዎች የተገለፁ ናቸውና “ነገር ቢያበዙት በአህያ አይጫንም” እንዲሉ፤ ድጋሚ ዝርዝር ነገሮችን ማንሳቱ እርስዎንም ሌላውን አንባቢም ማድከም ይሆናል ብዬ ተውኩት፡፡

ቪዲዮውን የተመለከቱ ወዳጆች አንዳንዶቹ እሰይ እንዲህ ልክ ልክህን ይንገሩህ እንጂ፤ አንተ ስንቱን ባለስልጣን ትተች የለ… ያሉኝ የመኖራቸውን ያህል በተቃራኒው ደግሞ እርስዎኑ “ተችተው ሞተዋል” ብለው ያንጓጠጥዎት ነበሩ፡፡ …መልስ ልሰጥበት እችል ይሆናል ማለቴን ጠቅሰውም “ያንን መልስ የት አስቀረኸው…” ብለው የጎተጎቱኝ የመኖራቸውን ያኸል፤ ”ምንም መልስ አትስጣቸው ንቀህ ተዋቸው” ብለው የመከሩኝ ወዳጆችም ነበሩኝ፤ እኔ ግን ምን በወጣዎ እርስዎ አክብረው እየተቹኝ እኔ ማነኝና ንቄ እተዎታለሁ… ብዬ አሰብኩልዎ.. ስለዚህ በእርስዎ ስም ለሌሎችም ይጠቅም ይሆናልና ለምን በአንድ አንቀፅ እንዲህ አልናገርም ብዬ ተከሰትኩ…

ማንም ብልጥ የሆነ ቢኖር፤ ያለፈውን ይርሳ ወደፊትም ይቀጥል ላለፈ ክረምት ጣሪያ አይታደስም ለሚመጣው ክረምት እንጂ፡፡ ማንም ብልጥ የሆነ ቢኖር፤ ከሌሎች ጋር ይተባበር ድር ቢያብር አንበሳንም ዝሆንንም ጨምሮ ማሰር ይቻለዋልና! ማንም ብልጥ የሆነ ቢኖር፤ አትተቹኝ አይበል ትችት ራስን ለማስተካከያ ይረዳል ያልተስተካከለ ደግሞ ሌሎችን ማስተካከል አይቻለውምና! ማንም ብልጥ የሆነ ቢኖር ተቺዎቹን እንደጠላት አይመልከት ለራሱ ብለው ሊሆን ይችላልና! ማንም ብልጥ የሆነ ቢኖር፤ ትክክለኛ በዳዮቹን ይለይ ከወዳጆቹ ጋር ሲጣላ በዳዮቹ በደላቸውን እንዲያጠናክሩ ያደርጋቸዋልና! ማንም ብልጥ የሆነ ቢኖር፤ ፍቅርን ይስበክ በፍቅር የማይገፋ መከራ የማይጠፋ ችግር የለምና፡፡ ማንም ብልጥ የሆነ ቢኖር፤ ከጥላቻ ይራቅ ጥላቻ ጥላቻን ትወልዳለች ጥፋትንም ታበረክታለችና!

መልሴ ይሄው ነው ወዳጄ!

አክባሪዎ!

አቤ ቶኪቻው!

በመጨረሻም፤

ከዚህ የተረፈውን ነገራችንን ፍትፍት አድርገው የሚያብራሩ ስማቸውም፤ ፕሮፌሰር ፍቃዱ ለሜሳ የተባለ በአዳማ ዩንቨርስቲ መምህር የነበሩ ሰው ፅሁፍ እጄ ላይ ነው… የላኩልኝ ነን ሰዎች ፈቃደድ ጠይቄ በድረ ገፃችን ላይ አትመዋለሁ፡፡

አዳ ቢሉስማ ኦሮሞ (ኦነግ) -ይነጋል በላቸው

ccccሰሞኑን ለድረገፆች የላክኋትን አንዲት ትርጉም ቢጤ ተመርኩዘው ብዙዎች ሲቆራቆሱባት ታዘብኩ፡፡ የኢሣቱ ልጅ ተክሌ የሚላት ነገር ትዝ አለችኝና በዚህ አጋጣሚ እሷን አስታውሼ ወደድኩለት፤ በቀጥታ ላልጠቅሰው እችላለሁ – የምጽፈው ነገር አቧራ ካላስነሳ የጻፍኩ አይመስለኝም – ይላል ልጅ ተክሌ፤ እውነቱን ነው፡፡ እየበሉ እየጠጡ ዝም… የሚባለው የመደሰቻ ድግስ ብሂል እንኳን መብላት መጠጣታቸው ስለሚታይ ነው፡፡ የአንድ ጽሑፍ መነበብና አለመነበብ የሚለካው ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ሰላማዊ ውርክብ ሲታይ ነው፡፡ በነገር መነታረክ መጥፎ አይደለም፤ ከብዙ ተጨቃጫቂ መካከል አንድና ሁለት የሚማማር ሰው ማግኘት ቀላል አይደለምና፡፡ ፍሬና ገለባ ከሚለይባቸው መንገዶችም አንዱ ይሄኛው ነው፡፡ ‹ከአነጋገር ይፈረዳል፤ከአያያዝ ይቀደዳል› እንደምንል፡፡
ዛሬ ደግሞ በ‹ጠዓመኒ ድግመኒ› የትግርኛ ብሂል መሠረት አንዲት ነገር ተርጉሜ ማስነበብን ወደድኩ፡፡ የዛሬው ወደአማርኛ በከፊል የተመለሰ ጽሑፍ ቀደም ሲል ከድረ ገፅ ያወረድኩትና ለክፉ ቀን ሳይሆነኝ አይቀርም ብዬ እንዳይዘነጋኝ በ‹ሾርት ከት› የኮምቡጦሬ ደስክቶፕ ላይ ያኖርኩት አንድ አስደናቂ የኦነግ ደብዳቤ ነው፡፡ የደብዳቤ መለያውን ፍርማት(head letter) በኦሮምኛ፣ በዐረብኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ያዘጋጀው ይህ ግምባር የጌቶቹንና የጃዝ ባዮቹን የኤሪዎች ትግርኛ – የኛም ነው ለነገሩ – አለመጨመሩ ገርሞኛል፡፡ (ሰዎች እየተጃጃሉ የማያስፈልግ ግጭት ውስጥ የሚዘፈቁት እኮ ቋንቋን ልክ እንደ አንድ የምርት መገልገያ መሣሪያ ወይም ልክ እንደሸሚዝና ከናቴራ ከመቁጠር አልፈው በዘር ሐረግ ባሕርያዊ ውርስ ከአባት ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ ትልቅ ቁም ነገር እየቆጠሩ ሥነ ልቦናዊ ቀውስ በመግባታቸው ነው – እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህም ላይ እመለስበታለሁ)፡፡
ትግርኛን አለመጨመሩ ድርጅቱ ዕድሜ ጠገብ በመሆኑ ሊሆን ይችላል ከወያኔ በተሻለ ይሉኝታን ያውቃል ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም ግምባሩ ለተቦረቦሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ለሚስተር ባን ኪ ሙን የላከውን ደብዳቤ ሙሉ ቃል ሳይሆን የተወሰነውንና ከሀገራችን ወቅታዊ የመጋኛ ምች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውን ይህን የተላላኪዎች ጦማር ተርጉሜ ላስቃኛችሁ ፈልጌያለሁና ለማንበብ ትብብራችሁን አትንፈጉኝ፡፡ ሁሉንም ያልተረጎምኩት ረጂም ስለሆነና ከወቅታዊነት አንጻር አስፈላጊ መስሎ ስላልታየኝ ነው፡፡ ለሁላችሁም መልካም ንባብና ለአንዳንዶቻችሁ በተለይ መልካም መናደድ ይሁንላችሁ፡፡
OROMO LIBERATION FRONT
Gaafa: 09-08-2011 Date:
ﺗﺎرﺦﻳ رﻢﻢ
His Excellency Ban Ki-moon
Secretary General of the United Nations,
The United Nations Organization,
New York, N. Y.
( በቀጥታ ለዋና ጸሐፊው ስለተጻፈ Your Excellency ቢባል ይሻል ይመስለኛል – ለማንኛውም እንደገባኝ ልቀጥል – በቅንፍ የሚገኙ ጭማሪዎችና ደብተራ የጫጫረው አሸንክታብ ያስመሰልኩበት ልዩ የቀለም አፅንዖት የኔ ናቸው፡፡)
ለተከበሩ ባን ኪ ሙን
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ
ይህን ደብዳቤ የምጽፍልዎ ሶማሊያንና ኢትዮጵያን የሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት (ከአሁን በኋላ የተ.መ.ድ በሚል አሳጥረዋለሁ) የቁጥጥር ቡድን ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ በጁን 21/2012 የተደረገውን የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለማደናቀፍ ታስቦ ተጠነሰሰ የተባለለትን ሤራ (የኢሕአዲግ መንግሥት) አከሸፍኩ ማለቱን ተከትሎ ኦነግን በዚህ የሽብር ድርጊት ውስጥ ከሌሎች ኃይላት ጋር ለማካተት ሙከራ የተደረገበትን ሪፖርት በመቃወም ነው፡፡
ይህ ዜና በልዩ ልዩ ሚዲያዎች በወጣበት ወቅት ኦነግ የአፍሪካ ኅብረትን ስብሰባ በቦምብ ለማጋየት ተጠንስሷል በተባለ በዚህ የሽብር ጥቃት ውስጥ (ከእውነት ተሞክሮና ከሽፎም ከሆነ) እጁ እንደሌለበትና እንዲያውም ይህን ዓይነቶችን ንጹሓን ዜጎችን ለዕልቂት የሚዳርጉ ተግባራትን እንደሚቃወምበጊዜው በማያወላውል ሁኔታ አስታውቋል፡፡ በብሉምበርግ የዜና ማዕከል የዜና ዕወጃ እንደተገለጸው “ኦነግ የአፍሪካ ኅብረትን ለማፈንዳት አላለመም ወደፊትም አያልምም”፡፡ እንደድርጅቱ ፖሊሲም “ኦነግ ሲቪሎችን፣ የሲቪል ተቋማትንና ንብረቶቻቸውን በጥቃት ዒላማው የዕቅድ ዝርዝር ውስጥ አይጨምርም፡፡”
እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ የኢትዮጵያን መንግሥት በኃይል የተቆጣጠረው የመለስ (ዜናዊ) አገዛዝ ኦነግን በተለያዩ የሽብር ተግባራት ሲከስ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ እነዚህም ማለቂያ የሌላቸው የሽብር እንቅስቃሴ ተብዬዎች በእውን የሚታዩ ሳይሆኑ በራሱ በኢሕአዲግ መንግሥት የፕሮፓጋንዳ ክፍል አማካይነት በቤተ ሙከራ እየተፈበረኩ መንግሥትን በሚቃወሙ ኃይሎች ላይ የሚለጠፉ መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ በቅርቡ በዚሁ የወያኔ መንግሥት የደኅንነት ሰዎች የተሠራውንና “ አዲስ አበባን እንደባግዳድ” በሚል ርዕስ ለዕይታ የበቃውን በዶኩመንተሪ ፊልምነት የቀረበ የቤተ ሙከራ ሥሪት ብንመለከት ኦነግን ከሽብር ተግባር ጋር ለማቆራኘት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ይህ የተ.መ.ድ የሶማሊያና ኢትዮጵያ ተቆጣጣሪ ቡድን ይህን የመንግሥት የውሸት ፕሮፓጋንዳ እንዳለ ገልብጦ በሪፖርትነት ማቅረቡ ድርጅታችንን ኦነግን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡ /ያን ቪዲዮ ለማየት ይህን አድራሻ ይጠቀሙ -http://www.diretube.com/etv-special/addis-like-baghdad-documentary-video_58f9ec467.html/. …
/የድርጅታችንን የኦነግን [የምሥራቅ አፍሪካ] አድራሻ ከፈለጉ ይሄውልዎ፡- P.O.Box 6973 Asmara, Eritrea Tel 2911 110236 Email: abamilki@gemel.com.er,http://www.oromoliberationfront.org /
ይህ የተ.መ.ድ ተቆጣጣሪ ቡድን (The MGSE group) ድርጅታችንን ከዚህ የሽብር ጥቃት ጋር በዕብለት ከማነካካቱም በተጨማሪ የኤርትራን መንግሥት ከኦነግ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለው ለማስመሰል ማለትም የኦነግን ዓላማዎች በማስፈጸም ረገድ የኤርትራ መንግሥት እንደሚሠራ ለማሳመን በተሳሳተ ሁኔታ ብዙ ርቀት ተጉዟል፡፡ (ለኢትዮጵያው የወያኔ መንግሥት የሚያዳላው) ይህ ቡድን የኤርትራ መንግሥት የኦሮሞን (ሕዝብ) ትግል በበላይነት እንደሚመራ ለማስመሰል ባደረገው ጥረት የተሳሳተ ግንዛቤን ሊፈጥር የሚችል ሪፖርት አሰራጭቷል፡፡ በበኩላችን ይህን ቡድኑ እያወቀም ይሁን ሳያውቅ ያሰራጨውን ስምና ዝናን የሚያጠለሽ ሪፖርት በተመለከተ የኤርትራ መንግሥት በራሱ መንገድ እንደሚሄድበትና ራሱን እንደሚከላከል ሙሉ እምነታችን ነው፡፡ ነገር ግን የኤርትራ መንግሥት በጉዳያችን ፈጽሞውን ጣልቃ እንደማይገባናየድርጅታችንን ነጻነት እንደሚጠብቅ ለሚመለከተው ወገን ሁሉ ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በሌላም በኩል የኤርትራና የኦሮሞ ሕዝቦች ከመቶ ዓመታት በላይ የዘለቀ ረጂም የጋራ ታሪክና መልካም ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እንሻለን፡፡ የኤርትራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ለሚገኝበት ሁኔታ ያለው ራሮትና ድጋፍም ከዚህ የረጂም ዘመን ትስስር የሚመነጭ ነው፡፡

ክቡር ዋና ጸሐፊ

ደግመን ደጋግመን ለመላው ዓለም እንዳሳወቅነው ኦነግ ማለት የኦሮሞን ሕዝብ ብሔራዊ ትግል በማስተባበር ኦሮሞንና ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ለማውጣት ቆርጦ የተነሣ ሕጋዊ ድርጅት መሆኑን አሁንም በዚህ አጋጣሚ ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ የኦነግ ግብ የኦሮሞ ሕዝብ ማንኛቸውም የዓለም ሀገራትና የተ.መ.ድ ራሱ የሚያምኑበትን መሠረታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲጎናጸፍ ማስቻል ነው፡፡ በተጨማሪም ኦነግ በአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦችና ሀገሮች ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር አበክሮ ይጥራል፡፡ …

የተከበሩ ዋና ጸሐፊ፤
ኦሮሞዎች፣ በአፍሪካ ቅርምት ዘመን የአውሮፓ ቅኝ ግዛት የፈጠሯት የቅርብ ጊዜይቱ አፍሪካዊት ቅኝ ገዢ ሀገር አቢሲኒያ ወይም ኢትዮጵያና አውሮፓውያን ራሳቸው በጫኑባቸው አስከፊ ጭቆናና መሪር ቅኝ አገዛዝ ካለፉት አንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ጀምሮ ስቃይ ላይ የነበሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ዛሬ ኦሮሞዎች በምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ሕዝቦች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የኦሮሞዎች ቁጥር 40 ሚሊዮን አካባቢ ይደርሳል፤ ይህ ደግሞ የጠቅላላውን ነዋሪዎች ቁጥር 40 በመቶ ያህል ነው፡፡ የኦሮሞዎች ሀገር – ኦሮሚያ – በተለይ ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ደግሞ ለአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ናት፡፡ ኦሮሞዎች ከማንም ሕዝብ በተለዬ ሁኔታ አንድ ዓይነት ባህል፣ አንድ የጋራ ቋንቋ፣ አንድ የጋራ ታሪክ፣ እንዲሁም አንድ ዓይነት የዘር ሐረግና ልዩ የመኖሪያ ግዛት ያላቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡ ኦሮሞዎች ከኢትዮጵያውያንና ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ጋር ሰፊ የባህልና የኢኮኖሚ ትስስር ያላቸው ከመሆናቸውም በላይ ከኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥታትና ከሌሎች በርካታ የቀንዱ ሀገራት ጋር በድንበር ይገናኛሉ፡፡
የሀበሻ ገዢዎችና የፖለቲካ ምጡቃን(ኤሊቶች) በኦሮሞዎችና በሌሎች ተገዢዎች አጠቃላይ ሕይወት ላይ መድሎን፣ አስገድዶ መግዛትን፣ አፈናና ጭቆናንና ብዝበዛን ጨምሮ ያልጣሉባቸው የክፉ አገዛዝ ቀምበር የለም፡፡ እነዚህ የሀበሻ ቅኝ ገዢዎች የኦሮሞን ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግና ልማድ ወዘተ. ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ በወራሪ የቅኝ ገዢ ኃይል ሥር እንደመገኘታቸው ኦሮሞዎች ሀበሾች በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ እንደሁለተኛ ዜጋ ይቆጠራሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምጡቃን ዘረኛ አመለካከትና መናኛ አስተሳሰብ እንዲሁም ሥልጣናቸውን በእጃቸው እንዳለ ለማቆየት ያደረባቸው ጉጉትና ቅዠት ዴሞክራሲንና ልማትን እውን ለማድረግ እንዳይቻል እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ዘረኝነትንና መድሎን አስወጋጅ የተ.መ.ድ ኮሚቴ በአንደኛው ሪፖርቱ “ … ከ1995 እስከከ 2005 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከታዩ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች አብዛኞቹ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የተከሰቱ ናቸው፡፡ ከነዚህ ዓመታት ውስጥ ከአንደኛው በስተቀር በሁሉም ዓመቶች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝና ብይን ውጪ ግድያና እሥር ተፈጽሟል፤ በነዚህ ዓመታት ውስጥ በኦሮሞ የተፈጸመውን ያህል ግፍና በደል በሌሎች ክልላዊ መንግሥታት ውስጥ መፈጸሙን የሚያመለክት ዘገባ ወይም ሪፖርት አልቀረበም፡፡ …”ሲል ገልጾኣል፡፡
በተጨማሪም በሰብኣዊ መብቶች መጠበቅ ዙሪያ የሚንቀሳቀስ አንድ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በዘገባው እንደገለጸው “የርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ተከታታይ የአማራ-ትግሬ ገዢ መደቦች የኦሮሞን ሕዝብ ነጥለው የጥቃት ዒላማ ማድረጋቸውን በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፎ ማቅረብ ይቻላል፡፡” ከዚህና ከሌሎችም ሪፖርቶች መረዳት እንደሚቻለው የአሁኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞን ሕዝብ በተለያዩ አጋጣሚዎችና ሰበቦች የጥቃት ሰለባ አድርጎ እያሰቃየው እንደሆነ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ … (የአማራውን ማለቅ ለመሸፋፈን ኢሣይያስ በኦነግ በኩል ለወያኔ የሰጠው ፖለቲካዊ ድጋፍና የዕርቅ መጎናበሻ ገጸ በረከት ይሆን?)
የኦሮሞ ሕዝብ የነጻነት ትግል ከቅኝ ገዢው የኢትዮጵያ መንግሥት ነጻ የመውጣት ፍላጎት የወለደው ተፈጥሯዊ የመብት ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ከውጭ ወራሪ ኃይል ራስን ነጻ የማውጣት ትግልና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ደግሞ የተ.መ.ድን ጨምሮ በሁሉም ሀገራት ዕውቅና የተሰጠው ዓለም አቀፍ መብት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይህን መብት ለኦሮሞ ሕዝብ ይነፍጋል፡፡ መንግሥት ይህን ሕገ ወጥ ድርጊት በመፈጸሙም የተባበሩት መንግሥታትን ሕገ ደንብ አንቀጽ አንድ፣ ንዑስ አንቀጽ አንድ ይጻረራል፡፡ ይህ ሕግ እንዲህ ይላል፡- “ሁሉም ሕዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት አላቸው፤ ይህን መብታቸውን አለገደብ በመጠቀምም የራሳቸውን የፖለቲካ ሥርዓት በነጻነት የመወሰን፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ዕድገታቸውን በፈለጉት አቅጣጫ የመምራትና የማሳደግ መብት አላቸው፡፡” …
ዳውድ ኢብሣ፤ የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ብሔራዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር
______________________________________________
እንደተለመደው የራሴን ጥቂት ሃሳቦች በመናጆነት መለጠፌ አልቀረም፡፡ አንጋፋውና የእንጨት ሽበቱ ኦነግ ይህን አስገራሚ ደብዳቤ ከአሥመራ በላከ ሰሞን በአድራሻው ‹አንጀት የሚበላ› አጭር ኢሜይል ብልክም ሣንሱር አድራጊው ሕግሓኤ በቅድሚያ ስለሚያነበው ይመስለኛል መልስ የሰጠኝ አልነበረም፤ ለነገሩ እኔም አልኩ ለማለትና ለኅሊናዊ ውርድ ከራስ እንጂ ዐውቆ የተደበቀ ቢጠሩት እንዳለመስማቱ ከእሥረኛው ኦነግ መልስ መጠበቁ የዋህነት መሆኑን አጥቼው አልነበረም፡፡ የኢትዮጵያን ነጻነትና ሉዓላዊነት ከገፈፈ አካል ነጻነትንና ሉዓላዊነትን በምፅዋት መልክ መለመን የለዬለት ጅልነት መሆኑንም ብዙዎች ከበፊቱ ጠንቅቀን እንረዳ ነበር፡፡ በመሠረቱም ነጻነትን ከሚደፈጥጥ ወገን፣ ኢትዮጵያውያንን በኤርትራ ታዳጊ ሕጻናት አእምሮ ውስጥ በማስፈራሪያነት ከሚያሰርጽና በተለይ አማሮችን ለተዋጊዎቹ የዒላማ ተኩስ መለማመጃ ከሚያደርግ፣ የጦር ምርኮኞችን ጨፍጭፍ ራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ አፈር የሚያለብስ፣ በሕይወት ካሉ ሰዎች የወርቅ ጥርስን በጉጠት እያወለቀ ከሚቀማ … የክፉዎች ክፉ የበላኤሰብ ቡድን ነጻነትን መጠበቅ ከብት ባልዋለበት ኩበት ፍለጋ እንደመሰማራት ነው፤ ይህን በጎ ነገር ከዚህ ዕኩይ ድርጅት መቀላወጥም ‹የጨነቀው ዱቄት ወደ ንፋስ ይጠጋል› እንደሚባለው የተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው – ያበጠው ይፈንዳ የሚሰማኝን እውነት እናገራለሁ፡፡ እንዴት ተደርጎ ነው ሻዕቢያ የኢትዮጵያ ነጻነት ሐዋርያ ሊሆን የሚችለው? የችግር መፈልፈያ ቋት በየትኛው ሒሣባዊ ቀመር ተገልብጦ ነው የመፍትሔ ምንጭ የሚሆነው?…
አሁን ኦነግ ፈራርሷል ተብሏል፤ ቢዘገይም ከቅሪቶቹ የተወሰኑት እየተጀነኑና በአስደግዳጊ ቅድመ ሁኔታም ታጥረው የኢትዮጵያን አንድነት ለመቀበል እየተዘጋጁ ነው ተብሏል፡፡ እውነቱን ለመናገር ኦነግ የፈረሰው ዛሬ ወይ ትናንት አልነበረም፡፡ የፈረሰው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቆርጠው ከተነሱ ወገኖች ትዕዛዝ እየተቀበለ በሰው ሣምባ እየተነፈሰ በብዙ የሞኝ ተግባራቱ ምክንያት ቀስ በቀስ ግን በሂደት ከኦሮሞ ሕዝብ ልብ መውጣት ሲጀምር ነው፡፡ ኦነግ ኖረ ከተባለ አንድ ጥጋት ላይ ቁጭ ብሎ ይህን መሰል መግለጫና ደብዳቤ በሚለቀልቅ የወረቀት ላይ ነብር የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ አማካይነት እንጂ በተግባር የኖረበትን ጊዜ ማስታወስ ያቅተኛል፤ እርግጥ ነው ድርጊቱ የተፈጸመው በበላይ ትዕዛዝም ቢሆን በበደኖና በአሰቦት ገዳም በጊነሰ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ሊመዘገብለት የሚገባው ሕጻናትና አእሩግ እንዲሁም መሣሪያ ያልታጠቁ ምሥኪን አማሮችን የመጨፍጨፍ ታላቅ ጀብድ ሠርቷል – በዚያ ድርጊቱ አለቆቹና ያን ግፍ የፈጸሙ የራሱ የኦነግ አባላት ተገቢ ዋጋቸውን ያገኛሉ – ዋናውን ፈላጭ ቆራጭ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ብዙዎቹ ወንጀለኞች ከአሁን በፊት ፍርዳቸውን እንዳገኙ ይገመታል፡፡ ከዚያ በመለስ ግን አንዲት የታወቀች መንደር እንኳን ይዞ ‹እዚህ አለሁ! ማን ነው ወንዱ! አካኪ ዘራፍ› ማለት ያልቻለና ሕይወቱን በስደት ኖሮ በዚያው በስደት ሕይወቱ ያለፈ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አንደኛው ተላላኪ እንጂ እውናዊ የነጻነት ፋኖ አልነበረም – መሪ ተብዬዎቹ የፈረንጅ ፓስቲ ሲገምጡና በዕርዳታና የውጭጭ ገንዘብ በቅንጦት ሲምነሸነሹ ኖረው በመጨረሻው በ’mission accomplished’ ፈረንጃዊ የቃቃ ጨዋታ ኦነግ ከጨዋታ ሜዳ መውጣቱን ለመሸፋፈን ቢሞከርም የኢትዮጵያ ትንሣኤ በሚበሰርበት ቅርብ ጊዜ ውስጥ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ጠላት የሥራውን እንደሚያገኝ ጥርጥር የለውም፡፡

እናም ኦነግ ለማያውቁት ይታጠን፤ ቋንቋን ማሣመር የኅልውና ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም – ደግሞም ወግ አይቀርምና ‹ሲቪል ዜጎችና ንብረቶቻቸው ከኦነግ የዒላማ ጥቃቶች ውጪ ናቸው› ይባልልኛል፡፡ ለመሆኑ ደካሞችንና መሸሻ መጠለያ የሌላቸውን ዜጎችን ከመግደል ያለፈ የጦር ሜዳ ውሎ አለው እንዴ ኦነግ? የምን ንገሩኝ ባይነት ነው? የሌሎች ሀገሮች ተቃዋሚዎችና አማጺያን በጥቂት ወራትና ዓመታት ውስጥ ግባቸውን ሲመቱና በተናጠል ወይም በሽርክና መንግሥት ሲመሠርቱ ኦነግ በግማሽ ምዕተ ዓመት አንዲትም ወረዳ ሳይቆጣጠር በወሬ ኖሮ በወሬ የተፈታው በአቅም ማነስና በአመራር ጉድለት ሳይሆን በዓላማ ተልካሻነት ነው፡፡ ወንዝ የማያሻግር እንቶ ፈንቶ ዓላማ አንግቦ፣ ያንንም የጥላቻ ዘፈን አይሉት መዝሙር በጠላት አማካይነት እንደቴፕ ሪከርደር ተሞልቶ አሥመራ ላይ ሆኖ እንደጣቃ መቀደድ ድል እንደማያስገኝ እናውቅ ነበር፡፡ ወያኔንና ሻዕቢያን ያመነና ጉም የዘገነ አንድ መሆናቸውንም እናውቅ ነበር፡፡ ሻዕቢያና ወያኔም ባቅማቸው የአፍሪካ ሞሳድና ኬጂቢ ወይም ኤም አይሲክስና ሲአይኤ ሆነው (በሥልት መመሳሰል ማለቴ ነው) ኢትዮጵያን ለመበታተን ይህን ጅላጅል ድርጅት መጠቀማቸውን ልብ ለምንል ወገኖች ለመጥፎ ዓላማም ቢሆን ተግተው ከሠሩ የማይቻል ነገር አለመኖሩን መገንዘብ ይቻለናል፡፡

ይሁንና እውነት ሁልጊዜም እውነት ስለሆነች በመጨረሻ ማሸነፏ አይቀርምና የኢትዮጵያ ጠላቶች አንድ ባንድ ግን በርግጠኝነት ወደ ከርሠ መቃብራቸው የሚነጉዱበት ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ይህን የምንለው ይህኛውን ወይም ያኛውን የተቃዋሚ ቡድን አለኝታ አድርገን ሳይሆን ፈጣሪን ተመክተን ነው፡፡ ከሰው የምንጠብቀው ነገር ብዙም አይደለም፤ ያልታዘዘ ምንም ነገር አያደርግም፡፡ ከታዘዘ ግን ሣምንትም፣ ቀንም፣ ሰዓትም፣ ደቂቃና ሴከንድም የማድረጊያ ጊዜ ናቸው፡፡ የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፣ እውነተኛው ሙሤ ሲላክ፣ … ያኔ የቁርጥ ቀን ሲመጣ አጭበርባሪውና ሆድ አምላኪው ሁላ የሚገባበትን ያጣል፡፡ …
በበኩሌ ይታየኛል፤ የሌቦች ዘመን እየተጠቀለለ ነው፡፡ የብርሃን ዘመን እየባተ ነው፡፡ ብዙ እንዳየን ብዙ እናያለን፡፡ እስካሁን ያየነው ሁሉ ባሳለፍነው አጭር ግን አስደንጋጭና አሰቃቂ ጊዜ ውስጥ እናያለን ብለን ካሰብነውና ከጠበቅነው በላይ ነው፡፡ የፈጣሪ ቀን አንዲት ብቻ አይደለችም፤ ቀናት ሁሉ የርሱው ናቸው፡፡ ነገን የማያውቁ ትናንትን የማያስቡና ማስታወስም የማይችሉ ወይም የማይፈልጉ ናቸው፡፡ ዛሬ አብዛኛው ዜጋ ለሆዱ ተሸንፎ ስለሆዱ አድሮ በሆዱ እያሰበ ቢያድር ቢውልም ፈጣሪ ይህን የእበላ ባይነትና የስግብግብነት ዘመን ሲገፍፈው፣ ኅሊናም ትክክለኛ የዳኝነት ሥፍራውን ሲይዝ የሀገራችን ቅርጽ በቅጽበት ይለወጣል፡፡ ያኔ የጠፋው ሃይማኖት ይመጣል፤ ያኔ የጠፋው መተሳሰባችንና መተዛዘናችን ይመጣል፤ ያኔ ቁሣዊነት ይጫጫና ሰብኣዊነት ይፋፋል፡፡ ያኔ ይሉኝታና ሀፍረት ይወለዳሉ፡፡
በነገራችን ላይ “አንበሣን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ” እንዲሉ አንዱን ፈርተን ወደ ሌላኛው ልንሸሽ ስንሞክር የኋለኛው ከፊተኛው የባሰ እየሆነብን ስንሰቃይ መቆየታችንን ስናስብ የሀገራችን ነገር የእግር እሳት ይሆንብናል፡፡ እናም እንዳለመታደል ሆኖ ኦነግ ትልቅ ደረጃ መድረስ እየቻለ ባነገበው ውራጅ ዓላማና ግብ እንዲሁም የሰው አሽከር ለመሆን በመቁረጡ ሣቢያ ከስሜትና ከልብ ወጥቶ መሬት ሊቆነጥጥ የሚችል ድል ሊጎናጸፍ አልቻለም፡፡ ይህ ሰባራ ዕድላችን ደግሞ ኦሮሞ ነን ለምንል ወገኖች ትልቅ የልብ ስብራትን ያስከትልብናል – የምትወደውን በማትወድለት ጠባዩ ምክንያት ማጣት ሌላው የእግር እሳት ነው – እየተወደዱ ከመጠላት ይሠውር፡፡ እኔ በኦሮሞነቴ ከማፍርባቸው ነገሮች አንዱ ይህ የኦነግ አይረቤነትና ለአሰለጦች ዓላማ ማስፈጸሚያ የመሆኑ ክፉ ዕጣ ነው፡፡
እኔ ኦሮሞ ነኝ ብያለሁ – እስካሁን ካላልኩም አሁን ነኝ እያልኳችሁ ነው፡፡ ኦሮሞ ለመሆን ደግሞ የማንም ፈቃድና ይሁንታ አያስፈልገኝም – የማንነት ጥያቄ እንደንግድ ሊቼንሳ ግድግዳ ላይ ለጥፈው የተቆጣጣሪ ባለሥልጣንን ተግሣጽና ግልምጫ የሚያስወግዱበት ቁሣዊ ነገር አይደለም፤ ብዙ ምሥጢር አለው፡፡ ኦነግም ሆነ በኦሮሞ ስም የተቋቋሙ ኆልቁ መሣፍርት የሌላቸው ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ኦሮሞነትን ለማንም ሊሰጡ ወይ ሊነሱ አይችሉም፤ ከሞከሩ ድፍረትና ብልግናም ነው፡፡ በምርጫቸው ኢትዮጵያዊ መሆንን የወደዱ ነጮች መኖራቸውን ስንረዳ የነኦነግ ኢትዮጵያን የመጥላት አባዜ አልገባችሁ ሊለን ይችላል፡፡ ሌላው ሁሉ ይቅር – ኦሮሞው መንግሥቱ ኃ/ማርያም ምን ይላቸዋል? የኦሮሞው የአጼ ኃይለ ሥላሤ አፅም ምን ይላቸዋል? የሌሎች ኢትዮጵያን አንቀጥቅጠው የገዙ የኦሮሞ ነገሥታት ዐፅሞች ምን ይሏቸዋል? እንደኦሮሞነቴ ቢቻለኝ አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ የሚናገረውን ቋንቋና የሚኖርበትን ባህል ባውቅ መልካምና ተጨማሪ ዕሤት በሆነልኝ፡፡ ያም ቢሆን የግድ ያህል አይደለም፡፡ በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች የተነሣ ቋንቋውንና ባህሉን ላላውቅ እችላለሁ፤ ኦሮሞነትን ግን በማንም በጎ ፈቃድ እንደማላገኘው ወይም እንደማላጣው አስረግጬ ልነግራችሁ እችላለሁ – ኦሮሞ ለመሆን ኢትዮጵያዊነቴ ብቻ ይበቃኛል፤ የኔ ደም የኦሮሞን ደም እንደማይመስልና ኦሮሞነቴን ሊያስከለክለኝ የሚችል ብቸኛው መንገድ ናሙና ደሜ ተመርምሮ ‹አንተ አጭበርባሪ! የኦሮሞ ደም የሚባል በደምህ ውስጥ የለም!› የሚል የምሥክር ወረቀት ከታወቀ የዘረመል ጥናት የሕክምና ማዕከል ሲሰጠኝ ብቻ ነው፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ኦሮሞ፣ የኢትዮጵያ ትግሬ፣ የኢትዮጵያ አማራ… የሚባለው ምናልባትም ከጭንቀት የሚመነጭ የማደናገሪያም ይሁን የማባበያ ፈሊጥም ትክክል አይደለም፡፡ ራሱን በሺህ ቦታ ይበጣጥሰው ብዬ እንዳልረግመው ከኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ከሃይማኖታዊ ቀኖና አንጻር ይከብደኛልና ‹ኦሮሞነቴን ያልተቀበለች ኢትዮጵያ በሺህ ቦታ ትበጣጠስ› በማለት ይህችን የሚሊዮናትን ሀገር የነገር ማጣፈጫ ለማድረግ የሞከረው ሰውዬም ልብ ሰጥቶት ወደኅሊናው እንዲመለስና በአንድ የጋራ ማንነት ውስጥ አብረን ኢትዮጵያዊነትን እንድንዘምር እጸልያለሁ፡፡
በተረፈ ኦሮሞ ለመሆን ኢትዮጵያዊነት ብቻውን በቂ ብያለሁ – አሁን አልደግመውም፡፡ በመሠረቱ ኦሮሞ መሆን ጮቤ የሚያስረግጥ አይደለም፤ አማራ መሆንም በሀዘን ማቅ እሚያስለብስ ወይም በደስታ ቱልቱላ እሚያስነፋ አይደለም፤ ትግሬ መሆን በከበሮና ክራር ጮቤ እሚያስረግጥ አይደለም፡፡ ምንም መሆን ምንም ማለት አይደለም – ትግሬ ወይም ጉራጌ ሆነህ ለመፈጠር አንተ ወይም አንቺ ምን ቤት ናችሁና? አንዳንዴ እኮ ማፈርም ጥሩ ነው፤ አመኑበትም አላመኑበትም የሃይማኖት መጻሕፍትንም መዳበስ አይከፋም – ሁሉም የአዳምና የሔዋን ዘር አይደለም እንዴ? ታዲያ ቄሱንና ኢማሙን ምን ነካቸው? በጎቻቸው በዘረኝነት ተጠልፈው ከፈጣሪ ትዕዛዝ ሲወጡ እነሱ የት አሉ? ወይንስ ካለበት የተጋባበት እንዲሉ በነሱም ብሶ ተገኘና ተያይዘው ጠፉ? ባልሠራነው ሥራና በማይመለከተን ጉዳይ ዘው ብለን ገብተን ለምንድነው ከሣሽና ፈራጅ ዳኛ መሆን የሚቃጣን? መጀመሪያ እኛነታችን ሰብኣዊነታችን እንጂ የሰው ዘር በሙሉ አንድ መሆኑን መረዳት ተገቢና ከጤናማ ማኅበረሰብም የሚጠበቅ ነው፤ ሰው አበደ ተብሎ ደግሞ ጨርቅ እንደማይጣል ሁሉ የተወሰኑ ሰሜነኛ ወንድምና እህቶቻችን በዘር ልክፍት አበዱ ብለን አብረን ተባብረን ማበድ አይጠበቅብንም፡፡ ማግኘትና ማጣት ባመጡብን ጣጣዎች ተከፋፍለን ሰብኣዊነትን መረጋገጥ አይገባም፡፡ ብዙ ነገሮች የወረት ናቸው፤ ወረት ደግሞ ያልፋልና በማያልፍ የታሪክ መዝገብ ላይ በጉልህ ፊደላት የሚሠፍር የታሪክ ጠባሳ መተው አይኖርብንም፡፡ አንድ ሁላችንም በጥልቀት ልናስብበት ነገር ልናገርና ላብቃ፡፡
እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ስፈጠር የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 25 ሚሊዮን ገደማ ነበር፡፡ አሁን ያ ቁጥር ተገቢው መንግሥት ስለሌለን ክፉኛ አሻቅቦ ወደ 87 ሚሊዮን አካባቢ ደርሰናል አሉ – ይህን አስደንጋጭ የሕዝብ ቁጥር ስናሰላው የያኔውን ሦስት ነጥብ አምስት ገደማ አጥፏል ማለት ነው ፡፡ ከእኔ ዕድሜ ወደኋላ ጥቂትና ብዙ ዓመታትን ለምሳሌ 50፣ 100፣ 200፣ 500… ሄደን ማየትም እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በነዚያን ዓመታት ስንት ሊሆን እንደሚችልም በምናባችን መቃኘት እንችላለን፡፡ ምናልባት 100 ሚሊዮን፣ 5 ሚሊዮን፣ 2 ሚሊዮን፣ ግማሽ ሚሊዮን… ይህ ሒሳባዊ ፖስቱሌትም እንበለው ቴኦረም እያለ እያለ ወደ ጥቂቶች ቀደምት ዝርያዎቻችን ይወስደናል፡፡ ታዲያን በጣት ከሚቆጠሩ አባት እናቶች ተነስተን 87 ሚሊዮን የገባነው ዘር እየተቋጠርን በመዋለድ ይሆን እንዴ? ብለን ደግሞ እናስበው፡፡ እርግጥ ነው – በአንድ አካባቢ ሰው ሲበዛ በተፈጥሮ ሀብት መሳሳትና ማለቅ እንዲሁም በቦታ ጥበት የተነሣ ወደሌላ አካባቢ ተዛውሮ መሥፈር የነበረና ያለ ነው፡፡ በዚያም የረጂም ዘመን ሂደት ውስጥ የቋንቋና የባህል መለያየት መከሰቱ የማይቀር ነው፡፡ ለዚህም ነው የሰዎች ባህልና ቋንቋ በብዙ መንገድ የሚመሳሰለው፡፡ … እግዚአብሔር አንድ አድርጎ የፈጠረውን ሰው ዘመንና መልክዓ ምድራዊ ልዩነቶች ሊለዩት ደግሞ አይቻላቸውም፡፡ መቅላት መጥቆርም፣ ማጠር መርዘምም… በአንድ ቤተሰብ ሳይቀር የሚታዩ ልዩነቶች በመሆናቸው ያን ያህል ጉባኤ የሚያስቀምጡ የልዩነት መንስኤዎች አይደሉም፡፡
በኔ በዚህች የግማሽ ምዕተ ዓመት በምትሆን ዕድሜየ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ25 ሚሊዮን ወደ 87 ሚሊዮን የደረሰው ኦሮሞ ከኦሮሞ፣ ትግሬ ከትግሬ፣ ኮንሶ ከኮንሶ፣ ከፊቾ ከከፊቾ፣ ጠምባሮ ከጠምባሮ፣ ዳዋሮ ከዳዋሮ፣ ጉራጌ ከጉራጌ ደራሳ ከደራሳ፣ ወላይታ ከወላይታ፣ ሃዲያ ከሃዲያ፣ ከምባታ ከከምባታ፣ አደሬ ከአደሬ፣ ቆቱ ከቆቱ፣ አማራ ከአማራ፣ አገው ከአገው፣ ወይጦ ከወይጦ… እንዲጋባ ሕግና ሥርዓት ተበጅቶ በዚያ ቀጭንና ኢተፈጥሯዊ ሕግ ተጉዘን ሣይሆን ሁሉም እንዳመቸው ካፈቀራትና ካፈቀረችው ጋር እየተጋቡና አንሶላና ጋቢ እየተጋፈፉ ነው – ያኔ እኮ ‹የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ፤ የሐረር ልጅ ነኝ፤ የደሴ ልጅ ነኝ፤ የአዋሣ ልጅ ነኝ፣ የቦንጋ ልጅ ነኝ…› እንጂ ‹የኦሮሞ ልጅ፣ የትግሬ ልጅ፣ የአማራ ልጅ…› የሚባል እንዲህ እንደዛሬው ዐይን ያወጣ የዘረኝነት ልክፍት አልነበረብንም፤ ይህ ዓይነቱ ነገር የመጣብን በተለይ ካለፉት 22 ዓመታት ወዲህ ወያኔ መርዙን ከረጨብን በኋላ ነው፤(አሁንስ ቢሆን እስኪ በየትምህርት ቤቱ ሂዱና እዩ … ተማሪዎች በዘፈቀደ ተበሰጣጥረው እንጂ በይሁንታ በዘር ኩይሣ ነው እንዴ የሚማሩትና በፍቅር ዓለምም የሚመላለሱት?)፡፡ አንዳንድ በስተቀሮችን ወደ ጎን እንተዋቸውና – በአብዛኛው – ጥንት ያኔ ኦሮሞው አማራዋን ያገባል፤ ትግሬው ይፋቴዋን ያገባል፤ አማራዋ ከጀምጀሙ ትወልዳለች፣ ሽናሻይቱ አገውን ታገባለች፤ ቢለኑ ሳሆዋን ያገባል፣ ትግረዋ ትግሬውን ታገባለች፣ ኢሮቡ አፋሯን ያገባል… ምኑ ቅጡ… በዚህ የአሥረሽ ምቺው የፍቅርና የጋብቻ ትስስር ‹ብዝሁ ተባዝሁ ወምሉዕዋ ለምድር› በሚለው ሕገ እግዚአብሔር ተመርተን ኢትዮጵያን ሞላናት – ምን አጠፋንና ነው ታዲያ ወያኔና ኦነግ ከአባታቸው ከሻዕቢያ ጋር በሃሳብ አንድነት ሥሙር ሆነው ሽል ምንጠራ ውስጥ የገቡትና በማን አባት ገደል ገባ ሊያመነቃቅሩን የሚሹት? እኔ አሁን ታዲያ ምንድነኝ ልበል? የትኛው ነው የኔ ‹ጥርት› ያለው ዘር? ‹እኔ የጎንደሬይቱ ልጅ! እኔ የጎጃሜይቱ ልጅ…› የሚለውን መንደርኛ ፈሊጥ ተውት፡፡ ይህ ዓይነቱ ከጠላ ቤት ድንፋታ ሊያልፍ የማይገባውን ተራ ጨዋታና ከዚህ ባስ የሚለውንም ተራ የቀልድ ልውውጥም ከምር አትውሰዱት፡፡ በእናቴ በኩል የምዛመዳቸውን ወንድሞቼንና እህቶቼን አስታውሰህ በቀልድ መልክ ‹ከወሎ ጎረቤት ይሻላል ባዶ ቤት› ብትለኝ እስቅ ይሆናል እንጅ ምንም አልልህም – በዚህ ዓይነቱ ተራ ቧልትም መነካከስ አይገባም፡፡ በአባቴ በኩል የምዛመዳቸውን እህቶቼን አስበህ ‹አንት ግድርድር ጎንደሬ› ብትለኝ ይብስ እየተኮፈስኩ በቀልድ አናድድህ ይሆናል እንጂ በዚህም ምንም አይሰማኝም፡፡ ኧረ ለመሆኑ ወሎስ የማን ሆነና? ስሙ ራሱ የኦሮሞ ስም አይደል እንዴ? ኦሮሞ ያልገባበትና ያልተዋለደው ኢትዮጵያዊ ግዛት ይኖር ይሆን? በኦሮሞነት ብዙም በማይታሙት ኤርትራና ትግራይ እንኳን ዕድሜ ለዚያ የደርግ ዘመን የርስ በርስ ጦርነት ሁላችንም በሁላችንም ውስጥ እንድንቀልጥ ተደርገን የለምን? ከሌላ ጋር የማይዋለድ መንወሳቀስ የማይችል ዛፍና ግንድ ብቻ ነው፡፡ ሰው በተፈጥሮው ተንቀሳቃሽ በመሆኑ ሌላ መሰል ፍጡር እስካገኘ ድረስ ይተኛል፤ ይዋለዳልም፡፡ ስለዚህ የጠራ ዘር ማግነት በነኦነጎችና መሰሎቹ አእምሮ ውስጥ ህልምና ቅዠት ሆኖ የሚቀር እንጂ እውን ሊሆን አይችልም – የነዚህ የበጥባጮቹ የዘር ሐረግ ሲታይ በአብዛኛው የዚህ የመጢቃነት ‹ሰለባ› ናቸው- ለምሳሌ የሕወሓቱን አዲስ ዓለም ባሌማን ብናይ የኦሮሞና የትግሬ መጢቃ ነው – በዚህ ረገድ መረጃው ያላችሁ እባካችሁን የበጥባጮቹን የዘር ሀረግ (pedigree) አሳዩን – እንድንማርበት፡፡ እኔን ታዲያ ማን ነው ከማን ነጻ የሚያወጣኝ? ራስን አለማወቅ ይሏል ይሄኔ ነው፡፡ ኦነግ ራሱን ሳያውቅ በስሜ እየማለና እየተገዘተ ድፍን ግማሽ ምዕተ ዓመት ቀለደብኝ፡፡ እሱ ሩጫውን እንደጨረሰ እኔም አሁን በሃሳብ መዳከሩ ቢበቃኝስ ወገኖቼ፡፡
ይነጋል በላቸው

አቡነ ጴጥሮስ መንፈስና ጴጥሮሳዊነት (ፕ/ር መሰፍን ወልደማርያም)

qqq
ቀደም ሲል « እግዚአብሔርና እኛ» በሚለው ርዕስ ስር የተነገረውን አንዳንድ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት ጸረ ሃይማኖት ሊያስመስሉት ይሞክሩ ይሆናል። አይደለም ። እንዲያውም ሃይማኖትንና ሃይማኖተኛነትን የሚያጸና ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ሃይማኖት ቢኖረው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅርና በእግዚአብሔርም ላይ ያለው እምነት ብርቱ ነው። ይህንን ከመገንዘብ የተነሳና በዚያው ፍቅርና እምነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በምንም መንገድ ጸረ ሃይማኖት መስሎ ሊታይ አይገባም።
wwችግሩ ሌላ ነው። ችግሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመንፈሳዊ ተግባርና ኃላፊነት የሚያበቃ ሁኔታ አለመኖርና ወደፍጹምነት የሚጠጋ የመንፈሳዊነት ድርቀት ነው። እ.አ.አ. በ1977 ዓ.ም. ጉለሌ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለካቶሊክ ሚስዮናውያን ንግግር እንዳደርግ ተጠይቄ የኅብረተሰባችን የመንፈስ ውድቀት (ክስረት) በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ተናግሬ ነበር። በዚያ ንግግር ውስጥ የሚከተለው በከፊል ይገኝበት ነበር።

በየቀኑ የጭካኔ ወሬ እንሰማለን። ወጣቱ ለወደፊት መዘጋጀቱን ትቶ፤ ክፉኛ ለሁለት ተከፍሎ እርስበርሱ ለመጫረስ ተነሥቶአል። ለበለጠ ግድያና መጨራረስ ጩኸት እንሰማለን፤ የእናቶችና የሚስቶችን ጩኸት እንሰማለን፤ የሐዘን ልብሳቸውንም እናያለን። የሞትን አደጋ በየአቅጣጫው እናያለን። የፍቅርን አለመኖር እንሰማለን፤ እናያለን፤ የተስፋን አለመኖር እንሰማለን፤ እናያለን። ንዴትን እናያለን፤ እንሰማለን፤ ተስፋቢስነትን እንሰማለን፤ እናያለን፤ ሐዘንን እንሰማለን፤ እናያለን። ከዚህም በላይ ንዴቱም ተስፋቢስነቱም ሐዘኑም ይሰማናል። ሕይወት አጠራጣሪና በቀላሉ የሚጠፋ ሆኖአል። እንሰማለን፤ እናያለን፤ እናያለን፤ እንሰማለን። ምንም አናደርግም። ይህ ምንም ያለማድረግ ውሳኔና ይህ በኅብረተሰቡ ኑሮ ውስጥ ያገባኛል የሚል ስሜት መጥፋት ግልጽ የሆኑ የወላጆችን፤ የአስተማሪዎችንና የሃይማኖት መሪዎችን የመንፈስ ውድቀት የሚያመለክቱ ናቸው። ለግፍ፤ ለበደልና ለጥቃት እንድንገብር፤ ግፍን በደልንና ጥቃትን አየሰማንና እያየን ምንም እንዳናደርግ የሚያደርገን ምንድን ነው?

እኔ እንደሚመስለኝና እንደማምነውም የጉዳዩ ባለቤት ራሳችን መሆናችንን ተገንዝበን ኃላፊነቱንና የሚያስከትለውንም ውጤት ላለመቀበል የፈጠርነው የመከላከያ ዘዴ ጉዳያችንን ሁሉ ወደእግዚአብሔር መወርወሩን ነው። የሚደንቀው ነገር የሃይማኖት መሪዎችን መለየቱ ለምን አስፈላጊ ሆነ? የሃይማኖት መሪዎች «ሥጋቸውን የበደሉ፤ለነፍሳቸው ያደሩ» ናቸው ይባላል። የሃይማኖት መሪዎች ለጽድቅ ማለት ለእውነት እንዲሁም ለፍትሕና ለእኩልነት የቆሙ ናቸው ተብሎ ይታመናል። ለሃብትና ለሥልጣን ግድ ስለሌላቸው ከዚህ ዓለም ጣጣ ውጭ ናቸው ይባላል። እንግዲህ እንደዚህ ዓይነቶቹ ለእግዚአብሔር አድረናል የሚሉ ሰዎች ለግፍ ለበደልና ለጥቃት እንዲገብሩ የሚያደርጋቸው ከየት የመጣ ኃይል ነው? ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም። ለዚህ ዓለም ሕይወት ካላቸው ጉጉት ብቻ የሚመነጭ ነው። የሚጎድላቸው ጴጥሮሳዊነት ነው።

የአቡነ ጴጥሮስ መንፈስ እንደሐውልታቸው የተረሳ ይመስለኛል። አቡነ ጴጥሮስ እንደሌሎቹ ሁሉ ኢጣልያ ኢትዮጵያን የወረረችው «የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ነው»፤ በማለት የኢጣልያ ወታደር የኢትዮጵያን ሕዝብ አበሳውን ያሳየው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው በማለት ሊገብሩና የተደላደለ ኑሮ ለመኖር ይችሉ ነበር። አቡነ ጴጥሮስ የራሳቸውንና የአገራቸውን ጉዳይ ወደ እግዚአብሔር ሳይወረውሩ ኃላፊነታቸውን ሳይሸሹ «እምቢኝ አሻፈረኝ!» አሉ። በእምቢተኛነታቸውም የኢጣልያን ክርስቲያንነትና ሥልጡንነት ፈተና ውስጥ ከተቱት። በእምቢተኛነታቸው ለእግዚአብሔር ለአምላከ ጽድቅ ያላቸውን ፍቅርና ክብር፤ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ጽናት፤ ለጨበጡት መስቀል ለመስዋዕትነት ምልክቱ ያላቸውን ስሜት ለአገራቸውና ለወገናቸውም ያላቸውን ታማኝነት አረጋገጡ። በመትረየስ ተደበደቡ።ዛሬ በዚህ ድርጊት ኢትዮጵያ ትኮራለች፤ ኢጣልያ ታፍራለች።

ጴጥሮሳዊነት የምለው የአቡነ ጴጥሮስን ዓይነት የእምቢተኛነት መንፈስ ነው። ጴጥሮሳዊነት በእግዚአብሔር አምላክ ጽድቅነት (ጽድቅ እውነት ማለት ነው) አምኖ የራስንም ኃላፊነት ከነውጤቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎ መቀበል ነው። ጴጥሮሳዊነት በመሠረቱ መንፈሳዊነት በመሆኑ የሚመካበት ኃይል መንፈሳዊ እንጂ አካላዊ ወይም ጠመንጃ አይደለም። የጴጥሮሳዊነትም ዓላማ አስፈላጊ ከሆነ ለእምነቱ ለመሞት እንጂ ለመግደል አይደለም። ሰው ሲገደል የሚቀረው በድን ሬሣ ነው። ገዳዩም ከዚያ ከበድን ሬሣ የተለየ፤ ወይም ከተጠቀመበት የመግደያ መሣሪያ የማይለይ ነው። በአካል ደረጃ ገዳይና የተገዳዩ ሬሣ ቢመሳሰሉም፣ በመንፈስ ደረጃ የማይገናኙ ናቸው። እውነትን እገድላለሁ ብሎ የሰውን ሕይወት የሚያጠፋ በድን፣ እውነትና የሰው ደም እንዳስደነበረውና እንዳቃዠው ከበድንነት ወደበድንነት ይተላለፋል። ለእውነት የተገደለው ግን እውነትን በሕይወቱ መስዋዕትነት አዳብሮና አፋፍቶ ያልፋል። መግደል የአእምሮ በሽተኞችና የልጆች ጨዋታ ነው። ለመሞት መዘጋጀትና ለእውነትና ለእምነት መሞት ግን ወኔን ይጠይቃል፤ መንፈሳዊ ወኔን።

የኢትዮጵያ ባህል ለጠመንጃ የሚሰጠው ክብር ከራሱ ከሰውነት ክብሩ ጋር የተያያዘ ነው። ጠመንጃ ኃይል ይሆናል፤ አያስጠቃም። ገዳይ ጀግና ተብሎ ይከበራል። ሠርቶ ከመክበር ያንድ መኳንንት ሎሌ ሆኖ ጠመንጃ መሸከም ያስከብር ነበር፤ አሁንም አልቀረም። ይህንን ክፉና የማይጠቅም ባህል በጴጥሮሳዊነት መለወጥ ያስፈልገናል። በጠመንጃ ኃይል ከመተማመን በመንፈሳችን ኃይል መተማመኑ ወደተሻለ የእድገት ጎዳና ያመራናል። ለጠመንጃ የማይበገር መንፈስ በመሀከላችን ሲዳብር ከጠመንጃ ይልቅ በጽሑፍ፤ ከጥይት ይልቅ በቃላት ቅራኔዎቻችንን ማለሳለሱ ወደሥልጣኔ ፈር ውስጥ ያስገባናል። እምነታችን የቱንም ያህል ቢለያይ፣ ሃሳባችን ቢራራቅና መግባባት የሚያስቸግር ቢሆንም ሃሳቦቻችን ይጋጩ፣ይፋጩ እንጂ እኛ ጎራዴ መዝዘን ወይም ጠመንጃ አጉርሰን፣ ከአእምሮና ከመንፈስ ደረጃ ወደእንሰሳነት ደረጃ ወርደን ስንጋደል እምነቶቻችንና አሳቦቻችን ያደፍጣሉ እንጂ እንደማይሞቱ ይግባን።

ጴጥሮሳዊነት በአቡነ ጴጥሮስ መስዋዕትነት ላይ የተመሠረተ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው። አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው፣ የተሰውበትም ዋና ምክንያት የኢትዮጵያ ነፃነት በመሆኑ ጴጥሮሳዊነትን ኢትዮጵያዊነት እንበለው እንጂ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሰው ልጆች ታሪክ በየአገሩ የሚያሳየው የሰው መንፈስ ነው። ስለዚህም ጴጥሮሳዊነት ዓለም አቀፋዊነት ባሕርይም አለው።

እውነትን ክዶ በውሸት ከመኖር ለእውነት ሞቶ እውነትን ሕያው ማድረግ የመንፈስ ዕርገት ነው። እንዲህ ዓይነቱ የመንፈስ ዕርገት የሚቀጥለውን ትውልድ ከእንሰሳት ደረጃ ወደላቀ የሰውነት ደረጃ ያነሣዋል። ከዚህ የተሻለ ውርስ አይኖርም። ጠመንጃ የያዘ ሁልጊዜም እንዲያሸንፈን መንፈሳችን ከተዳከመ ለጠመንጃ መድኃኒቱ ጠመንጃን ማንሣት እየሆነ እስከዛሬ እንደነበረው ወደፊትም ይቀጥላል። ይህንን የቁልቁለት መንገድ በጴጥሮሳዊነት ልናቆመውና ወደዕርገት እንዲያመራን ማድረግ እንችላለን። የእያንዳንዳችንን ውሳኔ የሚጠይቅ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ከየት ወዴት? ገጽ 42-43

ተጻፈ 1986 ዓ.ም.

ecadforem

Sexy Kangaroos (You Read That Right). It’s All About The Biceps

Panel Advises Annual Lung Cancer Screening for Current and Former Smokers

11For the first time, there’s evidence that screening smokers may save them dying of lung cancer.

The U.S. Preventive Services Task Force (USPSTF) , a government-based panel of experts, released a draft recommendation that smokers between the ages of 55 to 80 who have a history of smoking 30 packs or more a year, as well as those who have quit within the last 15 years, should get low dose CT scans of their lungs to look for possible tumors. Smoking accounts for about 85% of lung cancer, which is among the leading causes of cancer deaths in the U.S. each year.

The advice comes after the USPSTF determined in two previous reviews that there was not enough evidence to support the annual screenings. But new studies support the fact that the small risk of radiation exposure from the low dose scans was outweighed by the benefits of detecting abnormal growths early and intervening with treatments. The National Lung Screening Trial (NLST) study by the American College of Radiology Imaging Network (ACRIN), for example, found that low-dose CT scans reduced lung cancer deaths among former smokers as well as current smokers aged 55 to 74 by 20% compared to X-rays. Another study, published in the journal Cancer found that such CT screening could prevent up to 12,000 lung cancer deaths each year, which could also significantly lower health costs associated with the disease.

(MORE: A New Way to Detect Lung Cancer? Dogs Can Sniff It Out)

When the NLST results were released in 2011, the American College of Radiology issued a statement pledging to create better guidelines, standards, and staffing changes to support more widespread screening. “Evidence-based infrastructure will have to be put in place nationwide to ensure that patients have access to uniform, quality care and a similar life-saving benefit from these exams as demonstrated in the NLST,” the college wrote.

In recent years, the USPSTF has been issuing controversial advice concerning cancer screening, based on updated evaluations of the data. In 2009, the task force recommended that most women delay mammogram screening for breast cancer until age 50, a full decade later than previous guidelines. And last year, the panel found that widespread screening with the prostate specific antigen (PSA) test was not contributing to fewer deaths from prostate cancer, and advised men to skip the test altogether.

With the current lung cancer recommendation, the Task Force joins organizations such as the American College of Chest Physicians, American Society of Clinical Oncology, the American Thoracic Society, the National Comprehensive Cancer Network (NCCN) and the American Lung Association, which have been recommending lung cancer screening with low dose CT scans for those at-risk since May 2012.

(MORE: No More Chemo: Doctors Say It’s Not So Far-Fetched)

The proposed recommendation is available for public comment until August 26, after which the task force will make any suggested modifications and issue its final guidelines. At that point, insurance companies will have to reimburse annual lung cancer screenings for the appropriate populations, as designated under the the Affordable Care Act.

But with more screening, some experts say there will be confusion over the CT’s false positive and false negative readings. The test misses about 20% of lung cancers, and can falsely detect tumors at high rates as well, which means more people may be diagnosed with cancer who might not have malignant growths. “Overdiagnosis is guaranteed,” Dr. Peter Bach, the director of Memorial Sloan-Kettering Cancer Center’s Center for Health Policy and Outcomes told Reuters about the new recommendation.

Task Force member Dr. Michael LeFevre of the University of Missouri in Columbia says overdiagnosis is inevitable in screening in general, and in cancer screening specifically. The panel estimates that around 3% to 4% of the cancers that are detected through screening may never have caused a person a problem in their lifetime. “By contrast, from a Task Force perspective, back when we made our last recommendation about mammography, we were looking at a 10% overdiagnosis estimate,” he says. “We consider 3% to 4% pretty low considering the devastating consequences of lung cancer in the United States today.”

Screening, however, cannot substitute for the protective effect of quitting smoking, says the task force, and the panel stresses that the most effective way to lower deaths from lung cancer is to reduce smoking rates.

Read more: http://healthland.time.com/2013/07/30/panel-advises-annual-lung-cancer-screening-for-current-and-former-smokers/#ixzz2aWp0fWaz

Post Navigation