addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 3, 2013”

Army ousts Egypt’s President Morsi

saa
General Abdul Fattah Al-Sisi makes the televised announcement

The head of Egypt’s army has given a TV address, announcing that President Mohammed Morsi is no longer in office.

Gen Abdul Fattah al-Sisi said the constitution had been suspended and the chief justice of the constitutional court would take on Mr Morsi’s powers.

Flanked by religious and opposition leaders, Gen Sisi said Mr Morsi had “failed to meet the demands of the Egyptian people”.

Anti-Morsi protesters in Cairo gave a huge cheer in response to the speech.

The army’s move to depose the president follows four days of mass street demonstrations against Mr Morsi, and an ultimatum issued by the military which expired on Wednesday afternoon.TV stations belonging to Mr Morsi’s Muslim Brotherhood went off air at the end of the speech and state news agency Mena said managers at the movement’s Misr25 channel had been arrested.

Minutes later, a notice went up on Mr Morsi’s Facebook page denouncing the army move as a “military coup”.

The statement asked Egyptian citizens – both civilians and military – to “abide by the constitution and the law and not to respond to this coup”.

The ousted leader’s current whereabouts are unclear. However, earlier reports said security forces had imposed a travel ban on both him and other leading figures in the Muslim Brotherhood.’Roadmap’ for the future
General Sisi said on state TV that the armed forces could not stay silent and blind to the call of the Egyptian masses.

He spoke of a new roadmap for the future, and said that the chief justice of the Supreme Constitutional Court, Adli Mansour, would be given the task of “running the country’s affairs during the transitional period until the election of a new president”.

After Gen Sisi’s address, both Pope Tawadros II – the head of the Coptic Church – and leading opposition figure Mohammed ElBaradei made short televised speeches about the new roadmap for Egypt’s future which they had agreed with the army.

Mr ElBaradei said the roadmap aimed for national reconciliation and represented a fresh start to the January 2011 revolution.

“This roadmap has been drafted by honourable people who seek the interests, first and foremost, of the country,” added Pope Tawadros.
Fireworks
The army is currently involved in a show of force, fanning out across Cairo and taking control of the capital, BBC correspondent Quentin Sommerville reports.

He described seeing eight armoured personnel carriers heading for Cairo University in Giza, where one of the main pro-Morsi demonstrations was being held.

The tens of thousands of anti-Morsi protesters on the streets of Cairo are now celebrating, with fireworks lighting up the night sky and car drivers honking their horns in excitement.

But Morsi supporters elsewhere in the city are reported to have shouted: “No to military rule.”
Source http://www.bbc.co.uk/news/world-middle-east-23173794

በጎንደር ህገ ወጡ እስር ቀጥሏል -ወገራ ወረዳ ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጓል

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረጉና የንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም መንግስት ህገወጥ እስር እያካሄደ ይገኛል፡፡

ለቅስቀሳ ስራ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ ተንቀሳቅሰው የነበሩ አራት የፓርቲው አባላት ህገ ወጥ ወረቀት በትናችኋል ተብለው ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ማክሰኞ ሰኔ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው የአራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

እስሩ ህገ መንግስታዊ መብትን ለመጠቀም በተወሰደ እንቅስቃሴ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የተደረገ አፈና መሆኑን በመግለጽ አንድነት ታሳሪዎቹ እንዲለቀቁና ይህንን ባደረጉ የጸጥታ ሃላፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የዞኑን አመራሮች ቢጠይቅም በአፈናው በመቀጠል ዛሬ ረፋድ ላይ በጎንደር ከተማ ቅስቀሳ ላይ የነበረ አንድ አባላችንን አስረውታል፡፡

በተያያዘ ዜና በትላንትናው እለት በጎንደር ከተማ ለሰላማዊ ሰልፉ የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀት ሲያሰራጩ የነበሩት አቶ አምደ ማርያም እዝራ እና አቶ ስማቸው ግንቤ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ በዛሬው እለት አቶ ማሩ አሻግር የተባሉ የዞኑ የአንድነት አመራር ትላንት የታሰሩ አባላትን ለመጠየቅ ወደ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ በሚሄድበት ወቅት እሱንም በህገ ወጥ መንገድ ማሰራቸውን ታውቋል፡፡ በተጨማሪም በላይ አርማጨሆ ትክል ድንጋይ ከተማ አቶ እርሻው አደራጀው የተባለ የአንድነት አባል የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳውን የሚመለከት በራሪ ወረቀት በማሰራጨቱ በታሰሩንና በሰሜ ጎንደር ወገራ ወረዳ ተመሳሳይ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ ከነበሩ አባላት መካከል አቶ ጄጃው ቡላዴ የተባሉ የአንድነት አባል በህገወጥ መንገድ ሲታሰሩ አቶ ጋሻው ዘውዱ የተባሉ አባል ላይ በጥይት የግድያ ሙከራ ተደገርጎባቸው ማምለጣቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታውቀዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የህዝባዊ ንቅናቄ ግብረሀይል በፓርቲው አባላት ላይ እየተወሰደ ያለውን ህገወጥ እስርና የግያ ሙከራ አውግዞ፤የትኛውም የመንግስት ህገወጥ እርምጃ ከንቅናቄው እንደማይገታው ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡

በገንዳሆ ከተማ በመከላከያ ሰራዊትና ጸረ-ሽምቅ በሚባሉት ልዩ ሀይሎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውጥጥ በርካታ ሰዎች ተገደሉ

1111111111111
ኢሳት ዜና :-በመተማ ወረዳ በገንዳሆ ከተማ ሰኔ 25፣ 2005 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰአት ከ30 ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና ጸረ-ሽምቅ እየተባሉ በሚጠሩ ሀይሎች መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከ4 እስከ 7 የሚደርሱ ታጣቂዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ፣ 2 የወረዳው ባለስልጣናት ደግሞ ቆስለዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ጸረ- ሽምቅ እየተባሉ የሚጠሩ ከ 150-200 የሚደርሱ የመንግስት ታጣቂዎች ለወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና በሚል በቀድሞ ስሟ ሽንዲ በአዲሱ ስሟ ገንዳሆ ከተማ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተሰባሰቡ ሲሆን፣ ትናንት ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በአካባቢው ሰፍሮ ከሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ሌሊቱን ሙሉ ጎራ ለይተው ሲታኮሱ አድረዋል።

ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከመከላከያ 2 ከጸረ- ሽምቅ ሀይሎች ደግሞ 3 ሰዎች ሲገደሉ፣ አበበ የሚባል የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊና ሌላ ባለስልጣን ቆስለዋል። ከሟቾች መካከል ወረቀት የሚባለው ሰው አስከሬኑ ወደ ሳንጃ ተልኳል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የሟቾችን ቁጥር ከተጠቀሰውም አሀዝ ይልቃል።

የወረዳው የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኢንስፔክተር አስማማው ስብሰባ ላይ በመሆናቸው መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል። ምሽት ላይ በድጋሜ ስንደውልላቸው ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

በቅርቡ በመተማ ወረዳ ከመሬት ጋር በተያያዘ ከ50 እስከ 60 የሚጠጉ አርሶ አደሮች ጫካ መግባታቸው ይታወቃል። የአካባቢው ነዋሪዎች ብሎክ የሚል ስያሜ የሰጡትን መሬት የማከፋፈል ስርአት፣ የመንግስት ታጣቂዎች ሳይቀሩ ሲቃወሙት ቆይተዋል።

ሰበር ዜና ሞርሲ ተነሱ፣ ሕገመንግሥቱ ተቋረጠ

cccሕገመንግሥቱን ማቋረጣቸውንና ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲን ከሥልጣናቸው ማስወገዳቸውን የግብፅ ወታደራዊ አዛዥ አስታወቁ፡፡

የሃገሪቱ የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄነራል አብዱል ፋታህ ኻሊል አል-ሲሲ ከተቃዋሚዎች ተወካዮች እና ከሐይማኖት መሪዎች ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ ሕገመንግሥቱን በጊዜያዊነት ማቋረጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ተከታዩ መንግሥት በምርጫ እስኪሰየም ድረስም የሕገመንግሥታዊው ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ የሃገሪቱን የመንግሥት ሥራ አስፈፃሚ ሥራዎች እንደሚያከናውኑ አስታውቀዋል፡፡

የሽግግሩ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በወታደራዊው ዕቅድ የተሰየሙት የሕገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ አድሊ ማሱር ባሰሙት ንግግር ደም መፋሰስን ለማስወገድ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል፡፡ የአሁንን እርምጃ ያመጣው “ያለፈው መንግሥት” ለዕርቅ መሥራት ስለተሣነው መሆኑን የጠቆሙት አዲሱ ፕሬዚዳንት እርሣቸው ለዕርቅ እንደሚጥሩ ቃል ገብተዋል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችና ወጣቶች በፖለቲካው ሂደት ውስጥ እንዲሣተፉ እንደሚያበረታቱ አዛዡ አስታውቀዋል፡፡

በጣሕሪር አደባባይ የተሰበሰቡ ተቃዋሚዎች ደስታቸውን በከፍተኛ ድምፅ እና ርችት እየተኮሱ እየገለፁ ሲሆን የሙስሊም ወንድማማችነት መሪዎች ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ ነፃ ምርጫ የተመረጡ ፕሬዚዳንታቸውን ለመጠበቅ እንደሚፋለሙ ሲዝቱ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ሚስተር ሞርሲ ያሉበት ቦታ ለጊዜው አይታወቅ እንጂ የፕሬዚዳንቱ ፅሕፈት ቤት በትዊተር ገፁ ላይ ባወጣው መልዕክት “ስለ ግብፅ እና ለታሪክም ትክክለኛነት ስንል እየተካሄደ ያለውን በስሙ እንጥራውና ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ነው” ብሎታል፡፡

የአል አዝሃር መስጂድ ዋና ኢማም ሼኽ አሕመድ አል ጠይብና የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ በየተራ ባደረጉት ንግግር አምላክ ግብፅንና ሕዝቧን እንዲጠብቅ ለምነዋል፡፡

የተቃዋሚዎቹ ተጠሪ ሞሐመድ አል ባራዳይ ባሰሙት ንግግር የጦር ኃይሎቹ ያቀረቡት ዕቅድ “የግብፅ አብዮት ባለፈው ዓመት የተነሣሣለትን ማኅበራዊ ፍትሕ እና ነፃነት ለማስገኘት የመንደርደሪያ ደንጊያ ነው” ብለውታል፡፡ አልባራዳይ አክለውም ይህ ዕቅድ “የአብዮቱ መንገድ ማስተካከያ እርምጃ ነው”ም ሲሉ ጠርተውታል፡፡

ዕቅዱ ከሚያካትታቸው ቁልፍ ካሏቸው ተግባራት መካከልም “ፈጥኖ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማካሄድ፣ ሕገመንግሥታዊ ማሻሻያ ማድረግ፣ በሚሰየም የዕርቅ ኮሚሽን ብሔራዊ ዕርቅ መፍጠር” እንደሚገኙበት ዘርዝረዋል፡፡

የታማሮድ ወጣቶች መሪ ባሰማው ንግግር እርምጃው በግብፅ ታሪክ ውስጥ አዲስ እርምጃ መሆኑን ጠቁሞ “ግብፅ መገፋት የሌለባት፣ ለክብራቸው፣ ለነፃነትና ለማኅበራዊ ፍትሕ እምቢ ባይ የሆኑት የሁሉም ግብፃዊያን የሆነች ሃገር ነች” ብሏል፡፡

በጊዛው ካይሮ ዩኒቨርሰቲ ትናንት በተካሄዱ ግጭቶች የ18 ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡

ጄነራል ሲሲ የሃገሪቱን መፃዒ ዕጣ ፈንታ ዕቅድ ያሉትን ካነበቡና የፕሬዚዳንቱን መወገድ ካስታወቁ ወዲህ የተፈጠረ ግጭት ይኑር ወይም አይኑር ለጊዜው በግልፅ የወጣ ዘገባ የለም፡፡

ምንጭ፡ ቪኦኤ

ዜና በጨዋታ፤ ሙርሲ በህዝቡ ከይሲ በወታደሩ “ሂድ ከዚ” ተባሉ!

asዜና በጨዋታ፤ ሙርሲ በህዝቡ ከይሲ በወታደሩ “ሂድ ከዚ ተባሉ!”

ቢቢሲ የሙርሲን ደጋፊዎች እና የሙርሲን ተቃዋሚዎች ጎን ለጎን እያሳየ ነው፡፡ የሙርሲ ተቃዋሚዎች ርችት እየተኮሱ ባንዲራ እያውለበለቡ ይታያል፡፡ የሙርሲ ደጋፊዎች ደግሞ ፀጥ ረጭ ብለዋል፡፡

ሙርሲ በህዝቡ ከይሲ ተደርገው፤ በወታደሩ “ሂድ ከዚ…” ተብለው ወርደዋል፡፡

የተቃዋሚዎቹን እና የደጋፊዎቹን ትዕይንት ስንመለከተው፤ በፖለቲካ ሳይሆን በኳስ ግጥሚያ ተሸናንፈው ነው የሚመስለው፡፡ ሚስማር ተራ እና ዳፍ በሏቸው፡፡ አለመተላለቃቸው …የሚደንቅ ነው!

ከሁሉ በላይ የግብፅ ወታደር እንዲህ አይነት ፈርሃ እግዚአብሄር፣ አክብሮተ ሀገር እና አፍቅሮተ ህዝብ ያደረበት እንዴት ተደርጎ ቢሰራ ነው፡፡

አንድ ወዳጄ ግብፅ 2 ኢትዮጵያ 0 ያልከኝን በቅንፍ፤ (ማይ ፍሬንድ… እነርሱጋ እኮ አጋዚ የለም! ልልህ ነበር ግን አንዳንድ ወዳጆቼ “አታስፈራራን” ሲሉኝ ታየኝ) ከቅንፍ ውጪ… የምር ግን አነ አጋዚ እነ ፌደራል መቼ ነው እንደ አዲሳባ ፖሊስ እና እንደ ግብፅ ፖሊስ ከህዝብ ጎን የምትቆሙት…? ይህንን ጥያቄ በአጋዚ ወታደርኛ እና በፌደራል ፖሊስኛ ቋንቋ ተርጉሞ ላደረሰልኝ ውለታ ከፋይ ነኝ!
http://www.abetokichaw.com/

አሰቸኳይ ወገናዊ ጥሪ!

xzzJuly 3, 2013
ጎጠኛው የወያኔ ገዢ ቡድን በኢትዮጵያ ታሪክ ከነበሩት አገዛዝ ሁሉ እጅግ በከፋና በባሰ መልኩ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የጣለ፤ ሕዝብን ከቦታውና ከቀየው እያፈናቀለ ለከፍተኛ ሥቃይና መከራ በመዳረግ ለይ ይገኛል።

እንዲሁም በኃይማኖት እምነት ጣልቃ እየገባ፤ የአገሪቷን ድንግል መሬት ለባዕዳን በመሸጥ ወገኖቻችንን በማንነታቸው እንዲያፍሩና አገር አልባ እንዲሆኑ በማድረግ፤ ለእርስ በርስ ግጭትና ለከፋ ችግር ዳርጓቸዋል።

ከዚህም ባሻገር ይህ ጠባብ አረመኔ ቡድንና ጭፍሮቹ በሙስና የአገሪቱን አንጡራ ሀብት እየዘረፉ በማራቆትና ይባስ ብሎም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ለሆዳቸው ባደሩ ካድሬዎች አማካኝነት ስደተኛውን በመደለል ለማስበዝበዝ ከሚሞክሯቸው ስልቶች መሃከል ጥቂቶቹ፦

1. ለአባይ ግድብ ገንዘብ አዋጡ፤ ቦንድ ግዙ እያሉ ሕዝቡን ቁም ስቅሉን ማሳየት

2. ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሊውሉ የሚችሉ ምርቶችን በጭፍሮቻቸው አማካይነት ወደ ውጭ አገር በመላክ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለግል ኪሳቸው ከማጋበስ አልፈው ልጆቻቸውንም በዓለም ዙሪያ በታወቁ ታላላቅ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ በተቃራኒው ደግሞ የአገሪቱን ሕፃናት ትምህርት እንዳያገኙ ሥርዓተ ትምህርቱን ከማዳከም አልፈው የዕለት ጉርሳቸውን በመንፈግ ትውልድን ማጠፋት መቀጠሉ እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው።

3. አሁን በቅርቡ ደግሞ አርባ ለስልሳ (40/60) በሚል መርሃ ግብር መሬት እንሰጣለን መሬት በምደባ ወይም በማህበር እንድትሰሩ እናደርጋለን እያሉ የውጪ ምንዛሬ እጥረታቸውን ለማሟላትና የጭካኔ አገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘም በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ ለሌላ ዝርፊያ እየተዘጋጁ ነው።

ስለዚህ ከዚህ ከደሃ ህዝብ እየተነጠቀ የሚሰጣችሁ ወይም የደሃ ቤት እየፈረሰ የምትገዙት መሬት ለሚፈናቀለው ወገን ሥቃይና መከራ ከህሌና ወቀሳና ከታሪክ ተጠያቂነት አትድኑም።
በመሆኑም ማንኛውም ለአገርና ለወገን ተቆርቋሪ ነኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔ/ኢሕአዴግ አገራችንን ከነአካቴው ለማጥፋት የጠነሰሰውን ሴራ ለማከሸፍ ይረዳ ዘንድ፤

1. ወያኔ/ኢሕአዴግ በተለየ መልኩ በሙዚቃና በመዝናኛ ምሽት ሰበብ በሚያደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ (ፈንድሬይዚንግ) ዝግቶች አለመሳተፍ፣

2. ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎሮሮ እየተነጠቀ ውጭ አገር እየተላከ የሚሸጠውን እንጀራና ሌሎችንም ቁሳቁሶች አለመግዛት፤
ማሳሰቢያ

ሀ. የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ እያሳደደን ነው ብላችሁ ጥገኝነት ከጠየቃችሁና ከተፈቀደላችሁ በኋላ ከዚህ አምባገነንና ጎጠኛ አገዛዝ ጋር በመመሳጠር ህዝብን ከሚጎዳ ተግባር ካልተቆጠባችሁ ለሚመለከተው ህጋዊ አካል በማሳወቅ እርምጃ የምናስወስድ መሆኑን አሰቀደመን እናሳውቃለን።

ለ. ነጋዴዎችም ሆናችሁ ወይም ግለሰቦች ለውጭ ምንዛሬ ፍጆታ ይሆን ዘንድ የወያኔ/ኢሕአዴግን ጠባብና ጎጠኛ አገዛዝ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም ህጋዊም ሆነ ህገ ውጥ በሆኑ አጀንዳዎቻቸውና መልካቸውን እየተቀያየሩ ከሚመጡ ከወያኔ የእርዳታ ተቋማትም ሆነ ከሥርዓቱ አቀንቃኝ ሆዳም ግለሰቦች ጋር እንዳትተባበሩ፤ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችሁ የሥቃይና የመከራ ዘመን ማራዘሚያ አትሁኑ፤ ለዚህ ከልጅ ልጅ ከሚተላለፍ አሰነዋሪ ተግባር በመቆጠብ ከህሌና እዳ ነፃ በመሆን ወገናዊ ግዴታችሁን ተወጡ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

በቶሮንቶና አካባቢው የተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን
አሰተባባሪ ከሚቴ

source,,,http://ecadforum.com/Amharic/archives/8763/

በአዲስ አበባ የወተት እጥረት እጅግ አሳሳቢ ሆኖዋል

unity is power

DSCN3499በአዲስ አበባ የወተት እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።አስተያየታቸውን የነገሩን ነዋሪዎች እንዳሉት ፥ በምርቱ ላይ እጥረት ብቻ ሳይሆን የዋጋ መወደድም ይስተዋላል ።በካፌዎች የአንድ ስኒ ማኪያቶ ዋጋ እስከ 8 ብር መድረሱን የካፌ ተጠቃሚዎችም ያነሳሉ።የካፌ ባለቤቶች የወተት መጥፋት ለእነሱም ስራ ማነቆ መሆኑን በመግለፅ ፥ ቀደም ሲል ከሚገዙበት ዋጋ በላይ ለመግዛትም አንዳንዴ ጨረታ እንደሚገቡም ጭምር ይናገራሉ።በስድስት ኪሎና በሌሎች አካባቢዎች በተለይ ጠዋት ጠዋት ወተት በማከፋፈያዎች ሱቅ በር ላይ ረጃጅም ሰልፎችን ይስተዋላሉ።በእነዚህ ማከፋፈያዎች ውስጥም አንድ ሊትር ወተት እስክ ከ16 እስከ 18 ብር ድረስ ዋጋ ይሸጣል።ወተት የተትረፈረፈባቸው አከባቢዎችከዚህ በተቃራኒ ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች ወተታችንን የሚገዛን አጣን ፤ልፋታችንም ውጤት እያስገኘልን አይደለም ይላሉ።የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በበኩላቸው አልፎ አልፎ ገበያ የማናገኝ በመሆኑ ከአከባቢው የምንሰበስበው ወተት መጠኑ ይቀንሳል ብለዋል።የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲቲዩት በበኩሉ በዚህ አካባቢና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመፍታት እየሰራሁ ነው ብሏል ።ከሰሜን ሸዋ ዞን አንዱና ዋነኛው የወተት አምራች በሆነው የደገም ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መብራት…

View original post 154 more words

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ ከሥልጣናቸው እንደማይነቃነቁ በቁርጠኝነት አስታወቁ፡፡

saፕሬዚዳንቱ ፍንክች እንደማይሉ አቋማቸውን ዛሬ – ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ምሽት ላይ ባደረጉትና በሃገሪቱ ብሔራዊ ራዲዮና በቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ንግግር ያስታወቁት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎቻቸው አደባባይ ወጥተው እንዲወርዱ እየጠየቋቸው ባሉበት ወቅት ነው፡፡
የዛሬ ዓመት አካባቢ በሃገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ ነፃ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሞርሲ ሕገመንግሥታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በመወጣት እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ ጦር እጁን ከፖለቲካው ቀውስ ውስጥ እንዲያወጣም አሣስበዋል ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፡፡
የግብፅን ባንዲራ የሚያውለበልቡ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል – ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ምበሚስተር ሞርሲ እና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ያለው ልዩነት እስከነገ፤ ረቡዕ ባለው ጊዜ ካልተፈታ ለግብፅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይበጃል የሚሉትን የራሣቸውን የጎዳና ትልም እንደሚደነግጉ የጦር ኃይሎቹ መሪዎች ማስጠንቀቃቸውና ቀነ-ገደብ መቁረጣቸው ይታወሣል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን እያሰሙ በነበሩበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ተቃዋሚና ደጋፊዎቻቸው የሆኑ ሰልፈኞች የካይሮን አደባባዮችና ጎዳናዎች አጨናንቀዋል፡፡
ከመሪያቸው ጎን ቆመው እነርሱ “ማንኛውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት” ያሉትን የጦሩን እርምጃ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ እየዛቱ ያሉት የሞርሲ ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ናስር ቀበሌ የተሰባሰቡ ሲሆን ሞርሲ ሥልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚለውን ጥያቄአቸውን የሚያሰሙት ተቃዋሚዎች ደግሞ ማዕከላዊውን የካይሮ ጣሕሪር አደባባይ ሞልተውታል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሣ ግጭት ካይሮ ውስጥ ዛሬ (ማክሰኞ) የሰባት ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሕክምና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ወታደሮች ካይሮ ቤተመንግሥት አጥር ግቢ ላይ፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
ወታደሮቹ “ሕገመንግሥቱን ለማቋረጥ፣ ሕግ አውጭውን አካል ለመበተንና የሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም እየተዘጋጁ ነው” የሚል ሾልኮ የወጣና ለመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ሽው ያለ ጭምጭምታ ጠቁሟል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ አባላት “የተመረጠን ፕሬዚዳንት ለመገልበጥ የሚደረግን ሙከራ ለማቆም” ከታንኮች ፊት ቆመው መስዋዕት እንደሚከፍሉ እየዛቱ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ሞርሲ ተቃዋሚዎቹን ሰልፈኞች እያዳመጡ መሆናቸውን እንዲያሣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማክሰኞ ጠዋት ስልክ ደውለው ጠይቀው ተቃዋሚዎችም የግብፅን ዴሞክራሲያዊ ሂደት መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል፡፡
አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ለግብፃዊያኑ ጥሪ አሰምተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ በተካሄዱ ሰልፎችና በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ከሃያ በላይ ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል፡፡

V o A

አቶ ታምራት የገቡትን ቃል አፈረሱ፤ ቢተው ስልጣን ያዙ

( ከኢየሩሳሌም አርአያ)
zበአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ወገኖች፣ ታምራት ያንን ቢናገሩም በቃላቸው ግን እንዳልተገኙ አስረድተዋል። « የኢየሱስ አገልጋይ ሆኜ እኖራለሁ» ያሉት ታምራት አሁን ወደ ንግድ አለም መግባታቸው እንዳስገረማቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ሌላው ቢቀር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ለሰሩት ጥፋት ህዝብን ይቅርታ ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፣ በይፋ አደባባይ ወጥተው ህዝብን ይቅርታ የጠየቁት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ገብሩ ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል። አቶ ታምራትና አቶ ስዬ ግን ይህን ለማድረግ ጨርሶ እንደማይፈልጉ ከያዙት አቋም በቀላሉ መረዳት ይቻላል ብለዋል።

በሌላም በኩል የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል የነበሩትና ደቡብን በበላይነት ሲያሽከረክሩ ቆይተው በ1993ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተከሰው የታሰሩት አቶ ቢተው በላይ ለስድስት አመት ታስረው ከተፈቱ በኋላ በአቶ መለስ ዜናዊ የአፋር ክልል አማካሪ ተደርገው ተሹመው እንደነበረ ምንጮች አጋለጡ። ከአቶ አባተ ኪሾ ጋር ተከሰው የነበሩትና ከሕወሐት ተገንጥሎ ከወጣው ቡድን አንዱ የነበሩት አቶ ቢተው ተመልሰው የመለስ አገልጋይ መሆናቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአፋር ክልል አማካሪ ሆነው ለሶስት አመት የሰሩት ቢተው በአሁኑ ወቅት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሎጅ ተዛውረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። የአቶ ቢተው ወንድም ኮ/ል ሲሳይ (በቅፅል ስሙ ሃመዴ) ጀግና ኢትዮጲያዊና አገሩን የሚወድ ታታሪ እንደነበርና በአሰብ ውጊያ ከነሂሊኮፕተሩ ጋይቶ ማለፉን ምንጮቹ አመልክተዋል። አንድም ቀን ስሙ በነመለስ ተነስቶ የማያውቀውና የጡረታ መብቱ እንኳ ሊከበርለት ያለቻለው ሟቹ ኮ/ል ሃመዴ ልጆቹ ያለአሳዳጊ ተበትነው መቅረታቸውን ምንጮቹ ሳይገልፁ አላለፉም።

zehabesha.com

የጃዋር ቃለምልልስ በፓልቷክ

xzከያሬድ አይቼህ –

ጃዋር መሀመድ እንግዳ ሆኖ በፓልቷክ ዛሬ እሁድ ቀርቦ ነበር። ቃለ-ምልልሱን ከ1000 በላይ ሰዎች አዳምጠዉታል። ዋናዎቹ ጠያቂዎች የሲቪሊቲው አባ-መላ (አቶ ብርሃኑ እርገጤ) እና የቃሌው ማይጨው ነበሩ።

አባ-መላ ጃዋርን አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት ሞከረ። አንዴ ኦህዴድ አባል ነበርክ አለው። ጃዋር “የማንም ድርጅት አባል ሆኜ አላቅም አለ”። አባ-መላ ጃዋርን የኦሮሞ አስገንጣይ አርጎ ለማቅረብ ሞከረ ፤ አልተሳካለትም። ጃዋር መጀመሪያ ኦሮሞ ፡ ቀጥሎ ኢትዮጵያዊ መሆኑን አስረግጦ አቀረበ።

ኦሮሞ እና አማራ ምሰሶዎች ናቸው የሚለው ንድፈ-ሃሳብ ሲቀርብ ጥሩ ንድፈ-ሀሳብ ሆኖ አግኝቼው ነበር። ሆኖም ግን ኦሮሞዎችን እንደ መሰላል ተጠቅሞ ፡ የኦሮሞዎችን ብሄራዊ ማንነት ሳይቀበል ፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመፍጠር እንደማይቻል ግልጽ ይመስለኛል። አሁንም የኦሮሞ-አመራ ምሰሶነት ለአገራችን ነጻ መውጣት ብሩህ ተስፋ ብዬ አምናለሁ።

– ጥንድ-ምሰሶ –

የኦሮሞ-አማራ ጥንድ-ምሰሶነት ሃቅ ነው። በህዝብ ብዛት አንጻር ፡ በኢትዮጵያ መንግስት የ2004 ዓ.ም. መረጃ መሰረት ፡ የኦሮሚያ ህዝብ የኢትዮጵያ 36% ሲሆን ፡ የአማራ ክልል ህዝብ ብዛት የኢትዮጵያ 22% ነው። በድምሩ 58% ነው ፤ የሁለቱ ህዝቦች ምሰሶነት ከዚህ ጭብጥ የተነሳ ነው።

ምሰሶዎቹ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ተወዳዳሪ የሌለው የፓለቲካ ሃይል የመሆን እምቅ ችሎታቸው ግልጽ ነው። ነገር ግን እንዴት ነው ሁለቱ ሊሂቃን ጎን-ለጎን በመቆም የኢትዮጵያ ምሰሶ የሚሆኑት? አባ-መላ እና ማይጨው በሚሉት መንገድ ሊሆን አይችልም ፤ የኦሮሞ ሊሂቃን ፡ እኛ አማራዎች በቀረጽነው ኢትዮጵያዊነት ውስጥ እንዲካተቱ ማደርግ አይቻልም።

– ኦሮሚያ –

አንዱ በተደጋጋሚ ጠያቂዎቹ ጃዋርን ለማጥቃት የሞከሩበት መንገድ “ኦሮሚያ ሚባል አገር የለም” በማለት ነው። ለመሆኑ ወፍ ዘራሽ የሆነ አገር አለ እንዴ? ሁሉም አገር ሰው ሰራሽ እኮ ነው። አሜሪካ የዛሬ 400 አመት አልነበረም ፤ አሁን ግን አለ። ኤርትራ የዛሬ 20 ዓመት በፊት አልነበረችም ፤ አሁን ግን አለች።

ኦሮሚያም አለች። ባለፉት 22 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ስነልቦና በኦሮሚያዊነት ተጠግኗል ፡ ተቀርጿል ፡ ተደራጅቷል። የቁቤ ትዉልድም ወደ ሃላፊነት ተረካቢነት እየገሰገሰ ነው። የቁቤ ትውልድ የሚያቀው ኦሮሚያን ብቻ ነው ፤ ‘እምዬ ኢትዮጵያን’ አያቅም።

ይሄንን ጭብጥ አባ-መላ እና መሰል ወገኖቻችን ይክዳሉ። ነገር ግን የኦሮሞ-አማራ ሊሂቃን በህብረት መስራት ሚችሉት የአማራ ሊሂቃን የኦሮሞን ኦሮሚያዊነት ሲቀበሉና ሲያከብሩ ብቻ ነው። “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ፡ ቀጥሎ ኢትዮጵያዊ” የሚለውን ማንነት የማይቀበሉ የአማራ ሊሂቃን የኢህአዴግ እድሜ አስረዛሚዎች ናቸው።

የኢህአዴግ አምባገነናዊ ስርዓት ህዝባችንን በሙስና ፡ በኑሮ ውድነት ቸነፈር ፡ በፍትህ መጥፋት ፡ በሰብአዊ መብት ጥሰት ፡ በፓለቲካ እስረኝነት እና በሃይማኖት መብት ጥሰት በሚያንገላታበት በአሁኑ ጊዜ ፡ የኦሮሞዎችን ኦሮሚያዊነት አልቀበልም ማለቱ አርቆ አለማሰብ ነው።

– አማራዎች ምን እናድርግ? –

አማራዎች ራሳችንን እናስቀድም። አማራዎች በቅድሚያ ለአማራ ህዝብ መብት እንቁም። ያንን ለማድረግ የምንችለው ከኦሮሞ ወገናችን ጋር ጥንድ-ምሰሶ በመሆን እንጂ የኦሮሞን ሊሂቃን ማንነት በመናቅ አይደለም።

የኦሮሞን ማንነት ካልተቀበልን ፡ የቀድሞ ገዢዎቻችን በኤርትራ ላይ የፈጸሙትን አይነት የስትራቴጂ ስህተት እንደግማለን። የአጼ ሃይለስላሴ መንግስት ኤርትራን በኮንፌደሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር አዋህዶ ቢሆን ኖሮ የኤርትራ ህዝብ አሁን ባለበት ስቃይ ውስጥ አይገባም ነበር ፤ የብዙዎችም ህይወት በከንቱ አይጠፋም ነበር።

የአማራ ሊሂቃን እንንቃ!! ኤርትራ ጥቂት ሚሊዮን ህዝብ ብቻ የያዘ ነው ፤ ኦሮሚያ ግን ትልቅ ነው። አቅማችንን አውቀን ከኦሮሞ ሊሂቃን ጋር በመከባበር ፡ በመቀባበል እና በጋራ ጥቅም ላይ ባተኮረ ስትራቴጂ አሁን በላያችን ላይ የተንፈራጠጠውንና የበሰበሰውን የህወሃት መንግስት በቀላሉ ማንበርከክ እንችላለን።

አባ-መላ : ማይጨው እና እንዲሁም እነሱን መሳይ ወገኖቼ፦ የሻገተውን ፡ ያለፈበትን እና የነፈሰበትን ፤ እንዲሁም አማራዊነት የበላይ የሆነበትን ኢትዮጵያዊነት ለታሪክ እንተወው። ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን በቂ ምህዳር ባለው መድብለ-ብሄር ማንነት እንተካው።

ህወሃት በተንገዳገደበትና በበሰበሰበት በዚህ ወቅት አዲስ አስተሳሰብና አዲስ እይታ በመያዝ ለኢትዮጵያውያን ነጻነት እንታገል። የኦሮሞና-አማራ ሊሂቃን በዚህ መልክ በመስራት ወደ ድል እንገስግስ።

ከአክብሮት ጋር!

ቪቫ ኦሮሚያ! ቪቫ ኢትዮጵያ!

– – – – – – –

የጸሃፊው አድራሻ፦ yared_to_the_point@yahoo.com

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=4908

Post Navigation