addisnews

I'm standing for real freedom. I regard freedom of expression as the primary right without which one can not have a proper functioning democracy.

Archive for the day “July 6, 2013”

በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ?

ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?

workneh and bereket

July 6, 2013  02:27 am

ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ”ከፍተኛ” ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር “ምንጮቼ ነገሩኝ” በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ “ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች” በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም።

ሚዲያውን መዳፋቸው ስር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው “በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።

ከመለስ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያሳዩት አቶ በረከት ከድርጅታቸው ይሁንታ ውጪ “አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ይሆናሉ። የሚቀረው የስርዓት ማሟላት ጉዳይ ነው” ማለታቸው  የህወሃትና የኦህዴድ ሰዎችን ክፉኛ አበሳጭቶ እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች “አቶ በረከት አማካሪ ሆነው ወደ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ መዛወራቸው ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር የመገፋት ወይም ስራ አልባ የማድረግና ከቀጥተኛ ተሳታፊነት የመታቀብ ያህል ነው” ባይ ናቸው።

“በዜግነታቸው ብቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የመሳተፍ መብት የሌላቸው አቶ በረከት ሲፈነጩበት ከነበረው የኢህአዴግ ሚዲያ bereketመሰናበታቸው በራሱ በርካታ ጉዳዮችን የሚያመላክት ነው” የሚሉት ምንጮች “የፖሊሲና የጥናት ጉዳዮች ከፍተኛ የቀለም እውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ሃላፊነት ነው። አቶ በረከትም ሆነ አቶ ኩማ ለዚህ አይመጥኑም። ውሳኔው ማቀዝቀዣ ውስጥ የማስገባት ያህል ነው” ሲሉ አቶ በረከት ያላቸው የአደባባይ ሚና ማክተሙን ያወሳሉ።

በሌላ በኩል የተለየ አስተያየት የሚሰነዝሩ ክፍሎች እንደሚሉት “አቶ በረከት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ እለት እለት ሥርስራቸው ሆነው እንዲሰሩ የተሰጣቸው ስልጣን ነው። ይህ የሚያሳየው እሳቸው አሁንም ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቀጠላቸውን ነው” በማለት የሃሳብ ልዩነታቸውን ያስቀምጣሉ።

አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የቀረበ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ አቶ መለስ በህይወት እያሉም ቢሆን ሶስቱ እንደማይለያዩ ያመለከቱት ክፍሎች፣ የህወሃት የበላይ አመራርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር መሪ የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስትር ውስጥ የሚሰይሙት ሚኒስትር፤ ሪፖርትር እንዳለው አቶ በረከት ካልሆኑና የህወሃት ሰው ከተሾመ “በትክክልም አቶ በረከት ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ገብተዋል ማለት ነው” ሲሉ ሁለት ጫፍ ያለው አስተያየት ሰንዝረዋል።

አቶ ኩማ አሁን ባለው ኦህዴድ ውስጥ አንጋፋና ታማኝ፣ በቅጣት ከሶስት ዓመት ማዕቀብ በኋላ ወደ መንግስት ሃላፊነት የተመለሱ፣ kumaኦህዴድን ማጥራት ሲፈለግ በትር የሚጨብጡ፣ በመሆናቸው ከንቲባነቱን ሲለቁ እንዳያፈገፍጉ አዲሱ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አብዛኞች ይስማማሉ። አቶ ኩማ ካላቸው ልምድና ዕውቀት አንጻር አቶ ሃይለማርያምን በፖሊሲ ጉዳዮችና በጥናት ረገድ ለማማከር የሚችሉ ሰው እንዳልሆኑ ስምምነት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥቂት አይደሉም። ከዚህ አንጻር በዓለምቀፋዊ ዋና ከተማነት ከምትታወቀው አዲስአበባ ከንቲባነት ወደ አማካሪነት ኩማ ደመቅሳ “ሲሾሙ” እንደ ሥልጣን ሽረት ከተቆጠረ፤ የበረከት ስምዖን በተመሳሳይ መልኩ መታየት የማይችልበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል የሚከራከሩ አሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሥልጣን በምክትል ጠ/ሚ/ርነት ሲያድግና ኢህአዴግ በምርጫ የመሸነፍ ቅንጣት ችግር ሳይኖረው ኩማን ከከንቲባነት ሥልጣን ማንሳቱ የብቃት ማነስና አለመፈለግ እንደሆነ ተጨማሪ አስተያየቶች አሉ፡፡

ለሶስትና አራት ዓመት ህጻን “ከክልላችን ስለተባረርክ የትምህርት ገበታህ ላይ መቀመጥ አትችልም” የሚል ደብዳቤ የሚጽፉና በሙስና በከፍተኛ ደረጃ የሚታሙት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ትምህርት ሚኒስትርነት የተሻገሩት አቶ ሃይለማርያም ደቡብ ክልል ላይ ያለውን ሰንሰለት ለመበጣጠስ እንዲያመቻቸው እንደሆነ ይገመታል። ሃዋሳ ነዋሪ የሆኑ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ሽፈራው የዘረጉት ድር መበጣጠስ እንዳለበት የታመነው አሁን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠር የክልል በጀት እንደፈለጉ ከሚያስኬዱበትና ያለገደብ ሥልጣናቸውን ከሚያከናውኑበት የክልል ፕሬዚዳንትነት ወደ ሚኒስትርነት “መሾም”፤ የሥልጣን ሽረት ተብሎ ከመጠራት ውጪ ምንም ሊባል እንደማይችል በሽፈራው ሽጉጤ አመራር የተማረሩ ብቻ ሳይሆኑ ደጋፊዎቻቸውም ያመኑበት ጉዳይ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርን መምራት ያቃታቸው አቶ ደመቀ በስራ ብዛት ሰበብ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸውን ወንበር ብቻ እንዲይዙshiferaw መደረጉን ያመለከቱት ክፍሎች “አቶ ሽፈራው በሹመቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከሚቀርቧቸው ሰምተናል። ሃዋሳ በክልሉ መስተዳድር ውስጥ እሳቸው የሰገሰጓቸውም ስጋት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሃይለማርያም “ታማኛቸውን” በመሾም (“በማስመረጥ”) እውነተኛ የደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸውን እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል፡፡

ደመቀ መኮንን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸው ብቻ እንዲቀጥሉ የተደረጉት ምን አልባትም አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስቴር ውስጥ በአማራ ክልል ከነበራቸው “ልምድ” አኳያ ለኮታ ማሟያ ታስበው ነው በሚል ካድሬው በስፋት እንደሚያወራ እየተሰማ ነው። አቶ ደመቀ በአማራ ክልል የደህንነቱ መሪ እንደነበሩና በዚሁ በተግባራቸው “የተመሰገኑ ታማኝ” ለመሆን መብቃታቸውን የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።

ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት እየሰደቧቸው በመቸገራቸው እንደነበር የሚያስታውሱት እኒህ ክፍሎች “አቶ ደመቀ የአማራው ክልል መሬት ተላልፎ ሲሰጥ አቶ አያሌው ጎበዜ አልፈርምም ሲሉ፣ እሳቸው መፈረማቸው ይፋ ከሆነ በኋላ DemekeM‘ከሃዲ’ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ህጻናት ልጆቻቸውም ትምህርት ቤት መማር ያልቻሉት ለአባታቸው በተሰጠ ስም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቻቸው ስለሚያበሽቋቸው ነው” በማለት አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ጀምሮ ከደህንነቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት ታማኝ እንዳሰኛቸው አስታውቀዋል። ከዚሁ ውለታቸውና ልምዳቸው አንጻር በደህንነት መ/ቤት ውስጥ ይካተታሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ሰኔ 27 ቀን ለተሰየመው ፓርላማ በቀረበው ሹመት መነጋገሪያ ከሆኑት መካካል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ችግር እንደተጣባው የተመሰከረለትን የትምህርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ መመደባቸው፣ አንዲሁም የአቶ ደመቀ በ”ስልጣን በዛባቸው” ሰበብ የሚኒስትርነት ቦታቸውን መነጠቃቸው በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው።

የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።

በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።

አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው Workineh-Gebeyehu-መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።

አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።

ዝርዝር ጉዳዩን ለማብራራት እንደሚቸገሩ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንዲዋቀር አዋጅ የታወጀለት የደህንነት መ/ቤት ሚኒስትርና የበላይ ሃላፊዎች ይፋ ሲሆኑ ነገሮች ይበልጥ እንደሚጠሩ ተናግረዋል። በኢህአዴግ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረውና አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልጠራ የሚነገርለትን ልዩነት ተከትሎ የተሸናፊውን ወገኖች የማጥራት ስራ በተለያዩ ስልቶች እንደሚሰሩ የጠቆሙት እነዚህ ክፍሎች፣ የደህንነት ሚኒስትር ሲቋቋም የሚሾሙት ባለስልጣን ከቀድሞዎቹ መካከል እንደማይሆን ምልክት ማየታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን የአዲስ ሹመትና ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሃሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በአንድ ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።በዚህም መሰረት

አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ – የትምህርት ሚኒስትር

አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ – የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር

አቶ አህመድ አብተው አስፋው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር

አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ – የትራንስፖርት ሚኒስትር

ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር

ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው – የፍትህ ሚኒስትር

አቶ በከር ሻሌ ዱሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ – የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር

አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

ሆነው የተሾሙ ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።

source,,,http://www.goolgule.com/bereket-up-or-down/

ቤቲ ጥፋተኛ ከተባለች የ5 ዓመት እስር ይጠብቃታል

xx
በፌስቡክ ላይ እርቃን ፎቶግራፍ መለጠፍ በህግ ያስቀጣል
በ“ቢግ ብራዘር አፍሪካ” የሪያሊቲ ሾው ውድድር ላይ የተሳተፈችው የ26 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ቤተልሄም አበራ፤ በቅርቡ በተለያዩ ድረገፆች በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ ወሲብ ስትፈጽም መታየቷ በወንጀል የሚያስከስሳት መሆኑን የገለፁ የህግ ባለሙያዎች፤ ፍ/ቤት የጥፋተኝነት ብይን ከወሰነባት የ5 ዓመት እስር እንደሚጠብቃት ተናገሩ፡፡

በወጣቷ ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ለአዲስ አድማስ የገለፁት የህግ ባለሙያዎቹ አቶ ጳውሎስ ተሰማ እና አቶ ተስፋሁን ፀጋዬ፤ ቤቲ የፈፀመችው ተግባር የህብረተሰቡን ባህል የሚቃረን በመሆኑና ይህም በሚዲያ በመተላለፉ በኢትዮጵያ ህግ ያስከስሳታል ብለዋል፡፡
እንኳን ድርጊቱን በአደባባይ የፈፀመ ቀርቶ ለመፈፀም ሙከራ ያደረገም በወንጀል እንደሚጠየቅ የገለፁት ጠበቆቹ፤ ቤቲ በአደባባይ የኢትዮጵያውያንን ባንዲራ ይዛ መልካም ገጽታችንን ማሳየት ሲገባት ባህላችን ሀይማኖታችንና ህጋችን የማይፈቅደውን ነገር በአደባባይ ፈጽማለች ብለዋል፡፡
ክሱን መመስረት ያስፈለገው ሌሎች በተመሳሳይ ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ አካላትን ለማስተማር ታስቦ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡ እንደ ህግ ባለሙያነታቸው የማንም ውክልና ሳያስፈልጋቸው ክሱን በቅርቡ እንደሚመሰርቱና በወቅቱም በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል፡፡
እርቃን ምስሎችን በኢንተርኔት መለጠፍ በሕግ ያስከስሳል ብለዋል – ባለሙያዎቹ፡፡
ቤቲ የፈፀመችው ድርጊት በተለያዩ ድረ ገፆች መለቀቁን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በጉዳዩ ላይ ጐራ ለይተው በመደገፍና በመንቀፍ አስተያየታቸውን ሲሰጡበት የነበረ መሆኑን ያስታወሱት የህግ ባለሙያዎቹ፤ እኛ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ስናስብ ምን አገባችሁ ያሉንም አሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ግን በህጉ መሠረት ይህን የማለት መብት የላቸውም ብለዋል። ለመልካም ፀባይ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችን መፈፀም ከ1 ዓመት እስከ 5 አመት በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል ያሉት ባለሙያዎቹ፤ የቤቲ ጉዳይም እስከ 5 አመት እስር ሊያስቀጣ ይችላል ብለዋል፡፡
ዋናው አላማችን ቤቲን እንደማሳያ ወስደን እንዲህ አይነት ድርጊቶችም እንደሚያስቀጡ ለማሳየት ነው የሚሉት ጠበቆቹ፤ ዛሬ በፌስቡክና በተለያዩ የማህበራዊ ድረገፆች ላይ ሴቶች እርቃናቸውን ሆነው የተነሱትን ፎቶ እየለጠፉ መሆኑ ከዚህ የህግ ግንዛቤ ክፍተት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
“ከቢግ ብራዘር አፍሪካ” ውድድር የተባረረችው ቤቲ፤ በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጠችው ቃለምልልስ፤ ድርጊቱን አለመፈፀሟንና የታየው ነገር ለውድድሩ አስፈላጊ በመሆኑ በትወና የተደረገ እንደሆነ ገልፃለች፡፡

Boeing 777 crashes at San Francisco International Airport, injuries unknown

…ደግሞ በግብፅ እንጣላ እንዴ…!

xx…ደግሞ በግብፅ እንጣላ እንዴ…!

ሙርሲ ከስልጣን የተወገዱ ጊዜ አንድ ዜና በጨዋታ ለጥፌ ነበር፡፡ የዜና በጨዋታዋ አላማ፤ ወሬውን ከማድረስ በተጨማሪ ሁለት ነገር ነበር፡፡ አንደኛው፤ ህዝብ ግር ብሎ ከተነሳ የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለሚሰማን መንገር፣ ሁለተኛው ደግሞ የእኛዎቹ ፌደራል ፖሊሶች እና አጋዚ ወታደሮች እንኳንስ እንዲህ ጫን ያለ ነገር መጥቶ ይቅርና እንዲሁም እንዲሁ ናቸው የሚለውን ለሚመለከት ሰው ለማመላከት እና መልዕክት ለሚያደርስ ሰው ልቦና ግዙ… ተብላችኋል ብሎ ያደርስልን ዘንድ መንገር ነበር፡፡

(በነገራችን ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ እኮ “ሙደኛ” ነው፡፡ በተለይ በ97ቱ ጊዜ እንዳየነው ህዝቡ እምቢኝ ካለ ፖሊሶቻችን ከጎናችን መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡ ይሄንን ገዢው ፓርቲም ያወቃል፡፡ ምነው እንኳ ያኔ ራሱ እኮ የተሰጣቸው አንድ ክላሽ ከአንድ ጥይት ጋር ብቻ ነበር፡፡ “ይቺን ምን እንድናደርጋት ነው” ብሎ አንዱ ፖሊስ ሲጠይቅ አይደለም እንዴ “ለሚስኮል አንድ ጥይት መች አነሳህ…” የተባለው…!)

ወደ ነገራችን ስንመለስ… አንድ ወዳጄ “ሙርሲ በህዝቡ ከይሲ በወታደሩ ሂድ ከዚ ተባሉ” የሚለው የዜና በጨዋታ ርእሴን እንዳልወደዱት ሲነግሩኝ፤ “አረ አቤ… ነገሮችን ስትገልጽ ለሰው ሞራል ተጠንቀቅ…” ብለውኝ ነበር፡፡ አልገባኝም ወዳጄ… ለማን ሞራል ነው የምጠነቀቀው… መቼም ለሙርሲ ሞራል ተጠንቀቅ አይሉኝም… እንዲህ ያልኩት ሙርሲን ጠልቼ ወይም ንቄ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሙርሲ የእኔን አማርኛ አያነቡም፡፡ እንዴት አያነቡም… ትላለህ… ብሎ የሚቆጣ ካለ ምክንያቱም ሰውዬውን ወታደሮቹ እስር ቤት ጨምረዋቸዋልና ነው፡፡

የሚስቅ ስቆ የሚበሳጭ ተበሳጭቶ ካበቃ፤ አሁን ወደ ዋናው ጉዳይ እንግባለን፡፡ የግብጽ ወታደር የመንግስት ግልበጣ ነው ያደረገው… ወይስ ሃላፊነቱን ነው የተወጣው…!? እነሆ ዋናዋ ጥያቄ ተጠየቀች… ብለን አዲስ መስመር ላይ ተመቻችተን እናውራ፤

እንደኔ እምነት የግብፅ ወታደር ኩዴታ ፈፅሟል የሚያስብል ነገር አላየሁም፡፡ በርካታ ህዝብ አደባባይ ወጣ ተቃውሞውንም አሰማ፡፡ (አንዳንድ ወዳጆቼ፤ “ጥቂት ግብጻዊያን ስለጮሁ እንዴት ህዝብ ትላለህ?” ብለውኝ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ኢቲቪ የሚሰሩ መሆን አለባቸው፡፡ እነ ኢቲቪ በናታችሁ የጥቂት ብዛቱ ስንት ነው….!? ይሄንን ጥያቄ ስንት ጊዜ ጠየቅን… ዜና አንባቢውም ዝም ቲቪውም ዝም ሆነብን እንጂ…) ሀቂቃውን ለመናገር ግን በግብጽ ተቃውሞ የወጡት ብዙሃን አንደነበሩ እድሜ ለቴክኖሎጂ በወቅቱ በቦታው ተገኝተው ሲዘግቡ የነበሩቱ ቀጥታ ሲያነፃጽሩልን ነበርና፤ “ሙርሲ ይሂዱልን ከዚ…” ያሉት ብዙ እንደነበሩ ድንጋይ ነክሰን ብንምልም አንፈራም፡፡ ስለዚህ በእኔ በምስኪኑ እምነት የእነዚህ ብዙሃን አቤቱታ መሰማት አለበት፡፡ ለዚህም ወታደሩ ያደረገው መፈንቅለ መንግስት ሳይሆን አፍቅሮተ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ (ለብዙሃኑ ጆሮ ሰትቷልና!)

እርግጥ ነው ሙርሲ ከዚህ በፊት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተመርጠው ነው ወደ ስልጣን የመጡት፡፡ እና ቢሆንሳ “ተመረጥኩኝ ብለሽ አትበይ ደንበር ገተር… ከልተመቸው “ንኪው” ይልሻል ባላገር…” የሚል ዘፈን አለ አይደል እንዴ…! (ከሌለም እኛው እናስነካዋለን!) የምሬን ነው፡፡ ማንም ቢሆን ገና ለገና በምርጫ ነው የመጣሁት ብሎ በስልጣኑ ላይ መዘናጋት፣ መዝናናት ወይም ማዛጋት ቢያሳይ መራጩ ህዝብ ወግድ ሊልም መብቱ አለው፡፡ (ብዙሃን ይመውዕ ይላል መጽሀፉ) እርግጥ ነው እዚህ ጋ አንድ ነገር እረዳለሁ፡፡ መራጩ መብት እንዳለው ሁሉ ተመራጩም የተመረጥኩበትን ጊዜ ሳልጨርስ አልወርድም ብሎ “የመገገም” መብት አለው፡፡ ጋሽ ሙርሲም ያደረጉት ይህንኑ ነበር፡፡ ውጥረትም

የነገሰው በዚህ የተነሳ ነበር፡፡ ይሄኔ ነው የሆነ አካል ጣልቃ ገብነት የሚያስፈልገው፡፡ ለዚህም ነው ወታደሩ ጣልቃ የገባው፡፡

እንግዲህ ይህንን እኔ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ስለው ሌሎች ደግሞ ይሄማ መፈንቅለ መንግስት ነው ይላሉ፡፡ ታድያ ምን ችግር አለው…? እኔም ያልኩትን ልበል ሌሎችም ያሉትን ይበሉ፡፡

አሁን ከሙርሲ እና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ማረፊያ ቤት መውረድ በኋላ ተቃዋሚዎቹ የልባቸው ደርሶ ወደ ጎጇቸው ሲመለሱ የሙርሲ ደጋፊዎች ደግሞ “ይቺን ይወዳል የሙርሲ ልጅ” ብለው “እየቀወጡት” ይገኛሉ፡፡

ይህ ሊመጣ እንደሚችል ተንታኞቹ ድሮውንም ገምተዋል፡፡ ማለቂያው ምን ሊሆን እንደሚችል ግን የሚያውቀው የላይኛው ብቻ ነው፡፡

እኔ ይቺን እየተየብኩ ባለበት ሰዓት የወታደሩን ጣልቃ ገብነት በመቃወም በተቀሰቀሰው አዲሱ ተቃውሞ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሊደርስ እየተንደረደረ ነበር፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ተቃዋሚዎች እየጠየቁ ያለው ጥያቄ ትክክል ነው፡፡ “ድምጻችን የት ነው…! የመረጥነውን ሰውዬ የት አደረሳችሁት…!” እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡

መጨረሻ ላይ እንደኔ አስቴየት ያኛውም ትክክል ይሄኛውም ትክክል ሆነ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ዲሞክራሲ አጣብቂኝ ውስጥ የምትገባው ይሄኔ ሳይሆን አይቀርም፡፡ (የሚል ሌላ አስተያየት ልጨምራ!)

ለማንኛውም በቅርቡ ኢትዮጵያውንን ርስ በርስ ብናበጣብታቸውስ… ብለው ሲዶልቱ ያየናቸው ሙርሲ እና ባለስልታኖቻቸው አሁን ለራሳቸው ብጥብጥ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ለማንኛውም በቅርቡ ዜጎቻችንን ያለ አጥጋቢ ምክንያት መድረሻ ያሳጡት ግብፆች አሁን ርስ በርሳቸው እየተጣሉ መድረሻ ተቸግረዋል፡፡

እውነቱን ተናገር ካሉኝ ደስ አላለኝም፡፡ መጽሀፉ የጠሉህንም ውደድ ይለን የለ… ስለዚህ የግብጽ ህዝብን ባለቤቱ ይታደገው፡፡ እላለሁ!

በባለፈው ዜና በጨዋታ የተቀየሙኝ ወዳጄን ግን የምጠይቃቸው ጥያቄ አለኝ፤ ሀገራችን ስንት ጉድ እያለብን፤ እንዴት በግብጽ ጉዳይ እንጣላለን…! የግድ መጣላት ካለብንስ በሀገራችን ምርት ብንጣላ አይሻልምን…! (ዋጋውም ቀነስ ይላልናል)

http://www.abetokichaw.com/

NASA Finds Message From God on Mars

aa
NASA announced today that its Curiosity Rover has found an unambiguous message from God written on tablets in a Martian cave.

According to an official press release two giant stone slabs the size of small elephants were located deep inside a cavern abutting Aeolis Mons, a large mountain.

Upon one tablet is a copy of the Ten Commandments and the text of John 3:16 written in 12 languages – including English, Spanish, Chinese, Basque and Hebrew. On the other tablet is a simple message in English reading “I am real.”

According to top scientists who have studied the discovery extensively, these findings may have definitively established Christianity as the one true religion.

“This is amazing,” says Syms Covington, an Australian researcher working for NASA’s Mars Exploration Program. “We went into the cave looking for water, and we found proof of God’s existence instead.

“I mean how else did those tablets get there? I can tell you one thing: there’s not a single atheist inside NASA’s control room now. What we saw was jaw-dropping.”

Genesis 1:1

NASA’s Curiosity rover arrived on Mars in August of last year with a mission to explore the Martian climate and geology for signs for habitability.

Thus far the mission has been a success, with the discovery of an ancient seabed and chemicals needed for life suggesting that Mars was once suitable for life.

However the tablets, both of which are signed “Peace and Love – Yahweh,” represent the rover’s most significant find to date, and is perhaps the most important scientific event in history.

“When people find out about this, they will demand change in our society,” explains a political scientist at Georgetown University. “Democracy will have to give way to theocracy. We’re gonna have to build more churches and reintroduce prayer into schools. Abortion is defiantly going to be illegal within a few months.”

Despite its potential significance, Covington fears that the Earth-shattering discovery may not make the impact it should.

“Unfortunately, the mainstream media is so anti-Christian, they might not even pick up this story,” he explains. “But God is real. We have proof. And everyone deserves to hear the truth.”

Home

Eskinder Nega: Journalist unjustly jailed in Ethiopia

zaPlease add your name to Amnesty International’s petition to the Ethiopian authorities to release Eskinder Nega immediately.

Eskinder’s story

Eskinder Nega is an Ethiopian journalist and human rights activist.
Eskinder has been subjected to outrageous injustices. He was sentenced to 18 years in jail for writing articles calling for freedom of expression and an end to torture in Ethiopia.

Sadly, this is not the first time that Eskinder has been jailed for his activism. Eskinder and his wife, Serkalem, a newspaper publisher, were previously jailed for speaking out against the government in 2005 and released in 2007 after continued campaigning by Amnesty International.

His previous arrest came after the Ethiopian government ordered a violent crackdown on post-election protests in 2005. Security forces reportedly killed nearly two hundred people. Eskinder and Serkalem wrote and published articles criticizing the government’s actions. For this, they were both arrested and put in prison.Their son, Nafkot, was born in that prison.

For Eskinder, this was one more brutal act of oppression in a life spent being hounded by his government for defending human rights. Few families have sacrificed more for their people.

In recent years, the Ethiopian government has clamped down alarmingly on its citizens for speaking out. According to Serkalem, “freedom of expression and press freedoms are at their lowest point.” Now the regime has enacted a “terrorism” law that they use to silence anybody critical of them.

They used these laws to threaten Eskinder. To ban him from writing. To force Serkalem to stop publishing. To terrorize their family and threaten Eskinder with the death penalty.

And now – to arrest Eskinder alongside many other prominent journalists.

Amnesty International believes Eskinder Nega is a prisoner of conscience detailed solely for his peaceful and legitimate activities as a journalist. Join our call for his immediate release.

Human Rights in Ethiopia

In Ethiopia, the authorities routinely use criminal charges and accusations of terrorism to silence dissenters. Repression of freedom of expression has increased alarmingly in recent years. The Ethiopian government has systematically taken steps to crush dissent in the country by jailing opposition members and journalists, firing on unarmed protesters, and using state resources to undermine political opposition. More than a hundred other Ethiopians, including nine journalists, were charged under the antiterrorism law. About 150 Ethiopian journalists live in exile — more than from any other country in the world.

Use this form to add your name to Amnesty’s call for the Ethiopian government to immediately and unconditionally release Eskinder Nega from prison.

What else you can do

Write a letter

Write a polite letter in your words directly to Ethiopia urging the release of Eskinder. In your letter you can address some of the following points:

Release Eskinder Nega immediately and unconditionally on the grounds that he is a prisoner of conscience
Reunite his family and allow him to return to his work as a journalist
Until he is free he must be protected from torture and other ill-treatment
He should also have regular access to his lawyer, family, and to any medical care he may require
Address your letter to:

Prime Minister, Hailemariam Desalegn

P.O. Box 1031
Addis Ababa
Ethiopia

Minister of Justice, Berhan Hailu

P.O. Box 1370
Addis Ababa
Ethiopia

Postage cost: $1.85
http://e-activist.com/ea-action/action?

ሰበር ዜና የሰሜን ጎንደር የአንድነት ሰብሳቢ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው

09የሰሜን ጎንደር የአንደነት አመራሮችን ማሰር ቀጥሏል ዛሬ ዞኑ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ አለላቸው አታለለ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በሚፈፅመው ህገወጥ እስርና እንግልት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንደማያስሰርዘው ገልጧል፡፡

አንድነት በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የክልሉ መንግስት የሰሜን ጎንደር አንድነት የፓርቲውን አመራሮች የማሰር ዘመቻ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ አቶ አለላቸው አታለለ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን በመንግስት ህገወጥ እርምጃ እንደማይቀለበስ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከፍተኛ አመራሮቹም በንቅናቄው ላይ ግምባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን የሚመጣውን መስዋዕትነት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=4771#sthash.Zwt2rQUK.dpuf

Post Navigation